Bekafa Seventh Day adventist church

Bekafa Seventh Day adventist church “ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም

12/06/2023
30/12/2022

የአይሁድ ሕዝብ ከአንድ ሺህ ዓመታት በላይ የመድህንን መምጣት ሲጠባበቁ ቆዩ። ያ ወቅት የተስፋቸው መደምደሚያ ነበር። በመዝሙር፣ በትንቢት፣ በቤተ መቅደስ ሥርዓተ ማሕሌትና በቤተሰብ ጸሎትም ስሙ ተከብሮ ነበር። ነገር ግን በመጣ ጊዜ አላወ ቁትም። የሰማዩ ተፈቃሪ በእነርሱ ዘንድ «እንደ ቡቃያ ከደረቅ መሬት እንደ ሥር አድጐአል። መልክና ውበት የለውም። ባየነውም ጊዜ እንወደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።» «ወደ ወገኖቹ መጣ፤ ወገኖቹም አልተቀበሉትም»። ኢሳ53:2፣ ዮሐ1:11።
አይሁድ ስለ መሲህ መምጣት ቢመኙም ስለ ሥራው ግን በቂ ግንዛቤ አልነበራቸውም። ከሮማዉያን አገዛዝ ነጻ ለመውጣት እንጂ ከኃጢአት ለመዳን አልፈለጉም።
አይሁዶች ከሥርዓተ አገልግሎታቸው መንፈሳዊ ሕይወትን አላገኙምህ ይዘት የሌለው ቅርጻዊ አገልግሎትን የሙጥኝ አሉ። ሥርዓተ አገልግሎቱ በሚያመለክተው ላይ ከማተኮር ፋንታ በአገልግሎቱ ሥርዓት ላይ አተኮሩ። ካህናትና ጸሐፊዎች ያጡትን ደረጃ ለመተካት ሲሉ የራሳቸውን ብዙ መመሪያዎች አወጡ፤ አቋማቸውን እያከረሩ እንደ ሔዱ መጠን የእግዚአብሔር ፍቅር መግለጫ እየቀነሰ መጣ። የቅድስናቸው መለኪያ የአገልግሎታቸው ብዛት ሆነ፤ ልባቸውም በትእቢትና በግብዝነት ተወጠረ።

21/09/2022

በካፋ 7ተኛ ቀን አድቨንቲስት ቤተ-ክርስቲያን
ጃንተስ መዘምራን : ዘላለም ህያዉ ነህ!

https://fb.watch/fGKB4VXDZF/

ልዩ ፕሮግራም በበካፋ 7ተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ-ክርስትያን!
21/09/2022

ልዩ ፕሮግራም በበካፋ 7ተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ-ክርስትያን!

መልካም ሰንበት ዝግጅት ::“ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።”  — ዮሐንስ 19፥30ተፈጸመ አለና አንገቱን ደፍቶ መንፈሱን ሰጠ። ደ...
15/04/2022

መልካም ሰንበት ዝግጅት ::

“ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።”
— ዮሐንስ 19፥30
ተፈጸመ አለና አንገቱን ደፍቶ መንፈሱን ሰጠ።

ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ “ተፈጸመ” ብሎ ሲጮኽ ተመለከቱ። ነገር ግን የተጠናቀቀው የኢየሱስ ሕይወት አልነበረም—ከእግዚአብሔር ፍቅር የሚለየን ሁሉም ነገር ነበር።

እኛን ለማዳን ነፍሱን አሳልፎ በመስጠት “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” ሆነ።

ኢየሱስ መከራን የተቀበለው በእኛ መከራ የሚሠቃይ ዓለማችን እግዚአብሔርን በግል እንዲያውቅ ነው።

በመስቀል ላይ የተሰቀለው እና እኛን ለማዳን ሁሉንም ነገር የሰጠ ፍቅር ነው። "ተፈፅሞል " የድል ጩኸት ነበር, ምክንያቱም እኛን በምርኮ ያቆዩንን ሁሉ አሸንፈናል ::

18/12/2021

መዝሙር 147
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ሃሌ ሉያ። አምላካችንን በመዝሙር ማወደስ እንዴት መልካም ነው፤ እርሱን ማመስገን ደስ ያሰኛል፤ ይህ ተገቢም ነው።
² እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን መልሶ ይሠራታል፤ ከእስራኤል የተበተኑትን ይሰበስባል።
³ ልባቸው የተሰበረውን ይፈውሳል፤ ቍስላቸውንም ይጠግናል።
⁴ የከዋክብትን ብዛት ያውቃል፤ እያንዳንዱንም በስሙ ይጠራዋል።
⁵ ጌታችን ታላቅ ነው፤ እጅግ ኀያልም ነው፤ ለጥበቡም ወሰን የለውም።

መልካም ሰንበት ይሁንላችሁ 🙏        ተስፋ ቆርጣችሁኃል?አንተን ተስፋ የሚያደርጉ፣ ከቶ አያፍሩምመዝ 25፡3እርሱን ተስፋ ለሚያደርጉት፣ ለሚፈልገውም ሰው እግዚአብሔር መልካም ነው፡፡ ሰው ...
10/12/2021

መልካም ሰንበት ይሁንላችሁ 🙏

ተስፋ ቆርጣችሁኃል?

አንተን ተስፋ የሚያደርጉ፣ ከቶ አያፍሩምመዝ 25፡3
እርሱን ተስፋ ለሚያደርጉት፣ ለሚፈልገውም ሰው እግዚአብሔር መልካም ነው፡፡ ሰው የእግዚአብሔርን ማዳን ዝም ብሎ ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው፡፡ለቆ ኤር 3፡25-26
ነፍስን ተስፋ ማስቆረጥ የሰይጣን ስራ ነው ፤ በተስፋና በእምነት መሙላት ደግሞ የክርስቶስ ተግባር ነው፡፡
ሰይጣን ከእግዚአብሔር የተቀበልነውን የተባረከ ዋስትና ሊዘርፈን ሁልጊዜ ዝግጁ ነው፡፡ ማንኛውንም የተስፋ ጭላንጭል ሊያጠፋ ይሻል፤ ነገር ግን ይህንን እንዲያደርግ ልትፈቅዱላት አይገባም፡፡ እምነትን ተለማመዱ ፤ የእምነትንም መልካሙን ገድል ተጋደሉ፤ ከእነዚህ ጥርጣሬዎች ጋር ተፋለሙ ፤ ከጌታ የተስፋ ቃሎች ጋር ራሳችሁን አስተዋውቁ፡፡
አንተ ባዘጋጀህልን በጠባቡ መንገድ መሄድ እንድንችል እርዳን :: አሜን!

የሺኖ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ-ክርስቲያን ናታኒም መዘምራን መዝሙር ነሐሴ 29 /2013 ይመረቃል : :
25/08/2021

የሺኖ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ-ክርስቲያን ናታኒም መዘምራን መዝሙር ነሐሴ 29 /2013 ይመረቃል : :

11/12/2020

ምሳሌ8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁴ የሚሰማኝ ሰው ምስጉን ነው ዕለት ዕለት በቤቴ መግቢያ የሚተጋ፥ የደጄንም መድረክ የሚጠብቅ።
³⁵ እኔን ያገኘ ሕይወትን ያገኛልና፥ ከእግዚአብሔርም ሞገስን ያገኛልና።
³⁶ እኔን ያጣ ግን ራሱን ይጐዳል፤ የሚጠሉኝ ሁሉ ሞትን ይወድዳሉ።
መልካም ሰንበት

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bekafa Seventh Day adventist church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share