17/05/2026
በድጋሚ የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የሚጠባበቁ ተማሪዎች እስከ ግንቦት 12 ድረስ ምዝገባቸውን እንዲያካሂዱ ጥሪ ቀርቧል።
የቅድመ-ምረቃ ትምህርት የመውጫ ፈተና በድጋሚ በግል ለመፈተን እየጠበቁ የሚገኙ አመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ግንቦት 08 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት ይካሔዳል፡፡
የመመዝገቢያ ሊንኩን https://exam.ethernet.edu.et በመጠቀምና የተዘረዘሩ መስፈርቶችን በማሟላት እስከ ግንቦት 12/2018 ዓ.ም መመዝገብ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ተፈታኞች የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር በቴሌብር በኩል መክፈል የሚጠበቅባቸው ሲሆን ፤ ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ የግድ የሚያስፈልግ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የ2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ከሰኔ 02-12/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወሳል፡፡
16/03/2026
CAMBALLALA !!!
እንኳን ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፍቼ ጨምበላላ አደረሳችሁ !!! በዓሉ የሠላምና የፍቅር እንዲሆን #አትላስ ቢዝነስ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ መልካም ምኞቱን ይገልጻል !!
27/02/2026
#የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በመጪው ምርጫ ተሳተፍው ወደትምህርታቸው ይመለሳሉ፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር
ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች በመጪው አገር አቀፍ ምርጫ የሚሳተፉበትን አግባብ በማስመልከት ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስኩላር ልኳል (ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ የደብዳቤውን ትክክለኛነት አረጋግጠጧል፡፡)
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሚካሔደው አገር አቀፍ ምርጫ ላይ ተማሪዎች መምረጥ እንዲችሉ፣ የሚሰጠው ትምህርት ከምርጫው በፊት እንዲጠናቀቅና ተማሪዎች ወደ ቤታቸው እንዲሔዱ ታስቦ እንደነበር ሚኒስቴሩ አስታውሷል፡፡
ይሁን እንጂ ይህ አካሔድ በትምህርት አሰጣጥና ጥራት እንዲሁም በተማሪዎች የፈተና ዝግጅትና ስኬታማነት ላይ በሚኖረው አሉታዊ ተፅዕኖ ምክንያት አስቸጋሪ ሆኖ መገኘቱን ገልጿል፡፡
"ተማሪዎች ሔደው መርጠው ለመመለስ የሚያስፈልጋቸው ቀናት ብቻ ታስቦ እንዲፈቀድላቸውና መርጠው እንደተመለሱ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ" የትምህርት ሚኒስቴር እና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አመራሮች ከመግባባት ላይ መድረሳቸውን ሰርኩላሩ ጠቁሟል፡፡
በመሆኑም ተማሪዎች በተፈቀደላቸው ቀናት ውስጥ ሔደው መርጠው መመለስ እንዲችሉ ፍቃድ እንዲሰጣቸው ሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱን አሳስቧል፡፡
26/02/2026
የፈተና መርሐግብሩ ላይ ማስተካከያ ተደረገ።
አርብ ከቀኑ 5:00-7:30 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ሙሉ ቀን በሚሰጡ የመውጫ ፈተናዎች ላይ ማስተካከያ ተደርጓል።
አርብ ከቀኑ 5:00-7:30 ሰዓት የሚሰጠው ፈተና ከጁምዓ ሶላት ስግደት ጋር በተያያዘ እንዲሁም ቅዳሜ በሚሰጡ ፈተናዎች ላይ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን በኩል ቅሬታዎች መቅረባቸውን ተከትሎ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማስተካከያ ማድረጉ ታውቋል።
በዚህም አርብ በሁለተኛ ክፍለ-ጊዜ (ከ5:00-7:30) ፈተናዎች ላይ ሽግሽግ የተደረገ ሲሆን፤ ቅዳሜ ፈተናው የማይሰጥ ይሆናል።
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተስተካከለውን መርሐግብር (ከላይ ተያይዟል) ለተፈታኝ ተማሪዎቻቸው በማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ።
24/02/2026
የ2018 አጋማሽ ዓመት የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና መስጫ የተሻሻለው የጊዜ ሰሌዳ
በተሻሻለው መርሐግብር መሰረት ፈተናው ከየካቲት 18-27/2018 ዓ.ም ለስምንት ቀናት ይሰጣል።
24/02/2026
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዛሬ የተጀመረው የመውጫ ፈተና መሸጋሸጉን ገለጹ።
የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቷ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎትን ዋቢ በማድረግ ባሰራጩት መልዕክት ፤ የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) ዛሬ መጀመሩ ገልጸዋል።
" ነገር ግን ያልታሰበ የኃይል መቆራረጥ ችግር በዳታ ማዕከል ላይ በማጋጠሙ ችግሩን በመፍታት እንደገና ለማስጀመር ጥረት የተደረገ ቢሆንም የፕሮግራም መዛባትን አስከትሏል " ብለዋል።
በዚህም ምክንያት የፈተናው ሙሉ ፕሮግራም በአንድ ቀን መሸጋሸጉን ገልጸዋል።
ሁሉም ፕሮግራሞች የዛሬን ጨምሮ ባሉበት ክፍለ ጊዜ ላይ ሆነው በተዋረድ በአንድ ቀን የተሸጋሸጉ መሆኑን አማልክተዋል።
ዛሬ ፈተና ጀምረው የነበሩ ተፈታኞችም እንደሙከራ ፈተና (Mock Exam) በመውሰድ ነገ በተመሳሳይ ሰዓት እንደገና ይፈተናሉ ተብሏል።
24/02/2026
ማስታወሻ ለመውጫ ፈተና ተፈታኞች፡-
በመውጫ ፈተና ወቅት ከተፈታኞች የሚጠበቁ ነገሮች፤
1. ተፈታኝ ተማሪዎች በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የሞባይል ስልክ፣ ሚሞሪ ያለው የእጅ ሠዓት፣ ሳይንቲፊክ ካልኩሌተር፣ ማንኛዉም የጦር መሳሪያ የተጭበረበሩ ሰነዶችና የራስ ያልሆነ መታወቂያ ይዞ መገኘትየለባቸዉም፡፡
2. ተፈታኝ ተማሪዎች ከተመደቡበት ክፍል ውጪ መፈተን ውጤት ያሰርዛል፡፡
3. ተፈታኞች ከ3ዐ ደቂቃ ቀድመው በተመደቡበት ክፍል መገኘት አለባቸው፡፡ አላስፈላጊ ውዝግብ መፍጠር የለባቸውም፡፡
4. ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና አስፈፃሚን ትዕዛዝ ማክበር አለባቸው።
5. ተፈታኞች የፋይዳ መታወቂያ መያዝ ግዴታ ነው፡፡ እንዲሁም ራሳቸውን የሚገልፅ መታወቂያ መያዝና ለሚጠይቃችሁ ፈተና አስፈፅሚ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡
6. በፈተና ወቅት የፈተና መልስ ለሌላ ተፈታኝ መስጠት ወይም ማሳየት ወይም ማስካረጅ አይቻልም፡፡
7. በሌላ ስም፣ መለያ ቁጥር (Username) እና የይለፍ ቃል (Password) መፈተን አይቻልም፡፡
ከላይ የተዘረዘሩተን እና ሌሎች የፈተና ስርዓቶችን የጣሰ ውጤቱ ተሰርዞ በዲሲፕሊን ጥሰት ይጠየቃል፡፡
23/02/2026
Dear ABTC Campus Representatives,
The entrance ticket is now mandatory for first sitter students. Please ensure that your students obtain their tickets by providing them with their newly assigned username and password from your side. This will be required for eligibility verification when they report to their exam centers.
Please note that if a students exam center is at Addis Ababa University, the specific location and session time are also indicated on the entrance ticket.
URL : https://verify.ethernet.edu.et
Thank you.
22/02/2026
University
Exit Exam Schedule
17-6-18
28/01/2026
ስለ መውጫ ፈተና
*//*
ጥር 20/2018 ዓም
የመውጫ ፈተና (Exist Exam) የሚሰጥበት ጊዜ ከየካቲት 16 እስከ የካቲት 27 ቀን 2018 ዓ.ም መሆኑ ተገለጸ።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባወጣው መርሃ-ግብር መሰረት፣ የ2018 ትምህርት ዘመን አጋማሽ የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) ከየካቲት 16 - 27 ቀን 2018 ዓ.ም ይሰጣል ተብሏል።
አትላስ ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ