"ጎጃሜ ከሚገዛኝ ኢቶጵያ ትፍረስ" ተባለ
የአማራ ፋኖ በጎጃሞችን ኹኔታ በጥሞና ኹኜ ስመለከታቸው በጣም ነው የሚያሳዝኑኝ። የኢትዮጵያን ታሪክ ያላነበበ ንጹሕና ቅን አእምሮ የተሸከመ ጀግኖች እንደኾኑ ገባኝ። በነርሱ ዓይን ኢትዮጵያ ለጎጃም እናት እንጂ ጠላት አይደለችም። እሄንን ስጽፍ ጠልቻቸው ወይም አዝኜባቸው አይደለም። ወንድምነቴ አስገድዶኝ እንጂ። ያለውንና የነበረውን ነገር ግልጽ ለማድረግ ከመፈለጌ የተነሣ እንጂ። እናም ወደ ታሪኩ ስመለስ "ገበያ በወጣሽ ይሉሺን በሰማሽ" የሚባል ተረት ነበረ። ወደ ታሪክ ንባብ ገበያ ብቅ ቢሉ ምን እንደተባልን ይሰሙ ነበረ። በሌላ ወገናቸው ደግሞ ዛሬ ላይ ያሉት የጎጃም ወጣቶች በጣም አስቀኑኝ። የኢትዮጵያን ታሪክ አለማንበብ እንዴትኮ መልካም ነገር መሰላችኹ። ሾላ በድፍን እናታለም ኢቶጵያ እያሉ መኖር!!!
እነዚህ ምስኪን የጎጃም ልጆች የኢትዮጵያን ታሪክ ቢመለከቱ ኖሮ እንኳን ለአማራ ገዢነት ይቅርና ለተገዢነትም ያፍሩ ነበረ። ኢትዮጵያዊነት ራሱ ያስጠላቸው ነበረ። ከተናቀው ጎጃም ላይ ተወልደው ይህን ያኽል ያልተነካ ሞራል ከየት አገኙት? ብዬ ስመራመር ያው አሁን እንደገለጽኩት የኢትዮጵያን ታሪክ አንብበው እንዳላወቁ ያመለክታል። በመሠረቱ በጎጠኞች እጅ ተበለሻሽቶ የተጻፈው ዂሉ እንደገና ተስተካክሎ እስኪጻፍ ድረስ ማንበብም የለባቸውም።
ለመኾኑ የሚያሸማቅቀን ታሪክ ምን ይኾን? እስኪ በየምዕራፍ ገጹ እየተከታተልኩ ልጻፍላችኹ። አንዱ አንገት አስደፊ ታሪካችን እኛው ጎጃሞች ያበላሸነው ታሪክ ነው። ይኸውም የንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ታሪክ ነው።
ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ማለት በእምባቦ ጦርነት ጊዜ ጎጃምን አዋርደው የኼዱ ለነገ ታሪክ ግዴታ የማይሰማቸው ሰው ነበሩ። ወታደሮቹ ሳይሸነፉ "እዚህ ቦታ አካባቢ ቆሳስዬ ወድቄያለኹና መጥተኽ ማርከኝ" ብለው እርሳቸው ቀድመው ለንጉሠ ሺዋ አቤቶ ምኒልክ መልእክት የላኩ እና የተማረኩ ሰው ናቸው። ከተማረኩ በኋላ ወታደሮቻቸው ያለአዋጊ ብቻቸውን ኹለት ሰዓት ተዋግተው ያለቁበት ታሪክ እናገኛለን። በጥቅሉ ወታደርኽ ሳይሸነፍ አንተ ቀድመኽ ተላልከኽ በመማረክ ታሪክ ለማበላሸት ስትታገል መገኘት ማለት እኮ ነው። ባጭሩ የንጉሥ ተክላማኖት ነገር አሳፋሪ ታሪክ ነበር። ዓፄ ምኒልክም ከንቀታቸው የተነሣ "ጋሜው!" በማለት ይጠሯቸው እንደነበረ አለቃ ተክሌ ጽፈዋል። ጋሜ ማለት ለዓቅመ ሔዋን ያልደረሰች ሴት ማለት ነው። "ወይ ባልዘፈንሽ፣ ከዘፈንሺም ባላሳፈርሽ" እንደሚባለው በእንባቦው ጦርነት ባልገጠሙ ኑሮ መልካም ነገር ነበረ። ከገጠሙም ወዲያ ለኋላ ታሪክ ሲሉ ባላሳፈሩን ኑሮ መልካም ነበረ። ለነገሩ ይቅርታ እየጠየቅኹ የምነግራችኹ ነገር ቢኖር ለነገ ታሪክ የሚቆረቆር ጎጃሜ አይቼም ሰምቼም አላውቅም። ባለፈው ተሰማ ካሣሁን ብቻ ለታሪክ ሲጨነቅ ሰማሁ ።
ሌላው ማፈሪያ ታሪካችን ደግሞ የደጃዝማች ጎሹ እና የደጃዝማች ዘውዴ ታሪክ ነው። በነገራችን ላይ ደጃዝማች ጎሹ ማለት የንጉሥ ተክላማኖት ዓያት ናቸው። እርሳቸው አርኖ ሚሼል ዲ አባዲ እንደጻፈው፣ ገነት ዐየለ አንበሴ ወደ አማርኛ ተርጕማ እንዳሳተመችው ደጃዝማች ጎሹ ለራስ ዓሊ ዓድረው ልጃቸው ደጃዝማች ብሩን ለማስገደል ከልጃቸው ጋር ጦርነት የገጠሙ ሰው ነበሩ። በተጨማሪም አቤቶ አበጋዝ ዘብሔረ ሺዋ የጻፈው፣ ኮንቲ ሮሲኒ ያሳተመው የዘመነ መሳፍንት ዜና መዋዕል ገጽ 816 ላይ እንዲህ ይላል። "ወበምሴተ ቀዳሚት ተጓሕለውዎ ጎጃሞች ወሖሩ ኀበ ኦሮሞ እስመ ልማዶሙ ተጓሕልዎ፣ ቅድመኒ አቅተልዎ ለራስ መርዕድ በወገራ፣ ዮምኒ ኀደግዎ ለደጃዝማች ዘውዴ በከመ ልማዶሙ ---የጎጃም ሰዎች ቅዳሜ ምሽት (ማታ) ላይ ደጃዝማች ዘውዴን ሸንግለውት ወደጠላት ግንባር ወደኦሮሞ ሰራዊት ኼዱ። ጎጃሞች ሽንገላ ልማዳቸው ነውና። ቀድሞም ራስ መርዕድ የተባለውን መሪያቸውን በወገራ አስገደሉት። ዛሬም ደግሞ እንደልማዳቸው ደጃዝማች ዘውዴን ጥለውት ኮበለሉ" ማለት ነው።
አሁንም ይኸው ዜና መዋዕል ገጽ 844 ላይ "ወአዘዞሙ ራስ ይማም ለማርየ እኁሁ ወአንደዋ ሊቦ ወለዋግ ሹም ክንፉ ከመ ይኅልፉ በተንከተም ከመ ይዕቀብዎ ለደጃዝማች ማሩ ከመ ኢይዕዱ ምድረ በጌምድር። ወዐደዉ ፈለገ አባዊ ወተዐየኑ በይባባ። ወእምዝ አኀዙ ይትቃተሉ ራስ ይማም ወደጃዝማች ማሩ። ወደጃዝማች ጎሹ በዐመዳሚት። ወተድኅሉ ደጃዝማች ጎሹ ወሰራዊቱ። እስመ ልማዶሙ ለሰብአ ጎጃም ደኃል" ይላል። ትርጕሙም ራስ ይማም ወንድሙን ደጃች ማርየን፣ አንደዋ ሊቦንና ዋግ ሹም ክንፉ የተባሉትን፣ ደጃዝማች ማሩ ወደበጌምድር እንዳይሻገር ይጠባበቁት ዘንድ ፋሲል በሠራው ድልድይ አድርገው እንዲሻገሩ አዘዛቸው። የአባይን ወንዝ ተሻግረው በይባባ ከተማ ከተሙ። ከዚህ በኋላ ራስ ይማምና ደጃዝማች ማሩ ጦርነት ጀመሩ። ደጃዝማች ጎሹ ዘውዴም ዐመዳሚት ተራራ ላይ ነበረ። ደጃዝማች ጎሹና ሰራዊቲም አስቀድሞ ሽሽት ጀመሩ። የጎጃም ሰዎች መሸሽ ልማዳቸው ነውና" ማለት ነው። በሌላ ቦታ ደግሞ እኒሁ አለቃ አበጋዝ የጻፉት ብላንደል ያሳተመው ታሪከ ነገሥት ገጽ 120 ላይ ራስ ኀይሉ ዮሴዴቅ ሣልሳይ ዓፄ ኢያሱን ወደመንበረ መንግሥታቸው ለመመለስ ጎንደር በኼዱ ጊዜ ራስ ዓሊ መጣ ሲባል ሰምተው መሸሻቸውንና ጎጃሞች በጦርነት ሳይኾን ገና በወሬ በድምፅ ብቻ የሚሸሹ በማለት የመቄዶንያውን ንጉሥ እስክንድር ጥበብ ውጤት በማመሳሰል ጽፈውብናል።
ዜና እስክንድር የተባለው መጽሐፍ ስለ መቄዶኑ ንጉሥ ስለታላቁ እስክንድር ጥበበኛነት ሲጽፍ ብረቱን እንደሰው ድምፅ እንዲያወጣ አድርጎ ሠርቶ ሰባድዐት የተባሉት የአውሬና የሰው ተፈጥሮ ያለባቸው ፍጥረቶችን ወደከተማ እንዳይመጡ፣ ከታጎሩበት ዋሻም እንዳይወጡ፣ የሰው ድምፅ እያወጣ እንዲከላከልለት ከመንገዳቸው ላይ አሰቀምጦት እንደሚኖር ይተርካል። የኢትዮጵያ ታሪክ ጸሐፊው አቤቶ አበጋዝም ጎጃሞችም በጦርነት ሳይኾን ገና ድምፅ በመስማት ብቻ ሲሸሹ ይኖራሉ ብሎ ጽፏል።
እርግጥ ጎጃም ማለት ዂሉም ልጆቹ አገር አዋራጆች ነበሩ ማለት አይደለም። ጀግኖችም ነበሩበት። ለምሳሌ በጊዮርጊስ ወልደ ዓሚድ መጽሐፍ ላይ ታሪኩ ተመዝግቦ የሚገኘው ራስ ወረኛ ፋሲል ከጎጃም ጀግኖች መካከል አንዱ ነበረ። ነገር ግን አሁንም አቤቶ አበጋዝ ዘብሔረ ሺዋ በራስ ወረኛ ፋሲል ዙሪያ ሲጽፉ ፈርጣጭ ብለው ከመጻፍ አልተገቱም። የጎጃም ጠል መንፈስ የተጠናወታቸው ይመስላሉ።
እኔ የኢትዮጵያን ታሪክ ለማጥናት ፈልጌ ወደንባብ ስገባ እያገኘኹት ያለኹት እንዲህና እንዲህ ዓይነት ማፈሪያ ማፈሪያ ታሪክ ነው። ባጭር አገላለጽ አባቶቻችን ጎጃምን ገድለው አስረክበውናል። ዛሬ ላይ ከጎጃም በስተቀር ዂሉም የአማራ ምሁራን ታሪክ ዐዋቂ ነው። እና ታዲያ ይህን እያነበበ የሚኖር አማራ እንዴት ነው ጎጃምን ለመሪነት የሚቀበለው?
ለዚህ መዳኒቱ ጎጃም ሥልጣን ከፈለገ ራሱን መቻል ብቻ ነበር የነበረበት። አለበለዚያ አንገቱን ደፍቶ መኖር ነው። ለነገሩ እንገንጠል ቢባልስ የአባቶቻችን ልጆች ስለኾንን ይህን የወንድነት ወኔ ከየት አባታችን እናመጣዋለን? ራስን መቻል እኮ ከባድ ዐላፊነት ላይ መቀመጥ ማለት ነው። ስለዚህ ከባድ ወንድነትን ይጠይቃል። እና ጎጃም ነው ለዚህ ትልቅ ነገር ዝግጁ ኹኖ የሚገኘው? ይከብዳል።
አቦላ ተራራ
አቦላ ተራራ
የማርሻልነት መሥፈርቱ
ማርሻል ለመባል አንድ ትልቅ ጀብድ መሥራት ይጠይቃል። ያም የጀብድ ዓይነት አንድን አገር ወይም ጠላት ያለምንም ጥይት ተኩስ፣ ያለምንም የገንዘብ ወጪ፣ ያለምንም የጉልበት ድካም፣ ያለምንም እንቅስቃሴ መደምሰስ መቻል የሚያስችል ብልሀት ፈጥሮ ያንን ዘዴ ተግባራዊ አድርጎ ማሳየት ሲችል ነው። ለምሳሌ የኢትዮጵያ የቃኘው ጦር በኮሪያ ዘመቻው ጊዜ ያለምንም ወጪ ድል አርጎ ተመልሷል ልክ እንደዚህ ማለት ነው
በዘመናችን ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ለማርሻልነት ደረጃ በቅተዋል። በጀነራልነት ውስጥ ራሱ ብዙ ዕርከኖች አሉ። ብርጋዴር ጀነራል፣ ሜይጀር ጀነራል፣ ሌተና ጀነራል ይባላሉ። እንግዲህ ፊልድ ማርሻል ጀነራል ብርሃኑ ምን ጀብድ ፈጽመው ነው ለዚህ ትልቅ ሹመት ማዕረግ የደረሱት? ብዬ ስጠረጥር የመሰለኝን ልንገራችሁ። አማራን በራሱ ሰው ማጫረስ፣ በራሱ ሰው መደምሰስ፣ በራሱ ሰው መሠረተ ልማቶችን መዝጋት፣ በራሱ ሰው መምህራንን መግደል፣ በራሱ ሰው ዶክተሮችን መግደል፣ በራሱ ሰው ራሱን ማማረር፣ በራሱ ሰው ማጥፋት፣ ወዘተ፣ ወዘተ፣ ወዘተ... የመሳሰሉ እቅዶችን ፈጠሩ። ያንን እቅድ በረቀቀ ዘዴ ለፋኖ አስረከቡ። ያልተማረና ያልተመራመረ ፋናኖ የጠላት አጀንዳ ተሸክሞ እናቱን ገድሎ ሌላ ጠላት እናት የሚፈልግ እስኪመስለኝ ድረስ ጥርጥር አደረብኝ
ዛሬ አማራ 17 ትሪሊዬን ዶላር ካላገኘ ሰው መኾን እንደማይችል እየተነገረ ይገኛል። ልብ በሉ ያለምንም ጉልበት ያቀዱት ምት ሠርቷል ማለት ነው ስለዚህ የማርሻልነቱ ሹመት በሚገባ ይገባቸዋል ማለት ነው ።
"ሜጫ የነገሩ መምጫ "
--------------------
ይህ አባባል ያለ ምክንያት አልተነገረም ብዙ ስለሜጫ የተጻፉትን የታሪክ ድርሰቶች ስመለከት ማጫ ላይ ሲደርሱ አደገኛ ሥነ ጽሑፋቸውን ብቅ ከማድረግ ወደኋላ አይሉም ከነዚህም አንዱ ሚስተር አርኖ ሚሸል ዳባዲ ናቸው እርሳቸው ስለጎጃም ታሪክ በሰፊው ጽፈው በፈረንሳይኛ ቋንቋቸው አሳትመውት ለመቶ ዓመታት ያኽል ከኖረ በኋላ ገነት አየለ አንበሴ ወደ አማርኛ ተርጉማ ካስቀመጠችው ላይ እንመልከት
"መቼም የሜጫ ነዋሪዎች ለአገዛዝ የማይመቹ ነበሩ ልማዳቸው እንዴት ነው ቢባል በየዓመቱ ግብር ለመሰብሰብ የታዘዘ ወታደር ገና ብቅ ሲል ለአመጸኛ ምቹ የኾነውን ተዳፋትና ጉራንጉር የበዛበትን አገራቸውን ተማምነው በየ ጋራው በየተረተሩ ይሸጎጣሉ ቦታው ለመከላከል የሰጠ መኾኑ ብቻ ሳይኾን በጣም ጎበዝ ተዋጊዎችም የሞሉበት ነው ። ሜጫ በጎጃም ካሉት ግዛቶች ኹሉ የሚያጓጓ ግን ለአገዛዝ የማይመች ጀግና የሞላበት ግን ሽማግሌ የማይገኝበት ነው ይላሉ ። አዲስ አገረ ገዥ ራስ ተሹሞ በመጣ ቁጥር ግብግብ ነው በዚያችው በአካባቢያቸው እንደፈለጋቸው ኹነው መኖርን እንደሚመርጡ ተነግሮ ያለቀ ነገር ነው ። የሴቶቻቸው ቁንጅናና ውበት እንደተዘፈነለት ነው ምንም ዕንኳን በወረራ ከመጡ ከኦሮሞዎች የመጣ ዘር እንዳላቸው ቢታወቅም የሚናገሩት አማርኛ በአጎራባች ግዛቶች ከሚነገረው የበለጠ ጥርት ያለ አማርኛ እንደኾነ ተመስክሯል " በማለት ይጽፋል "በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራሮች ቆይታዬ" ቁጥር አንድ ገጽ 327 ላይ ይመልከቱ ።
30/03/2022
01/03/2022
የአጤ ቴዎድሮ የጠፋው ታሪካቸው
............/////////////////................
ከጳውሎስ ኞኞ የሚል የአጤ ቴዎድሮስ ታሪክ አገኘሁና ማንበብ ጂርሁ ገጽ 1 ከመጀመሪያዋ ፓራግራፍ ላይ አጤ ቴዲ ከጎንደር ከተማ ወጣ ብላ ከምትገኘው 12 ኪ ሜ ርቀት ላይ ከምትገኘው አዘዞ ላይ እንደተወለዱ ገለጠ ይህ የታሪክ መጣፍ ይህንን ገለጣውን ባንዴ ዘንግቶት ነው መሰለኝ ዝቅ ብሎ ገጽ 13 ላይ ካሣ ከእስር ቤት አምልጠው ተወልደው ወዳደጉበት ሰፈር ወደቋራ በረሐ ሔዱ ይላል እኒህ የታሪክ ተዘራፊ አጤ ቴድሮስ ምን አበሳ ቢኖርባቸው ነው እንዲህ ዝርጥርጡ የወጣ ትረካ የተዘጋጀላቸው ???
ሌላው ትረካ ደግሞ የኮሶ ሻጭ ልጅ መባላቸው ነው የኮሶ ገበያ በዚያን ጊዜ የለም ተወለዱበት የተባለው ቋራ በረሐም ኮሶ አያቀቅልም ደጋማው ወደደንቢያ ግንባር ያለው ላይ ቋራ እንደሆነ ብየ ለመመራመር መከርሁ እዚህም ገደማ ኮሶ አይበቅልም ታዲያ ነገሩ ምንድነው ???
ይብላኝልሽ አንቺ አገር !!!!
08/02/2022
ወዮ ለጎጃሜ
--------------
ባለፈው ወር ሕወሓት ደብረ ብርሃን ደርሳ " ከቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዓቢይ አሕመድ ዘምተው አባረሯት" እየተባለ የተወራ ሰሞን የትግሬ ዘር ከሰማይ በታች ተደምስሶ ሊጠፋ ነው መስሎን አንዳንድ የአማራ ተደስተን ነበረ ከደስታችን ብዛት የተነሣ የምንቆምበትን ምድር ኹሉ ስተን በመወላከፍ ጮቤ ረግጠን ነበረ እናም በዚህ የቆሻሻ ታሪክ ወቅት የሽዋ የጎንደር አማራ የኢትዮጵያ ሥልጣነ መንግሥት በመዳፉ የገባ እስኪመስለው ድረስ ጣዝማ እንዳገኘች ቀበሮ ፈንጥዞ ነበረ ጎጃሜም ምስጢሩ ሳይገባው አብሮ ከነዚህ መሠሪ አካላት ጋራ አሸ በል ገዳየ በማለት እየጨፈረ እንደነበረ የትናንት ማለዳ ታሪካችን ነው በሬ ካራጁ ጋር ይኖራል ማለት ይህ ነበረ የሚያሳዝነው ነገር ይህ ጎጠኛ አማራ ታሪክ እየተመዘገበበት መሆኑን መገንዘብ አለመቻሉ ነበረ ለነገሩ ታሪክ ጸሐፊ ከነርሱ ውጭ ማን አለና ነው ? ነገ ማለዳ አሳምረው ይጽፉታል
በዚህ ጨለማ ወቅት መሠሪው እና ጎጠኛው የሽዋ እና የጎንደር አማራ ምን ቢጀምር ጥሩ ነው መሰላችሁ ? አዲስ አበባ ላይ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሠማሩ የዋሓን ጎጃሜዎችን የኦሮሞ ባለሥልጣን ያባረራቸው በማስመሰል ከሥራ ገበታቸው እያፈናቀሉ ማባረር ተጀመረ ይሁንና ጎጄ በሙሉ ኦሮሞ ያባረረው እንጂ ሽዋ እና ጎንደር ተባብሮ በጥላቻ ያባረረው የጎጠኝነት ሤራ ከወገኑ የተሠራበት እንደሆነ አንዱም ጎጃሜ እንኳ አላወቀም ምክንያቱም ሽዋ የታሪክ ጸሐፊዎች አገር ስለሆነ የታሪክን ክፋትና ጥቅም ጠንቅቆ ያውቃልና ከታሪክ ተወቃሽነት ነጻ ለመሆን የኦረሞ አለቃ ከፊት ለፊቱ ሹሞ እሱ ደግሞ ከበስተጀርባ ምክትል ሹመኛ ፣ ስራ አስፈጻሚ ፣ ጸሐፊ ፣ የአስተዳደር ኮሚቴ ወዘተ.... እየሆነ በመጀራጀት የሸረበው ጽልመት ለበስ ሤራ ነውና ጎጃሜ ደግሞ ይህንን ዓይነት የሤራ አካሄድ አያውቀውም ሁላችን የጎጃም ዘሮች ላይ አጠቃላይ ርምጃ ሊወስዱ ዝግጅት ላይ በነበሩበት ሰዓት ፈጣሪ ረጅም እዴሜ ከጤና ጋር ይስጣቸውና ዶክተር ዓቢይ እነ አቦይ ስብሐትን ከእስረኝነት በመልቀቅ አማራ አቅዶልን የነበረውን ጨለማ እቅድ አከሸፉልን
እንግዲህ ዛሬ ታሪክ ጸሐፊ ጎጃሜ አልተፈጠረም እንጅ ቢኖረን ኖሮ እንዲህ እና እንዲህ ዓይነት የመሠሪ ታሪክ በጎጃሜ ላይ ተመዝግቧል ተብሎ ለተተኪው ልጆቻችን መጠንቀቂያ ታሪክ ይመዘገብ ነበረ ይሁንና እኛ ጎጃሞች የታሪክ መጻፍ ልምዱም መሠሪነቱም ስለሌለን ዛሬ የተሸረበብንን ይህን እኩይ ታሪክ የታሪክ ጸሐፊው አገር ሽዋና ጎንደር ነገ ነገ ማለትም ከዛሬ ኻያ እና ሠላሳ ዓመታት በኋላ ታትሞ የሚወጣ "የጎጃም ቡዳ ሰው የፈጀበት ዘመን" በሚል ርእስ ረጅም የታሪክ መጽሐፍ እያዘጋጀ እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም ምክንያቱም የታሪክን ጉልበት ተረድተውታልና የነርሱ ዘመን ሲመጣ አሳትሞ ይቸረችርበታል ራሱ ጎጃሜም እየገዛ በማንበብ ራሱን ሲጠላ ራሱን ሲያጠፋበት ይኖራል በቃ ኢትዮጵያ ማለት ይቺ ናት ።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the school
Website
Address
Shiromeda
Addis Ababa