የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር /Nazareth St. Joseph Alumni Association

  • Home
  • Ethiopia
  • Adama
  • የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር /Nazareth St. Joseph Alumni Association

የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association Nazareth St .Joseph School Alumni Association

ከልጅነት  እሰከ  እውቀት  በአብሮነት....በዓመታት የዕድሜ ጉዞ...በተለያየ የህይወት መስመር ተጉዛችሁ  ዛሬም ድረስ የጓደኝነት መሠረታችሁን ላለቀቃችሁ ሁሉ....HAPPY  FRIENDSHI...
31/07/2026

ከልጅነት እሰከ እውቀት በአብሮነት....በዓመታት የዕድሜ ጉዞ...በተለያየ የህይወት መስመር ተጉዛችሁ
ዛሬም ድረስ የጓደኝነት መሠረታችሁን ላለቀቃችሁ ሁሉ....
HAPPY FRIENDSHIP - DAY !!!

የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት የ1981 ዓ.ም  ባች ነች  እህት ላቀች አይናቸው ። በገጠማት የጤና እክል ለጥቂት ጊዜ በህክምና ብትቆይም  እንዳሰበችው ሣይሆን ከዚህ ዓለም ድካም አር...
20/07/2026

የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት የ1981 ዓ.ም ባች ነች እህት ላቀች አይናቸው ። በገጠማት የጤና እክል ለጥቂት ጊዜ በህክምና ብትቆይም እንዳሰበችው ሣይሆን ከዚህ ዓለም ድካም አርፋለች ። የእህታችን የላቀች አይናቸው የቀብር ስነስርዓት ስኞ ሐምሌ 13/2018 ዓ.ም ቤተሰቦቿ ፣ ወዳጅ ዘመድ ቀድሞ አብረዋት የተማሪ የቀድሞ ተማሪዎች የት/ቤት ጎደኞቿና የቀድሞ መምህራኖቿ በተገኙበት በናዝሬት ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያ በ9:00 ሰዓት ይፈፀማል። የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበርም ለቤተሰቦቿ፣ለወዳጅ ዘመድ አብረዋት ለተማሩ የቀድሞ ተማሪዎች ፣ ለቀድሞ መምህራኖቿ መፅናናት ለእህታችን ላቀች አይናቸው መልካም ዕረፍትን እንመኛለን ።
ነፍስሽ በሠላም ትረፍ !!!!

ለረጅም ዓመታት በቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ት/ቤት  አዳማ--ናዝሬት በመምህርነት ያገለገለው ..ቀደም ሲልም በዛው ቅዱስ ዮሴፍ  ..የተማሪነት ዘመኑን ያሣለፈው   መምህር አስራት ሀይሉ (አቡላ) ...
13/07/2026

ለረጅም ዓመታት በቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ት/ቤት አዳማ--ናዝሬት በመምህርነት ያገለገለው ..ቀደም ሲልም በዛው ቅዱስ ዮሴፍ ..የተማሪነት ዘመኑን ያሣለፈው መምህር አስራት ሀይሉ (አቡላ) ..በደረሰበት የጤና እክል ለረጅም ጊዜ በህክምና ክትትል ቢቆይም ....የተመኘው ሣይሆን ቀርቶ ስኞ ሀምሌ 06/2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፏል ። ማክስኞ ሀምሌ 07/2018 ዓ.ም ቤተሰቦቹ ፣ ወዳጅ ዘመድ፣ የሥራ ባልደረቦቹ ቀድሞ አብረውት የተማሩ ጓደኞቹ በተገኙበት ስርዓተ ቀብሩ ይፈፀማል።
ለመላው ቤተሰቡ መፅናናትን ለመምህር አስራት ሀይሉ መልካም ዕረፍትን እንመኛለን !!!

07/07/2026

አይ ሰኔ ሠላሣ ...አይ ሰኔ ሠላሣ
እንኳን የአፍላነቱ...የትናንት ተረሣ
ስንት አስበን ነበር...ስንት ተነጋግረን
ሰኔን መገናኘት...ዘንድሮ ቸገረን ......ለምን ይሆን ?......

CONGRATULATION !!
21/06/2026

CONGRATULATION !!

ስኞ ሚያዚያ 26/ 2018 ዓ.ም ..መልካም የቀን ገጠመኝ ነበር።  ኑሮዋን በእንግሊዝ ሀገር ያደረገችው የ1980  ዓ.ም ባች የቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ት/ቤት  አዳማ / ናዝሬት የቀድሞ ተማሪ ...
04/05/2026

ስኞ ሚያዚያ 26/ 2018 ዓ.ም ..መልካም የቀን ገጠመኝ ነበር። ኑሮዋን በእንግሊዝ ሀገር ያደረገችው የ1980 ዓ.ም ባች የቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ት/ቤት አዳማ / ናዝሬት የቀድሞ ተማሪ ስናይት ዘነበ ...ለአጭር ጊዜ ቆይታ ወደሀገር ቤት በመጣችበት አጋጣሚ ያላትን ጊዜ አጣባ የቀድሞ ት/ቤቷንና አብረዋት የተማሩ የቀድሞ ተማሪ ጓደኞቿን ጥቂትም ቢሆኑ ለማየትና የቀድሞ የተማሪነት ትዝታዎቿን ለማውጋት የነበራትን ጉጉት እውን ለማድረግ በዚህ መልኩ በሴንጆ ግቢ መልካም ቆይታ አድርጋለች ....ስለነበረን ጊዜ ስለመልካም ትሁት አሣብሽ የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር እያመሰገነ...የቀድሞ ተማሪዎች የቀድሞ ት/ቤታችሁን ፣ የቀድሞ መምህራኖቻችሁን እንዲሁም አብረዋችሁ የተማሩ የቀድሞ ተማሪ ጓደኞቻችሁን በተገኘው አጋጣሚ የማየት፣ የመጠየቅ እና የመጎብኘት ልማድ ይኑረን ለማለት እንወዳለን።

07/04/2026

እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ
ያ ሰውዬ ምንአለሽ ማታ
....የዛ ዘመንን የተማሪነት የልጅነት ጨዋታ
አለፍ ሲልም የወጣትነት...እስከአሁን የዘለቀ ትዝታ.......
ጊዜ ደጉ ....አሁን በAI ዘመን ደግም የብዙዎች የትዝታ ቋጠሮ የሆነው....እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ....ያ ሰውዬ ምንአለሽ ማታ............ይቀጥላል.........
መልካም የስቅለትና የትንሣኤ በዓል ይሁንልን...!!!

ዘመኑ  1978 ዓ.ም ነው ...የቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ት/ቤት  አዳማ / ናዝሬት  በንግድ ሥራ ትምህርት ካስመረቃቸው ባቶች ውሰጥ አንዷ ናት  ዘበናይ ፋንታዬ.....ኑሮዋን በአዲስ አበባ ኮተ...
06/02/2026

ዘመኑ 1978 ዓ.ም ነው ...የቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ት/ቤት አዳማ / ናዝሬት በንግድ ሥራ ትምህርት ካስመረቃቸው ባቶች ውሰጥ አንዷ ናት ዘበናይ ፋንታዬ.....ኑሮዋን በአዲስ አበባ ኮተቤ አካባቢ አድርጋ የነበረችውና ባለፈው የህይወት ዘመኗ የሁለት ልጆች እናት የነበረችው ዘበናይ በአጋጠማት የጤና ችግር ሀሙስ ጥር 28/2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም ያረፈች ሲሆን ጥር 29/2018 ዓ.ም ወዳጅ ዘመድ ቤተሰብ በተገኘበት በኮተቤ ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክርስቲያን የቀብር ሰነስርዓቷ ተፈፅሟል። የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር ለቀድሞ አብረዋት ለተማሩ ተማሪዎች፣ ላስተማሯት መምህራን ፣ ለጓደኞቿ፣ለወዳጅና ለመላው ቤተሰቦቿ መፅናናትን እንመኛለን ።
መልካም ዕረፍት !
ፈጣሪ ነፍስሸን በአፀደ ገነት ያኑርው !!

በ1977 ዓ.ም  በ25 ዓመቱ የቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ት/ቤት አዳማ/ናዝሬትን  በመምህርነት ተቀላቀለ..... ላለፉት አርባ አንድ ዓመታት በመምህርነት ሙያ በሴንጆ እያገለገለ ይገኛል...መምህር...
06/12/2025

በ1977 ዓ.ም በ25 ዓመቱ የቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ት/ቤት አዳማ/ናዝሬትን በመምህርነት ተቀላቀለ..... ላለፉት አርባ አንድ ዓመታት በመምህርነት ሙያ በሴንጆ እያገለገለ ይገኛል...መምህር ለማ ተሰማ ...ዛሬ ህዳር 27/2018 ዓ.ም ይህቺን ዓለም ከተቀላቀለ 66 ኛ ዓመት ሆነው ። እናም ....
እንኳን ተወለድክ መምህር
HAPPY BIRTHDAY TEACHER !!!

ወርቁ አበበበዘመናት ቃንቄ በህይወት ነበልባልነጥሮ እየወጣ ታሪኩ ያብባልመርሣት ያልጋረደው ዳናው ያልተፋቀበልጆቹ ልብ ውስጥ ዕውቀቱ የዘለቀምክሩ ከህሊና ተግሣፁ ከአይምሮየአባትነት ፍቅሩ ትውል...
06/11/2025

ወርቁ አበበ
በዘመናት ቃንቄ በህይወት ነበልባል
ነጥሮ እየወጣ ታሪኩ ያብባል
መርሣት ያልጋረደው ዳናው ያልተፋቀ
በልጆቹ ልብ ውስጥ ዕውቀቱ የዘለቀ
ምክሩ ከህሊና ተግሣፁ ከአይምሮ
የአባትነት ፍቅሩ ትውልድ አጠንክሮ
ነጥሮ እየወጣ በዘመኑ የስራው
የዘራው መልካም ዘር በክብር እያስጠራው
በዕውቀት ልጆቹ ሰርክ እየታወሰ
መርሣት ሳይጎበኘው እዚህ የደረሰ
እሱ ነው .....ሰውዬው
ወርቁ አበበ ሲባል..ነጥሮ ደምቆ የታየው .!!!
ጋሼ .......መምህሩ
ውለታህ አይረሣም.....!!!!

Address

Picoke--Aboseto-buluko, Abebe Bikila Street
Adama

Telephone

+251703841012

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር /Nazareth St. Joseph Alumni Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category