እማሬ ኦርቶዶክስ

እማሬ ኦርቶዶክስ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from እማሬ ኦርቶዶክስ, Religious school, Addis Ababa.

05/02/2021

እማሬ ኦርቶዶክስ:
እምነት
እምነት ሁለት አበይት ክፍሎች አሉት
እነሱም ማመን መታመን ።
ሀዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ማመን ከመስማት ነው"ሮሜ 10:17
እምነት አይተን ዳሰን ማረጋገጥ ስለማይቻል ብቸኛው አማራች መስማት ብቻ ነው።
በማመንና በማዳመጥ መካከል ልዩነት አለ ።
ማዳመጥ የሚሰጠውን ትምህርት ወይም የሚነገረውን ሀሳብ ትኩረት ሰጥቶ ይጠቅመኛል ብሎ መከታተል ነው። ማመን ግ ከዚህ ይዘላል የተማርነው የሰማነው ይሆነኛል ብለን የተከታተልነው መንፈሳዊ እውቀት በአእምሮና በልብ ፍፁም መቀበልን ያካትታል።

የምናምነው ወይም የምንቀበለው እውነት የቱ ነው?
ሀዋርያው ይቀጥላል "መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። "
ይህ በአእምሯችን ያመነው የእግዚአብሔር ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ና ያስተማረው ትምህርት ነው።
ይህ እምነት መታመን መታዘዝ ስራ ያስፈልገዋል።

ለዚህ ነው ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴ 7:21
"በሰማይ ያለው የአባቴን ፈቃድ የሚፈጽም እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግስተ ሰማያት ሚገባ አይደለም"
ይሄ ነው መታመን ድርጊትያስከተለ።

ለመሆኑ ጌታ ጌታ የሚሉት ፕሮቴስታንቶች የቱን ጌታ ነው?
ያላመነ ያልተጠመቀ አይድንም ያለውን ነው? ማር16:16
ስጋዬን ያልበላ ደሜን ያልጠጣ የዘላለም ህይወት የለውም ያለውን?ዮሐ 6:53
ግን የቱነው?

አስተውል ወዳጄ ማመንን ከመስማት መስማትን ከመመርመር ከመረዳት ከዛም ዘሎ መታመን ነው ።

ይህንን እውነት ደግሞ "ክርስቶስን ከለበሰች ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ "ትማራለህ ገላ 3:27

ዲ,ዳኛቸው ይልማ
28/05/13 ዓ.ም

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when እማሬ ኦርቶዶክስ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to እማሬ ኦርቶዶክስ:

Shortcuts

Share