07/03/2026
ዜና ዕረፍት፦ ታዋቂው የወንጌል መምህር ዘለዓለም ወንድሙ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለበርካታ ዓመታት በታማኝነትና በትጋት ሲያገለግሉ የቆዩት መምህር ዘለዓለም ወንድሙ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ተሰምቷል።
መምህር ዘለዓለም ወንድሙ ከገጠር እስከ ከተማ፣ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ሀገራት ድረስ በመዘዋወር ቅዱስ ወንጌልን ያለ ዕረፍት ያስተማሩ ታዋቂና ተወዳጅ መምህር ነበሩ። በወንጌል ስርጭት አገልግሎታቸው በርካታ ምዕመናንን ያጽናኑና የቀረጹ ታላቅ የቤተክርስቲያን ባለውለታ መሆናቸው ይነገራል።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ አገልግሎት መምህሩ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ መምህር ዘለዓለም ያበረከቱትን መንፈሳዊ ተጋድሎ በታላቅ አክብሮት አስታውሷል።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለተማሪዎቻቸው እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞች በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።
Via የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ አገልግሎት