Excellent
GAGE College
Gage college is a private higher institution established in 1995 to deliver higher education in dipl
10/12/2018
Excellent
Over 500 Contract Templates Free Download Download a variety of Templates for free include Balance Sheets, Budget Planner, Business Financials, Business Letters, Business Plan Templates, Business Startup Checklist, Business Startup Expenses, Cashflow Forecast, Client Profile Related Documents, Content Outsourcing, Contractor Documents Legal...
16/10/2018
16/10/2018
Register Now!! Don’t be late!!
Diploma! BA Degree! Master Degree!!
06/04/2018
ዜና አበው
"ሶስቱ ዕንቁዎች"
ግዜና ዘመን ያገናኛቸው ባለታሪኮች ቅድስት ቤተክርስቲያን ፓትርያርክዋን ከውስጥ ባሉ የስልጣን ጥመኞች ጭዳ አቅራቢነት አልቦ እግዚአብሔር ብለው በተነሱ ነፍሰ በላ የደርግ ወሮበሎች በገመድ ታንቀው በተገደሉበት ገዳማት ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ባይርቃቸውም ሐብታቸው በተወረሰበት ጉባኤ ቤቶች በተበተኑበት ዘመን እነዚህን ሶስት አበው አምላክ አስነሳ ከያሉበት ለመንጋው እረኛ ይሆኑ ዘንድ
አባ መልዕኩ ከወላይታ አምጥቶ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሐይማኖት ተብለው ተሾሙ
አባ መዝገበ ስላሴን ከኢየሩሳሌም መጥተው
ብጹዕ አባ ጎርጎርዮስ ጳጳስ ዘሸዋ ተብለው ተሾሙ
ሊቀ ስልጣናት አባ ኤልያስ ቀድመው ከራሻ መጥተው ነበርና የቅዱስ ፓትርያርክ ልዮ ጸሐፌ ቆይተውም አባ ኒቆዲሞስ ተብለው ሊቀጳጳስ ሆኑ፡፡
የወላይታው ሐዋሪያ አበል ሳይበሉ ደሞዝ ሳይቆረጥላቸው ሞንታርቦ ሳያስጭኑ በባዶ እግራቸው 400ሺ ህዝብ ከአረማዊነት የመለሱ ከበሶና ድንች ውጭ እህል የማይቀምሱ በምስሉ እንደምታዮት ባዶ እግራቸውን ከታቦቱም ሳይልቁ ከጳጳሱም ሳይገዝፉ ምንጣፍ አንጥፉልኝ ወንበር ዘርጉልኝ ሳይሉ የኖሩ ሐዋሪያ ዛሬ በየንግስ በዓላቱ ከታቦታቱ ይልቅ ከብረው ገነው የሚታዮ ቅጥ ያጣ ስርአት እያየን ነው አባታችን ደሞዛቸውን በፍጹም ሳይቀበሉ ነው ዘመናቸው ያለቀ ያን የደም መጣጮች ዘመን ጸሎታቸው ሐመር ሆኖ ቤተክርስቲያንና መንጋውን አሻግሮዋል፡፡
አባ መዝገበ ስላሴ አቡነ ጎርጎርዮስ
እምዬ እምዬ እምዬ ዜና መዋዕላቸውን ከልጆቻቸው ስንሰማ መንን የሚያሰኝ አንድ ሺ ብር ባልሞላ ደሞዝ ከ300 በላይ የሙት ልጆች ደሐ አደጎችን ለማሳደግ የተነሱ ደፋር ተከብሮ አስከባሪ የወንጌል ገበሬ በዘመኑ ለነበሩ የአራት ኪሎ ቅልብ ባለስልጣኖች ሳይሆን ለመንጋው ለሾማቸው ኢየሱስ ክርስቶስ መልዕክተኛ ሆነው በቃልም በህይወትም የሰበኩ የራስ ቅላቸው ሳይሆን ልባቸው የመነነ በዘር ከረጢት ያልተቁዋጠሩ አብረሐማዊ ድንገት ቦግ ብለው የወንጌልን ችቦ አቀጣጥለው የጠፉ የንጋት ኮከብ ዛሬ ለቤተክርስቲያን ማህቶት ለመናፍቃን እረመጥ የሆኑ ሰባክያን አባት ሳይጠገቡ ወጥተው በድንገት የቀሩ የወንጌል ገበሬ እምዬ ጎርጎርዮስ የማይሞት ስምና ታሪክ ባለቤት
አባ ኤልያስ ብጹዕ አቡነ ኒቆዲሞስ መነኮሰ ሞተን ያየንባቸው የምናኔው ንጉስ አንደበታቸው የተገራ ግርማቸው የሚያርድ AbcD የቆጠረው ሁሉ ቤተክርስቲያን ላይ እጁን ሲቀስር ከቤተክርስቲያን የወገኑ እውቀት መታበይን ያላሳደረባቸው ትጉሕ ሰራተኛ በሁለት የተሳሉ ሰይፍ በረከታቸው ይደርብን ዛሬም፡እንዲህ ያሉትን አይንሳን አያሳጣን ጸሎታቸው ይጠብቀን አሜን::
info@ Anteneh Haile
21/02/2018
2018 Australian Government Scholarship Application From 1st September, application opens for Australia Awards Scholarships 2017/2018. There are two categories of Award: Australian Awards Scholarships, to undertake higher degree studies in Australia…
16/02/2018
True! very true!
#ቅቤና #ማር ተከራከሩ ይባላል።
ማርም ተናገረች፡- “የምጣፍጠው እኔ አናት ላይ የምትወጪው ግን አንቺ ነሽ ለምንድነው?” አለቻት። ቅቤም፡- “እኔም ወድጄ አይደለም ገፍተው፣ ገፍተው ነው አናት ላይ ያወጡኝ” አለች ይባላል። ቅቤ፣ ቅቤ የሚኮነው ተንጦ፣ ተንጦ ነው። እግዚአብሔር ሁሉም ሎሌው ነው። በክፉዎች ሳይቀር ይሠራል። ወዳሰበልን የሚያደርሰን እየገፋን ነው። ካልተገፋን ያለንበትን ትንሽ ቦታ ተላምደን እንኖራለን። እርሱ በደጎች አይገፋንም፣ ደጎች መግፋት ባሕርያቸው አይደለምና። ክፉዎች ግን ቅድስናም ይሉኝታም የላቸውምና በእነርሱ ይገፋናል። እነርሱ የሚያውቁት ወደ ገደል እንደሚገፉን ነው፣ ሳያውቁት ግን ወደ ተራራ ይገፉናል። ጠላቶች የነጻ ሠረገላ ናቸው። ለኛ ከ ማይገባን ቦታ እየገፉን ወደ ሚገባን ቦታ ... ከ ዝቅታ ወደ ከፍታ ቦታ ያደርሱናል። በእውነት ጌታ ሆይ ጠላቶቻችንን ባርክልን። እነርሱ ባይኖሩ ሥራው አይበዛልንም ነበር። ይህን ጥንቁቅ ሕይወት፣ ይህን ዝግጅት፣ ይህን ቶሎ ቶሎ መሥራት ያገኘነው ከጠላቶቻችን ነው። እያንዳንዱን ቀን በትክክል እንድንኖር ያተጉንን ጠላቶች እባክህ ባርክልን። የሰዓት ደወል ብንሞላ ጠዋት 12 ሰዓት ሞልተነው፣ ማታ 12 ሰዓት ሊጮህ ይችላል። ቀስቅሱን ብንላቸው ወዳጆቻችን ከሥራችን ለእንቅልፋችን አዝነው ይተውናል። ክፉዎች ግን በሰዓቱ ያነቁናል። እንደዚህ ያሉ ነጻ ደወሎችን ያስቀመጠልን አምላክ ስሙ ይባረክ። እነርሱ እንዳይነቅፉን ስንጠነቀቅ የቅድስናን ሕይወት ያለማምዱናልና እነዚህ ጠባቂዎቻችን ናቸው። የተገፉ ሁሉ ከፍ እንጂ ዝቅ ሲሉ አይተን አናውቅም። ገፊዎች ሲገፉን ከእኛ የክፋት ሰፈር ምን ትሠራላችሁ? እልፍ በሉ እያሉን ነው። ጠላቶች ሐሰተኛ ወዳጆችን ወስደው እውነተኛ ወዳጆችን ያስቀሩልናል። ክፉዎች ጥሩ ማጣሪያ ናቸው። ተረስተን የምንኖረውን እነርሱ ያሳውቁናል። በነጻ ማስታወቂያ ይሠሩልናል። ሰዎች ስማችንን የሚያነሡት በሁለት ነገር ነው። ስለሚወዱንና ስላስደሰትናቸው ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ ስለሚጠሉንና ስላስጨነቅናቸው ነው። እንዲሁ ርእስ መሆን አይገኝም። የአትርሱኝ ሳንከፍል ላስታወሱን በረከት ይሁን። ዮሴፍ ባይገፋ ኖሮ ጎበዝ እረኛ ሆኖ ይቀር ነበር። በመገፋቱ የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ። ጠላት ያውቃል እንላለን፣ እንደ ጠላት ግን አላዋቂ የለም። ኢየሱስን ከኢየሩሳሌም ሊያጠፋ ገደለው፣ በሞቱ ግን በዓለም ሁሉ አበራ። ጠላት ሰፈር እየቀማ ዓለም ያወርሳል። ሰው ማፍረስ ይችል ይሆናል፣ እግዚአብሔር ደግሞ ማስነሣት ይችላል /ዮሐ. 2፡19/። “መገፋት ጥሩ ነው እጅግም ሳይወድቁ፣ የተገፉት ቆመው የገፉት ወደቁ
06/01/2018
ሰብአ ሰገል ኢትዮጵያውያን ናቸውን? [ሊነበብ የሚገባው]
✍በልደት ዋዜማ ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ተጻፈ
የሦስቱ ነገሥታት የአነሣሣቸውና የተነሡበት ሀገር ሊቃውንትን አነጋግሯል፤ የዓለም አቀፍ ተመራማሪዎችን ትኩረት ስቧል፤ ወንጌላዊው ማቴዎስ አመጣጣቸውምንና ስጦታቸውን ተናገረ እንጂ ሀገራቸውን አልጻፈልንም፨
♥♥♥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካፈራቻቸው ትምህርቷን በደንብ ጠግበው ከኖሩ ሊቃውንት ውስጥ ሊቁ አለቃ አያሌው ታምሩ ሦስቱ ኹሉ ኢትዮጵያውያን መኾናቸውን የኢትዮጵያ እምነት በሦስቱ ሕገጋት መጽሐፋቸው ላይ አስረግጠው ይገልጻሉ፤ ሊቁም ከአዳም ሲወርድ ሲዋረድ ትውልደ ካም ወደ ኾነው ወደ ኢትዮጵያዊው ወደ መልከ ጼዴቅ የደረሰው ወርቅ፣ ዕጣንና ከርቤን ለአብርሃም ሰጥቶት ከዚያም እስከ ሰሎሞን ደርሶ ቀጥሎ በጭካኔ አገዛዙ የታወቀው ነገደ እስራኤል እንዲበታተኑ ላደረገው ለሮብዓም ሳይኾን የሰጠው፤ ጌታችን በማቴ 12:42 ላይ በመሰከረላት ሰሎሞንን ጎብኝታ ከርሱም ፀንሳ ልጅን ባገኘችው ለኢትዮጵያዊቷ ለንግሥተ ሳባ ልጅ ለቀዳማዊ ምኒልክ ሰጥቶት እንደመጣና ንጉሥ ባዜን በኢትዮጵያ በነገሠ ጊዜ ጌታ ተወልዷልና ከዚኽ ይዘውለት እንደኼዱ ይናገራሉ እንጂ በትርጓሜው ሐተታ ላይ አይስማሙበትም ፨
♥♥♥ ነቢያት ስለነዚኽ ነገሥታት ሀገር ምን ትንቢት ተናገሩ?
ከነቢያት ዳዊትና ኢሳይያስ የሰብአ ሰገል አመጣጥ ተገልጾላቸው ትንቢት ሲናገሩ፤ ይልቁኑ ኢሳይያስ ሀገራቸው የሳባ ምድር ኢትዮጵያ እንደኾነና ኹሉም ከዚኽ እንደሚኼዱ፦
♥"የግመሎች ብዛት፥ የምድያምና የጌፌር ግመሎች፥ ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ይመጣሉ፥ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ የእግዚአብሔርንም ምስጋና ያወራሉ" (ትንቢተ ኢሳይያስ 60: 6) አለ፨
♥♥♥ዳዊትም "በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ። የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ፤ የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ" (መዝ 71:9-10) ያለ ሲኾን ይልቁኑ አጉልቶ "ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር" የሚለውን ትንቢት ተናግሯል፨ ይኽነን ቃል ዐይናማ የግእዝ ሊቃውንት የተለምዶውን ስሕተታዊ አፈታት በመተው "ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ታደርሳለች" ነው የሚሉት፨
♥ታላላቅ ሊቃውንት እንደገለጹት የግእዝ ቋንቋችን እንደሚያስረዳን "በጽሐ" የሚለው የግእዝ ቃል ቀጥታ የዐማርኛ ትርጉሙ (ደረሰ) ማለት ሲኾን ታበጽሕ ማለት ደግሞ (ታደርሳለች) ማለት ነው፨
"ሰፍሐ" ማለት ግን (ዘረጋ) ማለት ነውና ትሰፍሕ ቢል ትዘረጋለች ባልን ነበር፤ መዘርጋት ማንም ሊዘረጋ ይችላል፤ ዘርግቶም ሊቀበልም ላይቀበልም ይችላል፤ ይኽቺ ቅድስት ሀገረ እግዚአብሔር ግን "ታበጽሕ" (ታደርሳለች) ተብላ ተነግሮላታልና አምላኳ ሲወለድ ሥጦታን በማቅረብ በእውነት አድርሳለች ይኽም ከአምላኳ ለርሷ ብቻ የተሰጠና የተነገረላት ነው (መዝ 67:11)፨
♥♥♥ ሥጦታም መስጠት ጥንቱኑ በብሉይ ኪዳን በነ ንግሥት ሳባ የጀመረችው እንጂ ለሀገሪቱ እንግዳ አይደለም "ለንጉሡም መቶ ሀያ መክሊት ወርቅ እጅግም ብዙ ሽቱ የከበረም ዕንቍ ሰጠችው፤ የሳባ ንግሥት ለንጉሡ ለሰሎሞን እንደ ሰጠችው ያለ የሽቱ ብዛት ከዚያ ወዲያ አልመጣም ነበር" እንዲል (መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 10: 10)፨
♥♥♥ ከምንኖርባት ፕላኔት መሬት ላይ ካሉ የዓለም ሀገራት በብቸኝነት ጌታችን የተወለደበትን ወር ለክርስቶስ አምላኳ የሰጠች ብቸኛ ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት፤ ይኸውም ጌታ የተወለደበትን ወር "ታኅሣሥ" ብላለች በቋንቋዋ በግእዝ፤ ይኸውም በግእዝ ቋንቋ "ኀሠሠ" ማለት ፈለገ ማለት ሲኾን ታኅሣሥ ማለት "ወርኀ ተኀሥሦ" (የፍለጋ ወራት) ማለት ሲኾን፤ ሊቃውንት ይኽነን ያሉበት ምክንያት ሦስቱ ነገሥታት "የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና" እያሉ ፈልገውት ስላገኙት ይኽ ሥያሜን ቀደምት አባቶቻችን ሰጥተዋል (ማቴ 2: 1-2)፨
♥♥♥ ከዓለም ዐቀፍ ተመራማሪዎች ውስጥ ዊልያም ሊዮ ሀንስበሪና ኢ ሀርፐር ጆንሰን Africa's Golden Historical facts እና በሌሎች በጥልቅ ጥናታዊ ሥራቸው "Casapar king of Ethiopia, Melchior King of Ethiopia, and Balthazar king of Saba ... he brought the gift of frankincense ... which was for a thousands years the capital city of African Kingdom" የሚልና ሌላም ገራሚ ጥናትን እናነባለን፨
♥♥♥ በአውሮፓ የዜና መዋዕል ጥናትና ምርምር የያዘው የሰብዐ ሰገል ትውልድ የነበረውን ካህኑ ዮሐንስ (Prester John) የሚሉት ታሪካዊ መሪን ለማግኘት በዓለም ዙሪያ ባደረጉት ሰፊ ዐሰሳ ሥርወ መንግሥቱ ሕንድ ሳይኾን ኢትዮጵያ እንደነበር ገልጠው ጽፈዋል (Thornton, Joe (2012). A Cultural History of the Atlantic World, 1250-1820. Cambridge University Press. pp. 16–17).
♥♥♥ ታላቁ ተመራማሪ ጆን ጃክሰን "ethiopian and the origin of civilization" በሚለው ድንቅ መጽሐፉ ገጽ 28 ላይ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ የሥነ ጠፈር ጥናት የተጀመረባት ጋላክሲን ከነፕቶሎሚ አስቀድማ መሰየም የቻለች ሀገርና ለሌሎች ሀገር ጥናቱን እንዳስተላለፈች በስፋት ገልጾታል፤ እነዚኽም ነገሥታት የሥነ ጠፈር (የኅዋ) መርማሪዎች ከነበሩ ምንጩ እዚኽ መኾኑ ያስረዳል፨
♥♥♥ ሌሎች ተመራማሪዎች በ8ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሣው ቤዴን ጨምሮ ሜልኩ (ሜልኪዮር) የሚባለው የፐርሺያ ንጉሥ እንደነበር ወርቅን በጌታ ፊት እንዳቀረበና ከሰብአ ሰገል አረጋዊው ርሱ እንደኾነ ጠቅሷል፨
♥♥♥ ማንቱሲማር (ጋስፖር) ደግሞ ንጉሠ ሕንድ ሲኾን በጌታችን ፊት ዕጣንን ያቀረበው ርሱ መኾኑን ይጠቅሳሉ፨
♥♥♥ በዲዳስፋ (ባልዛር) ደግሞ ጥቁሩው ንጉሠ ኢትዮጵያ እንደኾነ ሲገልጹ መልኩም ጥቁር እንደነበር በመመስከር ከርቤን በአምላኩ በክርስቶስ ፊት እንዳቀረበ ጽፈዋል፨ ዛሬ ድረስ ምዕራባውያን በሚሠሩት የልደት የፊልም ተውኔትና ሠዓሊዎቻቸው በሚሥሏቸው የሰብአ ሰገል ሥዕሎች ላይ ኢትዮጵያዊውን አንዱን ጥቁር ያደርጉታል፨
♥♥♥ በኹሉም ብንመረምር የኢትዮጵያ የክርስትና ታሪክ በሀገሪቱ የሚጀምረው በ34 ዓ.ም. ሳይኾን ልክ ጌታችን ሲወለድ በ 1 ዓመተ ምሕረት ነው፨
♥♥♥ ኾኖም ግን ዲያብሎስ የጥፋት ሰዎችን እያስነሣ ከዮዲት ጉዲት ጀምሮ በርካቶች ድንቅ የቤተ ክርስቲያኗን ታሪክና ምስጢር የያዙ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ መጻሕፍቷና ቅርሷ እንዲወድሙ ሲያደርግ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ብራናዎቿ በምዕራባውያን ተዘርፈውባት በባሕር ማዶ ለምርምር ሥራ በመዋላቸው ብዙ ምስጢር ተሰውረውብናል፤ ብዙዎቹም ቅርሶቿና መጻሕፍቷ ከመሬት በታች ተቀብረው በዋሻ ውስጥ ተሰውረው ያሉ ናቸውና የሚያወጣው ትውልድ ሲመጣ ያላወቅናቸው ብዙዎች ነገራትን እንደምናውቅ ተስፋ አደርጋለሁ፨
♥♥♥[ደስ በሚያሰኘው በጌታችን ልደት በዓል ዋዜማ ስለ ሰብዐ ሰገል በጥቂቱ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ተጻፈ] ♥♥♥
GAGE COLLEGE , the right choice for education!!!!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Telephone
Website
Address
Bole Olompya, Shola, Megenagna, Piazza
Addis Ababa