11/05/2023
የቅዱስ ፓትርያርኩ የግንቦት 2015 ዓ.ም ርክበ ካህናት ጉባኤ መክፈቻ ንግግር።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና በሰሜን አሜሪካ የኒዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣
ብፁዕ አቡነ ሔኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ
አባላት፣
የሰላም አለቃ፣የምሕረት አባት የሆነው ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት የሆነችውን በዓለ ትንሣኤውን አክብረን ይህንን የረክበ ካህናት ቀኖናዊና ሲኖዶሳዊ ጉባኤ እንድናካሂድ ስለሰበሰበን ክብርና ምስጋና፣ አምልኮና ውዳሴ ለእሱ በማቅረብ፣እንኳን ደኅና መጣችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡
“ወይእዜኒ ንትልዋ ለሰላም በዘይት ሐነጽ ቢጽነ፡-እንግዲያው ስለሰላም የሚቆምበትን እርስ በርሳችንም የምታነጽበትን እንከተል” (ሮሜ. ፲፬፥፲፱)፤
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
በቅዱሳት መጻሕፍት በግልፅ እንደተቀመጠው እኛ የምናገለግላት ቤተክርስቲያን በምድር ያለች የእግዚአብሔር መንግሥት ማእከል ናት፤ የተመሠረተችውም በደመ ክርስቶስ ነው፡፡
የእግዚአብሔር መንግሥት ማእከል የሆነችው ቤተክርስቲያን ልትሰራው፣ልትጠብቀውና ልትፈጽመው የተሰጣት ዓቢይ ተልእኮ አለ፤ እሱም በእግዚአብሔርና በሰው፣ በሰውና በሰው መካከል ፍጹም ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ ነው፤
ይህ ዓቢይ ተልእኮ የሰማይና የምድር መዝሙር ሆኖ ሁሌም በመደበኛ ይዘመራል፤ጌታችንም ከሞት ከተነሣ በኋላ ያሰማው የመጀመሪያ ድምፅ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” የሚል ነው፡፡
የጌታ ምርጥ ንዋይ የተባለው ቅዱስ ጳውሎስም ”ሰላም የሚቆምበትን እንከተል” ሲል የሰላምን ተቀዳሚ አስፈላጊነት በአጽንዖት አስተምሮናል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ ሰላምን በቀዋሚ ምሰሶ አምሳላዊ ንጽጽር ገልፆአታል፡፡
ይህም ማለት ምሰሶ የቤትን ጣራ በቀዋሚነት ተሸክሞና ቀጥ አድርጎ እንደሚይዝ፣ሰላምም በተመሳሳይ የሰዎችን መንፈሳዊና አካላዊ ሕይወት ቀጥ አድርጋ የምትይዝና የምትጠብቅ መሆኗን ለመግለፅ እንደሆነ እንገነዘባለን።
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
እኛ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከኛ በታች ያሉ ውሉደ ክህነት፣እንዲሁም በእግዚአብሔር የልጅነት ጸጋ የከበሩ ምእመናንና ምእመናት ሁሉ፣ የቤተክርስቲያን መደበኛና ቀዋሚ ተልእኮ የሆነውን ሰላም የመጠበቅ፣ የማስጠበቅ፣ የማሥረጽና የማስቀጠል ኃላፊነት እንዳለብን ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም፡፡
በእግዚአብሔርና በሰው፣ በሰውና በሰው መካከል አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም እንዲኖር ጠንክሮ የማስተማር፣ የመምከርና የማስታረቅ ኃላፊነት የእኛ ነው፡፡
ከዚህ አንጻር ዛሬ የተሰበሰብነው የተሰጠን አምላካዊ ተልእኮ ምን ያህል በተግባር አከናውነናል? ምን ሰርተናል? ምንስ ይቀረናል? ተልእኮአችንን ለመፈጸም በምናደርገው ጉዞስ ምን ችግር አጋጠመን? ችግሩን ለመፍታትስ ምን እናድርግ? የሚሉትን መሠረታዊ ጥያቄዎች በማንሣት በዝርዝርና በጥልቀት በማየት ተልእኮአችንን በኣግባቡ ለመወጣት ነው፡፡
የቤተ ክርስቲያናችን ቀኖናም ከበዓለ ትንሣኤ በኋላ በሃያአምስተኛው ቀን የረክበ ካህናት ዓቢይ ጉባኤ እንዲደረግ ያዘዘበት ዋና ምክንያት ይህንን እንድናደርግ ነው፡፡
ሁላችንም እንደምንገነዘበው በአሁኑ ጊዜ ቤተክርስቲያናችን እንደ ቤተክርስቲያን፣ሕዝባችንም እንደ ሕዝብ በፈተና ውስጥ እያለፉ ያሉበት ጊዜ ነው፡፡
በመሆኑም ከምንም ጊዜ በላይ በአሁኑ ጊዜ በልዩ ትኩረት የምናያቸው ጉዳዮች እንዳሉ መገንዘብ ይኖርብናል፤የቤተክርስቲያናችንና የሕዝባችን ችግሮች የተራዘሙ እንዳይሆኑ ለቤተክርስቲያናችን ምጥዋን ሆነን የምንሰራበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በውል ማወቅ ይኖርብናል፡፡
ብፁዓን አበው ሊቃነጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!!
ጌታችን፡- “እንደ ርግብ የዋሆች፣ እንደ እባብም ብልሆች ሁኑ” ብሎ ያስተማረንን ጥበብ በዚህ ጊዜ በሚገባ መጠቀም ይኖርብናል፡፡በቤተክርስቲያን አጋጥመው ያሉ ችግሮች በዚህ ጥበብ ካልሆነ በቀር በመሳሳብና እልክ በመጋባት የሚፈቱ አይደሉም፡፡
በተለይም በትግራይና በኦሮምያ አካባቢዎች ያጋጠሙን ያሉ ፈተናዎች ከቤተክህነት አልፈው የሕዝብም ጭምር እየሆኑ ስለመጡ የሕዝቡን ጥያቄ በትክክል በማዳመጥ ሃይማኖቱንና ቀኖናውን በጠበቀ መልኩ በጥበብና በፍቅር ጥያቄአቸውን አክብረን መቀበል ያሻል፤ ጉዳታቸውንም መካፈል ይገባናል፡፡በአጠቃላይ አባትና እናት ለልጆቻቸው ሊያደርጉት የሚገባውን በማድረግ ልናቀርባቸውና ልናቅፋቸው ይገባል፡፡
እኛ ያጐደልነው፣የተሳሳትነውና ያስቀየምነው ካለም ይቅርታ ለመጠየቅም ሆነ ንስሐ ለመግባት ድፍረቱ ሊኖረን ይገባል፡፡ ታረቁ፣ ይቅር በሉ፣ንስሐ ግቡ ብለን የምናስተምር እኛ ይቅርታ ለመጠየቅና ንስሐ ለመግባት ዓቀበቱ ሊከብደን አይገባም፡፡የተከሠተው ችግር በዚህ ክርስቶሳዊ ጥበብ ሊቃለል እንደሚችል ጥርጥር የለውም፡፡
በሌላ በኩል በሀገራችን ያለው የሰላም ሁኔታ በአንድ ወገን የተረጋጋ ሲመስል በሌላ በኩል ደግሞ የመንገጫገጭ ሁኔታ እየተከሠተ እንደሆነ እያየን ነው፡፡ይህም ሂዶ ሂዶ ቤተክርስቲያንንና ሕዝብን፣ ሀገርን ልማትን መጕዳቱ የማይቀር ነው፡፡
በመሆኑም ቤተክርስቲያን ያለ ሀገርና ያለ ሕዝብ ህልውና የላትምና ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት፣ የሕዝቦቿን አንድነትና ልማት ለማረጋገጥ፣ በሃይማኖታዊ መርሕና መንፈስ፣በገለልተኛ አቋምና በሁሉም ዓቃፊነት ስልት ለሰላም ጠንክረን መስራት ይኖርብናል፡፡
ከዚህም ጋር የዛሬው ጉባኤ የቤተክርስቲያናችንን ዓቢይ ተልእኮ ለመፈጸም እንደመሳሪያ ሊያገለግሉ ይችላሉ ተብሎ ታምኖባቸው የተጀመሩትን ወሳኝ ስራዎች በዝርዝር በማየት ውሳኔ የምናሳልፍበት ጉባኤ ይሆናል፡፡
ከዚህም ሌላ በተፈጠረው አላስፈላጊ ከባድ ጦርነት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የፈራረሱ አብያተ ክርስቲያናትና የተፈናቀሉ ምእመናን ልጆቻችንን በፍጥነት ደርሰን የምናጽናናበትንና የምንደግፍበትን ሁኔታ በዚህ ጉባኤ ማየት ይኖርብናል፡፡
በመጨረሻም
በአሁኑ ጊዜ ኣላስፈላጊ በሆነ የእርስ በርስ ግጭት እየተሳተፉ ያሉ ወገኖች ግጭቱን ኣቁመው በሰላማዊ ውይይት ችግሮችን ለመፍታት እንዲጥሩ ኣባታዊ ጥሪያችንን በአጽንዖት እያስተላለፍን የ፳፻፲፭ ዓ.ም የረክበ ካህናቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በጸሎት የተከፈተ መሆኑን ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምእመናንና ምእመናት እናበስራለን።
እግዚአብሔር ጉባኤያችንን ይባርክልን!
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ !!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር !!!
አሜን፡፡
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
ግንቦት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት
አዲስአበባ - ኢትዮጵያ
06/05/2023
የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ያሬድ ሀይለማሪያም በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መልዕክት አስተላለፉ።
ሚያዚያ 28/2015ዓ/ም
አሻራ ሚዲያ
መንግሥተ ''ሕግ የማስከበር ዘመቻ በሚል በአማራ ክልል የጀመረው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ክልሉን መደለየለት ቀውስ ውስጥ ከመክተትም ባለፈ የአገሪቱን ሰላም እና አንድነት የሚያናጋ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ ከአመታት በፊት ከህውሃትና ከሸኔ ጋር በትግራይና በኦሮሚያ ክልሎች መንግስት ያደረጋቸው የሕግ ማስከበር ዘመቻዎች" ምንም ውጤት ሳያስገኙ ለአገሪቱ የተረፋት በሚሊዬኖች የሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀል፣ በመቶ ሺዎች መሞት፣ የበርካታ ከተሞች ውድመትና ዘርፈ ብዙ ቀውሶች ናቸው። ከዚህ ሁሉ እልቂትና ውድመት በኋላ ግን የትግራዩ ጦርነት በሰላም ድርድር ሲቋጭ፤ ከሽኔ ጋር ያለው ግጭትም መጨረሻ ላይ ወደ ጠረጴዛ ውይይት አቅንቷል። ቢዘገዩም የሚደገፉ እርምጃዎች ናቸው።
በአዲስ መልክ አማራ ክልል ላይ በመንግስት ታጣቂዎችና በክልሉ ታጣቂዎች መካከል የተጀመረው አስፈሪ ግጭት የሌሎች ሚሊዬኖችን ሕይወት ሳይቀጥፍ እና የአገር ሀብት ሳይጠፋ በፊት በሰላማዊ ውይይትና ድርድር እንዲፈታ መንግስትን መማጸንም፣ ማሳሰብም እወዳለሁ፡፡ በክልሉ ውስጥ እየደረሰ ያለው ቀውስና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ወደ መጥፎ አቅጣጫ ሊያመራ የሚችልበት ሁኔታ በግልጽ እየታየ ነው። መንግስት ለሰላም እድል እንስጥ፤ ጦርነት ይብቃ” የሚለውን መፈክር ከፕሮፖጋንዳ ፍጆታ በዘለለ ከልብ በሁሉም የአገሪቷ ክፍሎች እውን ሊያደርገው ይገባል። ጦርነትና ግጭት ይብቃን!!!
ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ :-Youtube:-https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw
Facebook:-https://www.facebook.com/asharamedia24
ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Ashara Media - አሻራ ሚዲያ - YouTube
Share your videos with friends, family, and the world
05/05/2023
27/08/2015 "መድሀኒአለም"
ጸሎት ኃይልን ታደርጋለች!!!
በህይወታችሁ ተስፋ የቆረጣችሁ እግዚአብሔር ግን ምነው ዝም አለ ያልን ካለን፤በእውነት እግዚአብሔር ኃያል ነው በሰው የማይቻል በእርሱ ዘንድ ይቻላል ቢዘገይም የሚቀድመው የለም መድኃኔዓለም።
እኛ ካሰብነው ይልቅ እርሱ ያሰበልን ነገር እንደሚበልጥ አምነን በጸሎት እንትጋ ምናልባት አጥብቀን የምንለምነው ነገር ቢሆንልን ምናልባት መጥፊያችን ሊሆንም ስለሚችልም ይሆናል እግዚአብሔር ልጆቹን ዝም የሚለን
ማማረርን ትተን ተመስገንን እንልመድ .... ግን......ቢዘገይም የሚቀድመው የለም እኔ ምስክር ነኝ በአደባባይ!!!
ለሰው ከምናማክረው በላይ አጥብቀን ችግራችንን ለእግዚአብሔር እናማክር የሰው ልጅ ልንሰለቸው እንችላለን
እግዚአብሔር ግን ከነ ኃጢያታችን ሁሌም ሄደን ብናለቅስበት አንሰለቸውም ስለዚህ ከልብ ከልብ እንትጋ
በሞት ጥላ ውስጥ እንኳን ብንሆን እርሱ የሚሳነው የለም
!!!
እግዚአብሔር በህይወታችሁ የዋለላችሁንም ውለታውን አትርሱ የበለጠ ጸልዩ ፣አገልግሉም እንጂ
ተናገሩ ድንቅ ስራውንም መስክሩ
እግዚአብሔር አባቴ፣ መመኪያዬ፣ መፅናኛዬ፣ኃይሌ.....አንተ ስላለኸኝ ሁሉ ሙሉ..ተመስገን!!!
04/05/2023
ፅንፈኛ ለሚሉን መራራ "እውነት"
one amhare01 on TikTok
❤️❤️ #ሸዋጠቅላይግዛት💚💛❤ 🇪🇹_tiktok #አማራ💚💛❤️ #አማራዬ💚💛❤አማራዬ💚💛❤️🐅ፋኖ❤️🐅የኔ
03/05/2023
መንግሥት በአማራ ህዝብ ላይ የጀመረውን ጥቃት በአስቸኳይ ያቁም!
በወቅታዊ ጉዳይ ከእናት ፓርቲ፣ ኢሕአፓ እና መኢአድ የተሰጠ የጋራ መግለጫ
ባለፉት 30 አመታት የተከተልነው “የጎሳ ፌደራሊዝም” የኢትዮጵያ ህዝብ በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች በሰብዓዊነቱ ሁለንተናዊ ተሳትፎ እንዳያደርግ አግዶታል፡፡ የሠላምና የጸጥታ ዕጦት፣ መረን የለቀቀ ሙስና፣ አድሏዊ አሠራር፣ ዘውገኛነትና ጎጠኝነት ሥር ሠዶ የገነገነበት ዘመን ላይ እንድንደርስም አስገድዶናል። በዚህ ላይ ስለሀገሩ ኅላዌ፣ አንድነትና ሉዓላዊነት የሚገደው ዜጋ ደግሞ ተብከንካኝና ባይተዋር እንዲሆን ተፈርዶበታል። ኢትዮጵያውያን ዛሬ የምንገኝበትን የብሶት ደረጃ “አላውቅም” የሚል የገዥው ፓርቲም ሆነ የመንግሥት ባለሥልጣን ካለ ያለበትን የኃላፊነት ሥፍራ የዘነጋና እውነታውን የካደ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በከፍተኛ ችግር፣ ምስቅልቅልና ብሶት ዉስጥ ነው።
ማንኛውም ዜጋ በሀገሩ ዉስጥ የህይወት ዋስትና ሊኖረው ሲገባ፣ ዛሬ ዘውግን ወይንም ሃይማኖትን፣ ወይንም ደግም ከገዥዎች ፍላጎት የተለየ ሃሳብ መግለጽን መሠረት ባደረጉ ፍረጃዎች የተነሳ በዜጎች ላይ ከባድ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል። በሠላም ወጥቶ መግባትም ፈታኝ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ በተለይም ማንነትን መሰረት ባደረገ የጥላቻ እሣቤ የአማራ ህዝብ ለመፈናቀል፣ ስደትና እንግልት ተዳርጓል፡፡ በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል-ጉምዝ ክልሎች ዜጎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፤ ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል፡፡
ሕወሓት መራሹ ኢህአዴግ በ1983 ዓ.ም. የፖለቲካ ሥልጣን ከጨበጠበት ወቅት ጀምሮ አማሮች በጠላትነት ተፈርጀው በተደጋጋሚ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ደርሶባቸዋል፡፡ የብልጽግና መንግስትም ይህንኑ ፈለግ ተከትሎ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የዚህ ጦስ የዜጎች ህይወት በሰብአዊነት መንጠፍ ውስጥ እንዲወድቅ አድርጓል። ከዚህ አኳያ የሁሉም ዜጎች ህይወት እኩል ዋጋ፣ እኩል ክብርና ዋስትና ሊያገኝ ይገባል ብለን እናምናለን። የመንግሥት ግንባር ቀደም ሃላፊነትና ሥራ የዜጎችን ህይወት መጠበቅ ሆኖ ሳለ ባለፉት አምስት አመታት የዜጎች ህይወት በእየለቱ ሲቀጠፍ መንግስት ያሳየው ዳተኝነት አሳፋሪ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጡ ሰሞን የነበረው የለውጥ ፍላጎትና ጠንካራ ትግል የተወሰነ ለውጥ መሣይ ብልጭታ በመፍጠሩ፣ ዜጎች ሀሳባቸውን በነፃነት ለመግለጥ የሚችሉበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። “ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት ይቻላል” የሚል ተስፋም አጭሮ ነበር። ይሁን እንጂ “ላም አለኝ በሰማይ …” በሆነ መልኩ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ተክዶ በተለመደው መልኩ በጎሳ ስሁት ትርክት ውስጥ የምትታሽ ሀገርና ሥርዓት ውስጥ እንድንኖር ተገደናል፡፡ ጋዜጠኞች፣ ምሁራንና ማኅበራዊ አንቂዎች፣ በተናገሩትና በጻፉት ህግን ጥሰው ከሆነ በፍርድ ቤት እንደሚጠየቁ እናውቃለን፡፡ ከዚህ ውጭ በሆነ መልኩ ዜጎችን በግፍ ማሰር፣ መደብደብ፣ ማንገላታት እና አፍኖ-መሰወርን ግን ምን አመጣው?
በቅርቡ ዳግም ጅምላ እስሩ መፈናቀሉ ግድያውና አፈናው የበረታው በአማራው ህዝብ ላይ መሆኑ ምሬትና ብሥጭት እንዲጨምር አድርጓል። በሀገራችን ዋና ከተማ አዲስ አበባ ሣይቀር ማንነትን ማዕከል ባደረገ ሁኔታ ማፈናቀልና ማሣደድ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ የብልጽግና መራሹ መንግስት የነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶች በላያቸው ላይ ማፍረስና ማባረር ከጀመረ ሰነባብቷል። በተለይም የዜጎችን በሀገራቸው ዉስጥ በነፃነት የመንቀሳቀስ መብት በሚደፈጥጥ መልኩ አማሮች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ እየተደረጉ ለከፍተኛ ችግርና እንግልት መዳረጋቸውም ሀገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። የአማራው
02/05/2023
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ
*****
የአማራ ህዝብ በተደጋጋሚ ከተከፈተበት የወረራ ጦርነት ወጥቶ አንጻራዊ መረጋጋት ካሳዬ ገና ጥቂት ወራቶች ብቻ ተቆጥረዋል። በተከፈተበት ተደጋጋሚ ወረራ ለከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት መዳረጉ ይታወቃል። የአማራ ህዝብ ግጭትና ጦርነትን በተግባር የተመለከተ እንጅ በሩቅ የሚያውቀው ጉዳይ አይደለም።
የአማራ ህዝብ ያነሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ከፍትህ እና እኩልነት ጋር የተገናኙ በመሆናቸው ከጥላቻና ፅንፈኛ ሃይሎች በስተቀር ሌሎች ወገኖች በተለይም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የሚያደምጧቸውና የሚደግፏቸው ናቸው።
በተለይ በጦርነቱ ወቅት የተከፈለውን ዋጋ በማይመጥን ደረጃና አግባብ የተመራው የሰብዓዊ ድጋፍ እና የመልሶ ማቋቋም ስራ እንዲሁም ድኅረ-ጦርነት በመንግስት በኩል እየተካሄደ ያለው ግልፅነት የሌለው የፖለቲካ እንቅስቃሴ በአማራ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እና ስጋት መፍጠሩን መተማመን ያስፈልጋል።
በዚህ ረገድ የአማራ ሕዝብ ለሀገሩ ያለውን ቀናኢነት እና ሀገሩን ለመታደግ የከፈለውን ዋጋ የሚያራክሱ ተግባራት መደበኛ ሆነው አደባባይ ላይ መዋላቸው ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል።
ከዚህ በተጨማሪ በድኅረ-ጦርነት ወቅት ከሕዝቡና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሰረታዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተከታታይነት ያለው ግልፅ ውይይት ባለመደረጉ ምክንያት የተፈጠሩ ችግሮች መሆናቸውን እንገነዘባለን።
ስለሆነም በአሁኑ ወቅት ለተፈጠረው የፀጥታ ቀውስ ምክንያቶቹ ለረዥም ጊዜ የቆየው የፖለቲካ ችግር እና ወቅታዊው የመንግስት ፍላጎትና አቅም ማጣት ናቸው።
በአንድ በኩል የአማራ ሕዝብ በተደጋጋሚ ሀገሩንና የማዕከላዊ ስርዓቱን ከአደጋ ለመጠበቅ በመንግስት የተደረገለትን ጥሪዎችን በክብር ተቀብሎ መስዋዕትነት ሲከፍል ቆይቷል። ሆኖም መንግስት ለአማራ ሕዝብ ፍትኅዊ ጥያቄዎች፣ ፍላጎቶች እና ስጋቶች በቂ ትኩረት አለመስጠቱ ችግሩን አባብሶታል ብለን እናምናለን።
በአማራ ሕዝብ በኩል መንግስት ፍፁም መወያየትና ማድመጥ የማይፈልግ አካል መሆኑን አንድምታ ከተወሰደ ቆይቷል። አጠቃላይ ፖለቲካው ግልፅነት የጎደለው በመሆኑ እና ማሕበረሰቡን የሚያስተዳድርበትን ፍኖት ስለማያሳይ ዘወትር ጥርጣሬና የሴራ ትንተና የበላይነት እንዲኖረው በር ከፍቷል። ይሄም በሂደት እየጎለበተ ሄዶ አሁን ለተፈጠው የፀጥታ ችግር አስተዋፅኦ አድርጓል።
ስለሆነም በመንግስት በኩል በቀጠናው ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር በቀጥታ በመወያየት ለተፈጠሩት ችግሮች እልባት የመስጠት ግንባር ቀደም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አናሳስባለን። በተለይ ለሀገራቸው ሉዓላዊነትና አንድነት በጋራ ተሰልፈው መስዋዕትነት የከፈሉት የአማራ ልዩ ሀይል፣ ፋኖ እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ቅራኔ ውስጥ እንዳይገቡና ለግጭት እንዳይዳረጉ በከፍተኛ ትኩረትና ጥንቃቄ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል።
መንግስት የክፉ ቀን አጋሩ ከነበሩትና በእውነትም ከሕዝብና ከሃገር ፍላጎትና ጥቅም በተፃራሪ የመቆም ተሞክሮ፣ ዝንባሌና ታሪክ ከሌላቸው የአማራ ገበሬዎች፣ ወጣቶችና ፋኖዎች ጋር ያልተገባ ግብግብ ውስጥ መግባት የለበትም። ይህ ጉዳይ በውይይት እና ምክክር ሊፈታ የሚችል መሆኑን ማስገንዘብ እንፈልጋለን።
በሌላ በኩል ግን የተለያዩ የፖለቲካ አጀንዳዎቻቸውን በሸፍጥ ለማስፈፀም የሚንቀሳቀሱ አካላት ባልተገባ መልኩ የአማራ ሕዝብ ተቆርቋሪ መስለው እንደሚቀርቡ ሊታወቅ ይገባል። ትላንት የአማራ ሕዝብ መጠነሰፊ የወረራ ጦርነት ሲከፈትበት ዳር ላይ ቆመው የነበሩ እና ከጠላት ጋር አብረው የከረሙ አካላት የአማራ ሕዝብ ድንገተኛ ወዳጅ እና ወኪል በመሆን ግጭት ለማስነሳት የ
01/05/2023
ገና ሲጀምር ብዙዎች ተስፋ ጥለውበት ነበር። ብዙዎችም ተከትለውታል፣ ወደውታል፣ ደግፈውታልም። በሂደት ግን በመሪነቱ ላይ ብዙዎች ጥርጣሬን ማንሳት ጀመሩ። እንደተፈራውም ሆነ! መሪነቱንም መቋቋም አቃተው። በጥርጣሬ ህዝቡን አወዛገበ። ደጋፊውን አራገፈ። መጣል የሌለበትን ነጥብ ሁሉ እዚም እዚያም መጣል ጀመረ። አሁን ብዙዎች ወዴት ነው ጉዞው እያሉ አፍጠው እየጠየቁ ነው 😳 (አርሴናል ሆይ ወዴት ነው ጉዞህ? 😏)
01/05/2023
አብይ ሚዲያ ኮርፖሬሽን - አሚኮ እንዲህ ነበር ፋኖ ተሰማራ እያለ ሲለፍ የነበረው። ይህ በጥቁር አማሮች ሚመራ ውለታ ቢስ ሚዲያ ዛሬ ተገልብጦ በፋኖ ላይ እየዘመተ ነው።