Habtamu Ethiopia

Habtamu  Ethiopia

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Habtamu Ethiopia, High School, Addis Ababa.

24/07/2022

ከባለቤቴ ጋር ትዳር ከመሰረትን 21 ዓመት ሞላን ባለቤቴ አንድ እራሴን እንድፈትሽበት ያደረገኝን ጥያቄ አቀረበችልኝ ሃያ አንድ ዓመት ካንተ ጋር ስኖር አንድም ቀን ከእናትህ ጋር ለመዝናናት ስትወጣ አይቼክ አላውቅም ዛሬ ማታ እናትህን እራት ምሽት ጋብዛትና አዝናናት አለቺኝ" ውዷ ባለቤቴ ባቀረበችልኝ ሃሳብ ከመገረም በላይ መሰጠኝ ተስማማሁኝ እናም ወደ እናቴ ጋር ደወልኩላት እማ ዛሬ ካንቺ ጋር ሽርሽር መውጣት እፈልጋለሁ አልኳት ደነገጠች "ምነው ሰላም አይደል ልጆችህ ምን ሆኑ ባለቤትህስ ሰላም አይደለች እንዴ ?" በማለት የድንጋጤ ጥያቄዎቿን አርከፈከፈችብኝ..."አብሽሪ እማ ሁሉም ሰላም ነው ካንቺ ጋር ለመዝናናት ፈልጌ ነው" አልኳት በጣም ደስ አላት ተስማማች ወደ ማታ ተዘጋጅተሽ ጠብቂኝ አልኳት

በቀጠሮዬ ሰዓት ወደ እናቴ ጋር ሄድኩኝ እናቴ በረንዳው ላይ ቆማ እየጠበቀቺኝ ነበር እናቴ ሁለመናዋ ተቀያይሯል እርጅና ተጫጭኗታል ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ወደ መኪናዬ አስገብቻት ጉዞ ጀመርን እናቴ በጣም ደስታ ይነበብባታል "ልጄ ዛሬ ካንተ ጋር ሽርሽር እንደምወጣ ለሰፈር ሰዎች ሁሉ እንዲሁም ለዘመድ አዝማዶቼ በሙሉ ተናግርያለሁኝ" በጣም ከመደሰቷ የተነሳ አንድም የምታውቀው አልቀራትም ወሬውን ለሁሉም አዳርሳዋለች

ወደ ሆቴል ይዥያት ሄድኩኝ አስተናጋጁ የምግብ ዝርዝር ወረቀት የያዘ ኩፖን ሰጠን "ኡሚ ምረጪ" አልኳት... ፈገግ አለች ከእርጅና የተነሳ ማየት እንደማትችል ተረዳሁ ... ላንብብልሽ አልኳት "ልጅ እያለህ ሆቴል ቤት ገብተን ልንመገብ ስንል የምግብ ዝርዝር አነብልህ ነበር አሁን እዳህን ክፈል" ብላ ፈገግ አለች እኔም ፈገግ ብዬ አነበብኩላት የለበሰችውን ልብስ ስመለከት ከአስራ ዘጠኝ ዓመት በፊት የሞተው አባቴ የገዛላት የመጨረሻ ልብሷ እንደነበር አስታወስኩ ምግቡ ቀርቦ እናቴ ከደስታ የተነሳ ምንም እየበላች አልነበርም ደስታ በደስታ ሆናለች በሕይወቴ እኔም በጣም የተደሰትኩበት አጋጣሚ ነበር ከእናቴ ጋር ተዝናንተን ስናበቃ ይህ ምሽት እንዲደገም ፈልጌ "እማ መቼ ተመልሼ ልምጣና ልውሰድሽ..?" አልኳት በእንደዚ ቀን ና ነገር ግን እኔ ነኝ የምጋብዝህ ከተስማማህ ና" አለቺኝ ፈገግ አልኩኝ "አብሽሪ ትጋብዥኛለሽ" አልኳትና ተለያየን በመሃል እናቴ ታመመች ከህመሟ ድናልኝ አብርያት የማሳልፍበት ምሽት ናፈቀኝ ነገር ግን ከእናቴ ጋር ዳግም አልወጣንም እናቴ ወደ ማይቀረው የሞት ጉዞ ተጓዘች በጣም አዘንኩ አለቀስኩ

ከእናቴ ጋር ቀጠሮ ይዘን በነበርንበት ቀን አመሻሹ ላይ ከአንድ ታዋቂ ሆቴል ቤት ተደወለልኝ "ዛሬ እራት ከባለቤትህ ጋር በነፃ ተጋብዛቹሃል" የሚል ነበር። ግራ ተጋባው ማነው እንዴት ለማንኛውም እሺ እንመጣለን ብዬ ስልኩን ዘግቼ ምሽት ላይ ከባለቤቴ ጋር ሄድኩኝ ግብዣው ከደብዳቤ ጋር ቀረበልን ደብዳቤውን ከፈትኩት እንዲህ ይላል:-
"ልጄ ሰላም ላንተ ይሁን የእራቱን ግብዣ ስንቀጣጠር መገኘት እንደማልችል አውቅ ነበር የሞት ቀጠሮዬ እየተቃረበ እንደነበር ነፍሴ ይነግረኝ ነበር ልጄ ይኸው እኔ በቃሌ መሰረት ጋብዥሃለው በኔ ፋንታ ውዷ ባለቤትህ አብራህ እንድትሆን ፈቅጃለሁ!" ይላል ሳይታወቀኝ እንባዬ ወረደ አለቀስኩ 21 ዓመት ሙሉ የዘነጋሁትን ውድ ዕቃ አሁን ነው ማጣቴን ያወኩት...!

ስንቶቻችን ይሆን ካገባን በኋላ እናቶቻችንን የምናስታዉሳቸዉ ? ሼር በማድረግ ለሌሎች ያካፍሉ ። ረጅም እድሜ ለእናቶቻችን!!

አንብባችሁ 👉ሼር አላደርግ ስትሉ 🙏ብሞት እንኳን 🚫🚫🚫የማትቀብሩኝ አይነት ስሜት ነው የሚሰማኝ 👉👉👉👉ልሙትላችሁ ሆሆ ፣ ለማንኛውም አሁንም
👉👉👉👉👉ሼር አድርጉልን

#ኢትዮጵያ

02/07/2022
28/04/2022

Abiy ahmad ka gonder lay ijehin ansa

Photos from Great Abyssinia's post 21/02/2022
Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


Addis Ababa