21/03/2022
ኤች አር 6600ን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ ሊካሄድ ነው
መጋቢት 11/2014 (ዋልታ) በአሜሪካ የሚኖሩ ዳያስፖራዎች የሚሳተፉበት ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 የተባሉ የሕግ ሰነዶችን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ በቀጣይ ሳምንት ሊካሄድ ነው።
ሰልፉ በኢትዮጵያ ላይ "የቅኝ ግዛት ወይም ድህነት" አማራጭ የሚሰጥ HR 6600 እና S3199 የተባሉ በሕወሓትና በግብፅ ሎቢስቶች የረቀቁ የሕግ ሰነዶችን በመቃወም በቀጣይ ሳምንት (March 28) ሰኞ ከጠዋቱ 3:00 ላይ እንደሚካሄድ ሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ማኅበር አስታውቋል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!