2006 Geem Students

2006 Geem Students

Share

Geographers make the world suitable for life

30/08/2022

''ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ''
አንድ የቆሎ ተማሪ ነበረ፤ ይህ ተማሪ ከሌሎች እሱን መሰል ተማሪዎች የሚለየው ስለ ማርያም ስለ እመብርሃን ብሎ ከለመነ በኋላ ያገሬው ሰው ሲዘከረው "ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ" ብሎ ተናግሮ ይሄዳል፡፡ እናም ይህ የቆሎ ተማሪ ባንድወቅት ወደ አንዷ ሴትዮ ቤት ገብቶ "ስለማርያም ስለ ወላዲተ አምላክ፤ ተዘከሩኝ" ብሎ ሲለምን የቤቱ ባለቤት ቁራሽ እንጀራ አውጥታ ተዘከረችው። እሱም የለመደው ነውና "ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ" ብሎ ይሄዳል።
በዚህ ግዜ ሴትዮዋ እንዴት ስዘከረው "እግዚአብሔር ይስጥልኝ" ብሎ መመረቅ ሲገባው ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ ይለኛል ብላ ትናደዳለች፡ እንዲህ ከሆነማ ጥሩ ብላ ነገ ሲመጣ አሳየዋለሁ ብላ ትፎክርበታለች። በነገታውም ወደ አመሻሹ ለእራት የሚሆነውን ሊለምን ወደ መንደሮቹ እንደለመደው "ስለ ማርያም" እያለ ሲሄድ ሴትዮዋም በጎማ ጠላ አዘጋጅታ ጠላው ውስጥ መርዝ ጨምራ ጠበቀችው ተማሪውም እሷ ቤት እንደደረሰ "ስለ ማርያም ስለ እመብርሃን" ብሎ ደምፁን እንዳሰማት ወድያውኑ ያዘጋጀችውን ጠላ የያዘውን ጎማ አውጥታ ሰጠችውና እዛው ቁጭ ብሎ ከጠጣው ቤቷ ውስጥ እንዳይሞትባት ስለፈራች፣ "በል እዚህ ቁጭ ብለህ ከጠጣኸው ስለሚመሽብህ ከቤትህ ሄደህ አረፍ እንዳልክ ጠጣት፤ እንዴት ያለች ጠላ መሰለችህ" ብላ ትልከዋለች፡፡ እሱም "ደግም ለራሱ፤ ክፉም ለራሱ" ብሏት ይሄዳል፡፡ እስኪ ደግም ሆነ ክፋት ለራስ ከሆነ እናያለን ብላ በውስጧ ሞቱን አስባ ተሳለቀችበት፡፡
እሱም የተዘከሩትን ምግብም ሆነ መጠጡን ይዞ ወደ ማደርያው ጉዞውን እንደጀመረ በመንገድ ላይ የሴትዮዋ ልጆች በረሃ ቆይተው በጣም ደከሟቸው ከተማሪው ጋር ተገናኙ ወደ ተማሪው ቀረብ ብለው "እባክህን በርሃ ቆይተን በጣም ደክሞን መግባታችን ነውና እቤት እስክንደርስ የውሃ ጥማችንን ቢያስታግስልን በጎማ ከያዝከው መጠጥ ትንሽም ቢሆን አጠጣን" ብለው ቢለምኑት "እኔም ለምኜው ነው ደግነትም ለራስ ነው" ብሎ ከያዘት ጎማ እንዲጠጡ ፈቀደላቸው፡፡
ሁለቱም ልጆች ከጎማዋ እንደጠጡ ወደያው ይሞታሉ ይህንጊዜ እሪታው ቀልጦ የመንደሩ ሰው በሙሉ ይሰበሰቡና ግማሹ ዱላ ይዞ "ደብድበን ካልገደልነው"፤ ገሚሱም "በድንጋይ መወገር አለበት" የተቀሩት ደግሞ "ለህግ መቅረብ አለበት" ሲባባሉ ሴትዮዋ የመንደሩን ግርግር ሰምታ ስትመጣ ሁለቱም ልጆቿ ሞተው አገኘቻቸው። መርዝ ከጠላ ጋር ቀላቅላ የሰጠችው ተማሪም ሰዎች አመናጭቀው ይዘውት ወደ ህግ እናቅርበው ብለው ሲወስዱት ታያለች፤ ይሄኔ ነበር "ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ" የሚለው አባባሉ ትዝ ያላት፡፡ ሴትዮዋም የሆነውን ነገር ሁሉ ተናግራ "በገዛ ክፋቴ የገዛ ልጆቼን የገደልኩት እኔው እራሴው ነኝ እናም ይሄ ሰው ንፁህ ሰው ነው ልቀቁት" ብላ እራሷን ለህግ ሰጠች፡፡
ደግነትም ሆነ ከፉ መሆን ለራስ ነው ከፉ መሆን በቅድሚያ የሚጎዳው እራስን ነው፡፡ ደግ እንሁን ከደግነት በላይ መልካም ነገር የለምና የዛሬው መለክታችን ነው፡፡

18/05/2022

Min yilutal yihenin?

13/03/2022

Yihen photo yemiystawus YeASTU 2006 GeEM classmate eski alen belu.
Alachiw woy

Untitled album 12/02/2016
Photos 10/03/2014

Field trip in Awash river

Photos from 2006 Geem Students's post 10/03/2014

Geographers collecting data on the field

Want your school to be the top-listed School/college in Adama?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Adama