Ethiopian Technical University

Ethiopian Technical University

Share

(ETU)

Photos from የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት / FDRE TVT Institute's post 05/10/2025
Photos from FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)'s post 05/05/2025
06/04/2025
05/04/2025

አስራ አምስተኛው ሳምንት የጥናትና ምርምር ጉባዔ የቴክኖሎጂ ሐሳብ በያዙ የምርምር ውጤቶች ላይ ተመስርቶ ተካሄደ።
******ጥር 28/2017 ዓ.ም******

በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በየሳምንቱ እየተደረገ ያለው የጥናትና ምርምር ሴሚናር በ15ኛ ሳምንት መርሐግብር አንድ የውጭ አገር አሠልጣኝ እና አንድ የክህሎት ኢትዮጵያ ተሳታፊ ባቀረቧቸው ሁለት ጥናቶች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ተከናውኗል።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ ዶ/ር አበበ ጥበቡ ጥናቶቹ ቴክኖሎጂና ፈጠራን የሚያበረታቱ መሆናቸውን ገልጸው ኢንስቲትዩቱን ጨምሮ ተቋማት ተቀናጅተው እውን ያደርጓቸዋል ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

የዝሆኔ በሽታ ተጠቂዎችን ማገዝን ትኩረቱ ያደረገውና A Customized Designed Footwear for Ethiopian Podoconiosis በሚል ርእስ የተሰራተው የኩማራቨል ሻንሙጋም ጥናት አንዱ ነው።

የዝሆኔ በሽታ ታማሚዎች እንደልብ ተንቀሳቅሰው መስራት የሚያስችል ምቹ ጫማ ለመስራት የሚያስችል ሲሆን ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ሲሆን ሚሊዮኖች ዜጎችን ለመጥቀም ያግዛል ተብሏል።

ኢንስቲትዩቱ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ ወደተግባር እንዲያስገባም ተጠቁሟል።

ሁለተኛውና ዘመናዊ መስኖ ላይ ትኩረቱን ያደረገው የጥናትና ምርምር ስራ ፕሮጀክት የክህሎት ኢትዮጵያ በሆነው ወጣት አንደበት ግዛው እና ጓደኞቹ የቀረበ ነው።

የጥናቱም ርዕስ Projectile Waterflow for Efficient Irrigation Systems: Mathematical and Physical Perspectives የሚል ሲሆን አንድ ቦታ የሚገኝን የውሐ ሐብት አስቸጋሪ መልክዓምድርን ተሻግሮ ጥቅም ላይ የሚውልበት ቦታ ላይ የሚያደረስ የፈጠራ ዘዴን የያዘ ነው።

ይህም ምንም አይነት የኤሌክትሪክ ወይም ሌላ የሐይል አማራጭ ጥቅም ላይ ሳይውል በግፊት ብቻ ለመስራት የታለመ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ተብሏል።

ወጣቶቹ ይህንን የጥናትና ምርምር ስራ ወደተግባር ለመለወጥ ያቀረቡተትን የንድፈሐሳብ ጥናት በተግባር ለመሞከር እየተዘጋጁ መሆናቸውንም አንስተዋል።

በውሃ ሀብት የበለጸገች ኢትዮጵያ አስቸጋሪ የመልክዓምድር አቀማመጦችን በመሻገር ግብርናን ለማዘመን የሚያግዙ ሀሳቦች እንዲቀርቡ ኢንስቲትዩቱ እገዛ ማድረጉን እንደሚቀጥል ከቀረቡት ሀሳቦች ለማወቅ ተችሏል።

ዌብሳይት http://www.ftveti.edu.et/
ፌስቡክ https://www.facebook.com/TVTI.EDU.ET
ቴሌግራም https://t.me/fdretvtinstitute
ቲክቶክ

21/02/2024

የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ እና አቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንደስትሪ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት አካሔዱ፡፡
*******************የካቲት 13/2016****************

በዩኒቨርሲቲው እና በኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግዱፕ የአቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንደስትሪ ጋር በስልጠና፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራ እና በኢንተርፕራይዝ ልማት ዙሪያ አብሮ ለመስራት የሚያስችል የትብብር ውይይት አካሔዱ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ትብብሩ ጥራት ላለው ስልጠና፣ ለቴክኖሎጂ ፈጠራ እና ለኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ልማት ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል፡፡

እንደ ዶ/ር ብሩክ ከድር ገለጻ ይህ አገራዊ ተልዕኮ እየተወጣ የሚገኝ ግዙፍ ኢንደስትሪ የበለጠ ጠንካራ ተቋም እንዲሆን ለማስቻል በዘመናዊ ማሽነሪዎች የተደራጀው፣ በማሰልጠን የካበተ ልምድ ያለው ኢንስቲትዩቱ ሰፊ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ትብብሩ በሦስት ቁልፍ ጊዳዮች ላይ አተኩሮ እንደሚካሔድ የተናገሩት ዶ/ር ብሩክ #በስልጠና ዙሪያ የኢንደስትሪው ሙያተኞችን ኢንስቲትዩቱ አቅማቸውን በማጎልበት እንደሁም የዩኒቨርሲቲ ሰልጣኞች በኢንደሰስሪ የተግባር ስልጠና እንዲሰለጥኑ በማድረግ አብረው ይሰራሉ ብለዋል፡፡
#በቴክኖሎጂ ልማት ስራ በዝርዝር በሚለዩ ፍላጎቶች ላይ በትብብር እንደሚሰሩ ገልፀው #በኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፍም ኢንደስትሪው ከኢንስቲትዩቱ ቴክኖቢዚያ ኢንተርፕራይዝ ጋር አብሮ የሚሰራበት ሁኔታ ይፈጠራል ብለዋል፡፡

የአቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንደስትሪ ምክትል ስራ አስኪያጅ እና ኦፕሮሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ ኢንደስትሪያቸው ለታቁቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና ሐይል፣ ለኢትዮ ቴሌኮም፣ ለስኳር ፋብሪካዎች እና ለሌሎችም ምንግስታዊና የግል ተቋማት ልዩ ልዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው ተቋሙ በበለጠ ጥራት፣ ባደገ ቅልጥፍና፣ ጥራት ባለው ምርት ወደ ደንበኞቹ እንዲደርስ የኢንስቲትዩቱ አብሮ መስራት ትልቅ እገዛ ይኖረዋል ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡፡
የኢንደስትሪ ሙያተኞች ዘመኑ የደረሰበትን ክህሎት እንዲጨብጡ ተከታታይነት ያለው ስልጠና ከኢንስቲትዩቱ የማግኘት ፋለጎት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ በዝርዝር የስራ አፈጻጸም ጉዳዮች ዙሪያ ውይይ እንደሚካሔድ ተጠቅሷል፡፡

Photos from South Radio and Television Agency's post 18/02/2024
Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Lambert
Addis Ababa