PICE Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from PICE, Education & Learning, https://goo. gl/maps/pRCrxGcKvqhzPxVB 6, Addis Ababa.

በ16ኛው የቴክኖሎጂ ሳምንት ላቅ ያለ ውጤት ላስመዘገቡ አካላት የምስክር ወረቀት ተበረከተአዲስ አበባ — ግንቦት 2018 ዓ.ምበ2018 በጀት ዓመት በከተማ አቀፍ በተካሄደው 16ኛው የቴክኖሎጂ...
21/05/2026

በ16ኛው የቴክኖሎጂ ሳምንት ላቅ ያለ ውጤት ላስመዘገቡ አካላት የምስክር ወረቀት ተበረከተ

አዲስ አበባ —
ግንቦት 2018 ዓ.ም

በ2018 በጀት ዓመት በከተማ አቀፍ በተካሄደው 16ኛው የቴክኖሎጂ ሳምንት ላይ ማዕከሉን ወክለው ተሳትፎ ለነበራቸውና ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላሳዩ የማዕከሉ አሰልጣኞች የዕውቅና እና የምስጋና ወረቀት የመበርከት ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ።

በዕለቱ በተከናወነው መርሀግብር ላይ በቴክኖሎጂ ሳምንቱ ላይ የተለያዩ የፈጠራ ፕሮጀክቶችን ለሰሩ እና ላቀረቡ ባለሙያዎች የምስክር ወረቀት የተበረከተላቸው ሲሆን፣ በተመሳሳይ መልኩ በተግባራዊ ጥናትና ምርምር ዘርፍ ላይ ማዕከሉን በመወከል በውድድሩ ላይ ለተሳተፉና ላቅ ያለ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም የምስጋና ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

የዕለቱን መርሀግብር በመምራት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቴክኖሎጂ ልማትና ኢንኩቤሽን ም/ዲን አቶ ተስፋዬ ወርቁ ማዕከሉ በቴክኖሎጂ ሳምንት ላይ ባሳየው እጅግ ከፍተኛ ተሳትፎና ባስመዘገበው ውጤት ምክንያት የዋንጫ ሽልማትና የምስክር ወረቀት እንደተበረከተለት ገልጸዋል።

የመርሀግብሩ ማጠቃለያ ላይ የማዕከሉ ዋና ዲን አቶ አድማሱ በቀለ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ይህ ታላቅ ውጤት ሊመዘገብ የቻለው በግለሰብ ጥረት ብቻ ሳይሆን በማዕከሉ ውስጥ የሚገኙ መላው አካላት በጋራና በህብረት በመስራታቸው መሆኑን አውስተዋል። ዋና ዲኑ አክለውም ይህ ስኬት እንዲመጣ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ የማዕከሉ አባላት በሙሉ ያላቸውን ጥልቅ ምስጋናና አክብሮት አቅርበዋል።

የልህቀት ማዕከሉ የሶሻል ሚዲያ ፕላት ፎርሞችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ

Websit ....
https://pice.sims.aatvetb.edu.et/

Telegram Channel …….PICE (https://t.me/pice1962)

YOUTUBE Channel ……. PICE1962
(https://www.youtube.com/)

Facebook Channel ………….PICE
(https://m.facebook.com/edu.pice.et/)

TikTok Channel ………Pice_1962
(https://www.tiktok.com/)

"የቴክኖሎጂ ልህቀት ለሃገር ብልፅግና"በሚል መሪ ቃል ለሦስት ቀን ሲካሄድ የቆየው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት በዛሬው እለት ተጠናቀቀ።ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ምበአዲስ አበባ አስተዳደር ስራና ክህ...
06/05/2026

"የቴክኖሎጂ ልህቀት ለሃገር ብልፅግና"
በሚል መሪ ቃል ለሦስት ቀን ሲካሄድ የቆየው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት በዛሬው እለት ተጠናቀቀ።

ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ "የቴክኖሎጂ ልህቀት ለሃገር ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል በአራዳ ፖርክ ለሦስት ቀን ሲካሄድ የቆየው 16 ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት በዛሬ እለት የተጠናቀቀ ሲሆን በኤግዚቢሽኑ ላይ በተካሄደው የተለያዩ ውድሮች ማዕከሉ የዋንጫና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል።

በዚህም በተደረገው ማምረቻ የቴክኖሎጂ ፋብሪኬሽን ኢንጅነሪንግ ውድድር ላይ በማዕከሉ 5 መካኒካል መሃንዲሶች አማካኝነት በለማው የወርቅ ደለል ማጠቢያ ማሽን የልህቀት ማዕከሉ የ3ኛ ደረጃን በመያዙ የምስክር ወረቀት የተበረከተለት ሲሆን በተጨማሪም የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ላይ ለሰራው ስኬት ልዩ የዋንጫ ተሸላሚ በመሆን አጠናቋል።

06/05/2026
04/05/2026
04/05/2026
01/05/2026

የወርቅ ማጣሪያ
16ኛው የቴክኖሎጂ ሳምንት

16ኛው የቴክኖሎጂ ሳምንት
01/05/2026

16ኛው የቴክኖሎጂ ሳምንት

30/04/2026

16 ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኖሎጂ ሳምንት
የቴክኖሎጂ ልህቀት ለሀገር ብልፅግና በሚል መሪቃል በልህቀት ማዕከሉ እየተከበረ ይገኛል፡፡

የልህቀት ማዕከሉን አሰልጣኞች አቅም መገንባት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ እንደሆነ ተገለጸ፡፡መጋቢት 25/2018 ዓ.ም ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል ለቴክኒክና ሙያ አመራሮችና አሰል...
03/04/2026

የልህቀት ማዕከሉን አሰልጣኞች አቅም መገንባት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

መጋቢት 25/2018 ዓ.ም

ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል ለቴክኒክና ሙያ አመራሮችና አሰልጣኞች፣ ለኢንዱስትሪ ሙያተኞች የክህሎት ክፍተቶችን ማዕከል ያደረገ አጫጭር ስልጠናዎችን መስጠት አንዱ ተልዕኮው እንደሆነ ይታወቃል በማዕከሉ ውስጥ ብቁ አሰልጣኞችን ማፍራትና ለዘመናዊ አሰለጣጠን ዘዴ ማብቃት ከማዕከሉ የሚጠበቅ ተግባር ነው፡፡

ለቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች፣ ለኢንዱስትሪ ሙያተኞች የክህሎት ክፍተቶችን የመሙላት ትልቁን ድርሻ የሚወስዱት የማዕከሉ አሰልጣኞች ሲሆኑ የልህቀት ማዕከሉን አቅም የመገንባት ስራ ደግሞ ከማዕከሉ ይጠበቃል፡፡

በዚህም የልህቀት ማዕከሉን አሰልጣኞች አቅም መገንባ ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ እንደሆነ የማዕከሉ የአቅም ግንባታ ም/ዲን የሆኑት አቶ መክብብ አሰፋ የገለፁ ሲሆን ለጊዜው በ5 ዋና ዋና ርዕሶች በ2 ዙር ለማዕከሉ አሰልጣኞች እየተሰጠ ያለ ስልጠና እንደሆነ አንስተው ስልጠናው ከፌደራል ቲቬት ኢንስቲትዩት በመጡ አሰልጣኞች እየተሰጠ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡፡፡










የስልጠናው ርዕሶች ከላይ የተጠቀሱት እንደሆኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የልህቀት ማዕከሉ የሶሻል ሚዲያ ፕላት ፎርሞችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ

Websit ....
https://pice.sims.aatvetb.edu.et/

Telegram Channel …….PICE (https://t.me/pice1962)

YOUTUBE Channel ……. PICE1962
(https://www.youtube.com/)

Facebook Channel ………….PICE
(https://m.facebook.com/edu.pice.et/)

TikTok Channel ………Pice_1962
(https://www.tiktok.com/)

Address

Https://goo. Gl/maps/pRCrxGcKvqhzPxVB 6
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 02:00 - 17:00
Tuesday 02:00 - 17:00
Wednesday 02:00 - 17:00
Thursday 02:00 - 17:00
Friday 02:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when PICE posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to PICE:

Shortcuts

Share