ብራና ሚዲያ Birana Media በመ/ር ስንታየሁ ማሞ

ብራና ሚዲያ Birana Media  በመ/ር ስንታየሁ ማሞ

Share

መንፈሳዊ ትምህርቶች የመወያያ መድረክ

01/08/2022

ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ሀብተማርያም

ወር በገባ በ 26
በቤተክርስቲያናችን ታስበው ከሚውሉት እግዚአብሔር አምላክ ቃል ኪዳን ከገባላቸውን ከሰጣቸው ቅዱሳን አባቶቻችን አንዱ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ፃዲቅ አቡነ ሀብተማርያም ይገኛሉ:: ታዲያ ጻድቁ ፃዲቅ አቡነ ሀብተማርያም ማን ናቸው ? ምን ቃል ኪዳን ተሰጣቸው? እናም ያደረጉትን ተጋድሎ በጥቂቱ እንመልከት

አምስቱን መቅሰፍቶች የማስወገድ ስልጣን የተሰጠው ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም የነበረበት ዘመን 1486 ዓ.ም ንጉስ እስክንድር በነገሰበት ጊዜነው፡፡ አባቱ ፍሬ ቡሩክ እናቱ ዮስቴና ይባላሉ፡፡ ፍሬ ቡሩክና ዮስቴና በህገ እግዚአብሔር በሃይማኖት በትሩፋት በምግባር ፀንተው የሚኖሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ነበሩ፡፡ የፃዲቁ አቡነ ሀብተ ማርያም እናት ቅድስት ዮስቴና ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያምን ከመውለዷ በፊት ሰው ሁሉ ዓለሙን ቢገዛ ነፍሱን ካጣ ምን ይጠቅመዋል የሚለውን የወንጌል ቃል ተረድታ መንና ወደ በረሃ ሄደች፡፡ በበረሃ ውስጥም ከሰው ተለይቶ የሚኖር ባህታዊ በዋሻ ውስጥ አገኘች፣ የመጣሁት ለምነና ነው ጌታ በወንጌሉ እርፍን ይዞ ወደ ኋላ የሚያርስ የለም እንዳለ ወደ ዓለም አልመለሰም አለችው፡፡ ሉቃ 9፣62 ይህም ባህታዊ ምናኔ ምንኩስና ለአንቺ አልተፈቀደልሽም ከህጋዊው ባልሽ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ እርሱም ለዓለም ሁሉ ይተርፋል በፀሎቱም ብዙዎቹን ይጠቅማል እንደ መልአክትም ክንፈ ጸጋ ተሰጥቶታል በማለት ነገራት፡፡

ቅድስት ዮስቴናም ከአረጋዊ ባህታዊ ይህን ነገር ሰምታ አደነቀች የፈጣሪዬ ፈቃድ ከሆነ ወደ ቤቴ እመለሳለሁ ብላ ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡ ጥቂት ጊዜያትከቆየች በኋላ ግንቦት 26 ቀን ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም ተወለደ፡፡ በአባቱና በእናቱ ቤት ታላቅ ደስታ ሆነ 40 ቀን በሞላው ጊዜ በኦሪትና በሉቃስ ወንጌል እንደተፃፈ በእግዚአብሔር ፊት ያቆሙት ዘንድ ወደ ቤተክርስቲያን ወሰዱት በተጠመቀ ዕለትም ሀብተማርያም ተብሎ ተሰየመ፡፡

ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም በፈሪሃ እግዚአብሔር በትምህርት አደገ፡፡ ከዕለታት በአንድ ቀን ካህናቱ በቤተክርስቲያን ምህላ ሲያደርሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" እያሉ ሲፀልዩ ሰምቶ በልቡናው ይህች ፀሎት በጣም ጥሩና መልካም ፀሎት ናት አለ በዚህ ፀሎት ከዓለም አሳችነት ከገሃነም እሳት እንድንባት ዘንድ አውቃለሁ የንስሐ መንገድ ናት ብሎ ተናገረ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አባታችን አቡነ ሀብተማርያም በዚህች ፀሎት ተጠምዶ በጾምና በፀሎት በስደት የሚኖር ሆነ፡፡

አባቱ ፍሬ ብሩክ አቡነ ሀብተማርያምን የበግ ጠባቂ አደረገው እግዚአብሔር ግን በኋላ ለብዙዎች ስውራን ቅዱሳንና በዓለም ለሚኖሩ ምዕመናን በጎች ጠባቂ ያደርገው ዘንድ ወዶ መርጦታልና ያ ቀን እስኪደርስ ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ አቡነ ሀብተማርያምን ይጠብቀው ነበር፡፡ አባታችን አቡነ ሀብተማርያም ከአባቱ አጠገብ ተኝቶ ሳለ ‹‹ሀብተማርያም ሀብተማርያም›› የሚል ድምጽ በሌሊት ከሰማይ መጣ፡፡ አባቱ በአጠገቡ ተኝቶ ስለነበረ የጠራው መስሎት አባቴ ሆይ አለሁ ሲል መለሰ ከዚህ በፊት ቃል ከሰማይ ጠርቶት አያውቅም ነበርና እንደ ሳሙኤል ጌታዬ ባሪያህ ይሰማሃል ተናገር አለ፡፡ ሳሙ3፤3 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አናገረው፡፡ከዚህም በኋላ አባቱ ከሀገሪቱ ታላላቅ ሰዎች አንዷን እጮኛ አጨለትና ታገባለህ አለው አባታችን አቡነ ሀብተማርያም አባቴ ሆይ እኔ ራሴን ለክርስቶስ በድንግልና ለመኖር አጭቻለሁ ተራክቦዬም ቃለ ወንጌልን መስማት እንጂ ሌላ አይደለምና ለምን እንዲህ ትለኛለህ አለ፡፡ አባቱም ያለ አቡነ ሀብተማርያምፈቃድ ሙሽራይቱን ለማምጣት ሄደ፡፡ አባታችን አቡነ ሀብተማርያምም ሀገር ጥሎ ለመሰደድ ከቤት ተደብቆ ወጣ፡፡ መንፈስ ቅዱስም በመብረቅ አምሳል አባቱን ገሰፀው በዚህ ድንጋጤ ምክንያት የስጋ አባቱ ከዚህ ኃላፊ ዓለም አረፈ፡፡

አባታችን አቡነ ሀብተማርያምም የአባቱን እረፍት ሳያይ አፋር ወደምትባል ሀገር ወደ አሰቦት አቡነ ሳሙኤል ገዳም ሄደ አባ ሳሙኤል ከሚባሉ ደግ መነኩሴ ቦታ ገብቶ ኖረ፡፡ በዚያም ገዳም ውሃ በመቅዳት እንጨት በመስበር፣ ልብስ በማጠብ እህል በመፍጨት አበው መነኮሳትን ሲያገለግል ኖረ፡፡ በአባታችን ላይ መነኮሳት ተቆጥተው ሲነሱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በገሃድ ተገልፃ ትገስፃቸውም ነበር፡፡ በዚህ አገልግሎት ላይ ሳለ ገዳሙ ካለበት ተራራ ላይ ወደ በረሃ ወርዶ ውሃ ቀድቶ ተሸክሞ ሲመለስ ውሃውን በእንስራ እንደተሸከመ እግሩን አደናቀፈው፡፡ የቀዳው ውሃ ሊደፋበትና እንስራውም ሊሰበርበት ሲል ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አድነኝ ትወድቅ ዘንድ አትተዋት ብሎ ፀለየ፡፡ ይህን ብሎ በተናገረ ጊዜ የውሃዋ እንስራ ሳትወድቅ ቆመች እጅም ሳይነካት ተመልሳ በትከሻው ላይ ተቀመጠች አባ ሳሙኤልም ይከተሉት ነበርና ይህን ጽኑ ተዓምር አይተው አደነቁ፡፡ ማር 9፡23እንዲሁ ከዕለታት በአንድ ቀን በሌሊት መብራት ለአባ ሳሙኤል እያበራ ሳለ መብራቱ ከእጁ ወድቆ ጠፋ፡፡ ስለ መምህሩ ስለ አባ ሳሙኤል ቁጣ፣ ፍራቻ፣ ታላቅ ድንጋጤ ደንግጦ ፈጥኖ ባነሳው ጊዜ በእግዚአብሔር ተዓምር ራሱ በራ፡፡ አባ ሳሙኤልም ይህን ተዓምራት አይተው የዚህ ቅዱስ ልጅ የዓለም ሁሉ የጥበብ መብራት ይሆናል ሲሉ ትንቢት ተናገሩ፡፡ በዚህችም ገዳም 12 ዓመት ከትህትና ጋር እየታዘዘ ቤተክርስቲያንን እያገለገለ ኖረ፡፡

ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም ከአባ ሳሙኤል ገዳም ወጥቶ እለ አድባር ወደ ተባለ ገዳም ሄደ፡፡ ከአባ መልኬጼዴቅ እጅ የምንኩስናን ስርዓት ተቀበለ፡፡ ከዚያም በመቀጠል በጥልቅ ባህር ገብቶ 150 መዝሙረ ዳዊትና አራቱን ወንጌልና ሌሎች የፀሎት መጽሐፍትን እየፀለየ አምስት መቶ ጊዜ ይሰግድ ነበር፡፡ እህል መብላትን ትቶ እንደ በረሃ ዋልያ ቅጠል መብላት ጀመረ፡፡ አርባ ቀን የሚጾምበት ጊዜና ሰማንያ ቀንም የሚጾምበት ቀን ነበር፡፡ ቅጠልም ቢሆን እህል ቀዝቃዛ ወይም ምንም አይቀምስም ነበር፡፡ ፊቱም እንደ ንጋት ኮከብ ያበራ ነበር፡፡አራቱን ወንጌላት እየፀለየ ሳለ ቅዱስ ገብርኤልንና ቅዱስ ሚካኤልን በቀኝና በግራ አስከትሎ ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለት፡፡ ወዳጄ ሀብተማርያም ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን አለው ያን ጊዜ አቡነ ሀብተማርያም ከፈጣሪው ግርማ የተነሳ ደንግጦ ከመሬት ወድቆ እንደ በድን ሆነ፡፡ ጌታችንም አንስቶ ክቡራን በሆኑ እጆቹ አፀናው ታላቅ የሆነ ቃል ኪዳንም ገባለት በፀሎትህ አምኖ በጎ ስራ ለሚሰራ ሁሉ በህይወት ሳለህ ልብስ በመስጠት ወይም ምግብ በማቅረብ፣ እግር በማጠብ፣ እንጨት ሳር በማቅረብ፣ ውሃ በመቅዳትና በመርዳት ለደከመ ሁሉ እምርልሃለሁ ዳግመኛ ከሞተ በኋላ መንግስተ ሰማያትንአወርሰዋለሁ አንተ ከሞትክም በኋላ ስምህን የጠራውን ዝክርህን ያዘከረውን ሁሉ የሀብተማርያም አምላክ ሆይ ከጠላት እጅ አድነኝ ያለኝን በህሊና ያሰበውን በልቦናው የወሰነውን እፈጽምለታለሁ አለው፡፡ ማቴ 10፡41-42

ጠላቶችህ አጋንንትን ያጠፋልህ እና ይጠብቅህ ዘንድ ቅዱስ ሚካኤል ካንተ አይለይም የሰጠሁህን ቃል ኪዳን እንዳልነሳ በራሴ ማልኩልህ ከእናትህ ማህፀን ጀምሮ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ አድርጌ መረጥኩህ እንጂ በብዙ ገድልህና በድካምህ ብቻ የወደድኩህ አይደለም፡፡ ይህን ቃል ኪዳን ከሰጠው በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር፣ በብርሃን፣ በቅዳሴ፣ በስልጣን ወደ ሰማይ አረገ፡፡

ቅድስት ዮስቴናም ባሏ ከሞተ በኋላ ለራሷ ምንም ሳታስቀር ገንዘቧን እናት አባት ለሞቱባቸው፣ ለባልቴቶች፣ ለጦም አዳሪዎች፣ ለድሆች ጨርሳ ሰጠች፡፡ በጾም በፀሎትና በስግደት ሰውነቷን አደከመች፡፡ እንዲህ ባለ ገድል ሳለች ከሰማይ እንዲህ የሚል ቃል ወደ እሷ መጣ እኔን ለማገልገል ሴቶች ወንዶች ባሮችሽን፣ ወንድሞችሽን እህቶችሽን ቤትሽን ስለ ተውሽ ሰማንያ ርስት ከተሞችን ሰባት አክሊሎችን እነሆ አዘጋጀሁልሽ አላት ደጋግ ስራን ሰርታ ከፈፀመች በኋላ አረፈች፡፡ መዝ 115/116 ፡ 6 እግዚአብሔር አምላክ አስቀድሞ ተስፋውን እንደነገራት ሰባቱን አክሊላት ሸለማት ሰማንያውን አህጉራት ገነት አወረሳት፡፡

ጻዲቁ አቡነ ሀብተማርያም ወደ ቤተክርስቲያን በሄደ ጊዜ ወንጌል ሲነበብ የክርስቶስ ጌትነቱን የሚናገር ወንጌል ሲነበብ "ወዮሴፍ ብእሊሃ ለማርያም ጻድቅ ውእቱ" የሚል ከቄሱ አፍ ይህን ንባብ ሲሰማ ደንግጦ ወንጌል ወደ ሚነበብበት ስፍራ ሄደ የሚያነበውን ቄስ ገሰጸው "ወዮሴፍሰ ፈሃሪሃ ለማርያም ጽድቅ ውእቱ" በል እንጂ ብእሲሃ አትበል ብሎ መከረው ቄሱም አቡነ ሀብተማርያም እንዳዘዘው ከስህተቱ ወደ ቀና ንባቡ ተመለሰ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ተገልጾ ወዳጄ አመሰገንኩህ እናቴን ድንግል ማርያም ስለ አከበርክ እኔም በመንግስተ ሰማያት ፈጽሜ አከብርሃለሁ አለው፡፡

ጻድቁ አቡነ ሀብተማርያም ከጌታ ጋር በተነጋገረ ጊዜ እንደ ነብዩ ሙሴ በፊቱ ብርሃን ተሳለ፡፡ ሰዎችም የፊቱን ብርሃን አይተው መቅረቡን ፈርተው አደነቁ፡፡ አቡነ ሀብተማርያምም ጌታ ሆይ ከንቱ ውዳሴ እንዳይሆንብኝ በፊቴ ላይ የተሳለውን ብርሃን ሰውርልኝ ብሎ ፀለየ፡፡ ጌታም ፊቱን እንደቀድሞው አደረገው፡፡ በጾም በፀሎት ላይ ሳለም በሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት ወደ ሰማይ ተነጥቆ ቅዱሳን የሚኖሩባቸውን ዓለማት መንግስተ ሰማያትንናሲኦልን ተመለከተ፡፡ሰይጣንም መጥቶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ በሀብተማርያም ላይ መከራ አፀናበት ዘንድ ፍቀድልኝ ብሎ ጮኾ፤ ተናገረ፡፡ እግዚአብሔር አምላክም በሰይጣን ላይ ተቆጥቶ በነፍሱም በስጋውም መከራ ታፀናበት ዘንድ አልፈቅድም ከእናቱ ማህፀን ጀምሮ መርጨዋለሁና በንፅህናና በቅድስና ኃጢአት እንዳይሰራ ዘወትር እጠብቀዋለሁ በእርሱ ላይ ብቻ ሳይሆን በሀብተማርያም ፀሎት በተማፀነኝ ሁሉ ላይ እንኳን አላሰለጥንህም ብሎ አሰናበተው ሰይጣንም ይህን ቃል ሰምቶ አፍሮ እያዘነ ሄደ፡፡ ያዕ 1፡12

አባታችን አቡነ ሀብተማርያም እንዲህ ባለ ስራ ላይ ሳለ ሰውነታቸው እንደ መርግድ የሚያሸበርቅ ዘጠኙ ክቡራን ሰዎች ወደ እርሱ መጡ፡፡ አብሯቸው ያለውን መልአክ ይህን ያህል ብርሃን የከበበው ይህ ሰው ማን ነው ብሎ ጠየቀው መልአኩም አባትህ ተክለሃይማኖት ነው አለው፡፡ ክቡር የሆነ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ጠርቶ ልጄ ሀብተማርያም ሆይ ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ስለወደደህ ብዙ ምርኮ እንዳገኘህ በአንተ ፈጽሞ ደስ ይለኛል፡፡ ነገር ግን የምለምንህ ነገር አለና እሺ በለኝ አለ፡፡ አባታችን አቡነ ሀብተማርያምም ጌታዬ ነገሩ ምንድን ነው አለ? ክቡር አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖትም ከተቀበርኩበት ቦታ እንድትቀበር ቃል ኪዳን ግባልኝ አለው፡፡

አቡነ ሀብተማርያምም ይህንን አደርግ ዘንድ ስለምን ትወዳለህ አለው አቡነ ተክለሃይማኖትም በሀገሬ ላይ የታዘዙ አምስት መቅሰፍቶች አሉና ነው፡፡እነሱም፡-

1. መብረቅ፣

2. ቸነፈር፣

3. ረሃብ፣

4. ወረርሽኝ፣

5. የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡

የአንተም አጽም በውስጡ የተቀበረ እንደሆነ አጥንቴ የተቀበረባት ሀገሬ ከነዚህ መቅሰፍታት ትድናለችና ልጄ ሀብተማርያም ሆይ አንተ የማታውቀው ከፈጣሪያችን ከእግዚአብሔር የተሰጠህ እኔ የማውቀው ክብር አለህና ስለዚህ ነው ቃል ኪዳን ግባልኝ ብሎ ማለደው፡፡ ይህን ሲባባሉ እንዲህ የሚል ቃል መጣ፡፡ ከወዳጄ ከሀብተማርያም አንደበት ይህ ቃል ኪዳን አይወጣም እርሱ በወደደው የሚቀበር አይደለም፡፡ እንዲህም ብለህ የምታስገድደው ለምንድን ነው እኔ በወደድሁት ቦታ ይቀበራል እንጂ የሚል ቃል ተነገረ፡፡ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖትም እየለመነና እየሰገደ ሶስት ጊዜ ከስላሴ ዙፋን ተንበረከከ፡፡ይሁን ይደረግ የሚል ቃል ከሰማይ ሰማ በወዳጄ በሀብተማርያም አጥንት ቦታህ የምትድን ስለሆነች ፈቃዴ ነው ብሎ ጌታ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡

ጻድቁ አቡነ ሀብተማርያም በፀሎት ላይ ሳለ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ የቆምክባትን ቦታ ምስራቁን፣ ምዕራቡን፣ ሰሜኑን፣ ደቡቡን ባርክ አለው፡፡ ሲባርክም ሶስት አጋንንት በፀሎቱ ስልጣን ታስረው በፊቱ ታዩት፡፡ እነዚህም አጋንንት ከኖህ ጀምሮ ሰውን በማሳት ከኖርን በኋላ ከአንተ ጋርምን ፀብ አለን አሉ አባታችንም አቡነ ሀብተማርያም በትዕምርተ መስቀል ሲያማትብ ሁለቱን አጋንንት ምድር ተከፍታ ዋጠቻቸው አንዱ ጊዜዬ ስላልደረሰ አታጥፋኝ አለው፡፡ ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አቡነ ሀብተማርያምን ይህንን ተወው ጊዜው አልደረሰም አለው፡፡ የጌታ ቃል እንዲህ ብሎ በተናገረ ጊዜ ሰይጣን ከአባታችን ተለይቶ ጠፋ፡፡ ማር 9፡23

ከዚህም በኋላ ዕለተ ሞቱ በደረሰ ጊዜ ለሞቱ ምክንያት የሚሆን ቸነፈር ያዘው፡፡ ጌታችንም በምስጋና ወደ እርሱ መጥቶ ወዳጄ ሀብተማርያም ሆይ ዛሬ ወደአንተ የመጣሁት ከድካም ወደ እረፍት እወስድህ ዘንድ ነው ሰባት የጽድቅ አክሊሎችን አዘጋጅልሃለሁ፡፡

1. ስለ ንፁህ ድንግልናህ፣

2. አለምንና በውስጡ ያለውን ንቀህ በመኖርህ፣

3. ስለ ፍፁም ምንኩስናህ፣

4. ዘወትር አራቱን ወንጌላትን በማንበብህና በመፀለይህ፣

5. ስለ እኔ ብለህ ስለተራብከው፣

6. በጾም ስለተጋደልክ፣

7. ቂምና ጥላቻን፣ ትዕቢትን፣ ትምክህትን፣ በልብህ ውስጥ ባለማስቀመጥህ ስለ ንፁህ ተልዕኮ ክህነትህ፣ ስለ ንፁህ መስዋዕትህ ነው ብሎ ቃል ኪዳንሰጠው፡፡

በተጨማሪም እኔ የሰጠሁህን ቃል ኪዳን ተስፋ አድርጎ መጽሐፈ ገድልህን ለሚጽፈው ስሙን በመንግስተ ሰማያት በእውነት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ፣ ለቤተክርስቲያንህ ዘይትን፣ ወይንን፣ ዕጣንን፣ ህብስትን እስከ ቀዝቃዛ ውሃ ድረስ በአንተ ስም መብዓ የሰጠውን የወደደውን ሁሉ አደርግለታለሁ፡፡ በመንግስተ ሰማያትም ከወዳጆቼ ከቅዱሳን ጋር በደስታ አኖረዋለሁ፡፡ የአቡነ ሀብተማርያም ፈጣሪ ኃጢአቴን ይቅር በለኝ ብሎ ያንተን ስም ጠርቶ ቢለምነኝ ኃጢአቱን አስተሰርይለታለሁ ብሎ ቃልኪዳን ገባለት ይህንንም ካለው በኋላ ጌታችን አፉን ሶስት ጊዜ ሳመው፡፡ ያን ጊዜም ከመድኃኒዓለም ጣዕምፍቅር የተነሳ ነፍሱ ከስጋው ተለየች መዝ 115/116 ፡ 6 በሰማያዊ መልአክት በምድራውያን ስውራን ቅዱሳን ዘንድ ታላቅ ደስታ ሆነ ህዳር 26 ቀን አረፈ፡፡ ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው በዝማሬ በማህሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በፃዲቁ መቃብር ቀበሩት፡፡

የአባታችን የአቡነ ሀብተ ማርያም በረከታቸው ይደርብን አሜን።

01/08/2022

ሐምሌ 25 በዚህች ዕለት ቁጥር የሌላቸው ተአምራትና ድንቆችን ባሳየባት በምስር አገር
የቅዱስ መርቆሬዎስ ቅዳሴ ቤተክርስቲያኑ ሆነ።

29/07/2022

አቡነ ጴጥሮስ ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ በጠላት የጥይት እሩምታ እስከተገደሉበት ጊዜ ድረስ የነበረውን ሂደት 'ኮርየር ዴላሴራ' (corriere della sera) የተባለው ጋዜጣ ወኪል እና የምሥራቅ አፍሪካ ዜና መዋዕል አዘጋጅ የነበረው 'ፖጃሌ' የተባለ ጋዜጠኛ እ.ኤ.አ. ሰኔ 15 ቀን 1936 ዓም አዲስ አበባ በነበረ ጊዜ ሂደቱን ባየውና በተመለከተው መንገድ እንደሚከተለው ጽሑፍ አቅርቦ ነበር:-

"ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቁመታቸው ረዘም ፊታቸውም ዘለግ ያለና መልካቸው ጠየም ያለ ዐዋቂነታቸውና ትሕትናቸው ከገጻቸው የሚነበብ ሲሆን በዚህ ጊዜ ለብሰውት የነበረው ልብሰ ጵጵስና ጥቁር ካባ ያውም በጭቃ የተበከለ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ችሎት ቀረቡ፡፡ ለፍርድም የተሠየሙት ዳኞች ሦስት ሲሆኑ እነዚህም ጣሊያኖችና የጦር ሹማምንት ናቸው፡፡ የመካከለኛው ዳኛ ኮሎኔል ነበር፡፡ የቀረበባቸውም ወንጀል 'ሕዝብ ቀስቅሰዋል፣ ራስዎም ዐምፀዋል፣ ሌሎችንም አንዲያምፁ አድርገዋል' የሚል ነበር፡፡ ዳኛውም 'ካህናቱም ሆኑ የቤተ ከህነት ባለሥልጣኖች ሊዳኛውም 'ካህናቱም ሆኑ የቤተ ከህነት ባለሥልጣኖች ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ቄርሎስም የኢጣሊያንን መንግሥት ገዢነት አምነው አሜን ብለው ሲቀበሉ አርስዎ ለምን ዐመፁ፣ ለምን ብቻዎን አፈንጋጭ ሆኑ?' ሲል ጠየቃቸው ፡፡
አቡነ ጴጥሮስም የሚከተለውን መልስ መለሱ...

“አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፣ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም፡፡ አኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ሐላፊነትም ያለብኝ የቤተ ከርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚህ ስለ ሀገሬና ስለ ቤተ ከርስቲያኔ አቆረቆራለሁ፡፡ ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም፡፡ ለፈጣረዬ ብቻ የምናገረውን አናገራለሁ፡፡ እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ ዐውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ፡፡ ግን ተከታዮቼን አትንኩ” አሉ፡፡
ይህንንም ብለው በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ እንዲያይ ተጋብዞ ለተሰበሰበው ሕዝብ የሚከተለውን ሕያው መልእከት አስተላለፉ፡፡

''አረማዊ የሆነው የፋሺስት መንግሥት ቤተክርስቲያንን ለማቃጠል፣ ሕዝበ ክርስቲያንን ለመግደል፣ ሃይማኖትን ለማጥፋት፣ ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው፡ እንጂ በጎ ለመሥራት፣ እውነተኛ ፍርድ ለመስጠት ስላልመጣ ለዚህ ለግፈኛ አትገዙ፡፡ ስለ ውድ ሀገራችሁ፣ ስለ ቀናች ሃይማኖታችሁ ተከላከሉ።ነጸነታችሁን ከሚረክስ ሙታቹህ ስማችሁ ሲቀደስ ታላቅ ዋጋ ያለው ክብር ታገኛላችሁ። የኢትዮጵያ ህዝብ ለዚህ ለጠላት እንዳይገዛ አውግዣለሁ፤ የኢትዮጵያ መሬት ጠላትን ብትቀበል የተረገመች ትሁን። በፈጣሪየ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተገዘተች ትሁን።''
ጋዜጠኛው ይቀጥላል

“እኒህ ጳጳስ ሐቀኛ ነበሩ። ነገር ግን ለኢጣሊያ ለጋስዮን ታዝዞ የመጣው አስተርጓሚ ዳኞች የሚሉትን ብቻ ከማስተርጎም በቀር ጳጳሱ የሚናገሩትን ሃቀኛ ንግግር አላስተረጎመም፡፡ እኔ እንኳን የሰማሁት በአዲስ አበበ ለሠላሳ ዓመት የኖረው የእቴጌ ሆቴል ኃላፊ የነበረው የግሪክ ዜጋ ማንድራኮስ አጠገቢ ተቀምጦ ስለ ነበር የተናገሩትን ሁሉ ስለ ገለጠልኝ ነው፡፡ እኔ እንደ ሰማሁት ፍርዱን ለመስማት በብዛት የተስበስቡት ጣሊያኖችና ታዝዞ የወጣው የአዲስ አበበ ሕዝብ ሐቀኛ የሆነውን ንግግራቸውን ቢሰማ ኖሮ ልባቸው ይነካ ነበር"። ሞት የተፈረደባቸው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በችሎት ፊት ለብዙ ሰዓታት ቆመው ስለዋሉና ደክሟቸው ስለነበር ለመቀመጥ ፈልገው ዳኛውን በትሕትናና በፈገግታ ጠየቁት። እንዲቀመጡም ፈቀደላቸው፣በመጨረሻም የሞታቸው ፍርድ ከተነበበ በኋላ የፈረዱባቸውን ዳኞች ጸልየው በመስቀላቸው ባረኳቸው።ብፁዕነታቸው እስከ መቃብር አፋፍ ድረስ የፍርሃትና የድንጋጤ ምልክት ያይደለ ከልብ ፍጹም ቆራጥነት ይታይባቸው ነበር።”
ምንጭ፡ ዜና ጳጳሳት ኢትዮጵያውያን

Photos from ብራና ሚዲያ Birana Media  በመ/ር ስንታየሁ ማሞ's post 29/07/2022

ስለ 7ቱ ሊቃነ መላእክት በዮሐንስ ራእ 8፡21 ላይ ያያቸው 7ቱ ዐበይት ሊቃነ መላእክት እነዚህ ናቸው፡-
1ኛ. ቅዱስ ሚካኤል
2ኛ. ቅዱስ ገብርኤል
3ኛ. ቅዱስ ሩፋኤል
4ኛ. ቅዱስ ሱርያል
5ኛ. ቅዱስ ሰዳካኤል
6ኛ. ቅዱስ ሰላታኤል
7ኛ. ቅዱስ አናንኤል ናቸው፡፡

ይኽም ይታወቅ ዘንድ መላእክት በሦስቱ ከተሞች ተከፍለው የሰፈሩበትን ሁኔታ፣ የእያንዳንዱን የነገድ ስምና በእየነገዳቸው የተሾሙት አለቆቻቸው ማን ማን እንደሆኑ በዝርዝር ማየት ተገቢ ነው፡፡ (በፎቶው ላይ ያለውን ሰንጠረዥ ይመለከቷል።)

በተለምዶ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት ተብለው የሚነገሩት ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ ሩፋኤል፣ ቅዱስ ራጉኤል፣ ቅዱስ ዑራኤል፣ ቅዱስ ፋኑኤል እና ቅዱስ ሳቁኤል ናቸው ተብሎ ይነገራል፡፡ ነገር ግን ይህ አቆጣጠር ስሕተት ነው፡፡ ምክንያቱም (ፋኑኤል፣ ራጉኤል እና ዑራኤል) ከዐሥራ ኹለቱ ሊቃነ መላእክት ውስጥ ገብተው ይቆጠራሉ እንጂ ዮሐንስ በራእዩ ካያቸው ከ7ቱ ዐበይት ሊቃነ መላእክት አይቆጠሩም፡፡ ይልቁንም ከዐሥራ ኹለቱ ሊቃነ መላእክት ውስጥ ገብተው ቢቆጠሩ (ሚካኤል፣ ገብርኤል፣ ሩፋኤል፣ ፋኑኤል፣ ራጉኤል፣ ዑራኤል፣ ሱርያል፣ ሰዳካኤል፣ ሰላታኤል እና አናንኤል) እንዲሁም ኪሩብ እና ሱራፊ ተደምረው ዐሥራ ኹለት ይሆናሉ፡፡

ቅዱስ ፋኑኤል፣ ቅዱስ ራጉኤል እና ቅዱስ ዑራኤልስ የተሾሙት እንዴት ነው ቢሉ ቅዱስ ራጉኤል ‹‹ሊቀ መላእክት›› ተብሎ መስከረም 1 ቀን በ12 ሊቃነ መላእክት ታጅቦ ‹‹ርዕሰ ሠራዊት›› ተብሎ በሰባቱ ከተሞች ላይ ተሾመ፡፡ ቅዱስ ዑራኤልም ‹‹ሊቀ መላእክት›› ተብሎ ጥር 22 ቀን በ12 ሊቃነ መላእክት ታጅቦ ‹‹ርዕሰ መላእክት›› ተብሎ ተሾመ፡፡

እንዲሁም አንዳንድ አባቶች ዓሥሩ ሊቃነ መላእክት ብለው ሦስቱን (ፋኑኤልን፣ ራጉኤልንና ዑራኤልን) ጨምረው ይቆጥራሉ፡፡ እነርሱም ሚካኤል፣ ገብርኤል፣ ሩፋኤል፣ ፋኑኤል፣ ራጉኤል፣ ዑራኤል፣ ሱርያል፣ ሰዳክያል፣ ሰላትያል እና አናንኤል ናቸው፡፡

በዛሬው ዕለት በዓመታዊ በዓሉ ታስቦ የሚውለውን ቅዱስ ሱርያልን ጥር 27 እና ሐምሔ 27 ቀን የሚነበበው መጽሐፈ ስንክሳር "ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት 4ኛው የሆነው መልአኩ ቅዱስ ሱርያል የበዓሉ መታሰቢያ ነው" በማለት ይገልጸዋል።

የመላእክት መዓርግ ሲነገር ሚካኤል ገብርኤል ሩፋኤል ብሎ ቀጥሎ የሚመጣው ሱርያል ነው:: በ3ቱ ሰማያት ካሉት 9ኙ ዓለመ መላእክት የአንዱ የሥልጣናት መሪ አለቃ ነው:: ለኖኅ መርከብን ያሠራው ከጥፋት ውሃም ያዳነው ይህ ቅዱስ መልአክ ነው:: በገድለ ሰማዕታትም ላይ እንደተጠቀሰው የሰማዕታት ረዳትና አዳኝ ነው።

የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሱርያል ጥበቃው አይለየን

25/07/2022

👉 #ውርጃ ሃጢያት ነው!

ከሶሻል ሚዲያ ያገኘሁት ጥሩ ትምህርት

ሴትየዋ ችግሯን ልታማክር ወደ ዶክተር ሄደች።
"ዶክተር እባክህ አንድ ችግር ገጥሞኛል።"
"ምን ገጠመሽ?"
".…ከወለድኩ ገና አንድ አመት አልሞላኝም። ሆኖም ሌላ ልጅ አርግዣለሁ። እኔ ደግሞ ተጨማሪ ልጅ በዚህ ወቅት እንዲኖረኝ አልፈልግም።"
"እና ምን ልርዳሽ?""
"ሆዴ ውስጥ ያለውን ልጅ ማስወረድ እፈልጋለሁ!"
ዶክተሩ ትንሽ አሰብ አደረገና “ለምን ከዚህ የተሻለ ሀሳብ አላቀርብልሽም?” ሲል ጠየቃት።
“ምን አይነት ሀሳብ?”
“አየሽ ይሄን ልጅ ከሆድሽ ለማስወረድ ብዙ ችግር ውስጥ ትገቢያለሽ፣ ደም ይፈስሻል ልትሞቺ ወይም በቀጣይ ላትወልጂ የምትችይበት አጋጣሚም ሊፈጠር ይችላል። ስለዚህ ይሄን ሁሉ ችግር ከምታይ ለምን በእጅሽ ያቀፍሽውን ልጅ አንገድለውም?” አላት
ሴትየው አደነገጠች። ዶክተሩ ንግግግሩን ቀጠለ።
“አዎ! ለእናት እንደሆነ ሁሉም ልጅ እኩል ነው። ስለዚህ አንዱ መሞት ካለበት ሆድሽ ውስጥ ያለው ከሚሞት ይሄኛው የተወለደው ቢሞት ምንም ችግር ሳይገጥምሽ ሀሳብሽን ታሳኪያለች…” እያለ ምክረ ሀሳቡን መተንተን ጀመረ።
ሴትየዋ ግን በጆሮዋ የሚንቆረቆረው የዶክተሩ ሀሳብ ሳይሆን የአምላክ ማሳሰቢያ መሆኑን እያሰበች ለማስወርድ የዘረጋቻቸውን ሁለት እግሮቿን ሰብስባ ብድግ ብላ ክፍሉን ለቃ መውጣት ጀመረች።..…ልጆቿን አንዱን በክንዷ ሌላውን በሆዷ እንዳቀፈች ወደ ቤቷ ተመለሰች። አዎ! የተወለደም በሆድ ውስጥ ያለም ቢሆን ለእናት ልጆቿ ሁሉ እኩል ናቸው!

ህጻናትን በውርጃ መግደል ወንጀልም ሀጢያትም ነው!

17/07/2022

በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ?(ዘፍ 18÷3)

አብርሃም ማለት አበ ብዙኃን ማለት ነው፡፡ ትውልዱም ከነገደ ሴም ነው አባቱ ታራ ይባላል የአዳም ሃያ አንደኛ ትውልድ ነው፡፡ ቤቱን ከተመሳቀለ ጎዳና ሠርቶ የወጣ የወረደውን ሰው በእንግድነት ሲቀበል ይኖር ነበር ፡፡ ሰይጣን ከዕለታት አንድ ቀን እራሱን በአብርሃም የተደበደበ አስመስሎ ከመንገድ ላይ በሰው አምሳል ቁጭ ብሎ እንግዶችን ወዴት ትሄዳላችሁ እያለ ይጠይቃቸው ጀመር ርቦን እንዲያበላን ጠምቶን እንዲያጠጣን ከአብርሃም ዘንድ ይሉታል፡፡ የድሮው አብርሃም መሰላችሁ እንዴ! እኔም እንደናንተ ርቦኝ ያበላኛል ጠምቶኛል ያጠጣኛል ብዬ ብሄድ እራሴን ደብድቦኝ አባረረኝ እያለ ሰዎችን ሁሉ ወደ አብርሃምም ያለ እንግዳ እህል አልበላም ውሃም አልጠጣም ብሎ ሦስት ቀን ቆየ በሦስተኛው ቀን በቀትር በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚያብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጡለት አይኑንም አነሣና አነሆ ሦስት ሰዎችን በፊቱ ቆመው አየ፡፡ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነስቶ ሮጦ ወደ ምድርም ሰገደ እንዲህም አለ ገሀሱ አጋዕዝትየ ቤተ ገብርክሙ ጌቶቼ ከቤት ገብታችሁ እረፊ አላቸው ደክሞናልና እዘለን አሉት አንዱን አዝሎ ሊገባ ሁለቱ በግብር አምላካዊ ገብተው ተገኝተዋል አብርሃምም ሦስት እንደሆኑ አውቆ ሣራን ሦስት መስፈሪያ ዱቄት ወስደሽ አንድ እንጎቻ አድርገሽ ጋግሪው አላት ሣራም ጋግራ አቀረበች አብርሃምም ሥላሴን በእንግድነት ተቀበለ፡፡

ትምህርት

· እንግዶችን በቤታችን ለመቀበል ዘወትር መዘጋጀት

· አንዳንዶች ሳያውቁ መላእክትን እንግድነት ተቀብለዋል (ዕብ 13÷1)

· እንግዶችን መቀበል ከእግዚያብሔር ዋጋ እንዳለው ማወቅ(ሮሜ 4÷37)

· አብርሃም እንግዳ ለመቀበል በረከትን አግኝቷአል መካን የነበረችው ሚስቱ ሣራም ልጅ ወለደች (ዘፍ 21÷1)

መልእክት

አባታችን አብርሃም ደግ እንግዶች ወደ ቤቱ ካልመጡ እህል የማይበላና ወኃ የማይጠጣ ሰው ስለነበረ እግዚአብሔር ባርኮታል ዘሩንም እንደምድር አሸዋ አብዝቶለታል፡፡ እኛም እንግዶችን በመቀበል ያለንን በማካፈል ወደ ኋላ እንዳንል ያጣነውን ፤የምናገኘው ተስፋ የቆረጠን ተስፋችን የሚቀጥለው አይሳካልንም ያልነው የሚሳካው፤ የተዘጋብን የሚከፈትልን በእምነት ስንኖርና እና እንደ አብርሃም እንግዶችን በመቀበልና በማስተናገድ የምንጠብቀውን ተስፋ በዓይናችን የምናየው በእምነት እየኖር የእግዚብሔርን እንግዳ ስንቀበል ነው፡፡

የእግዚአብሔርን በረከትም እንዳያልፈን አምላካችን በቸርነቱ ይርዳን አሜን!!

17/07/2022

+++/ምስክርነት /_____++++ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ ምዕራፈ ቅዱሳን "አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ" ገዳም!
~ሰላም ጆን ምስክርነት ለመመስከር ነበር እኔ ከአገባው አምስት አመት ሆኖኛል ልጅ እምቢ ብሎኝ ፃድቁን ለመንኳቸው ለሌሎች እህቶች እንደደረሱላቸው ለኔም ድረሱልኝ አልኳቸው ልመናዬ ተሰመቶ የሁለት ወር ነበሰ ጡር መሆኔን አውቄአለው ወልጄ ደሞ ለመታቀፍ ያብቃኝ ለኔ እነደደረሱልኝ ልጅ አተው ለተጨነቁ ሁሉ ፃድቁ ይድረሱላቸው

~ሰላም ዮሐንስ እንዴት ነህ
ምስክርነት ለመስጠት ነው
አባቴ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ለምኛቸው አፍሬ አላውቅም እግዚአብሔር ይመስገን
ጓደኛዬ በደረሰኝ ምክንያት 1 ዓመት ከ 4 ወር ተፈርዶበት ታስሮ ነበር እመቤቴ ድንግል ማርያምን አቡነ እጨጌ ዮሐንስን ቅ/ገብርኤል ቅ/ሚካኤልን ለምኛቸው ልመናዬ ሰምሮ በይግባኝ በዋስ ተለቋል እግዚአብሔር ይመስገን አባቴንም ለምስክርነት አብቁኝ ብያቸው ነበር ይኸው ምስክርቴ ::2 ተኛ እህቴ ያጨናነቃት ጉዳይ ነበር ለ አባቴ ነግረናቸው ሁሉም ነገር ካሰብ ነው በላይ በጥሩ እየሔደ ነው ሁሉን ላደረገ ለእግዚአብሔር ምን ይከፈለዋል ...
እናቴ እመቤቴ ምስጋና ይድረሳት ቅ.ገብኤል ቅ. ሚካኤል ምስጋና ይድረሳቸው :: ልመናን ፈጥነው የሚሰሙ አባቴ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ምስጋና ይድረሳቸው።

~Selam lant wnedem zarem bedegame meskernet lemsetet nbr ...ke kenat befit yetedrgelgn teamer yeh new...be sera bota yetshale sera lemagegnet le bezu ametat semokr aletsakam nbr amelak fekedo le ene emihon bota endemedeb gizew honoal yhenenem le gefet maryam ena le abun echge yhonanns selemen koyechalew bemechersham ende ene hatiyat sayhon ende amelak fekad ende enesu meleja amelak yefekedew bota tesetognal ahunem mechershawen endiyasamerlegn tseleyulegn

~ሰላም ወንድም
አባታችን አቡነ እጨጌ ዩሐንስ ያደረጉልኝን መስክርልኝ ልጄ አንዳንድ ቀን ምጥት ብላ ታስቸግረኛለች ትጮሀለች ታለቅሳለች...
እናም ትላንት በጣም አስቸገረችኝ እኔም በጣም ተማረርኩ እሳቸዉን ስማጸን ደና ሆናለች አሁንም ጨርሰዉ ይማርዋት።

~እንደምን ሰነበትክ ጆኒ ምስክርነት ለመስጠት ነው ሰብለወንጌል እባላለሁ ከእንግሊዝ ።ፃዲቁ አባቴ አቡነ እጨጌ ሁልጊዜም ጠርቻቸው የማያሳፍሩኝ ባለፈው ሳምንት ስራ ቦታ ሰባት የምን ሆን ሰዎች ኮቪድ ተያዝን የተወሰነው በጣም ታመምን በእውነት ቀላል አልነበረም ያመመኝ ከኔ አልፎ የልጄን ሚስትና የአንድ አመት የልጅ ልጄም ከኔ ተላለፈባቸው በተለይ የህፃኑ በጣም አስደነገጠኝ ሀይለኛ ትኩሳት ያዘው እዚህ ደግሞ ሆስፒታል መሄድ ክልክል ነው ቤት ሆነን በህመም ማስታገሻ ነው መቆየት ያለብን ይህችን ትኩሳት ሲበረታበት የአቡነ እጨጌን ምስላቸውን ሰውነቱን በሙሉ አሻሸሁትና ቅን ቅዱስ ቀብቼው የኡራኤልና የቃጥላ ማርያም ፀበል ስለነበረኝ ትንሽ አጠጥቼው ቀባብቼው እኔም ይልህፃኑም እናት እንደዛው አድርገን አደርን በማግስቱ ጠዋት ህፃኑም ድኖ እኔም ከኮረና ንፁህ ሆነን አደርን የአቡነ እጨጌ ምስል ፍቱን መድሀኒት ሆነን ምስጋና ይድረሳቸው ፃድቃኑን የሰጠን የእመቤታችን ልጅ ክብር ምስጋና ይድረሰው። ፃድቁ አባቴ ፈቃዳቸው ሆኖ ዳግም ለደጃቸውም እንዲያበቁኝ እየተማፀንኳቸው ነው አመስግኑልኝ አቡነ እጨጌ አባቴን ።

~በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን:: አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠግሮ ያደረጉልንን ተዓምር ለመመስከር ነው የኔ ፈጥኖ ደራሽ አባቴ በዛሬው ባለቤቴ በስራ ጉዳይ ፈተና ነበረው እናም አባታችንን ሁሉም ነገር በሰላም ካለፈ እመሰክራለው ብዬ ተስዬ ነበር እናም ጠዋት ወደ ፈተናው ሲሄድ በቦርሳው የአባታችን የአቡነ እጨጌ ዮሐንስን ገድል የአባታችንን የፃድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን ገድል የሰማዕቱን ቅዱስ ቂርቆስን ገድል ይዞ ነበር የሄደው እናም ካሰበው በላይ እነሱ ሞገስ ሆነውት በሰላምና በጥሩ ሁኔታ አልፎለታል እግዚአብሔር ይመስገን እልእልእልእልእልልልልል ብላችሁ አመስግኑልን ክብርና ምስጋና ለአባታችን ለአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ለመላእክት ለፃድቃን ለሰማእታት ለሁሉም እንደየ ክብራቸው ይገባቸዋል አሜን። አባቴ ፍፃሜውን አሳምረውልን ዳግም ለምስክርነት አብቁን አሜን። እግዚአብሔር አምላክ አገራችንን ከክፉ ሁሉ ይጠብቅልን አሜን።

~በስመአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ ለሚሆነው ለሚደረገው ነገር ሁሉ እግዛብሔር የመስገን የዛሬ 5ወር አካባቢ መስክሬ ነበር ጓደኛ እረጉዝ ናት የልጃ ለብ ምት አልሰማ ብሎ በፍርሀቴ በደሰታዬ ግዜ ከአይን ጥቅሻ ፈጥነው የሚደርሱልኝ አባቴ አብነ ወእጨጌ ዮሀንስ አስሙልኝ ዛሬ ደግሞ በለተ ቀናቸው በሰላም ተገለገለች እግዚብሔር ይመስገን እሷም መስክሬለኝ ብላለች 1ኛ ጤነኛ ለጅ 2ኛ ከተወለደ ጀምሮ እያለቀሰ ነበር ስማቸውን ጠርቼ ተኝቶል 3ኛው ደግሞ የምፈልገው አይነት ልጅ ልክ እንደጠየኮት ሰለሰጡኝ አመስግኑልኝ በላለች
የኔ ለጅም ትናንት ምስክርነት እያነበብኩ ተኝቶ ጥርሱን ያፋጫል መስላቸውን ስደባብሰው ወድያው ተወው እርሶ
አባቴ የልቤን ያወቃሉ
ጆን ተባረክ

~አባታለም ቀኜ አማላጄ ምርኩዜ ታምሩ ብዙ ነው። ባለቤቴ ተደውሎ ከምትፈልገው ቦታ ስራ ተመድበሻል ተብላ ተጠራች በለተ ቀኑ ደስታዋን እጥፍ አደረገላት።
የኔ አባት መመኪያየ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ መጨረሻውን ያሳምርላት አባቴ አሁንም ጣልቃ ይግቡ። ደስ ብሎኛል እልልልልልል ብላችሁ አመስግኑልኝ። 💚💛❤️

~Selam Johnny enkan aderaka le abatchan amet bale abune echage yadergulagn belta kenchaw betam kaschankagn n***r awotugn mecha abate tercha afera alawkam le hulchaw leka endana kechanka yawtchu abune echage embeta mednalem kedsan semata hulu keber mesgana yedrsachaw 🙏

~በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡ ሠላም ጆን እባክህ ይህንን ምስክርነት አስተላልፍልኝ አደራ፡፡ አራስ ልጄን ከባድ ጉንፋን አመመብኝ በጣም በረታበት በተለይ ሲመሽ ባሠበት መጥባት ሁሉ እምቢ አለ ማልቀስ ብቻ ሆነ በጣም ተጨንቄ ኧረ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ድረሱልኝ ብዬ አለቀስኩ ልመናዬን ሰሙኝ ሲነጋ በጣም ለውጥ አለው በነጋታው በደንብ ተኝቶ አደረልኝ፡፡ ክብር ለአጋዝዕተ አለም ስላሴዎች፣ ለአባቴ ለቅዱስ ሚካኤል ፣ ለቅድስት አርሴማ፣ ለአባቴ ሁሌም ጠርቼ ለማላፍርባቸው አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ይሁን፡፡

~ሰላም ጆኒ እንዴት ነህ ምስክርነት ለመስጠት ነበር አባቴ አብነዕጨጌ ዬሀንስ ያደረጉብዙነው የኔ ፈጥኖ ደራሽ ጠርቼ አፍሬ አላውቅም በየምክንያቱ ስማቸውን ጠርቼ ሁሉም የሚፈፅሙልኝ እናቴ በጣም አሞብኝነግሬአቸው ነበርየኔአባትበምህረት ደበሱልኝ እልልልልብላቹ አመስግኑልኝጨርሰውይማሩልኝ

~ጆኒ እንደምን አለህልኝ። እንደተለመደው ቸርነታቸው የማያልቀው አባቴ ዛሬም ተአምር አርገውልኛል። ባለፈው ምስክርነት ስሰጥ ሌላ የልጄ ጉዳይ አለ ይርዱኝ ብዬ ተስፋዬ ነበረች ይኸው አባቴ ሳይውል ሳያድር የተጨነኩበትን ነገር አሳኩልኝ። ስለቴንም ሰጠሁ። ለተጨነቃቹህ ሁሉ አባቴ አቡነ እጨጌ ደራሽ ናቸውና በፍፁም እምነት ጠይቋቸው። አያሳፍሩም። ህብስተ ገብርኤል

~Salam jon lememesker nw zemede argzaneber ena beselam endtgelagel teyikeachew beselam wend lij tegelaglalech abune ecege yohhansn yeseten ye eme amlak lij yimesgen yalmesekerkut yinoral yiker yibelugn hule yismune amen

~Selam johnny endet nh Abatachn abune echege Dingil mariyam kenlijua yadregulgn lmemsker nbr balebte yesra edgt fetna nberbet ena amot selnber altezgajm nbr ena le abune echge kelale endiyadrgulet ena kegonu endihonulet

~ስለማይነገር ስጦታው እግዛብሄር ይመስገን ለብዙ ቀናት እቃ ሳልሸጥ ቆየው አቡነእጨጌን በለተ ቀናቸው ተማፅኛቸው ብዙ እቃ ሸጥኩኝ እልልልልልል አመስግኑልኝ

~ሠላም ጆኒ እንዴት ነህ ምስክርነት ለመስጠት ነው ከዚህ በፊት ራሴን ያመኛል ያዞረኛል ብዬ በፀሎታችሁ አስቡኝ ብዬ ነበር አሁን ሙሉ ለሙሉ ተሽሎኛል ክብርና ምስጋና ምንም ጠይቄያቸው ለማያሳፍሩኝ ለአባቴ ለአቡነ እጨጌ ይሁን

~እግዚአብሔር ይመስገን አቡነ እጨጌ ዮሐንስ አባቴ ሁሌ እንደደረሱልኝ ነው ተመስገን ለሊት ቁርጠት በጣም አሞኝ ማሩኝ ብዬ በገድላቸው ተዳብሼ በአቡዬ እምነት ተቀብቼ ቀለል ብሎኛል ጨርሰው ይማሩኝ አባቴ አሜን 🙏🙏🙏

~በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ሰላም ጆኒ አባቴ ጨጓራውን አሞት አባታችንን አቡነ እጨጌ ዩሐንስን ተማፅኛቸው ተሽሎታል እሳቸውን የሰጠን የድንግል ማርያም ልጅ መድሃኒያለም ይክበር ይመስገን አሜን።
ገብረ ስላሴ ብላችሁ በፀሎት አስቡኝ

~Bsmeab weweldi wemnfesi kidus ahadu amlak amen .abatachin abune chege yadrgulngin lmemskeri niw ke balbete gar behone nger sangbaba tchkachken labatachin slam arguni bye ngriachiw wedyawinu slam honi.zare btam yaschnkingi ngeri ale ye sera guday niw abate abune echege astkaklulengi tsloti adrgulngi .sltedrglingi hulu kiber mmsgana ygbachiwali elelelelelele..... blacuhi abatachin abune echegen,embetachin ,mlaktin,tsadkani smaetatin,betklala amsgnulingi🙏

~ጆኒ እንደምን ከርምክ ወልደ ስላሴ ነኘ አቡነ እጨጌን ያደርጉልኘን ለመመስከር ነው ምንም ጠይቄአቸው አፍሬ አላቅም የእውነት ምን ማለት እንደምችል አላቅም እባክህ ሁሉም ነገር በእሳቸው ፈቃድ እየሆነልኘ ነው መስክርልኘ

~ምስክርነት ለመስጠት ነው፡፡ ወልደሚካኤል እባላለሁ፡፡ ሰኔ 11/12, 2014 ዓ.ም ወደ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም የነበረውን ጉዞ ለመጀመሪያ ጊዜ ከልጄ ጋር ሔጄ ነበር፡፡ የጻጽቁን ታምራት ምስክርነት ስሰማ እኔም ከሥራዬ ጋር በተያያዘ ያለብኝን ችግር ነግሬያቸው ነበር፡፡ ወዲያው እንደተመለስኩ ሁሉም ነገር እየተስተካከለና መስመር እየያዘልኝ ሲሆን ክ/ከተማ የማስፈጽመውም ጉዳይ በማይታመን ሁኔታ ተሳክቶልኛል፡፡ ስዕለቴንም አስገብቻለሁ፡፡ በቀጣይም የቀሩኝ ነገሮች እንደሚስተካከሉ እርግጠኛ ነኝ፡፡ የኛን ልመና የሰማ የአቡነ እጨጌ ዮሐንስ አምላክ የእናንተንም ልመና ይስማችሁ፡፡

~Selam J***y, misekerenet lemesetet neber. Dinget amogne techenke abune echegen ena emebeten lemegneachehu dehna hognealehu. Egziabher yimesgen. Misgana lemebete ena letsadeku abatachen.

~ሰላም ጆኒ እባክህ መስክርልኝ 🙏 ዛሬ እየፈራሁ የምሄድበት ቦታ ነበር ሰላም ደርሼ እንድመለስ ለምኛቸው የአባቴን ስም እየጠራሁ ነበር የሄድኩት በሰላም ተመልሻለሁ ክብር ምስጋና ለአቡነ እጨጌ እነሱንም ለሰጠን መድሃኒያለም ይሁን🙏አሜን

~በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱምላክ አሜን እንደምን አለህ ወንድማችን ጆን አባታችን አብነ እጨጌ ዩሀንስ ያደረጉልኝን ለመመስከር ነው አባታችንን በ ትንሹም በትልቁም ነገር ነው የምጠራቸው ሁሌም የጠየቁኳቸውን ነገር ያደርጉልኝል አሁን 1,አንድ ያስጨነቀኝ ነገር ነበር እግዛብሔር ይመስገን አስተካክለውልኝል 2,እናቴን አሙዋት የእሳቸውን እምነት እና ፀበል ቀብቻት እና ፀበላቸውን ጠጥታ አሁን ደህና ሁናለች ጨርሰው እንዲምሩዋት በፀሎታችሁ አስብን 3,አንድ የማውቀው ሰው ባለቤቱ የልብ ኦፕራሲን አርጋ ታማ ነበር የአባታችንን ፀበል ሰጥቻቸው በጣም ጥሩ ለውጥ አለ ብለውኛል ጨርሰው እንዲምሩዋት በፀሎታችሁ አስብን አሁንም ሌላም የጠየቛቸው ነገር አለ ሁሉንም የልቦናዬን መልካም መሻት እንደሚፈፅሙልኝ አምናለሁ በፀሎታችሁ አስቡኝ አባታችን አብነ እጨጌ ዩሀንስ ክብር ምስጋና ይግባቸው እሳቸውን የሰጠንን ልዑል እግዛብሔር እመቤታች ድንግል ማርያም ቅዱሳን መላዕክት ፃድቃን ሰማዕታት ሁሉም እንደየ ማዕረጋቸው ይመስገኑ 🙏ደጃቸው መጥቼ ሁሉንም ለመመስከር ያብቃኝ።አንተንም እግዛብሔር ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥህ እባክህን ጆን መስክርልኝ

~selam wendeme ebakek yichin teamer adereselegn matress defence betam chenekogn nber beselam alefoal .ader adereselegn
kiber mesgan yihun letsedeku amelak

~ሠላም ጆኒ አባታችን
ለአቡነ እጨጌዮሐንስ ክብር ምስጋና ይገባል እግዚአብሔር ይመስገን አመስግኑልኝ🙏🙏🙏 hayle mariyamen ebalalehugn
Endemn Aleh Abatie. Echegie yohannes yeregulignin Lememesker befew samnt malet Be 21 betam amogn neber enam ferech neber atatachenen lemenkuwachew esachewem wediyawen ashalehugn ahunm bezu lewt alew ahun demo lela yaltemeleselegn n***r ale esun asaketewelgn lelea mesekerenet endemeta yabekugn Abatachen tshlot ena meljawot ayeleyen dinegel mariyam kene leijuwa yetemesegenech tehun yenate n***r adera abate lesero setechowatalehugn amesgenalehu. 🙏🙏🙏

~Besmam weweld wemenfes kidus ahadu amlak amen selam jonny endemn aleh weleteslasse ebalalew tsadku abatachin abune echege yaderegulgnin lememesker newu bekrbu erguz endehonku aweku ena betam hayilegna hmem kenm lelitm kebad kurtet metegnatm mekemetm mayaschil ayinet eyamemegn betam yasleksegn neber tlant gn yabune echege siele adnoachewn hoden ashashche selam asadrugn byachew kelelawu ken betam teshilogn dehna honku egziyaber yimesgen esachewun abat adrgo yeseten

~ጆኒ እንደምን ሰነበትክ ወለተማርያም እባላለው አቡነ እጨጌ ያደረጉልኝን ለመመስከር ነው ቤት ውስጥ አይጥ አስቸግሮኛል አንደቀን ሌሊት ተነስቸ አቡነ አጨጌ አባቴን ለምኘ ፀልየ ተኛሁ እግዚአብሔር ይመስገን በሰላም አደርን አሁንም ጨርሰው ባይጠፉም ተመስገን ነው ጨርሰው እንዲጠፉልኝና የነገርኳቸውን እንዲሠጡኝ አብዝቸ እፀልያለው።

~።።የአመቱ 2014 አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ የመጨረሻ ጉዞ{ ሐምሌ 28/29}
፨ሐምሌ 28/29 ታላቅ በዓል ንግስ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ ዕረፍታቸው ሐምሌ 29 ነው።
፨ሐምሌ 28/29 የአመቱ የመጨረሻ ጉዞ ሲሆን ጸበሉ በክረምቱ ምክንያት ከጥንትም ጀምሮ ሐምሌ 29 የጻድቁ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ ዕረፍት ዕለት የሚዘጋ ሲሆን፤ጸበሉ ተባርኩ መስከረም 29/2015 የጻድቁ መስቀላቸው መቋሚያቸው ወጥቶ ጸበላቸው ጋር ሄዶ ተባርኮ የመጠመቅበት ዕለት ነው።
ለበረከቱ ያብቃችሁ!
ለበለጠ መረጃ፦
0911190212
0911481388
0979986969
0901002929
ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ!

11/07/2022

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሐምሌ 5-ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ሰባ ሁለቱ አርድእት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓላቸው ነው፡፡
+ መልአኩ ቅዱስ ሳቁኤል የበዓሉ መታሰቢያ መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳል፡፡
+ የሀገረ ጋዛው ሰማዕት ቅዱስ ይስሃቅና የደብረ ዓሣ ጻድቃንም መታሰቢያቸው መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳቸዋል፡፡
ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ፡- በአራማይክ ኬፋ፣ በግሪክ ጴጥሮስ ማለት ‹‹ዓለት›› ማለት ነው፡፡ አንድም ጴጥሮስ ማለት የሃይማኖት መሠረት ማለት ነው፡፡ ማቴ 16፡18፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ የመጀመሪያ ስሙ ስምዖን ሲሆን ጌታችን ኬፋ ብሎ ሰይሞታል፡፡ በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው በቤተሳይዳ ተወለደ፡፡ ትውልዱ ከነገደ ሮቤል ሲሆን አባቱ ዮና ይባላል፡፡ የተወለደው በገሊላ አውራጃ በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ከአምስት ዓመቱ ጀምሮ ያደገው በቅፍርናሆም ነው፡፡ ጴርቴዋ የምትባል ሚስት የነበረችው ሲሆን የሚተዳደረው ዓሣ በማጥመድ ነበር፡፡ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር ዓሣ ከሚያጠምድበት ተጠርቶ ሐዋርያ ሆኗል፡፡
ለደቀመዛሙርነት ሲመረጥ ዕድሜው 53 ዓመት እንደነበረ ይነገራል፡፡ ወደ ጌታችን ያመጣውም ወንድሙ እንድርያስ ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ፣ በርናባስ እና ወንጌላዊው ማርቆስ ቤተ ዘመድ ናቸው፡፡ የማርቆስ አባት አርስጦቡሎስ እና በርናባስ በእናት የሚገናኙ ወንድማማች ናቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ያገባው የበርናባስንና የአርስጦቡሎስን እኅት ስለነበር በጋብቻ ይዛመዳሉ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት ሲጠራ መተዳደሪያው የነበረውን መረቡንና ታንኳውን እንዲሁም አባቱን እርግፍ አድርጐ ትቶ ጌታውን የተከተለ ሐዋርያ ነው፡፡ የመጀመሪያ ስሙ ስምዖን ሲሆን ይህንንም እናቱ በነገዷ ስም ያወጣችለት ነው፡፡
በቂሳርያ ከተማ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «ማን ትሉኛላችሁ?» ብሎ በጠየቀ ጊዜ «አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ» ብሎ ለአይሁድ ሊቃውንት የተሰወረውን ምሥጢረ ተዋሕዶ ገልጦ በመመስከሩ ጌታችን «አንተ ጴጥሮስ ነህ» ብሎታል ይህም በላቲን ቋንቋ ዓለት ማለት ነው፡፡ በአርማይክ ደግሞ ኬፋ ይባላል፡፡ በመቀጠልም ቅዱስ ጴጥሮስ ይህን ሲመልስ ከጌታችን ዘንድ የተሰጠው መልስ ‹‹በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ስጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ፣ እኔም እልሃለሁ አንተ ጴጥሮስ ነህ፣ በዚህችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሠራለሁ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም፡፡ የመንግስተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፣ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል›› የሚል ነው፡፡ ይኸውም በወቅቱ የነበሩ ሐዋርያትና በኋላም በእርሱ እግር የሚተኩትን ካህናት አባቶችን ወክሎ የተቀበለው እጅግ አስደናቂና ቃልኪዳን ነው፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስ ከአዕማድ ወይንም የምሥጢር ሐዋርያት ከሚባሉት ከእነ ዮሐንስ እና ያዕቆብ ጋር በመጀመሪያ የሚቆጠር ነው፡፡ ከሐዋርያት ሁሉ ቀደም ቀደም የማለት ባሕርይ ነበረው፡፡ ጌታችን በጥብርያዶስ ባሕር ላይ ሌሊት በእግሩ ሲመጣ ቢመለከት ‹‹ወደ አንተ እመጣ ዘንድ እዘዘኝ›› በማለት ካስፈቀደ በኋላ ወደ ጌታ ለመምጣት መንገድ ጀምሮ በመሐል ጥርጣሬ ገባውና መስጠም ስለጀመረ ጌታችን «ያመንክ እንጂ ያላመንክ አትሁን» ብሎ ገሥጾ ከመስጠም አድኖታል፡፡ ማቴ 14፡22-33፡፡ በቅፍርናሆም ጉባኤ ጌታችን ምሥጢረ ቍርባንን ሲያስተምር አይሁድ ስላልገባቸው ወደ ኋላ አፈገፈጉ፡፡ ከደቀ መዛሙርቱም «ብዙዎቹ ወደ ኋላ ተመለሱ» በዚህን ጊዜ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁ?» ብሎ ሐዋርያትን ጠየቃቸው፡፡ በዚህ ሰዓት «ጌታ ሆይ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘለዓለም የሕይወት ቃል አለህ፣ እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆንክ እናምናለን» በማለት ሐዋርያትን ወክሎ የመለሰ እርሱ ነው፡፡ ዮሐ 6፡66-68፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችንን በጣም ይወድ ነበር፡፡ ፍቅሩ ግን ቅንዓት የተቀላቀለበት በመሆኑ ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ የሞቱን ነገር ቀድሞ ሲነግራቸው አይሁንብህ በማለት ተከራክሯል። ማቴ 16፡23፡፡ በኋላም «ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም» ብሎ በራሱ ቅንዓት ተማምኖ ተናግሮ ነበር፡፡ ጌታችን «ዶሮ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ» እያለው እንኳን «ከአንተ ጋር መሞት እንኳን የሚያስፈልገኝ ቢሆን ከቶ አልክድህም» በማለት ተከራክሯል፡፡ ማቴ 26፡34፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ አስቀድሞ የተናገረውን ቃል ለመጠበቅ ሞክሮ ነበር፡፡ ጌታችን ዛሬ «የሰው ልጅ ተላልፎ ይሰጣል» ብሎ አስተምሮአቸው ነበርና መከላከያ ይሆነኛል ብሎ ሠይፍ ደብቆ ይዞ ነበር፡፡ የሮም ጭፍሮችም ጌታችንን ለመያዝ ሲጠጉ የሊቀ ካህናቱን ባርያ (ማልኰስን) በሰይፍ ጆሮውን ቆረጠው፡፡ ዮሐ 18፡10፡፡ ጌታችን ግን ሞቱ በፍቃዱ ለድኅነተ ዓለም ነውና «ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ›› ሲል ገሠጸው፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስ የሚታወቅበት ሌላው ትልቁ ነገር ንስሓው ነው፡፡ ጌታችን በአይሁድ እጅ ከተያዘ በኋላ ጌታው አስቀድሞ ‹‹ትክደኛለህ›› ብሎ የነገረው መድረሱንና አምላኩን በመካድ መበደሉን እንዳወቀ ከግቢው ወጥቶ ተንሰቅስቆ አለቀሰ፡፡ በፍጹም ንስሓም ተመለሰ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በዕድሜው ታላቅነት በሐዋርያት ዘንድ እንደ አባት ይታይ ስለነበር ጌታችን ከተሰቀለ በኋላ ሐዋርያቱን ሊመግብ ወደሚያውቀው ሙያ ዓሳ ወደ ማስገሩ ተሠማራ፡፡ ጌታችንም አስቀድሞ የመረጠው እርሱ ነውና ቢክደው እንኳን በንስሐ በመመለሱ ንስሐውን መቀበሉን ዛሬም እንደሚወደው ይገልጽለት ዘንድ ዓሣ በሚያጠምድበት በጥብርያዶስ ባሕር ተገለጠለት፡፡ ሦስት ጊዜ ክዶት ነበርና ቀኖና ሰጠው፡፡ አሁን ቅዱስ ጴጥሮስ በራስ መተማመኑ እንዳላዋጣው ዐውቆአልና «ትወደኛለህን?» ተብሎ ሲጠየቅ «አንተ ታውቃለህ» ነበረ መልሱ፡፡ የራሱ ዕውቀት የት እንዳደረሰው ያውቃልና ጌታችንም በቀልን የሚተው ነውና ዛሬም እንደሚወደው በንስሓ ተመልሷልና ዛሬም ለእርሱ የሰጠውን ክብር እንደማያጐድልበት ሲነግረው (ግልገሎቼን አሰማራ፣ ጠቦቶቼን ጠብቅ፣ በጐቼን አሰማራ» በማለት ምእመናንን ልጆቹን በአደራ አስረከበው፡፡ ዮሐ 21፡15-17፡፡ ከዚያም በሞቱ እንዴት አድርጐ እግዚአብሔርን እንደሚያከብረው ነግሮት ወደ ሰማያት ዐረገ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በይሁዳ ምትክ ሌላ ሐዋርያ እንዲመረጥ ሐሳብ ያቀረበ እርሱ ነበር። የሐዋ 1፡16-23፡፡ በበዓለ ሃምሳም ለደቀመዛሙርቱ መንፈስ ቅዱስ በወረደላቸው ጊዜ ለተሰበሰቡት አይሁድ አፈ ጉባዔ ሆኖ ወንጌልን የሰበከ በአንዲት ዕለት ሦስት ሺህ ምእመናንንም አሳምኖ የመጀመሪያዋን አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በኢየሩሳሌም የመሠረተ እርሱ ነው፡፡ የሐዋ 2፡14-37፡፡ አስቀድሞ ፈሪ የነበረውና በሊቀ ካህናት ቀያፋ ግቢ ጌታውን የካደው ቅዱስ ጴጥሮስ የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ካገኘ በኋላ ግን በአይሁድ ሸንጐ ድውይ ፈወስክ ተብሎ በተከሰሰ ጊዜ በድፍረት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ መሰከረ፡፡ የሐዋ 4፡1-22፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ቆርነሌዎስን በማጥመቅ ወንጌልን ለአሕዛብ አስቀድሞ የሰበከው ሐዋርያ ነው። የሐዋ 10፡1-11፡፡
ሐዋርያው ልዑል እግዚአብሔር ባደለው ጸጋ ጥላው እንኳን ድውያንን ይፈውስ ነበር፡፡ የሐዋ 5፡15፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 15 ላይ እንደተጠቀሰው በ50 ዓ.ም አካባቢ በኢየሩሳሌም በተደረገው የሐዋርያት ሲኖዶስ ከአንጾኪያ ክርስቲያኖች ለቀረበው ጥያቄ የመጀመሪያውን መልስ የሰጠው እርሱ ነበር፡፡ ስለ ቅዱስ ጴጥሮስ መልክና ቁመና ጥንታዊያን መዛግብት እንደሚከተለው ያቀርቡታል። «ፊቱ ሰፋ ያለ ሲሆን ሪዛምና መካከለኛ ቁመት የነበረው ራሰ በራ ነው።
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ አባት ይታይ ስለነበረ ታዴዎስን ወደ ሀገረ ስብከቱ ለማድረስ አብሮት ተጕዞ ነበር፡፡ ወደ ከተማዋ ሲጠጉም አንድ የሚያርሱ ሽማግሌ አገኙ፡፡ ሐዋርያቱ ወደ ሽማግሌው ጠጋ ብለው የእግዚአብሔር ሰላምታ ሰጧቸው፡፡ የሚበላ ነገር ያላቸው እንደሆነም ጠየቋቸው፡፡ ሽማግሌው ገበሬም ደግ ነበሩና ‹‹ከቤት እስካመጣላችሁ ድረስ በሬዎቼን ጠብቁልኝ›› ብለው ወደ መንደር ገቡ፡፡ ሐዋርያቱም ‹‹የተጠመዱትን በሬዎች ተቀምጦ መመልከት ሐፍረት ነው›› አሉና ታዴዎስ ማረስ ጀመረ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም የስንዴውን ዘር አነሣ፡፡ ‹‹ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! በረከትህ በዚህ እርሻ ላይ ትውረድ›› ብሎ ጸለየ፡፡ ታዴዎስም ‹‹የምድር በረከት በዚች እርሻ ይታይ ዘንድ አምላኬ ሆይ ፈቃድህ ይሁን›› አለ፡፡ 30 ትልም አረሱና የስንዴውን ቡቃያ ዕለቱን ወዲያው አበቀሉት፡፡ ወዲያውም ዕለቱን ዐይንን የሚማርክ የስንዴ እሸት ሆኖ ታየ፡፡ አረጋዊው ገበሬ ሲመለስ የእርሻውን መለምለም ተመልክቶ አደነቀና ‹‹ጌቶቼ እናንተ እነማን ናችሁ? በእውነት እናንተ ከሰማይ የወረዳችሁ አማልክት ናችሁ›› ብሎ በእግራቸው ሥር ወደቀ፡፡ ሐዋርያቱ ግን ‹‹እኛ የአምላክ ባሪያዎች እንጂ አማልክት አይደለንም›› ብለው የመጡበትን ምክንያት ነግረውት ወንጌልን አስተማሩት፡፡ ገበሬውም እየተደነቁ እሸቱን ታቅፈው ለቤተሰባቸው ሊያሳዩ ወደ ቤታቸው ሮጡ፡፡ የከተማዋ ሰዎችም ነገሩ ገርሟቸው ከበቧቸው፡፡ ሽማግሌው ገበሬም ያዩትንና የሰሙትን ሁሉ ተረኩላቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በማናቸውም ነገር ፈጣንና ቀልጣፋ ነበር፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ መሠረት ቅዱስ ጴጥሮስ በፍልስጤም፣ በሶርያ፣ በጳንጦን፣ በገላትያ፣ በቀጰዶቅያ፣ በቢታንያ እና በሮሜ ወንጌልን ሰብኳል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በሮሜ አንድ ዓመት ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ካስተማረ በኋላ የሮሜ ክርስቲያኖች እየበዙ ከመምጣታቸውም በላይ የክርስትናው ጉዞ እስከ ሮማ ባለሥልጣናት ደረሰ፡፡ በትምህርቱና በተአምራቱ ካመኑት መካከል የሮማ ንጉሥ ባለሟልና የቅርብ ወዳጅ የሆነው አልታብዮስ ሚስቱ ክርስቲያን በመሆኗ በታላቅ ሀዘን ተለያዩ፡፡ በርካታ ሴቶችም አብረዋት ወደ ክርስትናው ዓለም ገቡ፡፡ የኔሮን የቅርብ ባለሥልጣናት የሆኑት የአልቢኖስና የአግሪጳ ሚስቶች ወደ ክርስትናው ገቡ፡፡ በዚህን ጊዜ ኔሮን ንጉሠ ሮማ በቅንዓት ተነሣባቸው፡፡ ኔሮን በሮም የነገሠው በ54 ዓ.ም ነው፡፡ በመንግሥቱ መጀመሪያ ደግ ሰው ነበረ፡፡ ነገር ግን በነገሠ በዓመቱ የጨካኝነት ዐመሉ ብቅ ማለት ጀመረና የአባቱን ልጅ አስገደለ፡፡ በ59 ዓ.ም ደግሞ እናቱን በመርዝ ገደለ፡፡ በ63 ዓ.ም እያስተማረ ያሳደገውን መምህሩን፣ በ62 ዓ.ም የልጅነት ሚስቱን አግታሺያን አስገደለ፡፡ ከእርሷም በኋላ ያገባትን ሚስቱን ፓፒያንም እንዲሁ ገደላት፡፡ ኔሮን በ64 ዓ.ም እርሱ ከከተማው ወጣ ብሎ በሚገኘው ቤተ መንግሥቱ ተቀምጦ የሮማን ከተማ እሳት ለቀቀባትና የሮም ሕዝብ በደረሰው አደጋ እጅግ መቆጣቱን ሲመለከት በክርስቲያኖች አመካኘ፡፡ በዚህም የተነሣ በሮማ ከተማ ሁለት ዓይነት ወሬ መናፈስ ጀመረ፡፡ ‹‹የሮማ አማልክት በክርስቲያኖች ሃይማኖት ስለተቆጡ በከተማዋ እሳት አዘነቡባት›› የሚለው የመጀመሪያው ሲሆን ‹‹ክርስቲያኖች ሆን ብለው ከተማዋን አቃጥለዋታል›› የሚለው ደግሞ ሁለተኛው ወሬ ነበር፡፡
የከተማው መጋየት ያበሳጨው የሮማ ሕዝብ፣ ክርስቲያን የሆነውን ሁሉ እያወጣ መግደሉን ተያያዘው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ሰዓት በእሥር ቤት ነበርና ተሰይፎ ዐረፈ፡፡ ይህን የሰሙት የአግቢኖስና የአግሪጳ ሚስቶች እነዚህም የሮም ባለሟሎች ነበሩና እነርሱም «ባይሆን አንተ ትረፍልን» ብለው ቅዱስ ጴጥሮስን በከተማዋ ግንብ በገመድ አሥረው በቅርጫት በማውረድ ቅጽረ ሮማን ለቅቆ እንዲወጣ አደረጉት፡፡ ሐዋርያው እንዳይታወቅ ራሱን ሰውሮ በኦፒየም ጎዳና ጉዞውን ቀጠለ፡፡ ሮማን ለቆ እያዘገመ በሸመገለ ጉልበቱ ሲጓዝ አንድ ቀይ ጐልማሳ መስቀል ተሸክሞ ወደ እርሱ ሲመጣ አየ፡፡ እየቀረበ ሲመጣ ግን ጌታችን መሆኑን ተረዳ፡፡ ወዲያው በፊቱ ተደፋና «ጌታዬ ወዴት እየተጓዝክ ነው?» ብሎ ጠየቀው፡፡ ጌታችንም ‹‹ልሰቀል ወደ ሮም ከተማ እሄዳለሁ›› አለው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ‹‹ዳግመኛ ትሰቀላለህን?›› አለው፡፡ አስቀድሞ በምን ዓይነት ሞት ይሞት ዘንድ እንዳለው ሲነግረው ‹‹አንተ ጎልማሳ ሳለህ ወገብህን በገዛ ራስህ ታጥቀህ ወደ ምትወደው ትሄድ ነበር፤ ነገር ግን በሸመገልህ ጊዜ እጆችህን ትዘረጋለህ፣ ሌላውም ያስታጥቅሃል፣ ወደማትወደውም ይወስድሃል›› ያለውን አስታውሶ እጅግ አዝኖ ወደ ሮም ከተማ ተመልሰ፡፡ የኔሮን ወታደሮችም እየፈለጉት ነበርና «እነሆኝ ስቀሉኝ» አላቸው፡፡ ያን ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስን ይዘው አሠሩት፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላም ሮማውያን የመስቀያውን እንጨት ሲያቀርቡ ተመልክቶ ‹‹እኔ እንደጌታዬ ልሰቀል አይገባኝም እንደ ጌታዬ ሳይሆን ቁልቁል ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ›› ብሎ ለመናቸው፡፡ እነርሱም ፈቃዱን ፈጽመውለት ሐምሌ 5 ቀን 67 ዓ.ም ዘቅዝቀው ሰቅለውታል፡፡ የሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን።
ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ሁልተኛ እትም ገፅ 521 እና 527፤ከገድላት አንደበት

07/07/2022

ወር በገባ 1 የሐዋርያዊ የቅዱስ በርተሎሜዎስ ወርኀዊ ብአሉ ነወ

>>ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ> ወንጌል ላይ እንደ ተጠቀሰው ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ በርተሎሜዎስ ነው። {ማቴ. ፲÷፫} ነገር ግን ዜና ሕይወቱ በስፋት ሲተረክ አንሰማም ቅዱሱ ሐዋርያ እንደ ሌሎቹ ወንድሞቹ ዓለምን በወንጌል ትምሕርት አብርቷል።

>> በትውፊት ትምሕርት መሠረት "በርተሎሜዎስ" የሚለውን ስም ያወጣለት ጌታችን ሲሆን ትርጉሙም 'ተክሎችን የሚያጠጣ' ማለት ነው።

>> ከሐዋርያትም ጌታ አስቀድሞ የስም ቅያሪ ያደረገለት ለእርሱ እንደ ሆነ ይታመናል። በርተሎሜዎስ የግብርና ሥራውን ትቶ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ሆኖ ከዋለበት እየዋለ ካደረበትም እያደረ ምሥጢረ ወንጌልን ተምሯል።

>> ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበለ በኋላም ከሐዋርያት ጋር ዓለምን በዕጣ ተካፍሏል ሃገረ ስብከቱም 'እልዋህ' እና 'አርማንያ' ናቸው የአርማንያ መንበርም የእርሱ ነው:: ቅዱሱ ገድሉ እንደሚለው አሕዛብን በስብከቱና በሚያስደነግጡ ተአምራቱ አሳምኗል::

>> ከቅዱስ ዼጥሮስ ከቅዱስ እንድርያስ ከክርስቶፎሮስና ከሌሎቹም ሰባክያን ጋር ዓለምን ዙሯል። ሙታንን አስነስቶ ድውያንን ፈውሶ አጋንንትን አውጥቶ ብዙወችን ወደ ሕይወት መልሷል። የደረቁ እንጨቶችም በእጁ ላይ እንዳሉ ለምልመው አብበው ያፈሩ ነበር።

>> ቅዱስ በርተሎሜዎስ እያስተማረ ወደ ኢትዮዽያም ደርሶ እንደ ነበር ይነገራል በመጨረሻም 'ለሚስቶቻችን ንጽሕናን አስተምረሃል' በሚል ተከሶ ንጉሥ አግሪዻ በሰቅ (ጸጉር) ጠቅልሎ አሸዋ ሞልቶ ባሕር ውስጥ ጥሎታል። በዚያውም ዐርፏል።

ቸሩ አምላካችን ከቅዱሳኑ በረከት ያሳትፈን እኛንም በፀሎታቸው አስቦ ይማረን አሜን

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address


Addis Ababa