Brand Fitness Machines

Brand Fitness Machines

Share

ዘመናዊ ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት ማሽኖችን ከኛ ያገኛሉ። 0953012345 ላይ ይደውሉልን።

14/05/2026

የእግር ስፖርት ስትሰሩ በሰውነታችሁ ላይ ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል?

1. የሆድ እና የጀርባ ጡንቻዎችን ያጠነክራል።
ሆዳችሁ እና ጀርባችሁ እንዲጠነክሩ ከፈለጋችሁ ከሌሎች ጡንቻዎች ጋር ተሳትፈው የሚሰሩበትን መንገድ መፈለግ አለባችሁ። የእግር ስፖርት ደግሞ ይህንን ለማሳካት ጥሩ አማራጭ ነው።

2. ልባችሁ ጤናማ ይሆናል።
የምታወጡት ሃይል ስለሚጨምር ልባችሁም ስራውን ይጨምራል።

3. ካሎሪ ታቀጥላላችሁ
ትላልቅ ጡንቻዎች የሚገኙት በእግራችን ውስጥ ነው። አንድ ጡንቻ ትልቅ በሆነ ቁጥር ተጨማሪ አክስጅን እና ምግብ ይፈልጋል። ይህም ተጨማሪ ካሎሪ እንድታቃጥሉ ያግዛችኋል።

እናንተ የእግር ስፖርት ስትሰሩ ያገኛችሁት ጥቅም ምንድነው? ኮሜንት ያድርጉልን።

ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡ 

 

13/05/2026

ስፖርት  ስታቆሙ ጡንቻችሁ በምን ያህል ፍጥነት የሚቀንስ ይመስላችኋል?

ለሁለት ሳምንት ስፖርት መስራት ካቆማችሁ የጡንቻችሁ መጠን እና ጥንካሬ እየወረደ ይመጣል። ለሶስት ወር ካቆማችሁ ደግሞ ከፍተኛ በሆነ መልኩ ይቀንሳል። መጀመሪያ የሚቀንሰው ጥንካሬያችሁ ሲሆን በመቀጠል የጡንቻችሁ መጠን ይከተላል። አብዛኞቹ ሰዎች የጡንቻቸው ጥንካሬ ያለ ስፖርት በአማካይ ከሦስት እስከ አራት ሳምንት ድረስ ሊቆይ ይችላል። ከዛ በኋላ ግን በሚታይ መልኩ እየቀነሰ ይሄዳል። ይህንን  ለመከላከል ወጥ በሆነ መልኩ መስራት ይመረጣል።

እናንተ ስፖርት ካቋረጣችሁ ምን ያህል ጊዜ ሆናችሁ? ኮሜንት ያድርጉልን።
 
ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡ 

12/05/2026

ስፖርት ስትሰሩ ራሳችሁን የሚያማቹ ለምን ይመስላችኋል?

1. የመጀመሪያው ከምንም አይነት የጤና ችግር ጋር  የማይገናኝ ሲሆን ከ 5 ደቂቃ እስከ 2 ቀን ድረስ ሊቆይ ይችላል። የሚሰማችሁ በሁለቱም ጎናችሁ ሲሆን እንደልብ ምት አይነት ስሜት አለው። ይህ በብዛት የሚከሰተው በሙቀት ሁኔታ ውስጥ ስፖርት ስትሰሩ ነው።

2. ሁለተኛው የራስ ምታት አይነት ከተለያዩ ህመሞች ጋር የሚያያዝ ሲሆን ከህመሙ በተጨማሪ ማቅለሽለሽ ፣ ማስመለስ ፣ የአንገት መድረቅ እና የእይታ ብዥታ ሊኖር ይችላል። ይህ ካጋጥማችሁ ወደ ህክምና መሄድ ይኖርባችኋል ።

እናንተ ራስ ምታት ሲይዛችሁ የምትወስዱት መድኃኒት ምንድን ነው? ኮሜንት ያድርጉልን።

ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡ 

11/05/2026

ስፖርት ስታቆሙ ጡንቻችሁ ወደ ስብ እንደሚቀየር ታውቃላችሁ?

ብዙ ሰዎች ስፖርት ሲያቆሙ ጡንቻቸው ወደ ስብ የሚቀይር ይመስላቸዋል። ነገር ግን ጡንቻ እና ስብ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ናቸው። አንዱ ወደ አንዱ አይለወጥም። ስፖርት ስታቆሙ ጡንቻችሁ መሟሸሽ ይጀምራል። ስብ የሚፈጠረው ደግሞ ከሚያስፈልጋችሁ በላይ ምግብ ስትመገቡ እና የካሎሪ ወጪ እና ገቢያችሁ ካልተመጣጠነ ነው። አመጋገባችሁን በማስተካከል እና ስፖርት አዘውትሮ በመስራት ጡንቻሁ እንዳይጠፋ እና ስብ እንዳይከማች ማድረግ ትችላላችሁ።

እናንተ በስፖርት ዙሪያ ያለ የምታውቁት የተሳሳተ አመለካከት ምንድነው? ኮሜንት ያድርጉልን።

ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡ 

10/05/2026

ስፖርተኞች ጂም ውስጥ ፌንት የሚያደርጉት ለምን ይመስላችኋል?

1.ብዙ ጊዜ ስፖርተኞች ከባድ ብረቶችን ሲያነሱ ትንፋሻቸውን ይይዛሉ። ይህ ደግሞ በሆድ እና በደረት ውስጥ ያለውን ውጥረት በመጨመር መጀመሪያ ላይ የደም ግፊት ከፍ እንዲል ያደርጋል። ነገር ግን ወዲያውኑ የደም ግፊትን በመቀነስ ወደ አንጎል የሚሄደው የደም ፍሰት ይቀንሰዋል። ይህም የጭንቅላት መቀለል ስሜት እና ከፍ ካለ ደግሞ ፌንት ማድረግን ሊያስከትል ይችላል።

2.በባዶ ሆድ ስፖርት መስራት እና የውሃ ጥም የደም መጠንን እና የደም ስኳርን በመቀነስ ፌንት የማድረግ ተጋላጭነትን ይጨምራሉ።

3.ከአቅም በላይ የሆኑ ብረቶችን ማንሳት የማዞር እና የማቅለሽለሽ ስሜትን ሊያስከትሉ ይችላሉ።

በቀጣይ ፓስት ይህንን እንዴት መከላከል እንደምትችሉ በሰፊው እንመለከታለን።

ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡ 

09/05/2026

ብረት ስትገፉ ጡንቻ ከማሳደግ በተጨማሪ ሌላ ምን ጥቅም የምታገኙ ይመስላችኋል?

1. የተሻለ የአእምሮ ጤና
የጭንቀት እና የድብርት ስሜታችሁ ይቀንሳል። እንዲሁም የራስ መተማመናችሁ እና ሙዳችሁ የተስተካከለ ይሆናል።

2. ጠንካራ አጥንት
የአጥንት ጥንካሬን በመጨመር የስብራት ተጋላጭነታችሁን ትቀንሳላችሁ።

3. የተሻለ እንቅልፍ
ጥሩ እንቅልፍ ተኝታችሁ ታድራላችሁ።

4. ማራኪ አቋም
ሰውነታችሁ ቀጥ ያለ እና ማራኪ እንዲሆን ያደርጋል። ከዛ በተጨማሪ የወገብ ህመምን ለመቀነስ ይረዳል።

5. ካሎሪ ለማቃጠል
ሰውነታችሁ ካሎሪ የሚያቃጥልበትን  ፍጥነት በመጨመር ስብ እንድታቀልጡ እና ውፍረት እንድትቀንሱ ይረዳችኋል።

እናንተ ብረት በመግፋት ያገኛችሁት ጥቅም ምንድነው? ኮሜንት ያድርጉልን።

ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡ 

fitness brandfitness

08/05/2026

ጭንቀት ውፍረትን የሚጨምረው እንዴት ይመስላችኋል?
1.የሆርሞኖች ለውጥ
- ረጅም ጊዜ የቆየ ጭንቀት በሰውነት ውስጥ የውጥረት ሆርሞንን ይጨምራል።  ይህም በጊዜ ሂደት ጣፋጭ እና ጨው የበዛባቸው ምግቦች እንዲያምሩን ያደርጋል። በዚህ ምክንያት ከልክ በላይ እንመገባለን።

2.የደም ስኳርን ማዛባት
- የደም ስኳር ስርዓትን በማዛባት በደማችን ውስጥ ስኳር እና የስብ መጠን እንዲጨምር ያደርጋል። ይህ በተለይ በሆድ አካባቢ ላይ በሰፊው ይከሰታል።

3.የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ
- ጭንቀት የድካም ስሜት በመፍጠር እና እንቅስቃሴ የማድረግ ፍላጎታችንን በመገደብ ስፖርት እንዳንሰራ ያደርጋል።

እነዚህ ሁሉ ሲደማመሩ በጭንቀት ምክንያት ውፍረትን እንጨምራለን። ሌሎች ሰዎች ደግሞ ሲጨነቁ ውፍረት ይቀንሳሉ። ይህንን በቀጣይ ፓስቶች የምንመለከት ይሆናል። እናንተ ሲጨንቃችሁ ትወፍራላችሁ ወይስ ትከሳላችሁ? ኮሜንት ያድርጉልን። 

ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡ 

07/05/2026

ስፖርት ቀን በቀን እየሰራችሁ ግን ለውጥ የማታዩት ለምን ይመስላችኋል?

ስፖርት መስራት ብቻ ሳይሆን እረፍት መውሰድ በራሱ ጡንቻ እንዲያድግ ያግዛል። በእረፍት ጊዜ በጡንቻ ውስጥ የፕሮቲን ምርት ይካሄዳል። ይህም በስፖርት ወቅት የተሰባበሩትን ጡንቻዎች መልሶ ለመጠገን ያግዛቸዋል። ያለእረፍት ቀን በቀን ስፖርት የምትሰሩ ከሆነ ይህ ጥገና አይካሄድም። በዚህ ምክንያት ጡንቻ ከማደግ ይልቅ እየቀነሰ እንዲሄድ ያደርጋል። በዛው ከቀጠላችሁ ደግሞ ለጉዳት ያጋልጣችኋል።

እረፍት የማድረግ ሌላው ጥቅም ደግሞ የውጥረት ሆርሞንን መቀነስ ነው። የውጥረት ሆርሞን በሰውነታችሁ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ሲገኝ የጡንቻ እድገትን ከመገደቡ በተጨማሪ በሽታ የመከላከል አቅምንም ይቀንሳል። ስለዚህ በሳምንት የእረፍት ቀን መመደባችሁን እንዳትረሱ።

ነገር ግን ይህ ማለት ጡንቻዎቹን እያቀያይሩ ሳምንቱን በሙሉ ቀን በቀን መስራት አይቻልም ማለት አይደለም።

ለምሳሌ
ሰኞ - ደረት ፣ ሆድ እና ትራይሴፕስ
ማክሰኞ - ጀርባ ፣ ትከሻ እና ባይሴፕስ
እሮብ - እግር
ሃሙስ - ደረት ፣ ሆድ  እና ትራይሴፕስ
አርብ - ጀርባ ፣ ትከሻ እና ባይሴፕስ
ቅዳሜ - እግር
እሁድ ደግሞ እረፍት እያደረጉ መስራት ይቻላል።

ስፖርት ስትሰሩ ያስቸገራችሁ ነገር ምንድነው? ኮሜንት ያድርጉልን።

ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡ 

06/05/2026

ጀማሪ ብረት ገፊዎች ጂም ስትሄዱ እየተሳቀቃችሁ ተቸግራችኋል?

ጂም ስትጀምሩ ከሚያስቸግሯችሁ ነገሮች አንዱ የመሳቀቅ ስሜት እና በዛ ምክንያት አጉል ፉክክር ውስጥ መግባት ነው። ይህ ደግሞ ለጉዳት ሊያጋልጣችሁ ይችላል። ይህንን ማስቀረት የምትችሉባቸው 5 መንገዶች

1.ስሜታችሁን መቀበል
ይህ የሚጠበቅ ስሜት ነው። ብዙ ጀማሪዎች ይህንን ስሜት ይጋሩታል። ብቻችሁን አይደላችሁም።

2.ግልጽ የሆነ እቅድ ማውጣት
ሀሳብ እና ጭንቀት ለመቀነስ ግልጽ የሆነ እቅድ ይዛችሁ መሄድ ይኖርባችኋል። የምትሰሩትን ስፖርት ፣ ምን ያህል እንደምትሰሩና ለምን ያህል ደቂቃ እንደምትሰሩ ማወቅ ያስፈልጋል።

3.ትክክለኛ ጂም መምረጥ
ከእናንተ ግብ ጋር የሚጣጣም እና ምቾት የሚሰጣችሁ ጂም ውስጥ ብትቀላቀሉ ጥሩ ነው።

4. ከጓደኛ ጋር መሄድ
ከጓደኛ ጋር ስትሰሩ የመደጋገፍ ስሜት ይኖራል። ይህም ብቸኝነት እንዳይሰማችሁ እና የጭንቀት ስሜታችሁ እንዳይባባስ ያደርጋል።

5.ሰአት መምረጥ
ሰው በማይበዛበት ሰአት መሄድ ትችላላችሁ።

እናንተ በጂም ውስጥ አጉል ፉክክር እና ጭንቀት ለመቀነስ የምታደርጉት ምንድን ነው? ኮሜንት ያድርጉልን።

ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡ 

05/05/2026

በቀላሉ ቤቶ ሆነዉ ስፖርት የሚሰሩባቸዉ ዘመናዊ የመሮጫ ማሽኖች እና የስፖርት ሳይክሎች ከታዋቂዉ Brand Fitness Machines አስመጥተናል።

በሚፈልጉት ሰአት ቤቶ ስፖርት የሚሰሩበት ጤንነቶን የሚጠብቁበት እና ዉፍረት የሚቀንሱበት

1.ያስመጣነው የመሮጫ ማሽን
• 3.5 የፈረስ ጉልበት ያለው
• 16 ኬሜ በሰአት ፍጥነት መስራት የሚችል
• 15 ዲግሪ ዳገት መሆን የሚችል
• 6 ሾክ አብዞርቨር የተገጠመለት
• የሰውነት ማሳጀር ላዮ ላይ የተገጠመለት
• 2 ባለ 1 ኪሎ ዳምፔል ያለዉ
• የወገብ ስፖርት እና የሆድ ስፖርት መስሪያ አብሮት ያለው
• ታጣፊ እና በቀላሉ መንቀሳቀስ የሚችል
• የአዉሮፖ ስታንዳርድ እና ሀይል ቆጣቢ
• ከሁለት አመት ዋስትና ጋር
የመሮጫ ማሽን - 180,000 ብር

2.ያስመጣነው የስፖርት ሳይክል
• ዘመናዊ ሞኒተር ላዮ ላይ ያለዉ
• የሰሩትን ሰአት ይይዛል
• የሰሩትን ኪሎሜትር ይመዘግባል
• የሚሰሩበትን ፍጥነት ይናገራል
• ያቃጠሉትን ካሎሪ ይናገራል
• የአዉሮፖ ስታንዳርድ
• ከሁለት አመት ዋስትና ጋር
የስፖርት ሳይክል - 75,000 ብር

ዛሬዉኑ ገዝተዉ ዘመናዊ ቤቶ ዉስጥ የጎደለዉን GYM ያሙሟሉ

ሁለቱንም አንድ ላይ ለሚገዙ ደንበኞቻችን - 250,000 ብር ብቻ

ይዘዙን ቤቶ ድረስ ከነፃ ዲሊቨሪ ጋር

ስልክ - 09-53-01-23-45

አድራሻ
📍አዲስ አበባ - ቦሌ ፣ ደምበል አደባባይ ፣ ራይዚንግ ስታር ህንፃ ፣ 11ኛ ፎቅ

📍አዳማ - ፖስታ ቤት ፣ ካራማራ ሆቴል ጀርባ ፣ ናፍራን ሞል ፣ 3ኛ ፎቅ ፣ 305

📍መቀሌ - ቀበሌ 17 ፣ አክሱም ሆቴል ፊት ለፊት ፣ ኣፀደ ወ/ሩፋኤል ህንፃ ፣ 3ኛ ፎቅ ፣ 312

📍ሀዋሳ - ፒያሳ ፣ አልያንስ ህንፃ ፣ 2ኛ ፎቅ ፣ 261

📍ድሬዳዋ - ሳቢያን ፣ ድሬ ሞል ፣ 3ኛ ፎቅ ፣ 309

📍 ጅማ - መርካቶ ፣ አዋሽ ህንፃ ፣ 2ኛ ፎቅ ፣ 206

📍 ባህር ዳር ፣ ፖፒረስ አደባባይ ፣ አድተራ ህንፃ ፣ ግራዉንድ ፣ ቁጥር 16

ብራንድ ፊትነስ
#ስፖርት

05/05/2026

እንኳን ለኢትዮጵያ አርበኞች ድል መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ!
ብራንድ ፊትነስ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
#የአርበኞችድል #አርበኞች

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Addis Ababa