24/11/2023
እውነት ለሁሉም ይገዛል
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from እውነት ለሁሉም ይገዛል, School, Addis Ababa.
24/11/2023
24/11/2023
እግዚኣብሄር የሂወታችን መሰላል ሰጥቶናል በዛችመሰላል የሄደ አለፈ ካልሆነ የሞትን ሞት ሞተ ማለት ነው እኚህ ኣባት እናክብራቸው ገዳማቸውን ሄደን በእግዚኣብሄር ትእዛዝ በእርሶ ፆለት ተፈወስን እንበል
16/03/2023
በርጠሚዎስ ነኝ አይነ ስውር ምስኪን
ከሩቅ የሰማሁት የጌታዬን ድምፁን
ከብዙ ሁካታ ጉርምርምታ መሀል
የጌታዬ ድምፁ በግልፅ ይሰማኛል
የልቦናዬ አይን ፈፅሞ ታውሯል
አይኔን ፈውስልኝ በርጠሚዎስ ይላል
አብዝቼ እጮሃለሁ ጌታ ማረኝ ብዬ
በውስጤ እየታየኝ ሲምረኝ ጌታዬ
አንተን አይሰማህም ይሉኛል ብዙዎች
በሃጢአት ሰንሰለት ታስረሃል እግር ተወርች
ስለዚህ አትልፋ ሲኦልን ጠብቃት
እንደዚህ ቢሉኝም እጮሃለሁ ሳልታክት
የከበበውን ሰው ገለል በሉ እያለ
በደሌን በደሙ ዋጋ የከፈለ
ስለኔ የሞተው ኢየሱስ ይመጣል
የልቦናዬን አይን ገልፆ ያሳየኛል
አብዝቼ እጮሃለሁ ጌታ ማረኝ ብዬ
በግልፅ እየታየኝ ሲምረኝ ጌታዬ
በውስጤ በደልስ ህይወቴ ዝላለች
በአምላኬ ቸርነት ህይወት ካላገኘች
የበርጠሚዎስን አይን ያበራ አምላክ የእኛንም መንፈሳዊ አይን ያብራልን🙏🙏
16/03/2023
እናትና ልጅ
:
አለቀስኩ ገረመኝ ዓለምን ፍቅርን ታማኝነትን ተመለከተኹ። አሁንም ገረመኝ።
ከሁለት ወራት በፊት እናቷን ተከትላ አስፖልት የምታቋርጥ ጩጩ ቡችላ እናቷ ድንገት በመኪና ስትገጭ ቡችላዋ ተረፈች። በቅርብ የነበሩ ሰዎች የውሻዋን አስከሬን ከመስመር ወጣ ባለ ኮብልስቶን ንጣፍ ላይ ጣሏት።
ቦታው ጎጃም ፍኖተ ሰላም ቀስተዳመና ድልድይ ጎን።
ጩጨዋ ቡችላ ከእናቷ ጎን ተኛች። ሲመሽ እናቷ ትነሳለች ብላ ብትጠብቅም አልነሳላት አለች በእግሮቿ በጥርሶቿ እናቷን እየፎገረች ብትቀሰቅስም እናት አልሰማችም።
ቡችላዋ ተስፉ ቆርጣ ከናቷ አስከሬን ጥግ ተኛች። እራበኝ ልብላ ሳትል ቁራሽ የሚሰጣት ሳይኖር ከናቷ ጎን ተኛች። እሄው እንደምትመለከቱት ከሁለት ወር በላይ ኢች ቡችላ ዛሬም ከእናቷ ጎን እንደተኛች ናት።
መቶ ሜትር ባልሞላ ርቀት የሚበላ ነገር ለቃቅማ እዛው አጥንቷ ከገጠጠው የናቷ አስከሬን ስር ትተኛለች።
ሰው ቢሆን ገማ ሸተተ ብሎ ተነስቶ በሄደ ነበር ጩጩዋ ቡችላ ግን ሁለት ወር ሙሉ የእናቷን አስከሬን ትጠብቃለች። ተፈጥሮ ነውና ቡችላዋም እያደገች ነው።
ውሾች ሲመጡባት በእናቷ አስከሬን ተሸሽጋ ትጮኸለች። በፍፁም አትሸሽም። ሰዎች እያባረሩ ባላዋቂ እየደበደቧት ቡችላዋ አሁን አንድ እግሯ ታነክሳለች።
የእናቷ አስከሬን ሸቶ በትል ተበልቶ ዛሬ ደረቅ አጥንት እና ደረቅ ቆዳ ብቻ ቀርቶ ልጇ አሁንም ከጎኗ ተኝታለች።
ያደኩት ከውሻ ጋር ነው በተለይ ባርጫ የሚባለው ውሻየ ከህሊናየ አይጠፋም። የውብ ዳር በሚለው መፅሐፌ ቅንጭብ ታሪክ አጋርቻልኋለሁ። ውሻ ለኔ ከጓደኛ በላይ ነው ። በተቻለኝ መጠን ቡችላዋ እንድትለምደኝ እየጣርሁ ነው። የእናቷን አስከሬን ትታ አንድ ቀን ከተከተለችኝ በቤቴ ተንከባክቤ አኖራታለሁ።
በዚህ እውነተኛ ታሪክ እና ምስል የእናትነትን ክብር ወስዳችሁ ተማሩበት።
በሌላ በኩል ሰዎችን ለክፉ የምታስቡ ሰዎችን የምትገድሉ ጨካኞች በቅርበት ያለ ሰው ልቡ እንደዚ ይሰበራል። ልጅ ያለ እናት ያስቀራችሁ አባት ያለ ልጅ ያስቀራችሁ እህት ከወንድም የነጠላችሁ ቋሚን እንደዚች ቡችላ የቁም ሙት እንዳደረጋችሁ እወቁት።
ዮሐንስ ላቀው
16/03/2023
የስውሯ ማርያም ድንቅ ተአምር
"ነርስ ነኝ ልጅ መውለድ አልችልም ነበር ብዙ ሆስፒታሎች ተመረመርኩኝ መውለድ አትችይም አሉኝ አንድ ጎደኛዬ ነይ ስውሯ ማርያም እንሂድ አለችኝ አይ የኔ ይሆናል ብለሽ ነው ብዬ ጥር 21 መጣው ይሀው ለሶ ሚሳናት ነገር የለም ነብሰጡር ነኝ ልጄን ክርስትና እዛ አስነሳለው በሰላም ትገላግለኝ ለኔ በእለት እደደረሰች ለናንተም ትድረስ🙏
የ እርሷን ፀሎት ልመና እንደሰማች
የእኛንም ፀሎት ልመና ትስማን🙏
16/03/2023
ነገኮ ❺ አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ናቸዉ
ከክፉ ሁሉ ነገር ይጠብቁን
16/03/2023
ልጅ ቢኒ እና ፓስተር ቢኒያም ሽታዬ ለወላይታ ለተክለሃይማኖት ሕንፃ ቤተክርስቲያን ገቢ እያሰባሰቡ❤
16/03/2023
"የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል!
ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ መጋቢት ፩/፳፻፲፭ ዓ/ም በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የቅድስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በላከው መረጃ ገልጿል።
ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ ከ፲፯ ዓመታት በፊት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእረ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ አንብሮተ ዕድ የተሾሙ ናቸው።
ብፁዕነታቸው አስኬማ መላእክት ከሚለበስበት የኤጲስ ቆጶስነት በፊት
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ አካባቢዎች ሲያገለግሉ እንደነበር ታሪካቸው ያስረዳል።
በተለይ አገልግሎታቸውን ከጀመሩበት ከአገው ምድር አዊ ጀምሮ በባሕርዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች አገልግለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ብፁዕነታቸው በድሬዳዋ ብሎም በቤተ ክርስቲያናችን ፈቃድ ጀርመን ሀገር ተልከው የሚገባውን ትምህርት የተከታተሉ ሲሆን ከዚያም በሰሜን አሜሪካ በኒውዮርክ ሀገረ ስብከት በሚገኘው በመንበረ ጵጵስና ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ከአገልጋይነት እስከ የበላይ ጠባቂነት በአባትነት አገልግለዋል።
ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንደነበሩ የአገልግሎት ፍሬ ታሪካቸው ያስረዳል።
የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ ዕረፍትን ተከትሎ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ያደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው ክቡር አስከሬናቸው በሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ መጋቢት ፱/፳፻፲፭ ዓ/ም ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጣ የገለጸ ሲሆን የቀብር ሥነ ሥርዓቱም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም አስታውቋል።
16/03/2023
በማኅበረ ቅዱሳን አርባ ምንጭ ማእከል በሕዝብ ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት ዋና ክፍል ውስጥ የትብብር አገልግሎት ክፍል አባል ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት መምህርት መሠረት ጥላሁን ባደረባቸው ሕመም የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከዚህ ዓለም መከራና ድካም አርፈዋል።
መምህርት መሠረት ከማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎት በተጨማሪ ቤተ ክርስቲያን በምትፈልጋቸው የአገልግሎት መስኮች ላይ በሙሉ ደከመኝ ሰለቸኝ የማይሉ ጠንካራ አገልጋይ ነበሩ።
ማኅበረ ቅዱሳን በእህታችን ዜና ዕረፍት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለመላ ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለማኅበራችን አባላት በሙሉ መጽናናቱን ይመኛል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa