የኦርቶዶክስ ድምፅ orthodox voice

የኦርቶዶክስ ድምፅ orthodox voice

Share

የኦርቶዶክስ እምነት ምን እንደሚመስል የሚዳሰስበት ፔጅ ነው?

17/11/2022
13/02/2022

ቅድስት አርሴማ(ቅዳሴ ቤቷ)

✝እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው።

✝መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና።"(ማቴ. ፭፥፲፩) የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል። ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት። ቅድስት አርሴማ ይህ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት። ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት። ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት። ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት። ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦ አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ቅዱሱ ጐርጐርዮስ የታላቋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው። በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት፦ ፩.ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት ፪.ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት ፫.የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት። ቅዱሱ ሦስቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ። ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት።

✝መከራው ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ፣ ይጾሙ፣ ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር። ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስን ጻድቃን የምንላቸው። በኋላ ግን ማኅደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኳ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ። በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ። ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው። የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ። በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግሥት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ። በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር። መከራው ግን አለቀቃቸውም። ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው። ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሳ መታገስ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት። ድንግሊቱ ግን "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ፤ አይሆንም።" አለችው። ሊያስፈራራት ሞከረ። ዓይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው። አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው። እጅግ ስላፈረ አስገረፋት፣ አሰቃያት፣ ዓይኗንም አወጣ። በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት። ከነገር ሁሉ በኋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት (እሪያነት) ቀየራቸው።

✝የንጉሡ እንስሳ (አውሬ) መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ። የንጉሡ እኅት ስታለቅስ በራእይ "ለእመ ኢያዕረግምዎ ለጐርጐርዮስ አልብክሙ ድኂን - ጐርጐርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም።" አላቸው። ወዲያውም ቆፍረው አወጡት። ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም። ለአሥራ አምስት ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው። ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው። የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አጽም በአሥራ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ኢትዮጵያ እንደ መጣ አባቶቻችን በትውፊት ነግረውናል። ለዚህም ነው ቡርክቷ እናታችን ከሌሎች ሃገራት ለይታ ለኢትዮጵያውያን ልዩ ፍቅር ያላት።

✝በዋናው ገዳሟ (ወሎ /ኩላማሶ/ ስባ ውስጥ የሚገኝ ነው።

12/02/2022

👉ነቢይን፡በነቢይ፡ስም፡የሚቀበል፡የነቢይን፡ዋጋ፡ይወስዳል፥ጻድቅንም፡በጻድቅ፡ስም፡የሚቀበል፡የጻድቁን፡
ዋጋ፡ይወስዳል።
👉ማንም፡ከነዚህ፡ከታናናሾቹ፡ለአንዱ፡ቀዝቃዛ፡ጽዋ፡ውሃ፡ብቻ፡በደቀ፡መዝሙር፡ስም፡
የሚያጠጣ፥እውነት፡እላችዃለኹ፥ዋጋው፡አይጠፋበትም።
👉ማቴ 10:41-42
👉መልካሙን፡የምሥራች፡የሚያወሩ፡እግሮቻቸው፡እንዴት፡ያማሩ፡ናቸው፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፡ካልተላኩ፡እንዴት፡ይሰብካሉ፧
👉 ሮሜ 10:15
👉የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በረከታቸው በሁላችን ላይ ይደር።አሜን🙏🙏

Photos from የኦርቶዶክስ ድምፅ orthodox voice's post 11/01/2022

ሰበር ዜና - አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጠራ !!!

***

የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ለመነጋገር አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጠርቷል።

በሀገር ውስጥ የሚገኙ ብፁዓን አባቶች በምልዓተ ጉባኤው እንዲገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ለብፁዓን አባቶች የስልክ ጥሪ እያደረገ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዓተ ጉባኤ ነገ ከቀትር በኋላከ 9:00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚከናወን ይጠበቃል

ምንጭ
ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

01/01/2022

እንኳን አደረሳችሁ።

26/12/2021

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ድምፅ

25/12/2021

በፈራጅ ላይ መፍረድ.......

10/08/2021

.......ባለ ንቅሳቷ.....

አንች የሀገሬ ልጅ ባለ ንቅሳቷ
ፀንታ የምትኖር የኮራች በዕምነቷ
በክርስቶስ መስቀል አምሮባታል ፊቷ።
ጥምጣምሽ የሚያምር የጎጃም ኮረዳ
አንች ትበልጫለሽ ከዘመኑ አራዳ።
ጎጃም ነው ያፈራሽ በዕምነት ያሳደገሽ
ልቤን ወስደሽዋል በውበትሽ ማርከሽ።
ማር ልስጥሽ እንዳልል የአንች ውበት ማር ነው
ወተት ልስጥሽ ብልም ሀገርሽ ወተት ነው:
የምሰጥሽ ባጣ ምንም ከጀ ባይኖር
ፍቅርን ታቂያለሽ በፍቅር እንኑር
ታስረን በቃልኪዳን መለያየት ሳይኖር።

........... ገጣሚ ታደሰ አበባው........
"ያልተቋጨ ፍቅር" ከሚለው ግጥሜ ውስጥ....

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


ADDIS ABEBA
Addis Ababa
0000