ባስኬቶ አልፋ

ባስኬቶ አልፋ

Share

ለማንኛውም መረጃ፤ ማስታወቂያ ለማሰራት እንዲሁም በነፃ ስለአከባቢያችሁ ለመላው አለም ለማስተዋወቅ በስልክ☎️0916172914/12376880 ወይም በቴሌግራም አድራሻችን ያግኙን https://t.me/+u-LTWUGf2TBmMTlk

Photos from EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት's post 05/06/2026
Photos from Basketo Zone Government Communication Affairs Department's post 05/06/2026
Photos from ጉርሻ page's post 02/06/2026
02/06/2026

ሕዝቡ ሕጋዊ ካልሆኑ ከማንኛውም ምንጮች ከሚወጡ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ
**********************

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መራጮች በትላንትናው ዕለት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በከፍተኛ ንቃት እና ትዕግሥት ድምፃቸውን ስለሰጡ አመስግኗል።

በምርጫ ሕጉ መሠረት ውጤት በቦርዱ ይፋ እስከሚሆን ድረስም በትዕግሥት እንዲጠብቁ እና ሌሎች አካላትም ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ፤ ሕዝቡም ከመሰል መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ ቦርዱ አሳስቧል።

01/06/2026

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ሒደት ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የድምፅ መስጠት ሒደቱ ከ12 ሰዓት በፊት ሰልፍ ይዘው የቆዩ መራጮች እስኪመርጡ ይቀጥላል አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፡፡

በዛሬው ዕለት ከጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝቡ በነቂስ በመውጣት ድምጹን እየሰጠ ይገኛል፡፡

01/06/2026

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ሒደት ሰልፍ ይዘው የቆዩ መራጮች እስኪመርጡ ይቀጥላል - ቦርዱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የድምፅ መስጠት ሒደቱ ከ12 ሰዓት በፊት ሰልፍ ይዘው የቆዩ መራጮች እስኪመርጡ ይቀጥላል አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፡፡

በዛሬው ዕለት ከጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝቡ በነቂስ በመውጣት ድምጹን እየሰጠ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስፈጸም ሒደት ላይ መሆኑ ይታወቃል።

ቦርዱ ድምፅ የመስጠት ሒደቱ እስከ 12 ሰዓት ሠልፍ ላይ የነበረው ድምፅ ሰጪ ድምፅ ሰጥቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድምፅ የመስጠት ሒደቱ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 49 (4) መሠረት ቦርዱ በልዩ ሁኔታ የድምፅ መስጫ ሰዓት ሊያራዝም እንደሚችል ይደነግጋል።

Photos from የቡርጂ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት / Burji Zone Prosperity Party Branch Office's post 01/06/2026
01/06/2026

"ሻወር ቤት ውስጥ ራቁቴን አስገብቶኝ፣ የቲቪውን ድምፅ ከፍ በማድረግ ንብረቴን ይዞብኝ ተሰወረ።"

የአካል ጉዳተኛው ደራሲ ማዕበል እንዳሻው ጥሪ፡
በረዳቱ ተዘርፎ ለአደጋ ተጋልጧል

በሸገር ሲቲ ኮዬ ፈጬ አካባቢ የሚኖረው ደራሲ ማዕበል እንዳሻው፣ በአካል ጉዳቱ ምክንያት በእርዳታ ላይ ጥገኛ መሆኑን የተጠቀመው ረዳቱ እጅግ አሳዛኝ እና የጭካኔ ድርጊት ፈጽሞበት ተሰውሯል።

ለተከታታይ ሦስት ዓመታት አብሮት የቆየውና ሲረዳው የነበረው በጸጋው ሳሙኤል ሻንቆ የተባለው ግለሰብ፣ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 7፡15 ገደማ ፍጹም የክህደት ድርጊት ፈጽሞባታል።

ግለሰቡ የደራሲ ሕይወት ለአደጋ በሚያጋልጥ መልኩ፣ ማዕበልን ሻወር ቤት ውስጥ ረዳት አልባ አድርጎ ካስገቡ በኋላ የጩኸቱ ድምፅ ወደ ውጭ እንዳይሰማ የቴሌቪዥን ድምፅን በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመር ዘረፋውን አከናውኗል።

የተዘረፉ ንብረቶች ዝርዝር፡

1. ሬድሚ 13 ፕሮ ፕላስ 5ጂ (Redmi 13 Pro+ 5G) ስልክ

2. አይፎን (iPhone) ስልክ

3. ሳምሰንግ ታብሌት (Samsung Tablet)

4. ሳምሰንግ ኤስ 24 (Samsung S24) ስማርት ስልክ

5. ፓወር ባንክ፣ ስማርት ሰዓት እና ኤርፎን

5. የተለያዩ ልብሶች፣ ጫማዎች እና 13,400 የኢትዮጵያ ብር በጥሬ ገንዘብ

ከቁሳቁሶቹ በላይ ደራሲ በከፍተኛ ልፋትና ጥረት ያዘጋጃቸው፣ ለተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሊቀርቡ የተዘጋጁ ውድ የስክሪፕት ድርሰቶች (ጽሑፎች) በእነዚሁ መሣሪያዎች ላይ በመሆናቸው፣ በደራሲው ላይ ከፍተኛ የስነ-ልቦና እና የኢኮኖሚ ቀውስ ፈጥሮበታል።

የሕግ አካላት ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተከታተሉት ሲሆን፣ ማህበረሰቡም ተጠርጣሪውን በፎቶ በመለየት መረጃ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

ማንኛውም ፍንጭ ወይም መረጃ ያለው አካል፡

በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በአካል በመቅረብ ወይም

በስልክ ቁጥር 0962017493 ቀጥታ በመደወል ለደራሲው እንዲያሳውቅ በአክብሮት ይጠየቃል።

ይህንን የጥበብ ሰው ለመደገፍ እና ፍትሕ እንዲያገኝ ለማድረግ መልዕክቱን Share በማድረግ ለሁሉም አጋሩ!

Via ማዕበል እንዳሻው

ጉርሻ page Subscribers

🌴🌴🌴

Photos from በባስኬቶ ዞን የላስካ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት Laska Communication's post 01/06/2026
Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Addis Ababa