05/08/2025
ትምህርት ለትውልድ በሚል መሪ ሀሳብ ለዘራይ ደረስ ትምህርት ቤት የትምህርት ቁሳቁስና ግብዓት ድጋፍ ተደረገ።
በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 7 ትምህርት ለትውልድ አስተባባሪ ኮሚቴ ትምህርት ለትውልድ በሚል መሪ ሀሳብ ለዘርዓይ ደረስ ትምህርት ቤት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አካሂዷል።
ድጋፍ የተደረጉት የትምህርት ቁሳቁሶችና ግብዓቶች በዋናነት ኮምፒውተር ፣መፅሐፍት፣ላፕቶፕ ፣ፕሪንተር፣ጠረጴዛና ወንበር ናቸው።
በድጋፍ ፕሮግራሙ የወረዳው አስተባባሪ ፣ አመራሮችና መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል።