12/08/2022
አስደንጋጭ ህግ ሊወጣ ነው፡፡
አዲስ የታራሚዎች መንደር ምስረታ ሊጀመር ነው፡፡
እሥር ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ሊዘጉ ነው!!!!
ህጎች ሊሻሻሉ ነው!! ላለፉት አመታት የምናውቃቸው ማረሚያ ቤቶች ደሃ ሃገር ን ይበልጥ ደሃ የሚያደርጉ ፤ በሙስና እና የተለያዩ ወንጀሎችን የሚፈጽሙትን ወንጀሎች አሁን ያለው ማረሚያ ቤት ከወጪ ቀሪ በሙስና ሀብት ታራሚዎችን የህግ አካላት አንዳንድ ግለሰቦችንም በወንጀል አትራፊ በማድረጉ፤ ወንጀል ሰርቶ እስር ቤት መግባትን ዝናን እና ታወቂነትን ለማትረፍ ጭምር የሚመኙና አስበውበት ወንጀል የሚሰሩ እየተበራከቱ እየመጡ ነው፡፡ ስለሆነም እስር ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ተዘግተው አደረጃጀታቸውንና አሰራራቸውን በተለዋጩ ህግ መሰረት ለመለወጥ መንግስት ወስኗል። ታራሚው በማረሚያ ቆይታው የሚመገበው ምግብ ጭመር እራሱ ከሚያመርተው ምርት ላይ ይሆናል።ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ እየታዩ ያሉ ወንጀሎች ታይተውና ተሰምተው የማያውቁ ፤ ከማህበረሰቡ የአብሮነት እሴት እያፈነገጡ፤ የሰውን ልጅ በአደባባይ መግደል፤ በጅምላ የሀገር ፣የህዝብን ፣ የግለሰብ ንብረት ማውደም እና ማቃጠል ፤በደሃ ሃገር ላይ ደሃው ህዝብ ሥራ እንዳይሰራ ማገት ፤ ከኖርሩበት ቀዬ ማፈናቀል፣ ፍትህ ማዛባት፣አድልዎና መድልዎ መፈጸም፣በዘር በሀይማት ጽንፈኝነት አጉራ ዘለል በመሆን ሀገርንና ህዝብን መበደል፣የትዕቢት እርምጃዎች የማህበረሰብን ማህበራዊ ህይወት ማናጋት መዝረፍ ማቃጠል ሴቶችን ህጻናትን፣ አዛውንቶችን ፣ወንድ ህጻናትን ሳይቀር መድፈር ወዘተ... የመሳሰሉት ኢትዮጵያ ውስጥ ያልተለመዱ እንግዳ ወንጀሎች እያደጉ በመምጣቸው የዘመኑን ወንጀል የሚመጥኑ ህጎችና ማረሚያ ቤቶች አስፈልገዋል።
በዚህም መሰረት ከመጪው 2015 አዲስ አመት ጀምሮ ደሃ ሃገርንና ህዝብን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የተራራ ላይ ማረሚያ ቤት አዲስ የታራሚዎች መንደር ምስረታ ሊጀመር ነው።በየትኛውም ክልል ያሉ እስከዛሬ ድረስ ፈጣሪ እንደፈጠራቸው ቁጭ ያሉ ተራሮች፣ባዶ መሬቶች፣ሸንተረሮች እየተከለሉና እየተጠበቁ በእነዚህ ወንጀለኞች የእስር ጊዜ እንዲለሙ የሚያደረግ ህግ ወጥቶ በ2015 ዓ/ም ስራ ሊጀምር ነው። በመሆኑም ለምሳሌ በቡድን ወንጀል የሚፈጽሙ በቡድኑ 10 ወንጀለኞች ያለው ቢሆንና በቡድን አሥር ሚሊየን ብር የሚያወጣ ንብርት አውድሞ ከሆነ እያንዳንዱ የወንጀሉ የቡድን አባላት 1 ሚሊየኑን ብር የድርሻውን እንዲከፍልና እንዲያካክስ ይፈረድበታል። በዚህም መሰረት የሚታረመው ታራሚ ያወደመውን 1 ሚሊዮን ብር በእነዚህ ተራሮች ላይ በሚመሰረትለት የታራሚዎች መንደር በልዩ ጥበቃ ውስጥ ሆኖ ይቆፍራል ፤አትክልቶች ይተክላል፤እህል ይዘራል፤ ይንከባከባል፤ ያመርታል በጎንዪሽ ከብቶችን ያረባል የእጅ ስራዎችን ቅርሳቅርጾችን ወዘተ..
ወንጀለኛው ሰው ገድሎ ከሆነ በቂ ካሳና የሟችን ቤተሰቦች በመርዳት ሟቹ ቢኖር የሚያደርገውን ሁሉ ለሟች ቤተሰብ ያደርጋል፡፡ለምሳሌ ሟች የሚጦራቸው ወላጆቹን እና አሳዳጊዎችን በማረሚያ ቤት በሚያመርተው ምርት ሽያጭና የምግብ እህል መንከባከብ ፤ለኑሯቸው አስፈላጊውን ሁሉ ማሟላት፤ሟች የሚያስተምራቸውና የሚያሳድጋቸውን ልጆችን ሙሉ ሀላፊነት ወስዶ እዛው አስር ቤት በሚያመርተው ምርት ማስተማር መመገብ፣ ማልበስ መንከባከብ ፤...ያወደመው የመንግስት ወይም የግለሰብ ንብረት ከሆነ ለባለ ንበረቱ በሚያመርተው ምርት ያወደመውን እንዲተካ ማድረግ ይህን ለመሳሰሉና በማህበረሰብና በግለሰብ ስነ ልቦና ላይ ለሚሰራ ወንጀልን ጨምሮ በሀገር ሽማግሌዎች ውሳኔ መሰረት የተጣለበትን ከቃጠናቀቀ በኋላ፣እንዲሁም በትምህርት አመለካከቱ ከተለወጠ በኋላ የእስር ቆይታውን ይፈፅማል ። ባወደመውና በህግ በተፈረደበት በገንዘብ የተተመነበትን ፍርድ ልክ የሚሆን ምርት ማምረቱና ለመንግስት ገቢ ማድረጉ ከተረጋገጠ በኋላ፤ በሀገር ሽማግሌዎች የሚጠበቅበትን ሁሉ ማጠናቀቁ ከተረጋገጠ በኋላ፣እንዲሁም በትምህርት አመለካከቱ ከተለወጠ በኋላ የእስር ቆይታውን ይፈፅማል ።
በዚህ በተራራ ላይ ማረሚያ ቤት ኦሮሚያ ወንጀል የሰራ…ትግራይ ክልል ተራራ ላይ…ትግራይ ላ ይ ወንጀል የሰራ ኦሮሚያ ተራራ ላይ ደቡብ ላይ ወንጀል የሰራ አፋር ተራራ ላይ ወዘተ .....የታራሚዎች ስብጥሩ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ምክያቱ ደግሞ አብዛኞቹ እንግዳ ወንጀሎች እየተፈጸሙ ያሉት አክራሪነትና ጽንፈኝነት አእምሯቸውን ባናወዘውና ባሰከረው ሰዎች በመሆኑ በእግረ መንገድ ከዚህ ከጽንፈኝነት እንዲፈወሱ እና ከበሽታው እንዲተነፍሱ የራሱ አስተዋጽኦ አለው ተብሎ በመታሰቡ ነው፡፡
መንግስት በበኩሉ አስተሳስባቸውን የማነጽ ፤በየደረጃችው የማስተማር ፤እንደየ ሀይማኖታቸው የማምለክ እንዲሁም የእስር ቆይታ መንደራቸው ንፁህ እና ለቆይታቸው ምቹ እንዱሆን የማድረግ ግዴታ አለበት ተብሏል። በተጨማሪም ምርት እንዲቀላጠፍ ታራሚው በዶማና በበሬ ከሚቆፍርውና ከሚያርሰው በተጨማሪ እንደሃገሪቱ እቅም የትራክተርና የኮምባይነር ለእደጥበብ የሚያስፈልጉ ዘመናዊ ማሽኖች የዘመናዊ አመራረት እገዛ ለታራሚዎቹ ያደርጋል።
ታራሚው በምርቱ እዳውን ከፍሎ መጨረሱ እና የአመለካከት ለውጡ ተመዝኖ በማህበረሰቡ ውስጥ በፍቅር፣ በሰላም ፣በአንድነት የመኖር አቅሙ ከተረጋገጠ በኋላ ከእስር ነፃ ይሆናል።
የሚል ህግ እንዲወጣ በአክብሮት ለመንግስት አመለክታለሁ።
አመልካች ኩሪ አየለ ኃይሌ አብራችሁኝ የምታመለክቱና በሃሳቡ የምትስማሙ ሼር አድርጉት
በ2013 ዓ/ም በዚህ ቀን የተለጠፈ ነው ጎግል አስታወሰኝና ደገምኩት፡፡
(ኩሪ አየለ ኃይሌ)
17/12/2021
28/09/2021
06/09/2021