ኢሳይያስ40:31:-እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።
ቃል ብቻ
“የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”
— ማቴዎስ 11፥15
ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፤
እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል።
መዝ 41:1
“በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል።”
— ዮሐንስ 15፥7
“እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።”
— ኢሳይያስ 41፥10
!
ሰይጣን የሚያጠቃህ አደጋ ስለምትሆንበት ነው!
ምክንያቱም አንተ ውስጥ አንዳች ዋጋ ያለው ነገር አለ።
አስታውስ፦
ሌባ ባዶ ቤትን ሰብሮ አይገባም።
ስለዚህ መቼም እጅ አትስጥ!
ፈጣሪህ ቢደክምህም
እየሞከርክ እንደሆነ ያውቃል።
እሱን አስቀድመው!
እሱ ሌባ ሰብሮት የማይገባ የበር ቁልፍ ነውና።
🥇አሸናፊዎች የተለዩ ነገሮችን የሚያደርጉ ሳይሆኑ፣
ነገሮችን በተለየ መንገድ ሚያደርጉ ናቸው!!!🏆
🎀🎀
"የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው፣ መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው"ይላል ማህሙድ "ዝምታ ነው| መልሴ"ን ሲያዜም::
ልሳን
ማቴዎስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።
²³ የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።
“ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ።”
— ኤርምያስ 33፥3
God is Good
“እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥”
— ዮሐንስ 14፥12
" እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” ዮሐንስ 14፥6
“ኢየሱስ"
የጌቶች ጌታ ችግሮቼን የሚፈታ
አልፋና ኦሜጋ ባንተ ምሽቴ ነጋ
ተመስገን
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Addis Ababa