20/10/2022
==============
ኸሚስ አይደለ በሉ መርቅኑ
እንድ ገጥማችሁ አማን አሚኑ
አሏህ ይግጠመን በሙራዳችን
ዱአ እንዳረግ ለኺታማቸን
ዛቱ ካንዳዱ ያልተሠተረው
ዓለሙን ሞልቶት የተረተረው፡፡
በዓለሙ ላይ ጥሎ ጥላውን
ዉጁዱን ሞልቶ ፈሰሰ ላዩን፡፡
ሐድራሁ ገግን ፊት የበቀለው
ከዉኑን በኑሩ ያንቀለቀለው፡፡
ሠባቱን ግርዶ በጁ ገለጠው
በኃላ መቶ ሁሉን በለጠው፡፡
አያገኘው መደዱን ዘንጊ
የጀነት ከፋች የጀሂም ዘጊ፡፡
ከዉኑን ተጣሩት፣ ሂድ አለው አቤት
አንዴ ግቡልን ባለንበት ቤት፡፡
በኛ ላይ ያብራ ያንቱ ወገገን
ከአሶሀቦች-ጋር ከኢዙ ግገን፡፡
ሙት ለማስነሳት ደህና ለመግደል
ፈይዱ መጣልን ሆኖ እንደገደል፡፡
ሹመቱ የለው ወደርና ድንበር
የጅብሪል አቅሪ የሩሁል አክበር፡፡
ወገቡ ቀጭን ትካሻ ሠፊ
ምነው በሆንኩኝ የሱ አሳላፊ፡፡
መላይካ ኮ-ነው አንድኛው ጁንዱ
የአብደላህ ልጅ ሙሀመድ አንዱ፡፡
የቋመጠለት የጀነት ጉረፍ
አድምጦ እንደሚያውቅ መደዱ ሲጎርፍ
ሳልጸነሰስ በናቴ ማህፀን
ፊት ጀምርያለሁ መድሁን መተንተን
መደዱን ሰጥቶ እያስፈለገኝ
አባቴን ገሎ እኔን ፈለገኝ
ፊት የጀመረው ማዱን መደዱ
እብራሒም ያሲን፣ ሸህ ሲራጅ ውዱ
ነፋብኝና በሸውቁ ወንፊት
አይን አረገልኝ ከኃላም ከፊት
ከሺ ሶስት መቶ ከስልሳ ሰባት
ካለፈው መጣ ፈይዱ እንደግብዓት
አይገርምህ ወይ ያለህ መለገስ
መካ ተወልዶ አርሽ ላይ መንገስ
የሱማ ኸበር የሱ እንደ ሰዉ
ስንቱን ገደለዉ ስንቱን አስነሳዉ
ሐድራ ለመግባት ሁሉም ይታጫል
ያገር ልጅ መቅረት እንዴት ይቆጫል
አንተን ለመምከር ወቅቱም አልሰፋ
እደጅ ውጣና ወደያ አንቀላፈ
በአላህ ተጀሊ የጠናው ባቱ
የአደም ጅስም ልጅ የሩህ አባቱ
ቅባት የሌለው እጁ ላይገባት
እኔ አንቱን እንጂ አላውቅም አባት
ላዩን ነገርኩህ ተወኝ እዚሁ ሁን
ኑን ወልቀለሚ ወማ የስጥሩን
ያደናግራል የሸዕኑ ኸበር
ላቡ የሚሸተው ከሚስክ ከአንበር
የኛ ሙስጠፋ የአላህ አያቱ
የዉጁዱ ሩህ አባቱ አያቱ
ጉድ ሆኖ መጣ ከአሃድያው
ከውኑን አኸረው በአህመድያው
ከሱብሃነቱ የተፈጠረው
በጌታው ቁድራ የተነጠረው
የአላህ ልግስና ፈድሉ ያመጣው
ዓለሙን በቃዉ ዉጁዱ ኑቅጣው
የሠማይ ቢሆን የአርሽ ማሹ
ከሱ ተጠርጎ ኾናልን ማማሹ
ያንቱ ሙሂቦች ያስታውቃሉ
ስሙህ ሲነሳ ይደለቃሉ
ያንቱማ ሐድራ በድሩ ባህነሳዉ
ስንቱን አፈጋዉ ስንቱን አነሳዉ