05/06/2024
ግንቦት ፴ (30)
፡፡
ወበዛቲ ዕለት፤ በዚህች ግንቦት 30 ቀንም የጻድቋ ዜና ማርያም በዓለ ልደቷ ነው፡፡
ጻድቋ፤
፠ በቅዱሱ ንጉሥ ላሊበላ ዘመነ መንግሥት በጎጃም ምድር ከአባቷ ገብረ ክርስቶስና ከእናቷ ዓመተ ማርያም ግንቦት 30 ተወለደች፡፡
፠ በዋሻ እንድርያስ ገዳም ገብታ ለ25 ዓመት በጾም በጸሎት ተጋደለች፤
፠ ከሦስት ቅዱሳን (አቡነ እንድርያስ ከጣራ ገዳም፤ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከዋሻ ተክለ ሃይማኖትና ቅድስት ዜና ማርያም ከደሪጣ ገዳሟ ሆነው) በጸጋ እግዚአብሔር ከያሉበት ሆነው ይነጋገሩ ነበር፡፡
፠ ቅዱስ ላሊበላ በ11ኛው ክፍለ ዘመን ገዳሟን አንጾላታል፤ ዐፄ ይስሐቅ በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በስሟ ገድሞላታል፡፡
ዜና ታሪኳን በበዓለ ዕረፍቷ ቀን በነሐሴ 30 ቀን በስፋት ጽፈነዋል፡፡
ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን፤ እኛንም በጻድቋ ዜና ማርያም ጸሎትና አማላጅነት ይማረን፤ አሜን፡፡
/ / ገጽ