29/03/2025
Eid mubarak
BREAKING NEWS: Eid Al Fitr 1446/2025 is tomorrow: Sunday, 30 March 2025
The Crescent for the month of Shawwal 1446 was SEEN in Saudi Arabia today subsequently tomorrow is the beginning of the month of Shawwal 1446

05/06/2023
መረጃዎችን እንሰብስብ፣እናደረጅ!!!
----------------
ኡስታዝ ሙሀመድ አባተ
የሸገር ከተማ አስተዳደር/የኦሮሚያ ክልል መንግስት የፈፀማቸው መስጂዶችን የማፍረስ ዘመቻ የፈጠራቸው ችግሮች በሀገር አቀፍ ደረጃ ከባድ ዋጋ እያስከፈሉን ይገኛሉ።የሚመለከተው የመንግስት አካልም የሸገር ከተማ አስተዳደር/የኦሮሚያ ክልል መንግስት ህዝበ ሙስሊሙን እና ተቋሙን በመናቅ እየፈጠረ ያለውን ሀገራዊ ቀውስ ትኩረት ሰጥቶ ለማስቆም አልቻለም።በቀጣይ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት አስቸኳይ መፍትሄ ያስፈልጋል።
በሸገር ከተማ አስተዳደር ግብታዊ እርምጃ በዘመቻ የፈረሱ መስጂዶችን የሚያሳዩ መረጃዎች እና ማስረጃዎች በአብዛኛው ተሰናድተዋል።የቀሩትም በመሰናደት ላይ ይገኛሉ።
-----
በሁለቱ ጁምዐዎች በአዲስ አበባ ከተማ በአንዋር እና በበኒ ኑር መስጂድ የሆነውን በትክልል ሊያስረዱ የሚችሉ:-የምስል፣የድምፅ እና የድምፅ ከምስል ማስረጃዎች ሌላ ምንም አይነት ፅሁፍም ሆነ ድምፅ ሳይጨመርባቸው መሰብሰብ፣ማደረጃት እና መሰነድ ያስፈልጋል።ይህ ስራ ኮሚቴው እየሰራ ላለው ስራ ግብአት ይሆናል።
******
በተለይ በሁለቱ ጁምዐዎች (ግንቦት 18/2015 እና ግንቦት 25/2015) በፀጥታ አካላት በተተኮሱ ጥይቶች ተመተው የሞቱ ምእመናን እና ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በሚመለከት በአዲስ አበባ ፖሊስ በኩል (ለህዝብ ይፋ እንደተደረገው ሁሉ) የሚሰራው የማጣራት እና የምርመራ ስራ እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሚቴውም ይህን ጉዳይ የመከታተል እና የሆነውን የማጣራት ለህዝብ ሙስሊሙ ብሎም ኃላፊነቱን ላሸከመው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ጠቅላላ ጉባኤ ይፋ የማድረግ ኃላፊነት ስለተጣለበት ሁሉም በቻለው አቅም በእጁ ያሉትን መረጃዎች በመጠበቅና ከላይ በተጠቀሰው አግባብ ለኮሚቴው በማዘጋጀት የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከት ያስፈልጋል።
******
"የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው" የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በኡማ ሆቴል በተካሄደ የአንደኛ አመት አስቸኳይ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በሙሉ ድምፅ የተሰየመና ከሸገር ከተማ መስጂዶችን የማፍረስ ዘመቻና ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ በተለያዩ የሐገራችን ክፍሎች "መስጂዶቻችንን አታፍርሱ!!!" በማለት ድምፁን በሰላማዊ መንገድ ለማሰማት በወጣ ምእመን ላይ የተወሰደው ኢ-ሰብአዊና ኢህገ-መንግስታዊ የሆነ የግድያና የደረሱ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳትን የማጣራት፣መረጃና ማስረጃን መሰረት በማድረግ ህግና ስርአት እንዲከበር፣ ተጠያቂነትም እንዲሰፍን የማድረግ እና ለችግሮቹ መነሻ ለሆኑ ጉዳዮችም አፋጣኝ የጋራ መፍትሄ ለማበጀት የተቋቋመ ኮሚቴ ነው።
******
በመሆኑም ማንኛው ከላይ ከተጠቀሱ መሰረታዊ ጉዳዮች ጋር ተያያዥነት ያላቸው መረጃና ማስረጃዎች በእጁ ያለ አካል መረጃዎቹን በሚመቸው መልኩ ለኮሚቴዎቹ እንዲያደርስ እየጠየኩ ኮሚቴው መረጃዎቹን የማሰባሰብ፣የማደረጀት፣ የመሰነድ እና የህግ ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚጠቀም ይሆናልና መረጃዎቻችንን አወንሰብስብ፣ እናደረጅ!!!
26/05/2023
በወቅታዊ ጉዳይ #ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ።
💫💫💫💫💫💫💫💫
መብቱን በሰላማዊ መንገድ ለመጠየቅ በወጣ ህዝብ ሙስሊም ላይ የተወሰደው እርምጃ ፍፅም ተቀባይነት የሌለው ፣ ኢ-ፍትሃዊና ኢ-ዲሞክራሲያዊ በመሆኑ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ያወግዛል።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ሲቲ የመስጅድ ፈረሳ እንዲቆምና የፈረሱትም በአስቸኳይ መተኪያ እንዲሰጣቸው እንዲሁም በጉዳዩ ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በተደጋጋሚ በደብዳቤ ለሚመለከተው አካል ለማሳወቅ የተሞከረ ሲሆን የመስጅድ ፈረሳው ባለመቆሙ ህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞውን በዛሬው እለት በአደባባይ ድምፁን በሰላማዊ መንገድ አሰምቷል።
ይህንንም ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ተከትሎ በታላቁ አንዋር መስጅድ የፀጥታ አካል በወሰዱት ኢ-ህገ መንግስታዊ እና ኢ ሰብአዊ እርምጃ የሰው ሂይወት አልፋል፣ብዙሃን ቆስለዋል።
በመሆኑም ይህንን አስከፊ ጥቃት የፈፀሙ እና ያስፈፀሙ የፅጥታ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ አጥብቀን እንጠይቃለን ።
በቀጣይም የሚመለከተው አካል በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ እየተከናወነ ያለውን ድርጊት እንዲያስቆምነና ወደ ውይይት በመምጣት ስር ነቀል የእርምትና እርምጃ ተጠናክሮ እንዲተገበር አጥብቀን እንጠይቃለን።
የሀይማኖት ጉዳይ እና የእምነት ተቋማት ጉዳይ ሁሌም ቢሆን በስክነት መታየት ሲገባው ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በእምነት በተቋማቱ ጉዳይ ሲከተሉት የነበረውን አካያሄድ እንደ ተሞክሮ ከመውሰድ ይልቅ በዚህ አከያሄድ የተሰራው አስነዋሪ ተግባር የሀገራችንን ብሎም የከተማችንን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ እየጣለ ይገኛል።
በሸገር ከተማ መስጅድን በተመለከተ እየተከናወነ ያለው ድርጊት፣ሀላፊነት የጎደለው፣የህዝበ ሙስሊሙን ክብር ያዋረደ፣ሀገራችን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ፣የመንግስት የለውጥ ሪፎርምን ወደ ሀላ የሚመልስ በመሆኑ ጉዳዩ እንደ ሀገር ሊታሰብበት ይገባል።
በዛሬውም እለት በመስጅድ ፈረሳ ሳቢያ በሰላማዊ መንገድ መብቱን ለመጠየቅ በወጣው ህዝበ ሙስሊም ላይ በተወሰደው ኢ-ህገ መንግስታዊ እርምጃ ሒይወታቸው ላለፉ አላህ (ሱ.ወ) ጀነትን እንዲወፍቃቸው፣ለመላው ህዝበ ሙስሊም መፅናናትን እንመኛለን።
የከተማችንም ህዝበ ሙስሊሙ በቀጣይ ጉዳዩን በሰከነ መንፈስ እንዲከታተል አደራ እንላለን።
ግንቦት 18/2015
26/05/2023
#በወቅታዊ #ጉዳይ #ከአዲስ #አበባ #እስልምና #ጉዳዮች #ከፍተኛ #ምክር #ቤት #የተሰጠ #መግለጫ።

ለመስጂዶች የተከፈ የህይወት ዋጋ! !
የሸሂዱ ወንድማችን ደ*ም በከንቱ ፈሶ አይቀርም ❗❗
#ሸገርሲቲ
#የመስጂድፈረሳ
#ሙስሊምጠልነት
#19መስጂዶች
26/05/2023
ኢና ሊላሂ ወኢና ዒለይሂ ራጂዑን ‼
መርካቶ ጭድ ተራ ላይ አንድ ወንድማችን ህይወቱ አለፈ።
ሸሂድ ሆኗል‼
ጌታችን አላህ (ሱወ) ከእውነተኞቹ፣ ከሰማዕታቱና ከደጋጎቹ ጎን ይቀስቅሰው! አሚን!
ግፉ ከመጠን አለፈ
ኢስላማዊ ድህረ ገፅ