Robust School

Robust School

Share

Official page to connect with our school community

29/03/2020

የተከበራችሁ ወላጆች እና ተማሪዎቻችን እንደምን ሰነበታችሁ። እስከ አሁን በሰላም እና በጤና ያቆየንን አምላክ እያመሠገንን የሚከተሉትን መልእክቶች እናስተላልፋለን።
1. ለወላጆች :
❤ ለእረፍቱ ጊዜ የሚሆን መልመጃ ወይም ሌላ ስራ መጽሀፍ፣ ለመስጠት ወላጅን እና መምህራንን መጥራት ካለዉ ስጋት አንጻር ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን አልመረጥነዉም። በተቻለ መጠን ከ 1ኛ - 8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ሁሉም ነገር እጃቸዉ ላይ ስላለ እንዲያነቡ ያበረታቷቸው።
❤ የ ኬ ጂ ተማሪዎች ፊደላትን እና ቁጥሮችን እንዳይረሱ እየጻፉ አና እንዲጽፉ እያደረጉ ያለማምዷቸው። የተረት መጽሐፍትን ያንብቡላቸው ማንበብ የሚችሉትን ደግሞ ያስነብቧቸው።
❤❤ ከዚህ በተረፈ ይህን መጥፎ ደዌ ከምድራችን አጥፍቶ ሲያገናኘን እየተመካከርን የማናካክሰዉ ነገር አይኖርም ሁሉም ነገር በእጃችን ስለሆነ አትስጉ። አሁን ላይ ማሰብ እና መስራት ያለብን እኛንም ልጆቻችንንም ከበሽታው በመከላከሉ ላይ መሆን አለበት። ለዚህም በየሐይማኖታችን እንፀልይ ፤ ተገቢዉንም ጥንቃቄ እናድርግ።
❤ በሚባክኑት ጊዜያት ልክ የትምህርት ጊዜው እንደሚራዘምም መንግስት ገልጿል።
❤ የሚከተሉትን መልእክቶች ለልጆቻችን ያስተላልፉልን

ለተማሪዎች:
❤ ወላጆቻችሁን ስሙ
❤ ቤታችሁ አርፋችሁ
በመቀመጥ ጤናችሁን ጠብቁ
❤ትምህርት ቤት የተዘጋው ኮሮና ትምህርት ቤት ብቻ ይከሰታል ተብሎ አይደለም። በየሠፈሩም ሊከሰት ስለሚችል ከቤት ባለመውጣት ጤናችሁን ጠብቁ። ብዙ የጨዋታ ጊዜያት ይመጣሉ። የጥንካሬ እና የእዉቀት መለኪያዉ የወላጅ ፣ የመምህር እና የባለሙያ ምክር መስማት ነው።
❤ በየቀኑ በክፍለጊዜያችሁ መሠረት አጥኑ። በረፍት ሰዓት እረፉ። በምሳ ሰዓት ምሳ ብሉ።
😂 ። ጤናችሁን ጠብቁ። እስከምናገኛችሁ በጣም ናፍቃችሁናል።
😂😂 አትጨነቁ ፣ ፀልዩ ፣ ተጠንቀቁ
❤❤❤ ፈጣሪ ይጠብቃችሁ።

29/03/2020

Hello, this is our school's official page. Keep following us for upcoming updates. Be Safe

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address


Addis Ababa