Civil engineer's work

Civil engineer's work

Share

�Construction document
�software class
let's Safe & Develop the construction Industry!

#share

13/06/2025

ካዳስተር ማለት ምን ማለት ነው?
*********
ካዳስተር ማለት የመሬት ይዞታን መሰረት ያደረገ የመሬት መረጃ ሥርዓት ሲሆን የሚደራጁት መረጃዎችም በዋናነት ሁለት ዓይነት ናቸው፡፡ ይኸውም የካርታ መረጃ (spatial data) የይዞታውን መገኛ ቦታ፣ ወሰኑን፣ ስፋቱንና ቅርፁን፣ አጎራባች ይዞታዎችን እና አዋሳኝ መንገዶችን የሚያሳይ ሲሆን ሌላኛው ገላጭ መረጃ (non-spatial data) በመባል የሚታወቀው የባለይዞታውን ማንነት (ስም፣ አድራሻ፣ ጾታ፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ ወዘተ.)፣ በይዞታው ላይ ያለው መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት፣ የቦታው አገልግሎትና ደረጃ፣ ወዘተ… እንደ ካዳስተር ዓይነቱ ተዘርዝረው የሚያዙ መረጃዎችን ያካትታል፡፡ እነዚህ ሁለት የመረጃ ዓይነቶችም በልዩ የይዞታ መለያ ኮድ እንዲገናኙ ይደረጋል፡፡

ካዳስተር በሦስት ዓይነት ይከፈላል፡-
>አንደኛው ህጋዊ ካዳስተር ሲሆን ለእያንዳንዱ ህጋዊ ወሰን ለተለየለት ይዞታ፣ የይዞታ መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት የሚያመለክት መረጃ ከይዞታው ካርታ ጋር አጣምሮ የያዘ ወቅታዊ የመሬት ይዞታ መረጃ ሥርዓት ሲሆን አስፈላጊነቱም የትኛው ይዞታ በማንና በምን አግባብ ተይዟል የሚለውን በማጣራት የባለይዞታውን የይዞታ ዋስትና ለማረጋገጥ ነው፡፡
>ሁለተኛው ዓይነት ፊስካል ካዳስተር ሲሆን በይዞታው ላይ ስላረፈው ቋሚ ንብረት ዝርዝር መረጃ እና የመሬቱን ወቅታዊ ግምት ከይዞታው ካርታ ጋር የሚይዝ ሆኖ ለቦታና ለንብረት ግብር ክፍያ የሚያገለግል ሥርዓት ነው፡፡
> ሦስተኛው ዓይነት ካዳስተር ሁለገብ/ሁሉን አቀፍ ካዳስተር/ የሚባለው በሁለቱ የካዳስተር ዓይነቶች የተገለፁትን መረጃዎች የሚይዝ ሆኖ በተጨማሪም የመሰረተ ልማት፣ የአካባቢ ጥበቃ እና ሌሎች መረጃዎችን እና ካርታን አካቶ የሚይዝ የመረጃ ሥርዓት ነው፡፡

የካዳስተር ሥርዓት በመገንባት ሂደት በርካታ ልምድ ያላቸውና ብዙ ርቀት የሄዱ አገሮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በዚህ የግንባታ ሂደት እያንዳንዱ አገር ከራሱ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር አጀማመሩና አካሄዱ የተለያየ ነው፡፡ አንዳንድ ሀገሮች ከፊስካል ካዳስተር ጀምረው ወደ ሁለገብ የሄዱ አሉ ለምሳሌ ፈረንሳይ፤ ሌሎች ደግሞ ከህጋዊ ካዳስተር ጀምረው ወደ ሁለገብ የካዳስተር ሥርዓት የተሸጋገሩበት ሁኔታም አለ ለምሳሌ ኔዘርላንድ፡፡ በእኛ አገር ደረጃም ከዚህ ቀደም በከተማ ደረጃ ሥርዓቱን ለመዘርጋት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ የተሞከሩትም ሁለገብ ካዳስተርን በመዘርጋት ነበር ሆኖም ግን የሚፈለገውን ውጤት ሊያመጣና የሥርዓቱን ዘለቄታዊነት የሚያረጋግጥ ሊሆን አልቻለም፡፡

በመሆኑም በቅድሚያ ባለይዞታውን ተጠቃሚ የሚያደርገው ከተማ አስተዳደሮችም መሬታቸውን ቆጥረው ሊያውቁ የሚችሉበትን የህጋዊ ካዳስተር በመዘርጋት በመቀጠልም የፊስካል ካዳስተር ብሎም ወደ ሁለገብ ካዳስተር የሚያድግ ሥርዓት መዘርጋቱ ሥርዓቱን ቀጣይ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ ተመርጧል፡፡ በዚህ ሂደት የካርታው መረጃ አንድ ጊዜ የሚዘጋጅ ሲሆን ለውጥን ተከትሎ ወቅታዊ ማድረግ የሚያስፈልግ ሆኖ ሁሉም የካዳስተር ዓይነት መሰረት የሚያደርገው በህጋዊ ካዳስተር የተዘጋጀውን የካዳስተር ካርታ ነው:: ሌሎች መረጃዎች ተደማሪ እየተደረጉ ወደ ሁለገብ ካዳስተር ሥርዓት የሚያድግ ይሆናል፡፡

የህጋዊ ካዳስተር ዝርጋታ ተግባራዊ መሆን የሚያስገኛቸው ፋይዳዎች

*******
✍️በአገር ደረጃ በአገልግሎት አሰጣጥ የሚስተዋለውን የተወሳሰበ ችግር ይህ የአሰራር ስርአት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ በሚሆንበት ወቅት ይሄን ችግር በመሰረታዊነት እንደሚፈታ ይታመናል፤
✍️በዘርፉ የግብይት ስርአቱን ቀላል፣ ግልፅ፣ ተደራሽ በማድረግ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ከማድረጉ ባሻገር በአገር ኢኮኖሚ እድገቱ ላይ የራሱን አውንታዊ ሚና መጫወት ይችላል፤
✍️በዘርፉ በመረጃ አያያዝ ጉድለት የነበረውን ችግር ተጠቅመው ጥቂቶች አላግባብ የሚበለፅጉበትንና ህጋዊ ባለይዞታዎችን ለተለያዩ ጉዳቶች ይዳርግ የነበረውን የአሰራር ችግር ሊፈታ ይችላል ተብሎ ይታመናል፣
✍️ በክልልም ሆነ በፌደራል ደረጃ በዘመናዊ መንገድ የሚደራጀው የከተማ መሬት ይዞታ መረጃ አዳዲስ ፖሊሲዎችን፣ አሰራሮችንና ህጎችን ለማመንጨት የተሻለ ግብአት ሆኖ ያገለግላል፤
✍️ የከተማ አስተዳደሮች የሚያስተዳድሩትን መሬት ቆጥረው እንዲያውቁ፣ የትኛውን መሬት ለየትኛው አገልግሎት ማዋል እንዳለባቸው አቅደው እንዲሰሩና በተገቢው መንገድ እንዲያስተዳድሩ ከፍተኛ እገዛ ያደርግላቸዋል፤
✍️ከተሞች ከመሬት ሃብታቸው መሰብሰብ የሚገባቸውን ግብር እና ኪራይ በተገቢው መንገድ በመሰብሰብ ለለከተማው የመሰረተ-ልማት ግንባታ በማዋል ከተሞች በስርአቱ ያድጋሉ፣ የከተማው ነዋሪም የልማቱ ተጠቃሚ ይሆናል፤
✍️የካዳስተር ስርአቱ በሚፈጥረው የመረጃ ምልዑነት በከተማ መሬት ይዞታ የሚስተዋለውን በዜጎች መካከል የሚፈጠረውን ክርክር ይቀንሳል፣ በዚህ ምክንያት የሚያጠፋውን ገንዝብ፣ ጊዜ እና የፍትህ መጓደል ይቀንሳል፤
✍️ማንኛውም ዜጋ በከተማ መሬት ይዞታ ዘርፍ ማግኘት የሚፈልገውን መረጃ ብዙ ውጣውረድ ሳይገጥመው በቀላሉ እንዲያገኝ ያደርጋል፤
✍️በከተሞች ህጋዊ ካዳስተርን መገንባት ከተቻለ የውጭም ሆነ የአገር ውስጥ ባለሃብቶች እምነት ስለሚያሳድሩ ሃብታቸውን ልማት ላይ ያውላሉ በዚህም ነዋሪው ተጠቃሚ ይሆናል፣ ከተሞች ያድጋሉ፣ ሳቢም ይሆናሉ፤
✍️በዘርፉ ሙያ ለተሰማራው አመራርም ሆነ ባለሙያ የእውቀት ሽግግር እንዲፈጠር ያደርጋል፣ አቅምም ይገነባል፣ በዚህም በየደረጃው ተጠቃሚ እንዲሆን ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡
=====//=========

03/05/2025

✅በአሜሪካ ኬንቲኪ Grace Farms ውስጥ በወንዝ አምሳያ የተገነባው "River building" ጥልፍልፍ ሕንፃ በምህንድስና ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ያለው እንደሆነ የተመሠከረለት ነው‼️

https://t.me/engineer03

20/04/2025

✅ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል ይሁንላችሁ፣ ይሁንልን።

https://t.me/engineer03

19/04/2025

👉አዲሱ የኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ መመሪያ :: ሚያዚያ 2017. ዓ.ም.
full pdf on our telegram ➾➾➾➾
https://t.me/engineer03

22/12/2024
11/10/2024

Why ?

11/10/2024

የቻይና መሃንዲሶች ለትራንስፖርት ተስማሚ የሆነ የመንገድ መሠረተ ልማት ለመገንባት የሚያግዳቸው ተራራማ፣ ኮረብታማ እና ጎበርባጣ መልከዓ ምድር የለም ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል።

https://t.me/engineer03

27/02/2024

💥የቅየሳ መሳሪያ/Surveying Equipment/

⏩ቅየሳ/surveying/ በተፈጥሮ ሳይንስ የሚመደብ የስራ ሙያ ሲሆን ሁለት የተለያዪ መገኛዎችን ርቀት/distance/፣ ከፍታ
ልኬት/Elevation/ እና በሁለቱ መካከል የሚገኘውን ማዕዘን/ Angle/ ለማውጣት የምንጠቀምበት ዘዴ ነው።

➡ሁለት አይነት የቅየሳ መሳሪያ ይገኛሉ
1. ቴዶላይት/Thedolite/
2. ቶታል ስቴሽን/Total Station/

➡ቶታል ስቴሽን ጂፒስ፣ጨረር እና የከፍታ መለኪያ ሴንሰር በመጠቀም ትክክለኛ የከፍታ ልዪነት/Elevation difference እና ርቀትን ለመለካት ይጠቅመናል።

➡ቴዶላይት ደግሞ በሁለት ነጥቦች መካከል ያለውን የከፍታ ልዪነት ለመለካት ሲያገለግል በመካከላቸው ያለውን ርቀት ግን
መለካት አይችልም።

🚩ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።

https://t.me/engineer03

07/02/2024

🪡 Post tension

ከቃሉ ስንነሳ post - ድህረ ማለት ነው። concrete ከተሞላ በኋላ ብረቱን ስንወጥር post tension (ድህረ መወጠር) concrete ከመሞላቱ በፊት ደግሞ ሲወጠር pre-tension ይባላል። ዛሬ ስለ post tension እናውጋ!

Post tension እዛው መስክ(site) ላይ የምናከናውነው የግንባታ ዘዬ ነው pretension ግን በ precast ማምረቻ warehouseኦች ላይ ሚተገበር ነው።

በpost tension ጊዜ መጀመሪያ ብረት እናነጥፋለን(bottom bar) ኮለኖች አካባቢ lower reinforcement እናበጃለን ከዛም ኮለኖች አካባቢ punching shear reinforcement እናበጃለን (drop panel in exceptional case ካልሆነ አንጠቀምም) ከዛም chair bar (“ከበሌቶ”) ካረግን በኋላ strand እንዘረጋለን ከዛም በ side formwork በኩል መወጠሪያ ብረቶቻችንን ካወጣን በኋላ anchorage እና grout vent እንዘረጋለን ከዛም እናጠብቃቸዋለን ከዛም top reinforcement (minimum reinforcement ለ shrinkage እና ለ temperature) ከዛም ኮንክሪት መሙላት ከዛም ያወጣነውን ቴንደን መወጠር ከዛም የተመዘዘውን መጠን መለካት ( measuring elongation) ከዛም የወጡትን የ strand ጫፎች መለካት ከዛም ክፍተቱን (void) በሲሚንቶ (cement screed) መሙላት።

https://t.me/engineer03

Photos from Civil engineer's work's post 04/02/2024

💥በስምንት ሰዓት ውስጥ 47 ሺህ ብሎኬት የሚያመርት ፋብሪካ ሥራ ጀመረ

በዱከም ከተማ በአንድ ፈረቃ ወይም በስምንት ሰዓት ውስጥ ብቻ 47 ሺህ የተለያዩ መጠን ያላቸውን ብሎኬቶችን የሚያመርት ፋብሪካ ሥራ መጀመሩ ተሰማ።

ቢውልደርስ አፕ ኮንስትራክሽን ማቴሪያል ማኑፋክቸሪንግ ኃ/ተ/ግ/ማ በዱከም ከተማ ያቋቋመው ፋብሪካ በከፍተኛ ጥራት የሚያመርታቸውን የብሎኬት እና ቴራዞ ምርቶች ለገበያ ማቅረብ መጀመሩ ታውቋል።

የፋብሪካው ባለድርሻና ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ወንደሰን መንግሥቱ እንደገለጹት፣ ፋብሪካው 34 ሺህ ባለ (40*15*20 ሳ.ሜ)፣ እና 25 ሺህ ባለ (40*20*20 ሳ.ሜ)፣ ውፍረት/ስፋት ያላቸውን ብሎኬቶች የማምረት አቅም አለው፡፡

ቢውልደርስ አፕ ኮንስትራክሽን ማቴሪያል ማኑፋክቸሪንግ 99 በመቶ የአገር ውስጥ ጥሬ ዕቃ ዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂን
በመጠቀም ጥራት ያለው ምርት ማምረት የሚችል የግንባታ ግብአት አቅራቢ ፋብሪካ ነው።

የፋብሪካ ግምባታ እና ማሽን ተከላ 18 ወራትን ወራትን የፈጀ ሲሆን፣ ፋብሪካው ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ከ400 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ይወጣበታል ተብሏል።

እንደ ፕሮጀክት ማናጀሩ ገለጻ፣ ፍላጎትን መሠረት አድርገን በተጨማሪ ፈረቃ ምርት ማምረት እንችላለን ብለዋል።

በተመሳሳይ የቴራዞ ማምረቻው በተለያየ ሞልድ በቀን ከ 2500 ካ.ሜ በላይ የሚሸፍን ከፍተኛ ጭነት መቋቋም የሚችሉ የወለል ንጣፎችን ማምረት እንደሚችል ታውቋል።

ፋብሪካው ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ከ150 በላይ ዜጎች ቀጥተኛ የሥራ እድል እንደሚፈጥር ተገልጿል።

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Addis Ababa