Kha-Abba Language Services and Consulting

Kha-Abba Language Services and Consulting

Share

KHABBA is a language and digital service provider based in Colorado, USA.

02/17/2025

Going against unity
You start big
And simplify on your way along
To a level indivisible
To end up tiny
And to settle down small!

(Picture, a sinking bench at a beachside park in Dallas, Texas, taken by self)

02/15/2025

ፍቅር እንደ አበባ መስጠት
ወይ እንደ የዓመት-አንዴ ስሜት
እንዲያ ቀላል ቢሆን በእውነት
የማይጠይቅ ቢሆን የልብን መስዋዕት
ሁሉም ባፈቀረ - ፍቅርም በዓለም በሰፈነ
ጥላቻም ቦታ አጥቶ እንደጉም በበነነ!
(ፎቶ እና ግጥም: የእኔው!)

Amco Views – Medium 08/11/2024

Observations, contemplations and commentaries in over 55 pieces!

Amco Views – Medium Personal stories, observations, views and some useful tips.

08/08/2024

ጋዜጠኛ እና ደራሲ ኣለማየሁ ማሞ፣ በመጀመሪያ በዴንቨር ለነበረህ ጊዜ እና ለሰጠሀን ማበረታቻ በግልህ ምስጋናዬን ያቀረብሁ ቢሆንም ኣሁንም በተከታዮችህና በኣድናቂዎችህ ኣደባባይ ላመሰግንህ እወዳለሁ። በመቀጠል፣ ብንከተለው ብዬ ስለማስበው የፊደል ኣጠቃቀም በዚህ የፌስቡክ ኣደባባይ ላጋራሀው ማጋራት ኣመሰግንሃለሁ።

ስለ ግእዝ እና ኣማርኛ ቋንቋዎች ግንኙነት ለመናገር ብዙ የጥናት ወረቀቶችን ማገላበጥ ላያስፈልግ ይችላል። ኣማርኛ የግእዝን ፊደሎች ሙሉ ለሙሉ ወስዶ እና እንደ "ሸ" እና "ጨ" የመሳሰሉትን ጨምሮ የተሟላ ቋንቋ ሆኖ ለዘመናት ኣገልግሎት እየሰጠ ያለ ድንቅ ቋንቋ ነው። በኣማርኛ ቋንቋ ምእሉነት እና ጥልቅነት ተደንቄ ኣላበቃም። እንግሊዝኛ እና ፈረንሳይኛ ተምሬያለሁ። ኣማርኛ በብዙ መልኩ ከሁለቱ የሚሻልበት የስነ ልሳናዊ ገጽታዎች እንዳሉት ብዙ ማስረጃዎችን መስጠት እችላለሁ።

ነገር ግን፣ ግእዝ በታሪኩ ከፍተኛ ተጽእኖዎችን ኣሳድሮበታል። ተጽእኖዎቹ ኣዎንታዊም ኣሉታዊም ናቸው። ኣዎንታዊዎቹ በጣም በርካታ ሲሆኑ ኣሉታዎቹ ጥቂቶች እና መታረም ወይም መስተካከል የሚችሉ ናቸው ብዬ ኣምናለሁ። ከእነዚህም ዉስጥ ኣንደኛው የፊደል ኣጠቃቀም ነው። ይህም በእውቁ እና አንጋፋው ደራሲ ሃዲስ ኣለማየሁ ፍቅር እስከ መቃብር እና በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናት መዝገበ ቃላት ዉስጥ ለማረም ተሞክሯል።

እኔም እነዚህን ሁለቱን ምንጮች መሰረት ኣድርጌ የኣማርኛ ፊደል የሚከተሉት ቢሆኑ ወጥ ኣጻጻፍ ይኖረናል የሚል ሙግት አቅርቢያለሁ።
(በምስሉ ላይ የሚታዩት፤ ቅደም ተከተላቸው ለተማሪዎቼ እንዲቀላቸው በፊደሎቹ ቅርጽ መሰረት የተቀመጠ ነው)

ከዚህ በተቃራኒ የሚሟገቱ ሰዎች፦ 1) የሚሰጡን ምሳሌ ኣድርገው የሚሰጡን ቃሎች ሙሉ ለሙሉ የግእዝ የሆኑ ወይም ኣማርኛ ያልሆኑ ናቸው። ለምሳሌ፦ ሠረቀ/ሰረቀ - በየትኛውም ሆሄ ቢጻፍ ይህ ቃል ኣማርኛ ዉስጥ ትርጉሙ ሳይታይ/ሳያስፈቅድ ወሰደ ማለት ብቻ ነው። ሌላ "ወጣ" የሚል ትርጉም በጭራሽ የለውም። "ወጣ" የሚለው በግእዝ እንጅ በኣማርኛ ኣይደለም። 2ኛ) የሚሟገቱትም ራሳቸው እንደሚሉት በወጥነት ጠብቀው መጠቀም ኣይችሉም። ተሟጋቾቹ በጻፏቸው ጽሁፎች ዉስጥ ብዙ ሳይደከም አንድ ቃል በሁለት የተለያዩ ፊደሎች ወይም ሆሄዎች ተጽፈው ማግኘት ከባድ ኣይሆንም። 3ኛ) በቀደሙት ዘመናት የኣማርኛ መምህራን የግእዝ እውቀት የነበራቸው በመሆኑ የግእዝ ባህሪዎችን ኣማርኛ እንዲጠብቅ ኣድርገው ያስተምሩ ነበር። ኣሁን ግን የኣማርኛ መምህራን (እኔንም ጨምሮ) ራሳቸው ይህ እውቀት በትክክል የሌላቸው በመሆናቸው የመማሪያ መጽሃፎቻችን እና የማስተማር ልምምዶቻችን ይህንን በጥልቀት ወይም በትኩረት ኣያስተምሩም።

ከእነዚህ እና ሌሎች ምክንያቶች የተነሳ ኣማርኛ ወጥ የሆነ ኣጻጻፍ የለውም። ጋዜጦችን፣ መጽሄቶችን እና መጽሃፎችን ገለጥ ገለጥ እያደረጉ መመልከት ነው። ህዝብ/ሕዝብ/ኅዝብ፤ ሰው/ ሰዉ/ ሠው/ሠዉ፤ ጸሃይ/ፀሐይ/ጸሀይ/ፀሓይ፣ ወዘተ ኣይነት ኣጻጻፎችን እናገኛለን።

ስለዚህ ያለምንም ኪሳራ (ማለትም የቋንቋ ለውጥ ባለመሆኑ የምናከስረው ነገር ኣይኖርንም፣ የተጻፉ ሰነዶች ተነባቢነታቸው ኣይነካም፣ በዚህኛው ኣጻጻፍ የሚጻፉ ጽሁፎችም ቀላል እንጅ ለማንም እይከብዱም)፣ ወጥ ማድረግ የተሻለ ኣይሆንምን? ይህን ማለት ታሪክን ወይም ቅርስን ማጥፋት ኣይደለም፤ ቋንቋን ማዘመን ወይም ወጥ ማድረግ ነው'ጅ!

ተጨማሪ (ቦነስ)፦ በኣጪር ጊዜ ዉስጥ ኣማርኛ ጡረታ የሚያወጣቸው ፊደሎች፦ ዠ እና ርቢዎቹ፣ ኸ እና ርቢዎቹ።

BE Amlaku – Medium 08/01/2024

Over 50 different pieces of writing (articles). Click on the link and read your choice!

BE Amlaku – Medium Read writing from BE Amlaku on Medium. Aspiring writer and story teller. I write about myself, my culture, humanity, religion, education, language, society, life and more.

07/27/2024

***ፍቅር ያሽንፋል?***
ፍቅር ይሸነፋል እንጂ አያሸንፍም
የማይሸነፍ ፍቅር አይደለም፣ ፍቅር የለም
ፍቅር ከሌለ፣ የለም ሰላም
ምክንያቱም ፍቅር ተሸንፎ ይተዋል
ይቅር ብሎ ለሰላም ቅድሚያ ይሰጣል፤
ከዚያም ሁሉም በሰላም እንዲኖር ያደርጋል!🤝🙏

07/14/2024
Photos from Kha-Abba Language Services and Consulting's post 07/06/2024

What do you see in these pictures?

VOA Amharic Interview 06/19/2024

VOA Amharic Interview በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ለሁለተኛ ጊዜ ቃለ መጠይቅ የመስጠት እድል አግኘሁ። በዚህ ጊዜ በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ በርክሌይ አማርኛን ቋንቋ በማስተማር ዙሪያ ለማውጋት ነበ...

Want your school to be the top-listed School/college in Denver?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Denver, CO

Opening Hours

9am - 5pm