10/12/2024
ብርቱ ሰራተኛ ሁኑ!
“ሕልምና ራእይ ወደ እውነታ የሚመጣው በምትሃት አይደለም፡፡ በላብ፣ በቆራጥነትና ጠንክሮ በመስራት ነው” - Colin Powell
አንድ ቀን የምመኘውን አገኘዋለሁ” በማለት ቁጭ ብሎ የሚጠብቅ ሰው አንድ ቀን የሚመኘውን የማግኘቱ እድል እጅግ የመነመነ ነው፡፡ ምናልባት እንኳ እንዴት እንደሆነ ባልገባን ሁኔታ አንድ ቀን የተመኘውን ቢያገኝም እንኳ፣ አንድ ቀን ደግሞ ያንን እንዲሁ በምኞትና ባጋጣሚ ያገኘውን ነገር ያጣዋል፡፡ ይህ የሚሆንበት ዋነኛ ምክንያቱት ቁጭ ብለን ያገኘነውን ነገር በዚህ ቁጭ ባለው ማንነታችን መጠበቅም ሆነ ማሻሻል ስለማንችል ነው፡፡
በላብ፣ በድካምና በብዙ ትጋት የመጣ ነገር በዚያ ድካም ምክንያት ባገኘነው የባህሪ ጽንአታችን ይቀጥላል፣ ይሻሻላል እንዲሁም ያድጋል፡፡ ስለዚህም ተቀምጦ አንድ ነገር ደጁ ድረስ እስኪመጣለት የሚጠብቅ ሰው ለብዙ ክስረት ራሱን ያጋልጣል፡፡ ከሁሉ የላቀው ክስረቱ ግን ተቀምጦ “እድል” ሲጠብቅ የኖረበት ዘመን የሚያባክንበት “ጊዜ” የተሰኘውን ሊመለስ የማይችል ውብ ሃብቱን ነው፡፡
ሕልምን ማለም ለሁሉ በነጻ የተሰጠ ስጦታ ነው፡፡ የታለመውን ሕልም ግን እውን ለማድረግ መንቀሳቀስ ጥቂቶች የሚለማመዱት ልምምድ ነው፡፡ ሁሉም ነገር በህልምና በራእይ ቢጀመርም የሚቀጥለው ግን በትጋትና በጠንካራነት ነው፡፡
በሚከተሉት ነጥቦች ላይ በሚገባ አስቡና እቅድን በማውጣት ለመጻፍ ሞክሩ . . .
1. መለወጥ፣ ማደግና መሻሻል የምፈልግባቸው ነገሮች ምን ምን ናቸው?
2. ለውጡን ለማምጣት መጀመር ያለብኝ ነገሮች ምን ምን ናቸው?
3. ለውጡን ለማምጣት ማቆም ያለብኝ ነገሮች ምን ምን ናቸው?
4. መቼ የት መድረስ እፈልጋለሁ?
5. ከነገ ጀምሮ ማድረግ የምጀምራቸው ነገሮች ምን ምን ናቸው?
መልካም ምሽት ይሁንላችሁ!
https://t.me/Ethio_Intelligence
http://Youtube.com/Ethio_Intelligence
https://www.facebook.com/EthioIntelligence/
Life Skill and Personal Development ! You can contact me Youtube.com/Ethio_Intelligence 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ