ሂዳያ ኢስላማዊዊ ገፅ
አላማችን ኢስላምን በጥቂቱ በማስተዋወቅ የሂዳያ ሰበብ መሆን
10/04/2022
❤️የአላህ መልዕክተኛ ነብዩ ሙሀመድ (ሰ ዐ ወ) እንዲህ ብለዋል ፡ እስቲግፋር የሚያዘወትር ሰው አላህ ከሁሉም ሃሳብ ነፃ ያወጣዋል ። ከሁሉም ጥበት መውጫ ያበጅለታል። ካሰበበት ቦታም ሲሳይን ይለግሰዋል። ብለዋል።
📖የአለህ መለእክተኛ በአላህ ይሁንብኝ እኔ በቀን ከሰባ ጊዜ በላይ ወደ አላህ ተመልሼ ምህረትን እጠይቃለሁ "እኔ በቀን መቶ ጊዜ ወደ አላህ ተመልሼ ምህረትን እጠይቃለሁ "
📖በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡አል-ዙመር - 53
📖ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡ እነዚያም አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጣል፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
ሱረቱ አል-ፉርቃን ከ 68__70
📖‹‹ ... ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ፡፡››
🍂 ሱረት አል-ኑር 31📚
📖‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ ንፁህ የኮነችን ፀፀት በመፀፀት ወደ አላህ ተመለሱ…..››አል ተህሪም 8
📖‹‹ ....አላህ (ከኃጢኣት) ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው፡፡››አል በቀራህ 222📚
📖በሐዲሰል አል ቁዱስ🌷
💌አላህ((ሱ ወ)) የአደም ልጅ ሆይ! በለመንመከኝና ከኔ በከጀልክ ቁጥር ያለብህን ወንጀል ሁሉ እምርልሃለሁ ግድ የለኝም።
የአደም ልጅ ሆይ! ወንጀሎችህ የሰማይ ዳመና ድረስ ቢደርስና ከዚያም የኔን ምህረት ብትጠይቅ እምርሃለሁ።
💌የአደም ልጅ ሆይ! መሬት ሙሉ ወንጀል ይዘህ ወደኔ ብትመጣና በኔ አንዳች ነገር ሳታጋራ ብትገናኝ እኔም መሬት የሚሞላ ምህረት ይዤ እጠብቅሃለሁ።ማለቱን
እናውስታውሳልን
┄┉┉✽🌹የሱሀቦች ዘመን🌹»✽┉┉┄
✍ሙሀመድ & ሳኒ ይመር
┄┄┉┉✽»🌹✿🌹»✽┉┉┄┄
https://t.me/joinchat/Vu1GglMumUw6ORpA
10/04/2022
❤️ ሰላት የኢስላም ምሰሶ ናት ❤️
ሰላታቹሁን አደራ ብለዋል ረሱል صلى الله عليه وسلم
ለምን አትሰግድም ወንድሜ? ለምን አትሰግጂም እህቴ? እስካልሰግድክ ድረስ ከእድሜህ ላይ በረካ ይነሳል .እስካልሰገድክ ድረሰ ከፊትህ ላይ ኑር ይገፈፋል...
እስካልሰገድክ ድረስ ምትሰራው ስራ ሁሉ ተቀባይነት የለውም.
እስካልሰገድክ ድረስ ዱዓህ ተሰሚነት አያገኝም.
•እሰካልሰገድክ ድረስ ሌሎች ሚያደርጉልህ ዱዓም አይጠቅምህም. ስትሞት፦
እስካለሰገድክ ድረስ እማትረባና የተዋረድክ ሆነህ ትሞታለህ.
እስካልሰገድክ ድረስ እንደተራብክ ትሞታለህ.
እሰካለሰገድክ ድረስ እንደተጠማህ ትሞታለህ. የባህርን ውሃ እንዳለ ብትጠጣ ጥምህን
አይቆትጥልህም. ቀብር_ውስጥ፦
እስካለሰገድክ ድረስ ጎንና ጎንህ እስኪተላልፈ ድረስ ቀብርህን አሏህ ያጠብብሃል.
እስካለሰገድክ ድረስ ቀብርህ ውስጥ እሳት ተቀጣጥሎብህ ነጋ ጠባ ትሰቃያለህ. እስካለሰገድክ ድረስ በቀን አምስት ጊዜ ከእባብ ጋር ቀጠሮ ይኖርሃል ! የፈጅርን ሰላት ባለመስገድህ ሲያሰቃይህ ዙሁር ይደረሳል፤የዙሁርን ሰላት ባለመሰገድህ ሲያሰቃይህ አስር ይደርሳል ፤እንደዚህ እያለ ስቃይህ ይቀጥላል (አንድ ጊዜ ምትመታው እሰከ 70 ክንደ ያህለ መሬት ውስጥ ያሰምጠሃል).. የቂያማለት፦ወንድሜ አሁንም አትሰግድም ?? እህቴ አሁንም አትሰግጂም ??
🕌Islamic Page & Channel 🕌
┄┉┉✽🌹የሱሀቦች ዘመን🌹»✽┉┉┄
✍ሙሀመድ & ሳኒ ይመር
┄┄┉┉✽»🌹✿🌹»✽┉┉┄┄
Join and Share our Page and Channel
👍 Facebook Website :Www.Suhabaa.com
👍 Telegram Link:
https://t.me/joinchat/Vu1GglMumUw6ORpA
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
ኢትዮጵያ
Addis Ababa