25/04/2025
ዛሬ ፋና በዘገባው የካሊፎርኒያ ኢኮኖሚ ከጃፓን እንደሚበልጥ የመረጃ ምንጮችን ጠቅሶ ጽፏል። ይሁን እንጂ ንጽጽሩ የተሰራው በNominal GDP ነው። ለመሆኑ Nominal GDP እና Real GDP ምንድን ናቸው?
Nominal GDP እውነተኛ የኢኮኖሚ መለኪያ አይደለም። ይህ ስልት በዓመቱ ወስጥ የተመረተውን የምርት መጠን በዓመቱ ዋጋ ተባዝቶ የሚመጣ ሲሆን ዋጋ ግሽበት ካለ የኢኮኖሚውን ዕድገት ከፍ ሊያደርገው ይችላል። በጣም ግሽበት ያለበት አገር ኢኮኖሚው በዚህ መንገድ ቢሰላ ዕድገቱ ከፍተኛ ሊሆን ይችላል። ግን የይስሙላ ዕድገት ነው። ስለዚህም በዚህ አሰላል ዕድገት እውነተኛ አይደለም። እውነተኛ ዕድገት የሚሰላው በ Real GDP ነው። ይህም በአጭሩ የዋጋ ግሽበትን ከግምት ሳያስገባ የምርትና አገልግሎት ለወጥን ልዩነት ብቻ ያሰላል። በመሆኑም ዘገባው ምንጩ ከየትም ይሁን በNominal GDP ስሌት ስለሆነ የተሰራው እውነተኛ የኢኮኖሚ ንጽጽር ላይሆን ይችላል።