16/02/2026
ሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡
ሰኞ የካቲት 09/2018 ዓ.ም
የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የጽ/ቤቱ ኃላፊ እንዱሁም የስራዎች አስተባሪዎች እና ሠራተኞች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
የሰኞ ማለዳ የሠራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር "የስራ ተነሳሽነት" በሚል ርዕስ ዙሪያ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የፈተና አስተዳደር ባለሙያ በሆኑት ወ/ሮ ኬሪያ ሳዲቅ የቀረበ ሲሆን በክፍለ ከተማው ጽ/ቤት ውስጥ ላሉ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች የስራ ተነሳሽነት በተቋም ያለው ጥቅም፣ የስራ ተነሳሽነት ላይ በጎ ተፅዕኖ ያላቸው ጉዳዮች እና አስፈላጊነት ዙሪያ የራሳቸውን ልምድ ያካፈሉ ሲሆን በእውቀት ሽግግሩ ላይ በተገኙ ሰራተኞች በቀረበው የእውቀት ሽግግር ርዕስ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጎበት የተገኘውን እውቀት መሰረት በግለሰብ ደረጃ የስራ ተነሳሽነትን በመጨመር የጽ/ቤታችንን አፈፃፀም ከፍ ለማድረግ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ የዛሬው የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር ተጠናቋል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisketemaeducationoffice