14/10/2023
Enjoy!
PBTAfrica College is an Accredited & Licensed Higher Education and Research & Consultancy company located in Addis Ababa,.
It is established by academicians & researchers aspiring to share their knowledge and skill to the Nation & the Continent at large.
14/10/2023
Enjoy!
14/10/2023
Congratulations
14/10/2023
Congratulations!
14/10/2023
PBTAfrica Cup winner 2023 and Gold Medalist from the Project Management Department! Engineer Merhatinsae... Congratulations!
14/10/2023
Academic staff with guests... Graduation 2023!
14/10/2023
Graduation 2023! Wishing you nothing but the best as you embark on this new journey!
14/10/2023
With us, , Chief Executive Officer for Academic Affairs, FDRE .
Buckle up, enjoy the ride and laugh a lot... Life is about to unfold for you in all its forms!
Congratulations!
14/10/2023
Congratulations! Graduation 2023. Enjoy your special day!
14/10/2023
Here at PBTAfrica, it is time for graduation. Officials are facing toward the sunshine. They are ready to turn mirrors into windows.
04/10/2023
የፕሮዤው ዕድል-ፈንታ፤
(ከአዲስ አበባ ጅማ በአንድ ሰዓት!)
==================
እንግሊዝ ጠንካራ ሀገር ነው፡፡ አንዱ ማሳያ ደግሞ ፓርላማውና ፓርቲዎቹ ያላቸው ግልፅና ንቁ የCheck and balance ሥርዓታቸው ነው፡፡ የፕሮጀክት ሥራ አመራር ስኬትን ከሚወስኑ ጉዳዮች ደግሞ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ከባቢ ጉዳዮች ዋነኛዎቹ ናቸው፡፡ እና ዛሬ የUK ጠቅላይ (ሪሺ ሱናክ) አንድ ፈተና ገጥሟቸዋል፡፡ እጅግ ጠቃሚ ተብሎ የታለመውና የተጀመረው ፕሮዤ “ካልተቋረጠ” መባላቸው ሲሆን እሳቸውም “ኧረ በሕግ!” እያሉ እየወተወቱ ይገኛሉ፡፡
Project High Speed 2 (HS2)
ፕሮዤው ለንደን ከተማን ከሌሎች ትልልቅ የእንግሊዝ ከተሞች የሚያገናኝ እጅግ ዘመናዊና ፈጣን የባቡር መስመር ግንባታ ነው፡፡ በመጀመሪያው ምዕራፍ ለንደን ከተማን ከበርኒንግሃም ሲያገናኝ በምዕራፍ ሁለት ደግሞ በርኒንግሃም ከተማን በሁለት መስመር ከማንቸስትርና ከሊድስ ከተሞች ጋር የሚያስተሳስር፤ 26 ሺህ ሰዎችን አሳፍሮ በሰዓት 400 ኪ.ሜ. የሚከንፍ ቅንጡና ፈጣን የባቡር መስመር ነው… ከአዲስ አበባ ጅማ በአንድ ሰዓት!
ፕሮዤው ከ2017-2026 የታለመ የአስር ዓመት ውጥን ሲሆን በየደረጃው አገልግሎት እየሰጠ እንዲዘልቅ የተዘጋጀ፤ ከ100 ቢልየን ፓውንድ በላይ የሚፈጅ ሜጋ ፕሮጀክት ነው፡፡ ይህ እንግዲህ በባሕር ሥር ከተዘረጋውና የአውሮፓ ምድርን ከእንግሊዝ ከሚያገናኘው ከቻነል ፕሮዤ (High Speed 1፡ Channel Tunnel) ቀጥሎ የታሰበና በሀገሪቱ መንግሥት በ2009 የታቀደ የእንግሊዝ ትልቁ የቴክኖሎጂ ፕሮጀክት ነው፡፡
ከሕንድ የዘር ሐረግ የሚመዘዙት ጠ/ሚ ሱናክ የመጀመሪያው እሲያዊ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሲሆኑ ቤተሰቡ በ1960ዎቹ በምስራቅ አፍሪቃ ዞረው ወደ እንግሊዝ ምድር የገቡ ስደተኞች እንደሆኑ ይነገራል፡፡ ፖለቲካን፣ ፊሎሶፊንና ምጣኔ ሀብትን ጥንቅቅ አድርገው እዚያው እንግሊዝ ሀገር የተማሩት ሱናክ፣ እንግሊዝ በመሪ እጦት ስትቸገር ብቅ ያሉ አስተዋይ መሪ ናቸው፡፡ በሀብትም ቢሆን የናጠጡ ቱጃር!
ታዲያ ዛሬ ላይ ከዚህ በፊት ይመሩት የነበረው የወግ አጥባቂው ፓርቲያቸው /Conservative Party/ “በፕሮጀክቱ ዙሪያ ማብራሪያ ካልሰጠኸን የምዕራፍ ሁለት ግንባታ ይቋረጣል” እያሉት ይገኛሉ፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያታቸው የኦዲት ሪፖርት ሲሆን ፕሮዤው “ከተቀመጠለት በጀት እጅግ የበዛ ወጪ እያስወጣ ከመሆኑም በላይ እጅግ ተጓቷል” የሚል ሲሆን “ፕሮዤው በመቆሙ ብቻ ከ34 ቢሊየን ፓውንድ በላይ ማትረፍ ይቻላል” ባይ ናቸው፡፡ ሱናክ ይህንን ንትርክ ፈር የሚያስይዝ ዕቅድ ይዘው ለፓርቲያቸው ገለፃ ሊያድርጉ ዛሬ ቀጠሮ ተይዞላቸዋል፡፡
እንግሊዝ ሀገር ከዚህ ቀደም ባሉ ዓመታት በHeathrow ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የማስፋፊያ ፕሮዤ ምክንያት ሊከሰት በሚችል የድምፅ ብክለት/Sound Pollution/ ዙሪያ ጠንከር ያለ ክርክርና ሙግት እንዲሁም የፕሮጀክት መስተጓጎል ሲደረግ እንደነበረ የሚታወስ ነው፡፡
ፒቢቲአፍሪካ ኮሌጅ እኝንና የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ፕሮጀክቶችን በመተንተን ለተማሪዎቹ ዓለም አቀፍ ዕውቀት የሚያስጨብጥ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ትምህርት ትክክለኛ ምርጫ ነው!!
Postgraduate College of Project, Business and Technology!
Go global: Global Standards in Project Management!
26/09/2023
Wishing you a Joyful Demera and Meskel Holiday!
=======
ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የፒቢቲአፍሪካ ቤተሰቦች፤
እንኳን ለደመራና ለብርሃነ መስቀሉ በሠላም አደረስዎ!
Happy Demera & Meskel 2023!
PBTAfrica College - Postgraduate College of Project, Business and Technology!