11/02/2022
ማይክሮሶፍት ለተወሰኑ የዊንዶዉ-10 “ቨርዥኖች” ከግንቦት ወር ጀምሮ የደህንነት ዝመና ማቅረብ እንደሚያቆም ገለጸ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2014: ማይክሮሶፍት ኩባንያ ለዊንዶዉስ-10 ቨርዥን 20H2 እና ከዚያ በፊት ለነበሩ ምርቶች የሚያቀርበዉን የደህንነት ዝመና ከፈረንጆቹ ግንቦት 10/2022 ጀምሮ እንደሚያቋርጥ ገለጸ።
በግንቦት ወር የደህንነት ዝመና ከሚቋረጡባቸዉ የዊንዶዉስ-10 ምርቶች ዉስጥም ቨርዥን (version) 1909 እና 20H2 ይገኙበታል።
እንደ ማይክሮሶፍት ማሳሰቢያ የዊንዶዉ ተጠቃሚዎች ወሳኝ የሆኑ ወርሃዊ የደህንነት ዝመናዎችን ለማግኝት፣ የሚከሰቱ የደህንነት ተጋላጭነቶችን ለመድፈን እና የኮምፒዉተራቸውን አገልግሎት ፍጥነት ለማሳደግ የዊንዶዉስ-10 ምርቶቻቸዉን ማሻሻል ይገባቸዋል ብሏል።
በፈረንጆቹ ጥር 21/2022 ለዊንዶዉስ-10 ተጠቃሚዎች የምርት ‘21H2’ ማቅረቡን ያስታወሰው ማይክሮሶፍት ከዚህ ባለፈም ለዊንዶውስ-11 ምርቶች ‘21H2’ ከፈረንጆቹ ጃኑዋሪ 27 ጀምሮ በስፋት ተደራሽ ማደርጉን ጠቁሟል።
በዚህም የዊንዶዉስ ምርት ተጠቃሚ ሆነዉ የሚጠቀሙበት ኮምፒዉተር ዊንዶዉስ-11 ለሆኑና መስፈርቶችን ለሚያሟሉ ደንበኞቹ በሙሉ የዊንዶዉስ 11 ኦፕሬቲንግ ሲስተም ማቅረቡን ገልጿል።
እርስዎም የዊንዶዉስ-10 ምርትዎን ለማሻሻል ካሰቡ በቅድሚያ ‘start’ የሚለዉን አማራጭ በመምረጥ፣ ‘setting’ የሚለዉን መጫን በመቀጠል ከቀረቡ ዝርዝሮች ዉስጥ ‘update & security’ የሚለዉ መምረጥ ‘check for update’ የሚለዉን በመጫን የቀረበልዎትን የኮምፒዉተር ዝመና መተግበር ይችላሉ።
ወይም “type here search” የሚለዉ ቦታ ላይ “check for updates” ብሎ በመጻፍ የሚመጣዉን አማራጭ በመጫን ኮምፒዉተርዎን ቨርዥን በማሳደግ በራስዎ፣ በተቋምዎ እና በሀገር ላይ ሊድርስ የሚችለዉን የሳይበር ጥቃት ይከላከሉ።
16/01/2022
መንግሥት ፋኖን ትጥቅ ሊያስፈታ ነው የሚለው አሉባልታ መሰረተቢስና የአማራን ሕዝብ ለመከፋፈል የታለመ የጠላት ሴራ መሆኑን የአማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ።
ባሕር ዳር፡ ጥር 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) መንግሥት ፋኖን ትጥቅ ሊያስፈታ ነው የሚለው አሉባልታ መሰረተቢስና የአማራን ሕዝብ ለመከፋፈል የታለመ የጠላት ሴራ መሆኑን የአማራ ክልል መንግሥት አስታውቋል።
የክልሉ መንግሥት ከፋኖ አደረጃጀት አባላት ጋር ተወያይቷል።
ፋኖ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ሀገርና ሕዝብን እየታደገ ያለ መከታ ኃይል ነው። ስለሆነም የፌደራልም ኾነ የክልል መንግሥት ፋኖን ትጥቅ የማስፈታት ሐሳብ የለውም፤ ሊኖረውም አይችልም ተብሏል በመድረኩ።
በቀጣይ የክልሉ መንግሥት የመሳሪያ አስተዳደር ሥርዓቱን ሊያሻሽል እንደሚችልም ተገልጿል።
ፋኖ በስምም ሆነ በግብሩ የአማራ ሕዝብ ክብር መገለጫ በመሆኑ በፋኖ ስም የሚነግዱ አካላትን ፋኖና መንግሥት በጋራ ይታገላሉ ተብሏል። ፋኖን ማደራጀትና ማጠናከር የክልሉ መንግሥት አቅጣጫና ተግባር ኾኖ ሳለ ትጥቅ ማስፈታት የሚለው አሉባልታ አማራን የመከፋፈል እርስ በርስ የማጋጨት የማዳከም ሴራ አካል መሆኑም ተገልጿል።
ዘጋቢ:- አቢዮት ከፋለ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
07/01/2022
አሁን በእኛ ዘመን የሰለጠነና ያደገ ጥቁር ህዝብ ወይም አገር ለምን እንደሌለ ግራ ይገባኛል።ጥቁርነታችን ነው ወይስ ኃላ ቀርነታችን ነው የቀደመው ?ማለቴ ኃላቀርነታችን አናዶን ጠቁረን ከሆነስ ብዬ ነው።በታሪክ ከመመፃደቅ እና በሌሎች ከማሳበብ ጥቁርነታችን ሳይሆን ስንፍናችንና አስተሳሰባችን ከሌሎች ውጫዊ ክስተቶች ጋር ተባብሮ ተፈጠረብንን እውነተኛ ጠላታችን ማሸነፊያ ጊዜው አሁን ነው።ጠላታችንም ስለራሳችንናዠ እና ስለሌሎች ተቀብለን የገዙን ውሸቶችናጨለምተኛ አስተሳሰባችን።እንጂ ውስጡ እኮ ሲታይ ሁሉም ሰው ቀይ ደምናነጭ አንጎል ነው ያለው።ቀለምን ካየን ምነው እሱን አናይም።ህይወት በደም አስተሳሰብም በጭንቅላት ውስጥ እንጂ በቆዳ ላይ አይደለምና !!!
11/12/2021
ሰበር ዜና‼️
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት ዋናውን የወልድያ መቀሌ ጎዳና ቆርጦታል
***************************
( ኢ ፕ ድ)
በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመሩት የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ በአሸባሪው ወራሪ ላይ በሰነዘሩት ክንደ ብርቱ ማጥቃት፣ በምሥራቅ ግንባር ስትራቴጂያዊ የሆኑትንና ወራሪው በፍጻሜ ዋዜማ ላይ መሆኑን የሚያሳዩትን የዞብል ሠንሠለታማ ተራሮችን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የአርጆ፣ ፎኪሳ እና ቦረን ከተሞችን ተቆጣጥሯል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ የጉራ ወርቄ አካባቢዎችን በመቆጣጠር የወልድያ መቀሌ ዋናውን አውራ ጎዳና በመቁረጥ ጠላት መውጫ አጥቶ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ ግንባር የድሬ ሮቃና የሶዶማ ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ከተሞችና ተራሮች በመቆጣጠር ጥምር ጦሩ ወደ ሐራ ከተማ እየገሠገሠ ይገኛል፡፡
በውጫሌ ግንባር ደግሞ የአምባሰል ከፍተኛ ሠንሠለታማ ተራሮችን ጨምሮ የሮቢትና የጎልቦን፣ በወረባቦ ወረዳ የሚሌ ኮትቻን፣ በሐብሩ ወረዳ የኮልቦን፣ የመርካታና የፋጂን አካባቢዎችን በመቆጣጣር ወደ መርሳ ከተማ እየገሠገሠ ነው፡፡
በእነዚህ ግንባሮች በተደረገው ኦፕሬሽን በአሸባሪው የጠላት ኃይል ላይ በተሠነዘረበት ማጥቃት ጠላት ሙት፣ ቁስለኛና ምርኮኛ ሆኗል፡፡ የወገን የመካናይዝድ ኃይልና ንሥሮቹ የአየር ኃይሉ በጥምረት ባካሄዱት ኦፕሬሽን የጠላት ኃይል ምንም ዓይነት ተሸከርካሪ እና ከባድ መሣሪያዎችን ይዞ እንዳይንቀሳቀስ ስላደረጉት፣ ጠላት በየአቅጣጫው ጥሎ ለመፈርጥጥ ተገድዷል፡፡
ለበርካታ ቀናት ያከማቻቸውን ቁስለኞችንም ጥሎ ፈርጥጧል፡፡ የዘረፈውን ንብረትም በየቦታው እያዝረከረከ እግሬ አውጪኝ በማለት ላይ ይገኛል፡፡ ጠላት ዋናው የቆቦ ወልድያ መንገድ ስለተዘጋበት በድንብርብር በጋሸና ላሊበላ በኩል ለማምለጥ ከፍተኛ ትንቅንቅ ቢያደርግም በወገን ጥምር ጦር እንደ ቅጠል ከመርገፍ አልተረፈም፡፡
በወረራ ውስጥ የቆየው ኅብረተሰብ በከፍተኛ ወኔና ጀግንነት በመነሣሣት ከወገን ጦር ጋር ተባብሮ በመሰለፍ አኩሪ ተጋድሎ ፈጽሟል፡፡ አሁንም ክንደ ብርቱውን የወገን ጥምር ጦር መቋቋም አቅቶት በየጢሻው የተበተነውን የአሸባሪውን ጀሌ፣ የየአካባቢው ሕዝብ በመማረክ፣ እምቢ ያለውንም በመደምሰስ የጀግንነት ተግባሩን እንዲፈጽም መንግሥት ጥሪ ያቀርባል፡፡
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለኢፕድ በላከው በዚሁ መረጃ "ነጻነታችንን የምናረጋግጠው በተባበረ ክንዳችን ነው!" ሲል ገልጿል።