የአቡዳቢ ተስፋ ስዱዳን ሰንበት ትምህርት ቤት

የአቡዳቢ ተስፋ ስዱዳን ሰንበት ትምህርት ቤት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የአቡዳቢ ተስፋ ስዱዳን ሰንበት ትምህርት ቤት, School, Abu Dhabi.

17/09/2026
13/09/2026

#መዝሙር #ማርያም #ተዋህዶ #ትርጉም ...

12/09/2026

#መዝሙር #ተዋህዶ #ማርያም ...

እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም አሸጋገርችሁ የ ፳፻፲፱ የተስፋ ስዱዳን ስንበት ት/ቤት  የአዲስ ዓመት አገልግሎት
12/09/2026

እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም አሸጋገርችሁ
የ ፳፻፲፱ የተስፋ ስዱዳን ስንበት ት/ቤት የአዲስ ዓመት አገልግሎት

ባሕረ ሐሳብ የሚለው ቃል የተዘዋወረ ቃል ሲኾን “ሐሳበ ባሕር” ማለት ነው፤ ትርጉሙም የዘመን ቍጥር ወይም ስሌት ማለት ነው፤ ደራሲዉም የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ የነበረው ቅዱስ ድሜጥሮስ ነው።...
10/09/2026

ባሕረ ሐሳብ የሚለው ቃል የተዘዋወረ ቃል ሲኾን “ሐሳበ ባሕር” ማለት ነው፤ ትርጉሙም የዘመን ቍጥር ወይም ስሌት ማለት ነው፤ ደራሲዉም የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ የነበረው ቅዱስ ድሜጥሮስ ነው።
የባሕረ ሐሳብ ቀመር በዘመናዊ ስሌት
የዐዲሱን ዓመተ ምሕረት ወንጌላዊ ለማግኘት
ዓመተ ምሕረት+ዓመተ ፍዳ=ዓመተ ዓለም ፥ ለአራቱ ወንጌላውያን
2019+5500=7519፥4=1879 ደርሶ ቀሪ =3 ይሆናል።
ዐዋጅ (ሕግ)፦
ቀሪው 1 ከኾነ ማቴዎስ ይኾናል።
ቀረው 2 ከኾነ ማርቆስ ይኾናል።
ቀሪው 3 ከኾነ ሉቃስ ይኾናል።
ቀሪው 0 ከኾነ ዮሐንስ ይኾናል፡፡
ከላይ በተሠራው ስሌት መሠረት ቀሪው 3 ስለኾነ የዘንድሮው ዓመት የ2019 ዓም ወንጌላዊ ቅዱስ ሉቃስ ነው።
መስከረም 1 ቀን የሚውልበትን ለማግኘት
ዓመተ ዓለም + መጠነ ራብዒት÷ለሰባቱ ዕለታት (7519+1879=9398፥7= 1342)
7519+1879፥7= 1342 ደርሶ 4 ይቀራል።
ቀሪው 1 ከኾነ ዕለቱ ማክሰኞ ይሆናል።
ቀሪው 2 ከኾነ ዕለቱ ረቡዕ ይሆናል።
ቀሪው 3 ከኾነ ዕለቱ ኀሙስ ይሆናል።
ቀሪው 4 ከኾነ ዕለቱ ዓርብ ይሆናል።
ቀሪው 5 ከኾነ ዕለቱ ቅዳሜ ይሆናል።
ቀሪው 6 ከኾነ ዕለቱ እሑድ ይሆናል።
ቀሪው 0 ከኾነ ዕለቱ ሰኞ ይሆናል።
ስለዚህ ቀሪው 4 ስለኾነ መስከረም አንድ ዐርብ ነው።



መደቡን ለማግኘት
ዓመተ ዓለም ፥ለንኡስ ቀመር (7519፥19=395) ቀሪ 14 ይኾናል። 14 ተረፈ ዘመን ወይም መደብ ይባላል።
ወንበሩን ለማግኘት
መደብ-1=(14-1=13)
ዐዋጅ (ሕግ)፦ “አሐደ አዕትት ለዘመን፤ አንዱን ለዘመን ስጥ፤” የሚል ሕግ ስላለ 14– 1= 13 ይኾናል። ስለዚህ በ2019 ዓ.ም ወንበር 13 ነው።
አበቅቴን ለማግኘት፦ አበቅቴ ማለት ተረፈ ዘመን ማለት ነው፤ አበቅቴ አገልግሎቱ ሌሊትን መሥፈር መቍጠር ነው።
የዘመኑ ወንበር × በጥንተ አበቅቴ ኾኖ ድምሩ ከ 30 በላይ ከኾነ ለ 30 ተካፍሎ ቀሪው፤ ከ 30 በታች ከኾነ ደግሞ ራሱ ይሆናል።
11×13=143፥30=4 ደርሶ 23 ይቀራል። የ2019 ዓ.ም አበቅቴ 23 ነው።
መጥቅዕን ለማግኘት፦መጥቅዕ ማለት ጸዋዒ አስተጋባዒ ማለት ነው፤ መጥቅዕ አግለግሎቱ ከዕለት ተውሳክ ጋር ተደምሮ መባጃ ሐመር በመኾን አጽዋማትንና በዓላትን ለይቶና አውጥቶ መስጠት ነው።
የዘመኑ ወንበር × በጥንተ መጥቅዕ ኾኖ ድምሩ ከ 30 በላይ ከኾነ ለ 30 ተካፍሎ ቀሪው፤ ከ 30 በታች ከኾነ ደግሞ ራሱ ይሆናል።
13×19=247፥30=8 ደርሶ 7 ይቀራል። የ2019 ዓ.ም መጥቅዕ 7 ነው።
ዐዋጅ (ሕግ)፦ “መጥቅዕ ወአበቅቴ ክልኤሆሙ ኢየዐርጉ እም ፴ ወኢይወርዱ እም ፴ ወትረ ይከውኑ ፴፤ መጥቅዕና አበቅቴ ኹለቱም ከሠላሳ አይበልጡም፤ ከሠላሳ አያንሱም፤ ምንጊዜም ሠላሳ ናቸው።” ስለሚል ኹለቱ ተደምረው ከ 30 አይበልጡም፤ ከ 30 አያንሱም። (23+7=30)
ዐዋጅ (ሕግ)፦ መጥቅዕ ከ14 በላይ ከኾነ በመስከረም፤ ከ 14 በታች ከኾነ ደግሞ በጥቅምት ይውላል።
መባጃ ሐመርን ለማግኘት፦ መባጃ ማለት ማቆያ ማክረሚያ ማለት ሲኾን፣ ሐመር ማለት ደግሞ መርከብ መጓጓዣ ማለት ነው፤ ይህም የመጥቅዕና የዕለት ተውሳክ ድምር ሲኾን አጽዋማትና በዓላት የሚውሉበትን ቀን ለማወቅ ያገለግላል።
የዘመኑ መጥቅዕ + የዘመኑ መጥቅዕ የወደቀበት የዕለት ተውሳክ
ዐዋጅ (ሕግ)፦ የዘመኑ መጥቅዕ ሲደመር የዕለት ተውሳክ ከ30 በላይ ከሆነ 30ውን ገድፎ (ለ 30 አካፍሎ) ትርፉን ቍጥር በመያዝ ጾመ ነነዌ የምትውልበትን ቀን ይሰጣል። የሚተርፈው ቍጥር ከ17 በታች ከኾነ ጾመ ነነዌ የካቲት ላይ ይኾናል። በሌላ መልኩ የዘመኑ መጥቅዕና የዘመኑ መጥቅዕ የወደቀበት የዕለት ተውሳክ ተደምሮ ቁጥሩ ከ30 በላይ ከኾነና በ30 ተገድፎ (ለ 30 አካፍሎ) የሚተርፍ ቍጥር ቢኖር ጾመ ነነዌ ወደ የካቲት ይሻገራል፤ ከ30 በታች ከኾነ በጥር ይኾናል።

የዕለታት ተውሳክ
የቅዳሜ = 8 የሰኞ = 6 የረቡዕ = 4 የዐርብ = 2 ናቸው፡፡
የእሑድ = 7 የማክሰኞ = 5 የኀሙስ = 3
የ2019 ዓ.ም መጥቅዕ (7) የዋለበት ዕለት ቅዳሜ ስለኾነ ተውሳኩ = 8 ነው። 7+8=15 ይኾናል። የ2019 ዓ.ም መባጃ ሐመር 15 ይኾናል።
የበዓላትና የአጽዋማት ቀመር
አጽዋማትን እና በዓላት የሚውሉበትን ቀን ለማግኘት የዘመኑ መባጃ ሐመር ሲደመር የጾሙ ወይም የበዓሉ ተውሳክ ኾኖ ድምሩ ከ30 በላይ ከኾነ ለ 30 ተካፍሎ ቀሪው በዓሉ (ጾሙ) የሚውልበትን ያስገኛል፡፡
ሀ/ ጾመ ነነዌ፦ ጾመ ነነዌ በመባጃ ሐመር ብቻ ስለሚወጣ ሰኞ የካቲት 15 ቀን ይውላል።
የአጽዋማት እና የበዓላት ተውሳክ
1. የዐቢይ ጾም = 14 6. የርክበ ካህናት = 3
2. የደብረ ዘይት = 11 7. የዕርገት = 18
3. የሆሳዕና = 2 8. የጰራቅሊጦስ = 28
4. የስቅለት = 7 9. የጾመ ሐዋርያት = 29
5. የትንሣኤ = 9 10. የጾመ ድኀነት = 1
ለ/ ዐቢይ ጾም፦ መባጃ ሐመር + የዐቢይ ጾም ተውሳክ = 15+14= 29 ስለኾነ ሰኞ የካቲት 29 ዐቢይ ጾም ይገባል።
ሐ/ ደብረ ዘይት፦ መባጃ ሐመር + የደብረ ዘይት ተውሳክ = 15+11=26 ስለኾነ ደብረ ዘይት እሑድ መጋቢት 26 ይውላል።
መ/ ሆሳዕና፦ መባጃ ሐመር + የሆሳዕና ተውሳክ = 15+2=17 ስለኾነ ሆሳዕና እሑድ ሚያዝያ 17 ይውላል።
ሠ/ ስቅለት፦ መባጃ ሐመር + የስቅለት ተውሳክ = 15+7= 22 ስለኾነ ስቅለት ዐርብ ሚያዝያ 22 ይውላል።
ረ/ ትንሣኤ፦ መባጃ ሐመር + የትንሣኤ ተውሳክ =15+9= 24 ስለኾነ ትንሣኤ እሑድ ሚያዝያ 24 ይውላል።
ሰ/ ርክበ ካህናት፦ መባጃ ሐመር + የርክበ ካህናት ተውሳክ = 15 +3 =18 ስለኾነ ርክበ ካህናት ረቡዕ ግንቦት 18 ይውላል።
ሸ/ ዕርገት፦ መባጃ ሐመር + የዕርገት ተውሳክ = 15+18= 33፥30=1 ደርሶ ቀሪ 3 ይኾናል። ስለዚህ ዕርገት ኀሙስ ሠኔ 3 ይውላል።
ቀ/ ጰራቅሊጦስ፦ መባጃ ሐመር + የጰራቅሊጦስ ተውሳክ 15+28=43፥ 30=1 ደርሶ ቀሪ 13 ይኾናል። ስለዚህ ጰራቅሊጦስ እሑድ ሠኔ 13 ይውላል።
በ/ ጾመ ሐዋርያት፦ መባጃ ሐመር + የጾመ ሐዋርያት ተውሳክ = 15+29= 44፥ 30= 1 ደርሶ ቀሪ 14 ይኾናል። ስለዚህ ጾመ ሐዋርያት ሰኞ ሠኔ 14 ይገባል።
ተ/ ጾመ ድኅነት፦ መባጃ ሐመር + የጾመ ድኅነት ተውሳክ = 15+1= 16 ስለኾነ ረቡዕ ሠኔ 16 ጾመ ድኅነት ይገባል።
ኢየዐርግና ኢይወርድ/ አለመውጣትና አለመውረድ
 ጾመ ነነዌ ከጥር 17 በታች አይወርድም፤ ከየካቲት 21 በላይ አይወጣም።
 ዐቢይ ጾም ከየካቲት 1 በታች አይወርድም፤ ከመጋቢት 5 በላይ አይወጣም።
 ደብረ ዘይት ከመጋቢት 28 በታች አይወርድም፤ ከሚያዝያ 2 በላይ አይወጣም።
 ሆሳዕና ከመጋቢት 19 በታች አይወርድም፤ ከሚያዝያ 23 በላይ አይወጣም።
 ስቅለት ከመጋቢት 24 በታች አይወርድም፤ ከሚያዝያ 28 በላይ አይወጣም።
 ትንሣኤ ከመጋቢት 26 በታች አይወርድም፤ ከሚያዝያ 30 በላይ አይወጣም።
 ርክበ ካህናት ከሚያዝያ 20 በታች አይወርድም፤ ከግንቦት 24 በላይ አይወጣም።
 ዕርገት ከግንቦት 5 በታች አይወርድም፤ ከሠኔ 9 በላይ አይወጣም።
 ጰራቅሊጦስ ከግንቦት 15 በታች አይወርድም፤ ከሠኔ 19 በላይ አይወጣም።
 ጾመ ሐዋርያት ከግንቦት 16 በታች አይወርድም፤ ከሠኔ 20 በላይ አይወጣም።
 ጾመ ድኀነት ከግንቦት 18 በታች አይወርድም፤ ከሠኔ 22 በላይ አይወጣም።

በመ/ር እስጢፋኖስ ሙላቱ

10/09/2026

22/08/2026

እንኳን ለቅድስት ኪዳነ ምሕረት በዓል አደረሳችሁ . | Check out የአ/ዳ/ም/ኀ/ መ/ገ/የተ/ ስዱዳን ሰ/ት ቤት's LIVE streams on TikTok! Watch, follow, and discover the latest content from የአ/ዳ/ም/ኀ/ መ/ገ/የተ/ ስዱዳን ሰ/ት ቤት...

21/08/2026

#ማርያም #መዝሙር #ትርጉም #ተዋህዶ #...

Address

Abu Dhabi

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአቡዳቢ ተስፋ ስዱዳን ሰንበት ትምህርት ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category