17/06/2025
Yeka industrial college
Seek Wisdom,Elevate your Intellect and Serve Humanity"
17/06/2025
17/06/2025
የካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በከተማ አቀፍ ደረጃ በ15 ኛው ቴክኒክና ሙያ ሳምንት "ብሩህ አእምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘውን ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ ፡፡
ሰኔ 09/2017 ዓ.ም
የካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ "ብሩህ አዕምሮዎች፣ በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ቃል ለ15 ተኛ ጊዜ በከተማ አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው ቴክኒክና ሙያ ሳምንት አንድ አካል በሆነው ስፖርታዊ ውድድር በአሰልጣኞች እግር ኳስ 2ተኛ ፣ ቴብል ቴኒስ 4ተኛ ፣ ቮሊቮል 2ተኛ እንዲሁም በሰልጣኞች እግር ኳስ 4ተኛ ደረጃን በመያዝና በአጠቃላይ 2 ብር ሜዳሊያ እንዲሁም በሁለት ዘርፍ 4 ተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል ፡፡
በሁሉም ዘርፎች ለተመዘገበው ውጤትና የቡድኑ አባላት ላደረጉት ከፍተኛ ጥረት ኮሌጁ ልባዊ ምስጋናውን እያቀረበ በቀጣይ ኮሌጁን ወክለው ለሚደረጉ ስፖርታዊ ውድድሮች ከዚህ በተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉንም ተናቦና ተቀኛጅቶ መስራት እንደሚጠብቅ ተገልፆል ፡፡
የተሳታፊ ቡድኑ አባላት በበኩላቸው ለተደረገላቸው ድጋፍ እና ማበረታቻ አመስገነው በቀጣይ ለሚካሄዱ ውድድሮች ከዚህ በላይ ጠንክሮ በመስራት ራስን ለውጤት ማዘጋጀት ማሰባቸውን ገልፀዋል ፡፡
10/02/2025
በኮሌጁ በዘላቂነት የሚተገበሩት የሌማት ቱርፋት ሥራዎች ተጠናክረዉ ቀጥለዋል ፡፡
ጥር 29፤2017 ዓ.ም (የካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ኮምኒኬሽን)
የካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሌማት ቱርፋት ተግባር በማጠናከር ለኮሌጁና አከባቢ ማህበረሰብ ጥሩ የስራ ባህልን በመፍጠርና የአመጋገብ ባህልን በመቀየር በኩል ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ በመገንዘብና በሀገርና በከተማ ደረጃ የተጀመረውን “ ምግባችንን ከጓሮአችን ” የሚለዉን መርህ በመከተል ፍጆታን መሰረት ያደረጉ የሌማት ቱርፋት ስራዎች እየተገበረ ይገኛል ፡፡
የዚሁ ተግባር አካል የሆኑትን የእንቁላል ምርትን ለማሳደግ 1,100 የእንቁላል ጣይ ዶሮዎችን በማስገባት ምርቱን በ4 እጥፍ ለማሳደግና በዚህም ለኮሌጁ ብሎም ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚያስፈልጉ ግባዓቶችን በራስ አቅም የመሸፈን ስራው ተጠናክሮ እንደቀጠለ ማሳያ መሆኑን ያመላክታል በማለት የኮሌጁ ም/ዲን አቶ ረቢራ ዱጋሳ ገልፀዋል ።
24/01/2025
ኮሌጁ የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ተካሄደ ፡፡
ጥር 16፣2017 ዓ.ም (የካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ኮምኒኬሽን)
የካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ኮሌጁ ላለፉት 6 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ነጋሽ ተስፋዬ ጨምሮ በኮሌጁ የተለያየ ዘርፍ የሚመሩ ም/ዲኖች እንዲሁም የኮሌጁ ሰራተኞች በተገኙበት ግምገማውን አካሄደ ፡፡
የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ነጋሽ ተስፋዬ÷" የሪፖርት ግምገማው ከዚህ ቀደም ብሎ ለኮሌጁ ፕሮሰስ ካውንስል፣ አካዳሚክ ኮሚሽንና ማንጅመንት አባላት መቅረቡን አስታዉሰው የሪፖርት ግምገማው ባሳለፍነው 6 ወራት የኮሌጁን መሪ እቅድ መሰረት አድርጎ ሲተገበር በነበረው እቅድ አፈፃፀም የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች በመገምገም ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ አጎልብተን፤ድክመቶቻችንን አርመን ለቀጣይ ዕቅዳችን በተሻለ ፍጥነትና ቅልጥፍና ለመፈጸም የሚያስችሉ ግብዓቶችን የምናገኝበት ነው" ሲሉ የሪፖርት ግምገማዉን አስጀምረውታል ፡፡
የ 2017 በጀት ዓመት 6 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በኮሌጁ እቅድና በጀት ክትትል ኃላፊ አቶ ሀብታሙ በየነ በኩል ለውይይት ቀርቧል ፡፡
የዉይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የኮሌጁን የመፈፀም ብቃት ከፍ ያደርጋሉ ያሏቸዉን ገንቢ ሃሳቦችን በማንሳት ተናቦና ተቀናጅቶ በመስራት በጋራ እቅዱን ለማሳካት ተናቦና ተቀናጅቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል ፡፡
በቀረበው ሪፖርት ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች የኮሌጁ አመራሮች በየዘርፋቸዉ ሰፋ ያለ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በመጨረሻም የኮሌጁን ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በማስቀመጥና ይህንንም ለማሳካት ኮሌጁ ከባለድርሻ አካላት ጋር ጭምር በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ በማሳሰብ የሪፖርት ግምገማው ተጠናቋል ፡፡
29/11/2024
በስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የተመራ ቡድን በኮሌጁ ድጋፍና ክትትል አካሄደ ፡፡
ህዳር 20፤2017 ዓ.ም (የካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ኮምኒኬሽን)
በየካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ እንዲሁም ከየካ ክ/ከተማ ስራና ክህሎት ፅ/ቤት የተወጣጡ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ቡድን ድጋፍና ክትትል ተደረገ ፡፡
የድጋፍና ክትትል ቡድኑን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለትና አዲሱን የቴክኒክና ሙያ እሳቤ ጨምሮ 11ዱን የዘረመል አተገባበረና የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት የኮሌጁን እቅድ አፈፃፀም የተመለከተ ገለፃ በኮሌጁ ዋና ዲን ወ/ሮ ሰርካለም ጌታቸው አቅርበው ውይይት ተደርጓል ፡፡
በዚህም የክትትል እና ድጋፍ ቡድኑ አባላት በኮሌጁ የተሰሩና ዉጤት እያስመዘገቡ በሚገኙ እንዲሁም በምርጥ ተሞክሮነት ሊቀመሩ በሚችሉ ስራዎች የኮሌጅ ምድረ ገፅን ማስዋብ፣በከተማ ግብርና (ከብት እርባታ እና የዶሮ እርባታ ) ፣ ዘመናዊ ቤተ-መፅሀፍት አደረጃጀት እንዲሁም የማሰልጠኛ ወርክሾፖችን ማዘመን ላይ የተሰሩ ስራዎችን በአካል ተዘዋወረው ጎብኝተዋል ፡፡
በመጨረሽም የክትትል እና ድጋፍ ቡድኑ አባላት በበኩላቸው ለተደርገላቸው አቀባበል አመስገነው አጠቃላይ በመስክ ምልከታው ላይ ኮሌጁ ለያዘው ዓላማ መሳካት የሚጠቅሙ ምክረ ሃሳቦችን በመስጠት የዕለቱ የስራ ላይ ጉብኝቱ ተጠናቋል ፡፡
14/11/2024
የካ ኢንዱስትሪያል iso 21001:2018 ለመተግበር የሚያስችለዉን ስምምነት ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲቲዩትጋር ተፈራረመ ።
ህዳር 05፤2017 ዓ.ም (የካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ኮምኒኬሽን)
የካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ተወዳዳሪ፣ ተመራጭ እንዲሁም ጥራቱን የጠበቀ ሥልጠና በመስጠት ሀገራዊ ብሎም ዓለማቀፋዊ ተወዳዳሪ የሰው ሀይል ለማፈራት iso 21001:2018 መተግበር እውቅና ለማግኘት እንደሚያስችል በስምምነቱ ወቅት ተገልፆል ፡፡
ስምምነቱን የካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዋና ዲን ወ/ሮ ሰርካለም ጌታቸው የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተርነት ዶ/ር መሰረት በቀለ ተፈራርመውታል ።
01/11/2024
በየካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የጋራ ዉይይትና የመስክ ምልከታ ተካሄደ ፡፡
ጥቅምት 22፤2017 ዓ.ም (የካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ኮምኒኬሽን)
የካ ኢንዳስትሪያል ኮሌጅ በዛሬው ዕለት በየካ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 ዋና አስተዳዳሪን አቶ ሚኪያስ ጨምሮ በወረዳው ተለያዩ ፅ/ቤት ኃላፊዎችና የቀጠና አመራሮች የተሳተፉበት አዳዲስ ሰልጣኞችን ወደ ቴክኒክና ሙያ በአጫጭርና በመደበኛ ስልጠና የሙያ ባለቤት ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የጋራ ወይይትና የመስክ ምልከታ አካሄዱ ፡፡
በዚህም አዳዲስም ሆነ ነባር የኮሌጁ ሰልጣኞች የሚሰለጥኑበትን የማሰልጠኛ ክፍሎችና ወርክሾፖች በተጨማሪም የኮሌጁን ላይብረሪ እንዲሁም በኮሌጁ የሚሰሩ የከተማ ግብርናና የሌማት ቱርፋት የምርት ስራዎችን በአካል ተዘዋውረው ጎብኝተውዋል ፡፡
በተያያዘም የኮሌጁን Online Registration system በተመለከተ አጭር ገላፃና ማብራሪያ የተሰጣቸው ሲሆን ተሳታፊዎችም በበኩላቸው ለተደረገላቸው አቀባበልና ማብራሪያ አመስግነው በቀጣይ በአጫጭርም ሆነ በመደበኛ ስልጠና ዜጎች በተለይም ወጣቶች የብቁ ሙያ ባለቤቶች በመሆን ራሳቸዉንና ቤተሰባቸውን ከማገዝ በተጨማሪ ሀገራቸዉን መጥቀም ይቸሉ ዘንድ የበኩላቸዉን ድርሻ እንደሚወጡና ለዚህም ከኮሌጁ ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸዉና ገልፀዋል ፡፡
በሙያው የመሚተማመን ብቁ ዜጋን ማፋራት ዋነኛ ዓላማችን ነው !!
የካ ኢንድስትሪያል ኮሌጅ
28/10/2024
26/10/2024
በ ኮሌጁ የ 2017 ሰልጣኞች ቅበላን አስመልክቶ የጋራ ውይይት ተካሄደ ፡፡
ጥቅምት 16፤2017 ዓ.ም (የካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ኮምኒኬሽን)
የየካ ኢንዳስትሪያል ኮሌጅ 2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞችን ቅበላ አስመልክቶ ለ ክፍለ ከተማ አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራኖች፣ የወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች እና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ያካተተ የጋራ ውይይት ተካሄደ ፡፡
በውይይቱም የካ ኢንዳስትሪያል ኮሌጅ ዋና ዲን ወ/ሮ ሰርካለም ጌታቸው÷የ2017 ትምህርት ዘመን በተለያየ የሙያ ዘርፍ ኮሌጁን ለሚቀላቀሉ ሰልጣኞች ምዝገባ መጀመሩን አስታውሰው በዚህም በኮሌጁ ለሰልጣኞች ቅበላ የተደረጉ ዝግጅቶች በተመለከተ የንድፈ ሀሳብ መማሪያ ክፍሎች ፣ የማሰልጠኛ ወርክሾፖች፣ በአዲስ መልክ የተደራጀ ቤተ መፅሃፍትን ጨምሮ ከዚህ በፊት በሰልጣኞች የተሰሩ ስራዎችን እና ሌሎች በኮሌጁ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለተሳታፊዎች ገለፃና በአካል ተዘዋወረው የጎበኙ ለተደረገላቸው ገለፃ አመስግነው በቀጣይ ከኮሌጁ ጋር በትብብር መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል ፡፡
የየካ ኢንዳስትሪያል ኮሌጅ በ2017 የትምህርት ዘመን በAgro_Food processing, Leather Technology, Garment Technology,Hotel and Tourism management, Construction Technology,Electirical and Electronics Technology,Surveying and Drafting Technology, Manufacturing Technology, Automotive Technology እና ሌሎች የስልጠና ዘርፎችን የሚሰጥ መሆኑ ተመላክቷል ።
በሙያው የመሚተማመን ብቁ ዜጋን ማፋራት ዋነኛ አለማችን ነው !!
የካ ኢንድስትሪያል ኮሌጅ
25/10/2024
ኮሌጁ አዳዲስ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ምዝገባ ጀመረ፡፡
ጥቅምት 15፤2017 ዓ.ም (የካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ኮምኒኬሽን)
የካ ኢንድስትሪያል ኮሌጅ የ2017 ዓ.ም አዳዲስ ሰልጣኞችን ዛሬ ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ∙ም በበየነ መረብ /online Registration/መመዝገብ ጀመረ።
በዛሬው የወረቀት አልባ ኦንላይን/Online Registration/ምዝገባ ላይ በ2017 ዓ.ም 12ኛ ክፍልን ያጠናቀቁና ከዚያ በፊት ጨርሰው የተቀመጠውን የቅበላ መስፈርት ያሟሉ አዳዲስ ሰልጣኞች መመዝገብ በይፋ ተጀምሯል ።
ኮሌጁ በ15 የስልጠና ዘርፍ ዓይነቶች እና ወደ 40 በሚደርሱ ሙያዎች እስከ 1529 የሚደርሱ አዳዲስ ሰልጣኞችን ከደረጃ 1 እስከ ደረጀ 4 ተቀብሎ ለማሰልጠን እቅድ ይዟል።
https://yic.aatvetb.edu.et/
በሙያው የመሚተማመን ብቁ ዜጋን ማፋራት ዋነኛ አለማችን ነው !!
የካ ኢንድስትሪያል ኮሌጅን የመጀመሪያ ምርጫችሁ አድርጉ፣፣
የካ ኢንድስትሪያል ኮሌጅ
አድራሻ፡ ፈረንሣይ ለጋሲዮን ወደ ብርት ደልድይ መሄጃ መዞርያ አደባባይ ።
ስልክ፡-+251111549309
+251111548511
Website:-httpts://yekaindustrialcollege.edu.et
P.O.box 30752
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the school
Website
Address
Addis Ababa