New Paradigm Academy - ኒው ፓራዳየም አካዳሚ
A place where your children will have the complete freedom to be what they aspire to be with love
30/06/2024
💕ልጆቻችን እርስ በእርስ እንዲዋደዱ ፣ መቀናናት እንዳይፈጠር ካገዛቸው ነገር አንዱ እርስ በእርስ የሚያወዳድራቸው ሲስተም የማንከተል መሆናችን እና ሁሉንም ልጆቻችንን በአንድ አይን መመልከታችን ነው። በልጆች መሀል ግጭቶች ተፈጥሯዊ ቢሆኑም እርስ በእርስ የሚኖራቸውን ፍቅር ግን አይቀንሰው።
ከሌሎች ልጆች በተለየ መልኩ ትኩረት የሚሰጠው ልጅ የለንም። ሁሉም ልጆቻችን የእኛ ሙሉ ትኩረት ይፈልጋሉ። ልጆች በተፈጥሮ ፍቅር ናቸው። ቅናት ፣ የበላይነትን ወይም የበታችነትን ፣ አንዱን አቅርቦ ሌላውን ማግለልን የምናስተምራቸው እኛ "አዋቂዎች" ነን። ጥሎ ለማለፍ የሚደረግ ፉክክር ጓደኝነትን ያበላሻል፣ የቅናት ስሜት ይፈጥራል፣ ደስተኝነትን ያርቃል፣ በሌሎች ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት ከጓደኞቻቸው መብለጥ እንዳለባቸው ይሰማቸዋል። ይህ ደግሞ ጤናማ የሆነ ማህበራዊ ክህሎት እንዳያዳብሩ ያደርጋቸዋል። ልጆቻችንን በዋናነት ማስተማር ያለብን ሰዎችን በማንነታቸው መቀበልን ፣ ሀዘኔታን ፣ መልካምነትን ፣ ራሳቸውንም ሰውንም ማክበር፣ የመሳሰሉትን ማህበራዊ ክህሎቶችን እንጂ የበላይነትን ወይንም ጥሎ ማለፍን አይደለም። ይህን ደግሞ በምክር ብቻ ሳይሆን እኛም ሆነን በማሳየት ነው ። እኛ ሌሎች ሰዎችን እያመናጨቅን ፣ እየሰደብን ፣ ክብራቸውን የሚነካ ነገሮች እያደረግን ልጆቻችንን መልካምነት ልናስተምር አንችልም።
12/05/2024
💕💕እናትነት የእውነተኛ ፍቅር መገለጫ ነው
እናትነት ከራስ በላይ መሆን ፣ መስዋትነት፣ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረት ፣ መጨረሻ የሌለው ጥልቅ የፍቅር ስሜት ፣ የጥንካሬነት ፣ የደግነት ፣ የትዕግስት … መገለጫ ነው።
በብዙ መስዋትነት ልጆቻችሁን ለምታሳድጉ መልካም እናቶች ሁሉ መልካም የእናቶች ቀን እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።💕💕
💕የልጆች አፍ አለመፍታት ሊያሳስበን የሚገባው መቼ ነው❓
👉በቅርብ ጊዜ ቤተሰቦች በተመሳሳይ እያጋጠሟቸው ካሉ ጭንቀቶች ውስጥ አንዱ የልጆች በሚጠበቀው ዕድሜ አፍ አለመፍታት ነው። በርግጥ አያሳስብም የሚባል ጉዳይ አይደለም ። ነገር ግን ማገናዘብ ያሉብን የተወሰኑ ነገሮችን ለማለት እወዳለሁ።
👉ልጆች ከተወለዱ ከ 6 ወር ጀምሮ ለቋንቋ ልምምድ የሚመስሉ ድምፆችን ማውጣት ይጀምራሉ ፣ አንድ አመት ሲሞላቸው ደግሞ በተወሰነ ደረጃ ትርጉም ሊሰጡ የሚችሉ ቃላቶችን መናገር ይጀምራሉ። ከዛም የቋንቋ ዕድገቱ ፈጣን ለውጥ እያሳየ ይመጣል።
👉ይህ የቋንቋ ዕድገት ከልጅ ልጅ ይለያያል።ቀድሞ አፍ መፍታት ወይንም ከዚህ እድሜ ዘግይቶ አፍ መፍታት ምንም ማለት ላይሆን ይችላል።
👉አፍ መፍታት አሳሳቢ ሊሆን የሚችለው መቼ ነው?
ልጆች 3 አመት ሲሞላቸው ምንም ቃል የማያወጡ ከሆነ ወይም በእድሜያቸው ማሳየት የሚጠበቅባቸውን የቋንቋ እድገት ካላሳዩ ትኩረት መስጠት ይኖርብናል። ምንም አይነት ቃል የማያወጡ (non - verbal) ከሆኑ የኦቲዝም ምልክት ሊሆን ስለሚችል በፍጥነት ባለሞያ ጋር መውሰድ ያስፈልጋል። ይህ ሊረጋገጥ የሚችለው በባለሞያ ብቻ ነው። ምክንያቱም ከእዚህ ዕድሜ ዘግይተወም አፍ ሊፈቱ ስለሚችሉ። ነገር ግን ችላ ማለት የለብንም። በሰዓቱ መፍትሄ ከተገኘለት በፍጥነት ለውጥ ሊመጣ ስለሚችል።
👉ይህ ተፈጥሯዊ ሂደቱ ላይ ያተኮረ ሲሆን ከዚህ ውጪ ልጆች በጨቅላ ዕድሜያቸው ከስክሪን ጋር ቁርኝት ሲኖራቸው፣ ከእኩዮቻቸው ጋር አብረው የማይውሉበት ሁኔታ ሲፈጠር የአፍ መፍታት እድገቱን ሊያዘገየው እንደሚችልም መዘንጋት የለብንም።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the school
Website
Address
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 07:30 - 17:00 |
| Tuesday | 07:30 - 17:00 |
| Wednesday | 07:30 - 17:00 |
| Thursday | 07:30 - 17:00 |
| Friday | 07:30 - 17:00 |
19/08/2025