ንምዕባለ ትግራይ

ንምዕባለ ትግራይ

Share

ትግራይ ተኮር

Photos 27/10/2020

ይሄን ፅሁፍ ማንበብ 100 መፅሐፍት እንደማንበብ ነው
==================================
በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ፤ ሁሉንም ካላየሁ
አላምንም አትበል ። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ።
የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም ። ሰማንያ
ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ።
ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር
እወቀው ። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው ። ብልህ ከሆንህ በሰው
ከደረሰው ትማራለህ ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ።
የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው።
ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን ። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣
የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል ። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ
ምስጋና አታብዛ ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል ።
ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ ።
የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ ።
የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ
አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ
እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው ።
ክፋት አይሙቅህ ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ ። ለክፋት አቅም ካለህ
ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት ።
ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል
ብለህ አታስብ ። ላለው አትሩጥ ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ
ከአቅምህ አትነስ ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት
አትበደር ። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው ።
ለሀብታም አትሳቅ ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው
አትጥላ ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር ፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና ፣ ያየኽውን ሴት
ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን ፣
ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል ፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን ፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን
አታባክን ፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን ፣
ነገርህን በልክ ፣ ቃልህን በጣዕም ፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው ።
እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል ። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን
ጩኸት እሰማለሁ አትበል ። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ። ነገር
አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ። አንድ በጎ ዕውቀት
ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው ፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ ፣
አዋቂዎችን ጠይቅ ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ ።
ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን ፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ
ሆነህ አትቅደም ።
በዓላማ ኑር ፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ ።
ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ ።
የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤ የትላንቱንም አስብ ፤
አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ።
ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች
። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ።
ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ!
መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤
ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ በአበዳሪዎች
አንቀጽ አትካሰስ ፤ የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ
ነው ። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠላሃል ።
ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች
ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ
ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው።
ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ
መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ።
ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና
አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው ። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት
ተጠንቀቅ ።
ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት
ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና
ስታከብርላቸው ነው ።
ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ
ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ
ለምትዘራው ተጠንቀቅ ።
የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ
አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን
አላዋቂዎችን እርዳቸው !!
ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና
የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ
የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና
ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።
ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ።
ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ።
አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን
አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ
አትደለል።
እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው
እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም
የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ።
የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ
አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን
አላዋቂዎችን እርዳቸው ።
ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ
ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ
ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።
ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና
የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ
የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ።
ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።
ቂም አፍን የሚያመር ፣ ልብን የሚያነቅዝ ፣ ተግባርን የሚያልፈሰፍስ ነውና ለበደለህ
ሰው ቅያሜህን ግለጥለት ፤ ቂመኝነት በክፉ መሸነፍ እንጂ ጀግንነት አይምሰልህ ።
ከህሊናህና ከመንፈሳዊ አማካሪህ ሳትመክር ምንም ነገር አትወስን ፤ አጥርተህ
ሳትሰማ ቃል አትግባ ። መከራ ካልደረሰ በቀር ባል በሌለበት ቤት ውስጥ ከሚስቲቱ ጋር
ብቻህን አትቀመጥ ።
የሚበልጥህ ልኩራብህ እንዳይልህ ፣ ያነሰህ ልድረስብህ ብሎ እንዳያጠፋህ
የሀብትህን ልክ እንዳታወራ ፤ በገዛ አፍህ ባንዱ ትከብራለህ ባንዱ ትቀላለህና።
በጣም በማክበርህ እንዳታመልከው ፤ በጣም በመናቅህ እንዳታዋርደው ሠው
እንዳንተ መሆኑን እወቀው ።
የእኔ መናገር ምን ይለውጣል? ብለህም ስህተትን አትለፍ ፤ የእኔ አስተዋፅኦ ምን
ይጠቅማል ? ብለህም ስጦታህን አትጠፍ ።
መልካም ቃል ከስጦታ ይበልጣልና መልካም ቃል ተናገር ፤ ማንኛውም ስጦታ ከልመና
ወንበር አያስነሣም ። የተስፋ ቃል ግን እንደሚያስነሣ አውቀህ ለሰዎች የተስፋ ቃል
ስጣቸው ።
ትምህርት ለዕውቀት ያዘጋጃል እንጂ ዕውቀትን አይጨርስም ። ዕውቀትህን
የምትይዝበትን ሥነ-ሥርዓት ግን ያሳይሃል ። አእምሮህን ለማረቅ ትምህርት ፣ ሰውነትህን
ለመግዛት ትዕግስት ፣ ከማንም ጋር ለመኖር ሥነ-ሥርዓት ያስፈልግሃል ። ለህሊናህ እረፍት
ግን እምነት ያሻሃል ። ተከታይ ለማበጀት ደግሞ ግልጽ መሆንና ታማኝነት ግድ ይልሃል ።
አንተው እውነትን ጠልተሃት ዘመኑ እውነትን ጠልቷል አትበል ። ዘመን እኔና አንተ ነን ፤
በራሱ ክፉና ደግ የሆነ ዘመን የለም።
መልካም ምክር ብትሰማ ሕይወት ቀላል ይሆንልሃል ። ትክክለኛም ውሳኔ ከመልካም
ምክር ነውና..!!
አንብበው ለወዳጅዎ ካላካፈሉት እንዲሁም የተሰማዎትን ካልፃፉ ሲበዛ እራሥ ወዳድ ነዎት
ማለት ነው!!!!

እናንተስ ምን ትላላችሁ እስኪ ሀሳባችሁን አጋሩን!!!

ለሌሎች እንዲደርስ አትርሱ
ፔጃችንን ያላረጋችሁ እያረጋችሁ
youtube channal አችንን ያላረጋችሁ

https://youtu.be/72eiKWmTHnk
እያረጋችሁ ቤተሰብ ሁኑ።አስገራሚና እውነተኛ መረጃ
ታገኛላችሁ
ለጓደኞቻችሁም አድርጉላቸው
እግዚህአብሔር ኢትዮጵያን ባርኳታልና ህዝቦቿን ግን ይባርክ!!!

Photos from ጽማር tsmar's post 21/10/2020
16/10/2020

ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዜግነት ግብፃዊ ናቸው በተጋድሎ ኢትዮጵያዊ ናቸው:: ቁጥራቸው ከባሕታዊያን እንደመሆኑና ተጋድሎአቸው በኢትዮጵያ እንደመሆኑ ግብፃውያን ጨርሶ አያውቁአቸውም:: ስለ እርሳቸው ቅድስናም የሚሰሙት ከእኛ አንደበት ነው::
በአንጻሩ እኛም ስለ ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ሙሴ ጸሊም የምንሰማው ከግብፃውያኑ አንደበት ነው:: በእነርሱ አንደበት ኢትዮጵያዊው ሲባል ብንሰማም እኛ ግን በለመድንበት ጥቁሩ ሙሴ ብለን መጥራት ይቀናናል እንጂ ኢትዮጵያዊነቱን ብዙም አጉልተን አናነሳሳም::
በዛሬይቱ ኤርትራ ሐማሴን የተወለደው ቅዱስ አብደል መሲህ አል ሐበሺንም እንዲሁ ግብፃውያን የሚያከብሩትን ያህል በኤርትራውያንና በኢትዮጵያውያን እምብዛም አይታወቅም:: ቅዱሳኑ የዚህ ዓለም ስደተኞች መሆናቸውን ስለሚያስተውሉ መነኩሴ ሀገር የለውም ብለው የሔዱበት ሀገር አድርገው ይኖራሉ

🌲🌲🌲🌲🌳🌳🌳🌳🌳🌿🌿🍀🌿🌿🌿

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዙሪያቸውን በአንበሳና በነብር ተከብበው የሚሔዱ አባት ነበሩ:: አቡነ አረጋዊን ደግሞ ከዘንዶ ጋር እናያቸዋለን:: ይህ ነገር ምንድር ነው? ቅዱሳኑ ከአራዊት ጋር ምን አላቸው?

ነገሩ ወዲህ ነው ሰው በጥንተ ተፈጥሮ በቅድስና ይኖር በነበረበት በአዳምና ሔዋን ዘመን ከአራዊት ጋር ሰላም ነበረ:: አራዊትን ሳይቀር ያዝዛቸው ያነጋግራቸው ነበረ:: ሔዋን ከዕባብ ጋር በተነጋገረች ጊዜ ዕባብ አፍ አውጥቶ መናገሩ ብርቅ ያልሆነባት ለዚህ ነው:: ሰው ከእግዚአብሔር ሲጣላ ግን የሚፈሩትንና የሚታዘዙለት አራዊት መፍራት ጀመረ::

በሐዲስ ኪዳን የሰውን ክብር ወደ ቀድሞ ሥፍራው የመለሰው ሁለተኛው አዳም መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ግን "በምድረ በዳም ከሰይጣን እየተፈተነ አርባ ቀን ሰነበተ ከአራዊትም ጋር ነበረ" ማር 10:13

እኔ ክርስቶስን እመስላለሁ ያለው ጳውሎስም የበረሃ ዕባብ ስትነድፈው ትንኝ እንደነካችው ያህል ምንም ሳይሆን ወደ እሳት አራግፎአት ቁጭ ብሎአል:: በዙሪያው የነበሩ አሕዛብ ከባሕር አደጋ ተርፎ በዕባብ መነደፉን አይተው "ይኼስ ነፍሰ ገዳይ ነው ከባሕር ስንኳ በደህና ቢወጣ እግዚአብሔር በሕይወት ይኖር ዘንድ አልተወውም" ብለው ከፈረዱበት በኁዋላ ተነድፎ ምንም እንዳልሆነ ሲያዩ ይህስ አምላክ ነው እስከማለት ደርሰው ነበር:: ሐዋ 28:6

ወደ ጥንተ ተፈጥሮ አዳማዊ ቅድስናህ ስትመለስ አራዊት ይገዙልሃል:: ክርስቶስን ስትመስል እንደ አቡየ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንበሳና ነብር ይሰግዱልሃል::
አንበሳና ነብር ባታገኝ አውሬው ምላስህ አራዊት ምኞቶችህ ይታዘዙልሃል::

ቅዱስ ላሊበላ በአት ላንጽልዎ እያለ እየተማጸናቸው እንቢ ብለው የዝቋላን በረሃ የመረጡት መናኝ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወደ ጥንተ ተፈጥሮ ቅድስና ተመልሰው ከውድቀት ወዲህ የመጣውን የቆዳና የቅጠል ልብስ ሳይሹ በጸጋ እግዚአብሔር በብሩ ጠጉር ተሸፍነው ለሀገራችን ጸልየዋል:: ጻድቁ አባታችን አራዊትን በገሠጹበት ጸሎት ዛሬም በሀገራችን የተሠማራውን የጥላቻና የመለያየት አራዊታዊ ጠባይ ይገሥጹልን::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥቅምት 5 2013 ዓ ም

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ
FB: https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
Telegram: https://t.me/deaconhenokhaile
Instagram: https://www.instagram.com/p/CBnMF0nnhcQ/?igshid=549jvl607bv4
Youtube: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g

15/10/2020

ስልኮ አልከፍት ብሎታል?
የስልኮትን ፓተርን ረስተውት
የተረሳውን ፓተርን አጥፍተን
እንዴት ስልኩን እንደገና
መክፈት እንደሚቻል እናያለን።
ግን አንድ ማወቅ ያለቦት ነገር
ቢኖር Install ያደረጉት
አፕሊኬሽን እንዲሁም የመዘገቡት
ስልክም ካለ መጥፋቱ የማይቀር
ነው። እነዚህን 6 ስቴፖች
ይጠቀሙ።........
step1:-ስልኮትን switch off
ያድርጉትና ለጥቂት ሰከንዶች
ይጠብቁ።
step2:- ከዛም እነዚን ቁልፎች
ማለትም ድምፅ መጨመሪያውን
(+), Home key, power
በተኑን በአንድ ላይ ይጫኗቸውና
ስልኮትን ያስነሱት።
step3:- ከዛም የተለያዩ
ኦብሽኖች ይመጡሎታል።
step4:- ከዛም "Restore
factory defults" ወይም
"Delete all user data"
የሚለውን ይምረጡ።
step5:- ከዛም "Reboot
system now" የሚለውን
ይምረጡ።
step6:- ከዛም ስልኮት
Reboot አድርጎ እስኪጨርስ
ይጠብቁ።
ከዚያም ስልኮት እንደ አዲስ
ይከፈታል።.......... ከወደዱት ፔጁን ላይክ ያርጉት
ለወዳጆት ያጋሩት።

Profile pictures 15/10/2020
10/10/2020
Want your school to be the top-listed School/college in Adama?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Adama