01/12/2023
❤ ኅዳር ➋⓵ ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ።
“ #ጽዮን” ማለት “ #ጸወን – #አምባ – #መጠጊያ” ማለት ነው:: አንድም በምሥጢሩ “ ” ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን : ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል::
ይህን በዓል በተለየ መልኩ የምናከብርበት ምክንያት የተወሰኑት
✨በብሉይ ኪዳን ታቦተ ጽዮን የፈጸመችውን ልዩ ልዩ ገቢረ ተአምራትን ለማሰብ
✨ቀዳማዊ ምኒልክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛርያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበት ዕለት በመሆኑ
✨በሦስት መቶ ሠላሳ ዓመተ ምሕረት በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ይሁን ተብሎ ዐዋጅ የታወጀበት
✨ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ምሳሌ ራእይ ያየበት
✨ነቢዩ ሕዝቅኤል በተቆለፈች ቤተ መቅደስ
✨ዕዝራ በቅድስት ሀገር ምሳሌ ራእይ ያየበት
✨አብርሃና አጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተመቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያናትን ስታቃጥል ታቦተ ጸዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሐይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን፡፡
“ መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ።ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ።አሮጊቶችዋን እጅግ እባርካለሁ፥ ድሆችዋንም እንጀራ አጠግባለሁ።ካህናቶችዋንም ደኅንነትን አለብሳቸዋለሁ፥ ቅዱሳኖችዋም እጅግ ደስ ይላቸዋል።”
#መዝ 131:13
የወላዲተ አምላክ አማላጅነት የቅዱሳን ተራዳኢነት ከእኛ አይለየን፡፡
ወስብሐት #ለእግዚአብሔር ፡፡
ወለወላዲቱ #ድንግል፡፡
ወለመስቀሉ #ክቡር፡፡
30/11/2023
30/11/2023
30/11/2023
30/11/2023
30/11/2023
30/11/2023
22/11/2023