Misael Lemma

Misael Lemma Political Commentary, Situation Analysis, and perspectives International Relations! Pro Ethiopian Unity through Diversity!

🇫🇷France becomes the third major power after the US and Russia supporting Ethiopia’s quest for sea access, calling it “p...
12/07/2025

🇫🇷France becomes the third major power after the US and Russia supporting Ethiopia’s quest for sea access, calling it “perfectly legitimate” for the world’s most populous landlocked nation. Training support for Ethiopia’s navy underway, says Amb. Lamek.💪

ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ የኖቤል ሽልማትና የህዳሴው ግድብ!ፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ. ትራምፕ ዛሬ በትሩዝ ሶሻል ሚዲያ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት በርካታ ግጭቶችን በመፍታት ረገድ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ...
21/06/2025

ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ የኖቤል ሽልማትና የህዳሴው ግድብ!

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ. ትራምፕ ዛሬ በትሩዝ ሶሻል ሚዲያ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት በርካታ ግጭቶችን በመፍታት ረገድ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ በመዘርዘር የሰላም ኖቤል ተሸላሚ መሆን ይገባቸው እንደነበር ገልጸዋል። ከነዚህ መካከል፣ በኢትዮጵያና ግብፅ መካከል የነበረውን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ አለመግባባት ጠቅሰው፣ የሚከተለውን ብለዋል፡

“በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል ሰላም ማስጠበቄም የኖቤል የሰላም ሽልማት አላሰጠኝም፣ ይህ ግዙፍ ግድብ በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ እየተሰራ ያለ ወደ ናይል ወንዝ የሚፈሰውን ውሃ በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንስ ነው..."

ዶናልድ ጄ. ትራምፕ በተለያዩ አህጉራት ሰላም ለመፍጠር ባደረጉት ድንቅ ጥረት ኖቤል የሰላም ሽልማት ማሸነፍ ይገባቸዋል። ለዘመናት ዕውቅና ተነፋፍገው የጎሪጥ ሚተያዩ የአረብ አገራትንና እስራኤልን ያስማሙበት ታሪካዊው የአብርሃም ስምምነት (Deal of the Century) ብቻውን በቂ መሆን ነበረበት። የፓኪስታ መንግስት የዘንድሮ ኖቤል ለትራምፕ እንዲሰጥ በይፋ መጠየቁ ልብ ይሏል። ነገር ግን፣ በመልዕክቱ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) የተገለጸው ጉዳይ ከእውነታ የራቀ ነው። አንደኛ ግድቡ የናይል ወንዝ ፍሰት በከፍተኛ ሁኔታ አይቀንስም። ጉዳዩ የሀይል ፍላጎት የሟሟላት እንጂ ውሃውን አስሮ የታችኛዎቹን ተፋሰስ አገራት መጉዳት አይደለም። ሁለተኛ በኢትዮጵያ ህዝብ ላብና ጥሪት እየተገነባ ያለ የጽናት ምስክር እንጂ የአሜሪካ ገንዘብ ውጤት አይደለም።!

ነገረ አያቶላህ!አያቶላህ ኻሜኒን መግደል ወይም ከውጭ በኢራን የመንግሥት ግልበጣ ለማምጣት የሚደረገው እንቅስቃሴ እቃወማለሁ:: አያቶላህ መንፈሳዊ መሪ እንደመሆናቸው የእርሳቸው ሞት ቀድሞውኑም...
20/06/2025

ነገረ አያቶላህ!

አያቶላህ ኻሜኒን መግደል ወይም ከውጭ በኢራን የመንግሥት ግልበጣ ለማምጣት የሚደረገው እንቅስቃሴ እቃወማለሁ:: አያቶላህ መንፈሳዊ መሪ እንደመሆናቸው የእርሳቸው ሞት ቀድሞውኑም ስሱ በሆነው ቀጠና ሃይማኖታዊ ግጭትና አዲስ አሸባሪ ድርጅት የመፍጠር አደጋ አለው:: በተጨማሪም ታሪክ በግልጽ እንደሚያስተምረን በውጭ ኃይሎች የሚጫኑ የመንግሥት ለውጦች እምብዛም አዎንታዊ ውጤት አያስገኙም— ይልቅስ በአብዛኛው ኬዞች ከፊት ይልቅ የከፋ የእርስ በርስ ጦርነት ፣ አምባገነንትና ድህነትን ያዋልዳሉ:: ሊቢያ ምስክር ነች። ✌️

ሰላም ለሁላችን!

ትራምፕ በግብፅና በኢትዮጵያ የአባይ ግድብ ጉዳይ ላይ “ቢያንስ ለአሁኑ ሰላም ያመጣሁት እኔ ነኝ” ብለዋል። ግድቡ በቀጣይ በመስከረም ወር ሲመረቅ (ከተመረቀ) ትራምፕ በክብር እንግድነት ሲገኙ...
15/06/2025

ትራምፕ በግብፅና በኢትዮጵያ የአባይ ግድብ ጉዳይ ላይ “ቢያንስ ለአሁኑ ሰላም ያመጣሁት እኔ ነኝ” ብለዋል።

ግድቡ በቀጣይ በመስከረም ወር ሲመረቅ (ከተመረቀ) ትራምፕ በክብር እንግድነት ሲገኙ እናይ ይሆን?

ፎቶ: AI

Address

Addis Ababa

Telephone

+251912832062

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Misael Lemma posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Misael Lemma:

Shortcuts

Share