Henok

Henok

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Henok, Education, Addis Ababa.

“ብዙዎቻችን ዛሬ እንደ ሞላ ብርጭቆ ሆነናል —
በሀሳብ፣ በስሜት፣ በአካል ተጨንቀን።
እዚህ ግን ቁጭ ብለን እራሳችንን እናዳመጣለን፣
ብርጭቆው እንዲቀንስ፣ ህይወታችን እንዲገልጽ።
👉 Practical self-improvement for young people (18–35).”

30/12/2025

#ቻናላችንን

27/12/2025
26/12/2025

#ቻናላችንን

23/12/2025
23/12/2025

እራሳችንን እንመርምር አዕምችን በምን እንደተሞላ እንመልከት





22/12/2025

እኛ ልክ ሞልቶ እንደ ሚፈስ ብርጭቆ ሆነናል።

👉 The Henok Way

የእኛ አዕምሮአችን ልክ ሞልቶ እንደ ሚያፈስ ብርጭቆ ሆኖል?

ብዙ ጊዜ አዕምሮአችንን በራሳችን አሉታዊ አስተሳሰብ፣ በመጥፎ ልማዳችን እና በሱስ እንሞላዋለን። ስለዚህ የምኖርባት ዓለም ጠባብ ይሆናል።

መፍትሔ ከውጪ አይመጣም ፤ ከውስጥ ነው እንጂ!!
ራስህን መርምር፣ ብርጭቆህም በምን እንደ ተሞላ እወቅ።

የአዕምሮ አስተሳሰብ(አመለካከት) ካልቀየርክ ከውጪ ምንም ነገር ሊቀየር አይችልም !!!
#ቻናላችንን

22/12/2025

በህይወታችሁ መቀየር የምትፈልጉ ከሆነ፣ ከዚህ መጀመር አለባችሁ👇

የውስጥህን ሸክም የማቃለል ጥበብ

👉 The Henok Way

በህይወታችን ሁኔታዎች ለምን እንደሚከብዱብን ታውቃላችሁ?

ብዙ ጊዜ የሚያስጨንቀን የምንሸከመው ነገር አይደለም፤ መልቀቅ ያልቻልነው ነገር ነው።

በውስጣችን የምንይዘው፦
ጥላቻ፣ ያልተፈታ የጥፋተኝነት ስሜት እና ራስን መውቀስ እነዚህ ናቸው በዝምታ የሚያደክሙን።

መልቀቅ (መተው)
ይቅር ማለት
ስህተትን መቀበል ድክመት አይደሉም፤ አዲስ መጀመር ናቸው።

✨ ሸክምህን ዛሬ አቃል
✨ የራስህን ድክመት በይቅርታና በፍቅር ተሸከም

💬 ማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት ካለህ Comment ላይ ፃፍልኝ።

10/12/2025

የውሳጣችሁን 'ትርምስ' ወደ 'ውበት' መቀየር ትችላላችሁ !!

በህይወታችን ሰላምና ደስታ ይሰጡናል ብለን ያሳካናቸው ነገሮች ፣ የውስጥ ውድቀታችን ምንጭ ቢሆኑስ? ዞር ብለን እንመልከት!

የውጪው ዓለም የሚሰጠን ስኬት የውስጥ ሰላማችንን ሊገዛ አይችልም። እውነተኛ ሰላም እና ደስታ የራሳችንን ውስጣዊ ትርምስ በውጫዊ ነገሮች ለመሸፈን መሞከርን ስናቆም የዛኔ ይገኛል።

ዋናው ሰላም የሚገኘው በውጪ ሳይሆን ውስጡን በመንፈሳዊ ስነምግባር፣ ዓላማን በማወቅ፣ እና ከሕሊና ጋር በመታረቅ መኖር ስንችል ነው። አቋራጭ መንገድ የለም— ትዕግስት እና ጊዜ ቢፈልግም፣ ስራህ በጊዜ ሂደት ፍሬ ሲያመጣ፣ የምትፈልገውን ደስታና ሰላም ከራስህ ታገኛለህ። አንተ ራስህ የራስህ ሀብት ትሆናለህ!

ነገ የሚባል ጊዜ የለም። አሁን ነው ያለህና አሁን ተነሳ! የራስህን ድክመት ለመሸከም አትፍራ! እዛኔ ነው መጀመር የምትችለው። ይህንን ጠቃሚ መልእክት ለምትወደው ሰው አጋራ።

Telegram: Contact @TheHenokWay

29/11/2025

💥 ዓላማ ከደስታ በላይ ነው (ክፍል 2፡ ጥሪያችንን መኖር)

ዓላማ | PURPOSE

ብዙ ጊዜ "ዓላማዬን እየኖርኩ ነው" ወይም "ዓላማዬን መኖር እፈልጋለሁ" እንላለን። ነገር ግን ዓላማ እውነተኛ ጥሪ እንዲሆን፣ የሚከተሉትን ሁለት ነገሮች ማሟላት ይኖርበታል፦

ውስጣዊ እርካታ (Passion): ሰዎች ስለ ስራችን ጥሩ ሲናገሩ ብቻ ደስተኛ የምንሆን ከሆነ፣ በስራችን በራሱ ደስተኛ (Passionate) አለመሆናችን ግልጽ ነው። ጥሪያችን በውጪ እውቅና ላይ የተመካ አይደለም።
ውጫዊ ተጽዕኖ (Impact): በምንሰራው ስራ እና በብቃታችን እኛ ደስተኛ ሆነን፣ ነገር ግን ያ ሥራህ ማንንም ግድ ካልሰጠው ወይም ሰዎችን የማይጠቅም ከሆነ፣ ዓላማችን (Passion) ውጤታማ አይደለም።

በአጭሩ፣ ከሁለት አንዱ ከጎደሉ ጥሪያችንን እየኖርን አይደለም ማለት ነው! ጥሪያችንን ኖርን ማለት፦ ከሚያስገኝልን እውቅና፣ ገንዘብ ወይም ጊዜያዊ ስሜት ውጪ በራሱ የሚያስደስተን እና ሰዎችን የሚጠቅም ሊሆን ይገባል።

❓ እና ዓላማችንን እንዴት እንወቅና እንኖረው?
ዓላማን መፈለግ የልብና የአዕምሮ ትብብር ይጠይቃል፦

❤️ የልባችን ድምጽ (The What): ጥሪያችንን ለማግኘት የልባችንን መሻት እና የሚፈጠሩብን ስሜቶች ማዳመጥ ይኖርብናል። ልባችን ምን እንደምንሠራ (ዓላማውን) ይወስናል።

🧠 የአዕምሮ ሚና (The How): ዓላማን ወደ ተግባር ለመቀየር ስልታዊ ዕቅድ፣ ዲሲፕሊንና ቋሚነት ያስፈልጋል። አዕምሯችን ደግሞ ጥሪያችንን እንዴት መኖር እንዳለብን (ስልቱን) ያመላክታል።

✨ ጥሪያችንን መኖር ስንጀምር የሚፈጠሩ ውስጣዊ ስሜቶች
ዓላማችንን በትክክል መኖር ስንጀምር በውስጣችን የሚፈጠሩት ስሜቶች፣ በሕይወት ዘመን እየተለዋወጡም ቢሆን፣ እነዚህን ይመስላሉ፦

ሕያውነት (Alive): ሕይወትን እንደ አዲስ የማጣጣም ስሜት።

ፍሰት (Flow): ከሕይወት ጋር እንደ መታገል ሳይሆን በቀላሉና በቅልጥፍና አብሮ እንደ መጎዝ ያለ ስሜት። ጊዜ በፍጥነት ይሮጣል።

ምቾት (Comfort): ሰዎች ቢመጡም ቢሄዱም፣ በራሳችን መሞላት እና ውስጣዊ ሰላም የመላበስ ስሜት።

ወጥነት (Consistency): ተግባሩ ቢደጋገምም፣ ሁሌም አዲስ ጉልበትና ትርጉም መስጠት።

አዎንታዊነት እና እድገት (Positivity and Growth): ከሌሎች ውድድር የጸዳ፣ በራስ ፍጥነት የማደግ እና የመሻሻል ስሜት።

📝 ወደ ተግባር
ዓላማ ለዘለቄታው የሚቆም ነገር ሳይሆን በየጊዜው የሚያድግ ጉዞ ነው።
ለራስዎ የሚጠይቋቸው ተግባራዊ ጥያቄዎች:

ገንዘብና እውቅና ባይኖርም በደስታና በነጻነት ሰዓታትን አሳልፌ የምሠራው ነገር ምንድን ነው?
ያንን ነገር ስሠራ ማን ላይ ወይም በምን ጉዳይ ላይ አዎንታዊ ለውጥ አምጥቻለሁ?

መልካም የዓላማ ጉዞ! #ቻናላችንን አብረን እሳድገው

Telegram: Contact @TheHenokWay

22/11/2025

🎯 ዓላማ ከደስታ በላይ ነው።

በመጨረሻው የተስፋ መቁረጥ ጉድጓድ ውስጥ ስትሆን፣ ያን ጊዜ ነው እውነተኛ ክብር እና የሕይወት ትርጉም የሚገኘው። ✨
ያንን የተገነዘብኩት እኔ ሙሉ በሙሉ ስደክም ነበር። እንዴት እንደሆነ አሳያችኋለሁ።

👤 ስሜ ሄኖክ ነው።

ዓለሜ ተገልብጦብኝ ወደ የማንነት ጥያቄ ውስጥ ገባሁ፤ ኮቪድ ሲመጣ ከኔ ጋር የነበረኝ ፀጥታ ነው።
የኮሌጅ ግቢ ሲዘጋ፣ ለሁሉም ነገር መልስ ነበረኝ ብዬ የማስበው ልጄ በጭንቀት ደመና ውስጥ ዋኘው።
'እኔ ማን ነኝ? ዓላማዬስ ምንድን ነው?' የሚሉት ጥያቄዎች በቀን 24 ሰዓት አእምሮዬን ይደበድቡ ጀመር።
የምተነፍሰው አየር እንኳ ከብዶኝ ነበር።
በዚያን ጊዜ ነበር ልቋቋመው የማልችለው የማንነት ፈተና ውስጥ የገባሁት።

🛠️ ራሴን ከዚህ የማንነት ጉድጓድ ለማውጣት ያልሞከርኩት ነገር አልነበረም።

የዳዊት ድሪምስ ማንያዘዋል እሸቱ እንደጉድ በደመቁበት ጊዜ ከነሱ አንድም አልቀረኝም ነበር።
የዩቲዩብ ቪዲዮዎች
አነቃቂ ቃላት
ፖድካስቶች
መጻሕፍት እነዚህን ሁሉ ሞክሬ እንኳ የበለጠ ባዶነት ተሰማኝ። የምሞክረው በጨመረ ቁጥር፣ የምወድቀውም እንዲሁ ጨመረ።
"ከድጡ ወደ ማጡ"
እፎይታ ለማግኘት የሰጠሁት ሩጫ እስር ቤት ሆነብኝ።

✨ ታዲያ እንዴት ነበር ከዚህ ሁሉ የራሴ ጥረት አዙሪት የወጣሁት?

ዋናው ስህተቴ የተረዳሁት ያኔ ነበር።
ይህን ሁሉ የማደርገው ደስታን ለመፈለግ ነበር፣ ህመምን ለመራቅ ነበር።
ደስታ ግን የእኔን ህይወት የማያድን መሆኑን አላወቅኩም።

የሚያድነው ዓላማ (Purpose) ነው።

🧭 'ለምን እኖራለሁ?' 'ለምን እለፋ?'

የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ ስጀምር፣
ችግሮች የመጨረሻ ምልክት አይደሉም፣ የሂደቱ ክፍል ናቸው።
በሂደት ተቀየርኩ፣ ፈተናዎችንም ማሸነፍ ቻልኩ።

🙏 ይህ ታሪክ እርስዎንም የሚነካ ከሆነ
ወይም 'ዓላማ ከደስታ በላይ ነው' የሚለውን ትምህርት ከተቀበሉ፣
በአስተያየት መስጫው ላይ 👉 'ዓላማ!' ይፃፉ።





Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


Addis Ababa