Gulilat Geletaw Aschenaki.

Gulilat Geletaw Aschenaki. Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gulilat Geletaw Aschenaki., 6395 Little River Turnpike Alexandria, VA 22312, Alexandria, VA.
(1)

እውቁ ኢትዮጵያዊ ገጣሚ፣ ባለቅኔ፣ ፀሃፊ ተውኔት . . . ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን "እናት ዓለም ጠኑ" (1967) ትያትር ቃለ ተውኔት ላይ :-'አፋዊ ሆንን!ሕያዊ ሳንሆን አፋዊ!ቃለ ሕይወ...
09/04/2026

እውቁ ኢትዮጵያዊ ገጣሚ፣ ባለቅኔ፣ ፀሃፊ ተውኔት . . .
ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን "እናት ዓለም ጠኑ" (1967) ትያትር ቃለ ተውኔት ላይ :-

'አፋዊ ሆንን!
ሕያዊ ሳንሆን አፋዊ!
ቃለ ሕይወት ሳንሆን፣ ብኩን ቃለ-አፍ ብቻ!
እንጂ! ቤታችን አንድ ነው፡፡

“ቤት” ብለን ለልጆቻችን ያወረስናቸው
ፍቅር የሞተበት ቤታችን! አንድ ነው፡፡
አባቶቻችን ልባም
እኛ አፋም፡፡
እሳት ዐመድ ወለደ ሆንን እንጂ- ቤታችንስ አንድ ነው፡፡ . . . ' በማለት የዛሬውን መራር እውነት ይተነብያል።

በፖሊሲ እና በቴክኖሎጂ ጉዳዮች መወያየት እና መከራከር የነበረበት የዛሬው ትውልድ ወርዶ ወርዶ በባህል ልብስ ሲነታረክ ትዝ ብሎኝ ፈልጌ አጋራኋችሁ🙏🙋

የተስፋዋ ምድር ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!!!በጊዜም ያለጊዜም ጽናት ‼
07/15/2026

የተስፋዋ ምድር ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!!!
በጊዜም ያለጊዜም ጽናት ‼

07/15/2026

ኢትዮጵያ የምትመክርበት ፣ ኢትዮጵያ የምትከብርበት ፣ ኢትዮጵያ የምትደመጥበት ፣ታሪካዊውና ብሩህ ተስፋ ፈንጣቂው ብሔራዊ ምክክር
****
ሀገራዊ የዘመናት ቅሬታዎችን ለመፍታት፣ በጋራ እሴቶች ላይ ለመስማማትና ለነገዋ ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም መሠረት ለመጣል የሀገራዊ ምክክር የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንገኛለን።

ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚፈልጓትን ሀገር ለመገንባት እንዲሁም ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠርና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት፤ የመነጋገርና የመደማመጥ ኢትዮጵያዊ እሴትን ለመመለስ ብሎም በሀገራችን የተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓት እንዲፈጠር ማድረግ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው።

ይህ የምክክር ሂደት ኢትዮጵያ ልዩነቶችን በሰለጠነ ባህል የምትፈታ ሀገር እንደሆነችም በተጨባጭ የምናረጋግጥበት፤ በኢትዮጵያ ለዘመናት የቆዩ አለመግባባቶችን በመፍታት ለዜጎቿ ምቹ የሆነች ፣መደማመጥ ፣ መተሳሰብ እና መፈቃቀር የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመገንባት፤ የልዩነት ምንጭ የሆኑ ጉዳዮች በሙሉ ወደ ጠረጴዛ ቀርበው የሚመከርባቸው በውጤቱም መግባባት የሚሰፍንበት ይሆናል ።

ሀገራችን ታሪካዊ ለውጥ ሊታይ የምትችልበት ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በየቀበሌውና በየዞኑ ሲወያዩባቸው የቆዩባቸው አጀንዳዎች ተጠቃልለው የመጨረሻ ውሳኔና አቅጣጫ የሚቀመጥበት ታሪካዊ መገናኛ ነው።

ስለሀገራቸው ባላቸው አመለካከትና አቋም ለረጅም ጊዜ ተገናኝተው የማያውቁ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ ግለሰቦች እና ተመራማሪዎች በጥቅሉ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድነት ቁጭ ብለው በጋራ መክረው ለሀገራዊ ምክክሩ የውይይት አጀንዳ ሰጥተዋል። የዜግነት አበርክቶአቸውን ተወጥተዋል።

ሀገራዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ ስብራት ጥያቄዎች ተለይተው፣ የጋራ መፍትሔ ምክረ-ሐሳብ የሚቀረጽበት ከጉባኤው የሚወጡት ውጤቶችም ለሀገራችን የፖለቲካ እና የሕግ ማሻሻያዎች እንደ ፍኖተ-ካርታ የሚያገለግሉ ናቸው።ባለፉት ትውልዶች የተገነቡ የልዩነት ግንብ አፍርሶ ለሚቀጥለው ትውልድ የምንሻገርበት ድልድይ ነው።

የቀይ ባሕር ጥሪ እና የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ትንሳኤ*****************​ጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረቶችና የኃያላን የሽኩቻ መድረክ በሆነው በአፍሪካ ቀንድ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ህልውና እና ዘላ...
06/27/2026

የቀይ ባሕር ጥሪ እና የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ትንሳኤ
*****************

​ጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረቶችና የኃያላን የሽኩቻ መድረክ በሆነው በአፍሪካ ቀንድ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ህልውና እና ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ከቀይ ባህርና ከባህር በር ጥያቄ ጋር በቀጥታ የተሳሰረ ነው።

ተፈጥሮና መልክዓ-ምድራዊ እውነታዎች በግልጽ እንደሚያሳዩት ቀይ ባህርና አባይ የዚች ታላቅ ሀገር የደም ስሮች ናቸው።

ከዚህ ተፈጥሯዊ ትስስር ባሻገር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የባህር ህግ አንቀጽ 69 እና 125 የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት በአካባቢያቸው ካለው ባሕር የተፈጥሮ ሀብት እኩል የመጠቀም እና የመሸጋገሪያ አለም አቀፍ መብት እንዳላቸው በግልጽ ይደነግጋል።

ኢትዮጵያ ይህንን ህጋዊና ተፈጥሯዊ መብቷን ለማስከበር ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያከናወናቻቸው ስራዎች የሀገራችን መጻኢ ዕድል አዲስ አቅጣጫ ላይ ያስቀመጣት ሆነዋል።

​በሀገራችን የመጣውን ለውጥ ተከትሎ በባህርና ቀጠናዊ ተወዳዳሪነት ዙሪያ ከተከናወኑት ተግባራት መካከል ዋነኛውና ደማቅ ስኬት ሆኖ የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ ባህር ኃይል እንደገና መመስረቱና መዋቀሩ ነው።

ለሶስት አስርት ዓመታት ተዘንግቶ የነበረውን ይህንን ወሳኝ ዘርፍ በቁርጠኝነት ዳግም በማንሳት የባህር ኃይል አድሚራል በመሾም ተቋማዊ ኃይሏን በተግባር አጠናክራለች።

ይህ ስኬት በምኞት የተገነባ ሳይሆን አለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ አጋርነቶችን በመጠቀም፣ ለባህር ኃይሉ ዘመናዊ ስልጠናና ሁለንተናዊ የቴክኒክ ድጋፍ በማሰባሰብ የተመዘገበ ታላቅ ውጤት ነው።

ይህ ተቋማዊ ትንሳኤ ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ኮሪደር ላይ ሊኖራት የሚገባውን ስትራቴጂካዊ ተፅዕኖ እና የተጠቃሚነት ፍላጎት በፅኑ መሠረት ላይ ያቆመ ኩነት ነው።

​የተከናወኑት እነዚህ ስራዎች የባህር በር ጉዳይን ከስሜታዊነት በራቀ፣ በጥንቃቄና በመርህ ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ኢኮኖሚ እሳቤ መሆኑን ለአለም ማህበረሰብ ያሳዩ ናቸው።

10 በመቶ የሚሆነው የአለም ንግድ በሚያልፍበት፣ በዘይትና በከበሩ ማዕድናት በበለፀገው እና በቢሊዮኖች የሚቆጠር የንግድ እንቅስቃሴ በሚስተናገድበት በቀይ ባህር ቀጠና ውስጥ፣ ኢትዮጵያ የነበራትን የጥገኝነት መገለጫ በመቀየር የራሷን የባህር ኃይል መገንባቷ ወደፊት ለሚደረጉ የዲፕሎማሲ ድርድሮች ትልቅ አቅም ፈጥሯል።

ይህ ስኬት የቀድሞ መሪዎች ስለ አባይ መብት ሲናገሩ "እኔ አቅም የለኝም ልጆቼ ይሰራሉ" እንዳሉት ሁሉ ዛሬ የተጣለው መሠረትም ትውልዱ የቀይ ባህርን መብት በሰላማዊ መንገድና በአለም አቀፍ ህግጋት መሠረት አስከብሮ እንዲረከብ የሚያስችል አርቆ አሳቢ እርምጃ ነው።

​ባለፉት ዓመታት በዘርፉ የተመዘገቡት ስኬቶች ኢትዮጵያ ጦር ሳትሰብቅ፣ የወንድማማች ሀገራትን ሉዓላዊነት ሳትደፍር፣ የራሷን ስትራቴጂካዊ ቦታ የምታስከብርበትን መዋቅር የፈጠሩ ናቸው። የባህር ኃይሉ መደራጀት ሀገራችን በአለም አቀፍ የባህር ህግ የተሰጧትን መብቶች በተግባር ለመተርጎም ያላትን ዝግጁነት ያረጋገጠ ሲሆን ለቀጣዩ ትውልድም ከስሜት ነጻ በሆነ መንገድ የተሰላ፣ የታመቀ አቅም እና ብሩህ የባህር በር ተስፋን የጫረ ታሪካዊ ስራ ነው።

ኢቢሲ ዶትስትሪም

አንድ አባት ወፍ ልጁን እንዲህ እያለ  ሲመክረው  "ልጄ ፤ ሰው የሚባለው ፍጡር እጅግ ክፉና ተንኮለኛ ነው። ጥሬህን እየለቀምክ በአጠገብህ ሲያልፍ ድንገት 'ዝቅ' ካለ ፈጥነህ ብረር። ምክንያ...
06/25/2026

አንድ አባት ወፍ ልጁን እንዲህ እያለ ሲመክረው "ልጄ ፤ ሰው የሚባለው ፍጡር እጅግ ክፉና ተንኮለኛ ነው። ጥሬህን እየለቀምክ በአጠገብህ ሲያልፍ ድንገት 'ዝቅ' ካለ ፈጥነህ ብረር። ምክንያቱም ዝቅ ያለው ድንጋይ አንስቶ ሊወረውርብህ ሊሆን ይችላልና!"..
የወፉ ጫጩትም በረዥሙ አሰበና እንዲህ ሲል ጠየቀ። "እሺ አባባ፣ ይሁን! ግን ዝቅ ሳይል ድንጋዩን አስቀድሞ ከኪሱ ይዞ ቢመጣስ?" አባትየውም ልጁን እያየ "ልጄ እኔ የነገርኩህ የኔን ዘመን ችግርና መፍትሔ ነው። አንተ ደግሞ ለዚህ ለተራቀቀው ለዘመንህ አዲስ አስተሳሰብና ጥንቃቄ ጨምርበት" አለው።..
የትናንት መፍትሔ የዛሬን አዳዲስ ፈተናዎች ሙሉ በሙሉ አይፈታም። ዘመን ሲቀየር የክፋትም ሆነ የችግሮች ስልት አብሮ ስለሚራቀቅ፣ እኛም ዘመኑን የሚመጥን ንቃት፣ ጥንቃቄና አዲስ አስተሳሰብ ሊኖረን ይገባል!

የታላቋን ሀገር  #በጂኦግራፊእስርቤት መቆየት የማይፈቅደው #የቀይባሕርትውልድ ---ኢትዮጵያ በዓለም ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከ130 ሚሊዮን በላይ የሚሆን እጅግ ሰፊ ሕዝብ ይዛ የባሕር ...
06/07/2026

የታላቋን ሀገር #በጂኦግራፊእስርቤት መቆየት የማይፈቅደው
#የቀይባሕርትውልድ
---

ኢትዮጵያ በዓለም ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከ130 ሚሊዮን በላይ የሚሆን እጅግ ሰፊ ሕዝብ ይዛ የባሕር በር አልባ ሆና እንድትቀጥል የተፈረደባት ብቸኛ ሀገር ናት።

ይህ ታሪካዊ ኢ-ፍትሐዊነት ትውልዱ ላይ ጥልቅ ቁጭት እና የሕልውና ጥያቄ የፈጠረ እና ምላሽ የሚሻ ነው።

ከቅድመ አክሱም ዘመን ጀምሮ እስከ 1985 ዓ.ም ድረስ ኢትዮጵያን እና ቀይ ባሕር ተነጣጥለው አያውቁም።

ከ1985 ዓ.ም እስከ 'መደመር ትውልድ' መነሣት ድረስ ያለው ትውልድ ግን በታሪክ "የሥነ-ልቦና ስብራት" ዘመን ተብሎ የሚታወቅበትን የባዶነት እና የቁጭት ጊዜ አሳልፏል።

በወቅቱ ሥልጣንን የተቆጣጠሩት ኃይሎች ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ተመሳጥረው ታሪኩን የነጠቁት ያ ትውልድ፣ የባሕር በር ማጣትን እንደማይቀየር ቋሚ ዕጣ ፈንታ በመቁጠር ሲብሰለሰል ኖሯል።

ከ12 በመቶ በላይ የሚሆነው የዓለም የንግድ እንቅስቃሴ የሚተላለፍበትን እና በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘውን ቀይ ባሕርን ዝም ብሎ ማየት ያንገፈገፈው "የመደመር ትውልድ" ዛሬ ተፈጥሯል።

የመደመር ትውልድ ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነውን አምራች እና ወጣት ሕዝብ የሚወክለው የቀይ ባሕር ትውልድ ነው።

ይህ ትውልድ የባሕር በር አልባነትን እንደ ቋሚ ዕጣ ፈንታ ሳይሆን እንደ ታሪካዊ እና ሕጋዊ ስህተት ይመለከተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት እንደገለጹት፣ በ2050 ዓ.ም የሕዝብ ብዛቷ ወደ 150 ሚሊዮን ተብሎ የምትገመተዋ ታላቅ ሀገር መተንፈሻ አልባ ሆና መቀጠል አትችልም።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደጋግመው እንደገለጹት ይህን ያህል ግዙፍ ሕዝብ ያላትን ሀገር በጂኦግራፊያዊ እስር ቤት ውስጥ አስገብቶ ለቀጣዩ ትውልድ ማውረስ የታሪክ ባለእዳነት ነው።

የቀይ ባሕር ትውልድ ታሪክን የማረም እና የታላቋን ኢትዮጵያን ትክክለኛ የጂኦግራፊ እና የኢኮኖሚ ስፍራ የመመለስ ታሪካዊ አደራ ወድቆበታል።

ይህ ትውልድ የባሕር በር ጥያቄ የፖለቲካ ቅንጦት ሳይሆን፣ የ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ሕልውና እና የዕድገት መሠረት መሆኑን በሚገባ የተገነዘበ ጠንካራ ሥነ-ልቦና አለው።

የቀይ ባሕር ትውልድ ታሪካዊ ስህተቶችን ለማረም የሚንቀሳቀሰው በጦርነት አዙሪት ሳይሆን፣ በጋራ ተጠቃሚነት፣ በኢኮኖሚያዊ ውህደት እና በብልህ የፓን-አፍሪካኒዝም ዲፕሎማሲ ነው።

ትውልዱ ኢትዮጵያ የምትገነባቸውን ግዙፍ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ከቀይ ባሕር ጂኦ-ፖለቲካዊ ስትራቴጂ ጋር በማስተሳሰር፣ ቀጣናውን የጋራ ብልጽግና ማዕከል ለማድረግ ይተጋል።
#ቀይባሕር

“It's not done...አላለቀም!” ሻምፒዮኑ የዴክላን ራይስ ቃል---እዚሁ ያገኘሁት--- ሕይወት እንዲህ ይቀጥላል!ቃላት በሰው ልብ ውስጥ ሀያል ናቸው። ቃል ያፈርሳል፤ ደግሞ ሰውን  ከወ...
05/24/2026

“It's not done...አላለቀም!”
ሻምፒዮኑ የዴክላን ራይስ ቃል
---
እዚሁ ያገኘሁት
---
ሕይወት እንዲህ ይቀጥላል!

ቃላት በሰው ልብ ውስጥ ሀያል ናቸው። ቃል ያፈርሳል፤ ደግሞ ሰውን ከወደቀበት አንስቶ የማይቻል የተባለውን እውን ያደርጋል። በአርሰናል ቤት የሆነውም ይህ ነው!

ባለፉት ሳምንታት አርሰናል በተለይም በቦርንመዝና በማንቸስተር ሲቲ ተረቶ፣ ተስፋ ቆርጦና አንገቱን ደፍቶ በነበረበት በዚያ በፈተና ወቅት... አይደክሜው የቡድኑ ሁለገብ ተጫዋች ዴክላን ራይስ የቡድን አጋሮቹን የልብ ስብራት ተመልክቶ በታላቅ ወኔ ጮኸ። “Hey... It's not done!” አላለቀም!” አለ💪

“..አላለቀም” ቀላል ትመስል ነበር። ነገር ግን በውስጧ ፅናት፣ ትዕግስት፣ ራስን ማመንና እስከመጨረሻው የመታገል አይበገሬነትን የያዘች የውስጥ እሳት ነበረች። የምትፋጅ🔥

“It's not done” የሚለው የራይስ መሪነትና ቃል በፈጠረው ተአምር አርሰናል ሽንፈቱን ጠግኖ፣ ጎል ሳይቆጠርበት ተከታታይ ድሎችን አስመዝግቦ ወደ ስኬት ማማው ተመለሰ።
መመለስ ብቻ አልነበረም ከ22 አመታት በኋላ የእንግሊዝ ሻምፒዮንም ሆነ 🏆

የራይስ ንግግር በታሪክ ውስጥ ስማቸው ከደመቀ ታላላቅ ሰዎች ሃሳብ ጋር ተሰልፏል፡፡👇

ከኔልሰን ማንዴላ፦

“It always seems impossible Until it's done - እስኪሳካ ድረስ ሁሉም ነገር የማይቻል ይመስላል” ፣

ከቤዝ ቦሉ ዮጊ ቤራ፦ “It ain’t over till it’s over! እስኪያልቅ ድረስ አያልቅም”

ከዊንስተን ቸርችል፦ Success is not final, failur is not fatal, It is the courage to continue that counts - ስኬት መጨረሻ አይደለም፤ ውድቀትም ጥፋት አይደለም፤ ዋናው ነገር ትግሉን የመቀጠል ድፍረቱ ነው” ከሚሉ ታሪካዊ ንግግሮች እንደ አንዱ ሆኗል፡፡

“It's not done ” ከእግር ኳስ በላይ... ለሕይወታችን!

ሰው በሚደክምበት ጊዜ ጡንቻው ብቻ ሳይሆን መንፈሱም ይደክማል። ዛሬ በዓለማችን ላይ ብዙ የተሰበሩ ልቦችና ተስፋ የቆረጡ ነፍሳት አሉ። እነዚህ ሁሉ የሚፈልጉት ገንዘብ ብቻ አይደለም።

የሚያነሳና የሚያበረታታ ትክክለኛ ቃል እንጂ!

“አልችልም” የሚል ሰው መንገዱን በራሱ ይዘጋል።
“እሞክራለሁ” የሚል ግን ለራሱ የስኬት በር ይከፍታል።

ያጋጠመህ ውድቀት እንጂ የሕይወትህ ጉዞ ገና አላለቀም! ሕልምህ አልሞተም፣ ተስፋህም አልደበዘዘም።

በአርሰናል ቤት “It's not done” ወደ “Done” ተቀይሮ ዋንጫው እንደተሳመ ሁሉ... አንተም በሕይወትህ ድል ታደርጋለህ!

ከረባት መሳዩ የሸፍጥ መዝጊያ እና የኔትውልድ የቤትስራ -----የምቀኛ ሰፈር ልጅ እና የስልጣን ጥማት ያነወረው ብሔራዊ ክህደት ፤ድንበር ማካለል "ኧረ ውይይይይ" ያሰኛል።💀ለኢትዮጵያ የባህር...
05/04/2026

ከረባት መሳዩ የሸፍጥ መዝጊያ እና የኔትውልድ የቤትስራ
-----
የምቀኛ ሰፈር ልጅ እና የስልጣን ጥማት ያነወረው ብሔራዊ ክህደት ፤ድንበር ማካለል "ኧረ ውይይይይ" ያሰኛል።
💀
ለኢትዮጵያ የባህር በር ባለመኖሩ ምክንያት የምትከፍለው ዋጋ ከቀጥታ ክፍያ በላይ የኢኮኖሚዋ ማነቆ ብቻ ሆኖ ሳይሆን ዘላለማዊ ሃገር እና ትውልድን መግደል ነው።

1. የቀጥታ የወደብ አገልግሎት ወጪዎች (Direct Costs)
ኢትዮጵያ የጅቡቲን ወደብ ስትጠቀም በየቀኑ እና በየወሩ የምትከፍላቸው የተለያዩ ክፍያዎች አሉ።

እነዚህም፦

ሀ. የመርከብ ማቆሚያና የማራገፊያ ክፍያ ፤ (Stevedoring & Shore Handling) ዕቃዎች ከመረከብ ላይ ወርደው መሬት እስኪያርፉ የሚከፈል ከፍተኛ ዶላር።

ለ. የኮንቴይነር መቆያ (Demurrage):

ዕቃዎች በወቅቱ ከወደብ ካልወጡ በየቀኑ የሚታሰብ ቅጣት። ይህ ክፍያ ብቻውን በየዓመቱ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ይፈጃል።

ሐ. የወኪል አገልግሎቶች (Forwarding Fees):
በጅቡቲ በኩል ለሚሰሩ የጉምሩክና የትራንዚት ወኪሎች የሚከፈል ክፍያ።

2. የሎጂስቲክስና የትራንስፖርት ውስብስብነት (Logistics Burden) የባህር በር አለመኖር የንግድ ሰንሰለቱን ረጅም እና ውድ ያደርገዋል።

መ. የመንገድ ትራንስፖርት ጥገኝነት:-

ወደ 95% የሚሆነው የሀገሪቱ ንግድ በጅቡቲ ኮሪደር ላይ የተንጠለጠለ ነው። ይህም ለመንገድ ጥገና፣ ለነዳጅ እና ለከባድ መኪናዎች መለዋወጫ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ያንረዋል።

ሠ. የጊዜ መባከን:-

ዕቃዎች ከወደብ ተነስተው አዲስ አበባ እስኪገቡ ያለው ረጅም ጊዜ የንግድ እንቅስቃሴውን (Inventory turnover) ያቀዘቅዘዋል። ይህም ነጋዴዎች ባላቸው ካፒታል ብዙ ጊዜ ደጋግመው እንዳይነግዱ ያደርጋቸዋል።

3. በኢንዱስትሪና ግብርና ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ

ረ. የግብርና ግብዓቶች ዋጋ መጨመር:-

ማዳበሪያና ኬሚካሎች በወቅቱና በዝቅተኛ ዋጋ አለመግባት በምርታማነት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል።

ሰ. የወጪ ንግድ ተወዳዳሪነት:-

ለምሳሌ አንድ የኢትዮጵያ ምርት (እንደ ቡና ወይም ጨርቃጨርቅ) የአውሮፓ ገበያ ላይ ሲደርስ፣ ከባህር በር ክፍያና ከትራንስፖርት ውድነት የተነሳ ዋጋው ይጨምራል። ይህም የባህር በር ካላቸው ሀገራት ጋር ለመወዳደር አስቸጋሪ ያደርገዋል።

4. ስልታዊና ጂኦፖለቲካዊ ተጽዕኖ (Strategic Risks)

ሸ. የአንድ አማራጭ ስጋት፦

ሀገሪቱ በአንድ ወደብ ላይ ብቻ ጥገኛ መሆኗ ለብሔራዊ ደህንነትና ለኢኮኖሚው ስጋት ነው። በወደቡ ላይ የሚፈጠር ማንኛውም መስተጓጎል (የሰራተኞች አድማ፣ የቴክኒክ ብልሽት ወይም ፖለቲካዊ አለመረጋጋት) የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ሙሉ በሙሉ ሊያቆመው ይችላል።

ቀ. የውጭ ምንዛሬ እጥረት፦
በየዓመቱ የሚከፈለው ከ3 እስከ 4 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ በቀጥታ ከሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ላይ የሚቀነስ በመሆኑ፣ ለሌሎች የልማት ስራዎች (ለፋብሪካዎች ጥሬ ዕቃና ለመድኃኒት ግዢ) የሚውለውን የገንዘብ መጠን ያጥባል።

5. "Landlocked" የመሆን የስነ-ልቦና እና የኢንቨስትመንት ተጽዕኖ
ብዙ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ሲያደርጉ "የባህር በር የላትም" የሚለውን እንደ ትልቅ አደጋ (Risk) ይቆጥሩታል። ይህም ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት (FDI) በከፍተኛ ሁኔታ እንዳያድግ እና እንዳይስፋፋ እንቅፋት ይሆናል።

በአጠቃላይ በእነዚህ እና ሌሎች ተጨማሪ ምክንያቶች የባህር በር አለመኖር ለኢትዮጵያ "የድህነት ግብር" (Tax on development) እንደመክፈል ይቆጠራል።

ይህ የተቀነባበረ ችግር ካልተቀረፈ የሀገሪቱ ለእድገት ለምታደርገው ጉዞ ሁሌም ፈታኝ ሆኖ ይቀጥላል።
---
ቀይባሕር ለኢትዮጵያ -ኢትዮጵያ የቀይባሕር ‼️
#አሰብ
#ቀይባሕር
#ቀይባሕርለኢትዮጵያ
#ኢትዮጵያየቀይባሕር

05/03/2026

ሻዕቢያ ገና በ1983 አንድ ብሎ ወገኖችችን ከአሰብ ሲያባርር በዚህ መልኩ ነበር ፤ አሳዛኙ ደግሞ አዲስ አበባ ያለው የሻዕቢያ ወኪል ህወሓት አላውቃችሁም ማለቱ ነው።
#ኢትዮጵያ #አሰብ #ቀይባሕር

ሕልመኛው ታዳጊ ገና በልጅነቱ በሰማይ የሚበሩ አውሮኘላኖችን ሲመለከት ትኩረቱን ይስቡት ነበር። ወላጆቹን ስለ አውሮኘላኖች አዘውትሮ ይጠይቅም እንደነበር ይናገራል። ከጥያቄ አልፎ ግን ያለውን ...
04/22/2026

ሕልመኛው ታዳጊ

ገና በልጅነቱ በሰማይ የሚበሩ አውሮኘላኖችን ሲመለከት ትኩረቱን ይስቡት ነበር። ወላጆቹን ስለ አውሮኘላኖች አዘውትሮ ይጠይቅም እንደነበር ይናገራል። ከጥያቄ አልፎ ግን ያለውን ተሰጥኦ ከሰፈር የሚያገኛቸውን የወዳደቁ ዕቃዎችን በመጠቀም የፈጠራ ክህሎቱን "ሀ" ብሎ ጀመረ፤ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኤሮ ስፔስ ኢንጅነሪንግ የሁለተኛ ዓመት ተማሪው አማኑኤል መኳንንት።

በየቀኑ እየጠየቀ የሚያገኘውን ምላሽ ወደ ተግባር በመለወጥ በካርቶን አውሮፕላን አስመስሎ በመሥራት ሕልሙን ዕውን የማድረግ ሥራውን ጀምሯል። ከዚያም የባትሪ ድንጋይ በመጠቀም የሚንቀሳቀስ መኪና የሚመስል ትንሽ ሞዴል ፈጠራ መሥራቱን ነግሮናል።

እያደገ ሲመጣ ከትምህርቱ ጎን ለጎን መረጃዎችን ከዩቲዩብ በመሠብሠብ ክህሎቱን ማሳደጉን ገልጾልናል። ፈጠራውንም አስቀጥሏል።

በወቅቱ ግን የፈጠራ ሥራውን መስሪያ ቁሳቁስ ለመግዛት ገንዘብ እንዳልነበረው አውስቷል። ከዚያም በትርፍ ሰዓቱ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ሥራዎችን በመሥራት ገንዘብ ማግኘቱን የሚናገረው ተማሪ አማኑኤል ባገኘው ገንዘብ መስሪያ ቁሳቁስ በመግዛት በሪሞት የሚንቀሳቀስ አውሮፕላን የፈጠራ ውጤትን ዕውን አድርጓል።

ከብዙ ጥረት በኋላ አኹን ላይ የልጅነት ሕልሙ እያደገ በሪሞት የሚንቀሳቀሱ ሰው አልባ አውሮኘላኖችን እየሠራ የፈጠራ ሥራውን እያሳደገ ይገኛል።

በፈጠራ ሥራውም ከተለያዩ ተቋማት ዕውቅና ማግኘቱን ገልጿል። ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በሚያደርግለት እገዛም የተሻሉ የፈጠራ ሥራዎች እየሠራ መኾኑን ተናግሯል። የወላጆቹ ድጋፍ ከፍተኛ መኾኑን የሚገልጸው ተማሪ አማኑኤል "አኹንም የማሳካው ሕልም አለኝ" ይላል።

ለወደፊትም የፈጠራ ተሰጥኦ ያላቸውን ልጆች ለማበረታታት፤ በግብርናው ዘርፍ ለኬሚካል ርጭት የሚያገለግሉ በሪሞት የሚንቀሳቀሱ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመሥራት ወደ ገበያ ለማቅረብ አልሟል። ይህ ደግሞ የአርሶ አደሮች ጊዜ፣ ገንዘብ፣ ጉልበትን ለመቆጠብ እና ጤንነቱን ለመጠበቅ ድርሻው የጎላ እንደሚኾን ነው የተናገረው።

ለአብነት ተማሪ አማኑኤልን አነሳን እንጂ በተለያዪ ዘርፎች በርካታ ሕልም ያላቸው ታዳጊዎች አሉ። እነዚህ ታዳጊዎች የሀገሪቱን ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ዕውን ለማድረግ ተስፋ ተጥሎባቸዋል። እንደነዚህ አይነት የፈጠራ ሥራዎች ወደ ተግባር እንዲለወጡ ማድረግ እንደሚገባም ተማሪ አማኑኤል ተናግሯል።

የፈጠራ ሥራዎች የማኅበረሰቡን ችግር ቀላል እንዲያደርጉ የሚመለከተው አካል የሚያደርገውን ክትትል እና ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቋል።

አሚኮ

Address

6395 Little River Turnpike Alexandria, VA 22312
Alexandria, VA

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gulilat Geletaw Aschenaki. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Featured

Share