12/05/2024
ቅዱስ ቁርዓን የማን ቃል (ንግግር) ነው?
ሱረቱ ሐ ሚም አል-ሰጅዳህ 41:2–(ይህ ቁርአን) እጅግ በጣም ርኅሩኅ በጣም አዛኝ ከሆነው (አላህ) የተወረደ ነው።
“ከአለማት ጌታ የተወረደ ነው።” (ሱረቱል አል ዋቂዐህ 80)
✔ቅዱስ ቁርአን የአላህ ንግግር (ከላመሏህ) ነው።
✔ቅዱስ ቁርአን ቃላቱንና ፍቺውን አጠቃሎ የያዘ የአላህ (ሱወ) ቃል (ንግግር) ነው::
✔ ከአላህ (ሱወ) የተወረደ (የተላለፈ) ፍጡር ያልሆነ የፈጣሪ ቃል ነው ።
ቅዱስ ቁርዓን ለእኛው ውዱ ነብይ ሙሀመድ (ሰአወ) ከአላህ (ሱወ) የተሰጠ እውነተኛ ለመሆናቸው ማረጋገጫ የሆነ ተአምር (ሙእጅዛ) ነው ::
እስከቂያማ (ትንሳኤ) ድረስም በአላህ (ሱወ) ሙሉ በሙሉ የተጠበቀ ነው :: ከቁርአን ውስጥ አንድንም ነገር የተስተባበለ ጉድለት ወይም ጭማሬ ወይም ማዛባት በጭራሽ የለበትም።
ቁርአን የአሏህ ቃል ነዉን By Dr Zakir Naik Amahric
Downlod p1Mp3▶ http://goo.gl/c0u1AE
P2 Downlod Mp3▶ http://goo.gl/9lP3rD
P1 Youtub▶ https://youtu.be/bsEMWf_dN2Y
P2 Youtub➤ https://youtu.be/XS_NTBHaBFc
ቅዱስ ቁርአን የአላህ(ሱወ) ቃል መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም!! እንዴት ካሉም ማስረጃችን እነሆ ….
————————————–
“ከአለማት ጌታ የተወረደ ነው።” (አል ዋቂዐህ 80)
አል-በቀራህ 2:2–ይህ መጽሐፍ (ከአላህ ለመኾኑ)
ጥርጥር የለበትም፤ ለፈራህያን** መሪ ነው፡፡
(** አላህን ለሚፈሩ)
ሱረቱ አል-ሰጅዳህ 32:2–የመጽሐፉ መወረድ ጥርጥር
የለበትም፤ ከዓለማት ጌታ ነው።
“እኛ ቁርዓንን ባንተ ላይ ማውረድን እኛው አወረድነው።” (አል ኢንሣን 23)
“ያ ፉርቃን በባሪያው ላይ ለአለማት አስጠንቃቂ ይሆን ዘንድ ያወረደው(አምላክ) ክብርና ጥራት ተገባው።” (አል ፉርቃን 1)
“እኛ ቁርአኑን እኛው አወረድነው እኛም ለሱ ጠባቂዎች ነን።” (አል ሂጅር 9)
“ከአጋሪዎች አንዱ ጥገኝነት ቢጠይቅ የአላህ ቃል ይሰማ ዘንድ አስጠጋው… ” (አል ተውባ 6)
ሱረቱ አልሹዐ 26:5–ከአልረሕማንም ዘንድ፣ አዲስ
የተወረደ ቁርአን አይመጣላቸውም፤ ከርሱ የሚሸሹ ቢሆኑ እንጂ።
————————————–
“ወደ እናንተም ገላጭ የሆነ ብርሃን “ቁርዓን” አወረድን” (አል ኒሳእ 174)
መፅሀፉም ለሁሉም ነገር አብራሪ መሪም እዝነትም ለሙስሊሞች አብሳሪ ሆኖ ባንተ ላይ አወረድነው “(አል ነህል 89)
“መፅሀፉም ለሁሉም ነገር አብራሪ መሪም እዝነትም ለሙስሊሞች አብሳሪ ሆኖ ባንተ ላይ አወረድነው።” (አል ነህል 89)
“ከቁርአንም ለምእመናን መድሃኒት እዝነት የሆነ እናወርዳለን።” (አል ኢስራእ 82)
”እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ(ቁርዓን) በእርግጥ መጣችላችሁ።” (ዩኑስ 57)
”ሙሉ የሆነ ጥበብ በተሞላበት ቁርአን(መጣቻቸው) ግን አስፈራሪዎቹ አይብቃቁም።” (አል ቀመር 5)
ሱረቱ አል-ነምል 27:6–አንተም ቁርአንን ጥበበኛና ዐዋቂ
ከሆነው (ጌታህ) ዘንድ በእርግጥ ትሠጣለህ።
—————————————
ሱረቱ ዩሱፍ 12:3–እኛ ይህንን ቁርአን ወደ አንተ በማውረዳችን በጣም መልካም ዜናዎችን በአንተ ላይ እንተርክልሃለን፤ እነሆ ከርሱ በፊት (ካለፉት ሕዝቦች ታሪክ) በእርግጥ ከዘንጊዎቹ ነበርክ።
—————————————
”ያሲን ጥበብ በተመላበት ቁርኣን እምላለሁ።” (ያሲን 1-2)
ሱረቱ ሙሐመድ 42-2 –እነዚያም ያመኑ፣ በጎዎችንም
የሠሩ በሙሐመድ ላይም በተወረደው እርሱ ከጌታቸው ሲሆን እውነት ስለ ሆነ ያመኑ ከነርሱ ላይ ኃጢያቶቻቸውን
ያብብሳል፤ ሁኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል።
47:9–ይህ እነሱ አላህ ያወረደውን ስለጠሉ ነው፤ ስለዚህ ሥራዎቻቸውን አበላሸባቸው።
47:26–ይህ እነሱ ለነዚያ አላህ ያወረደውን ለጠሉት በነገሩ ከፊል እንታዘዛችኋለን ያሉ በመሆናቸው ነው፤ አላህም መደበቃቸውን
ያውቃል።
—————————————
ሱረቱ አል- ረዕድ 13:1–አ. ለ. መ. ረ (አሊፍ ላም ሚም ራ)
(1) ይህች (አናቅጽ) ከመጽሐፉ አንቀጾች ናት፤ ያም ከጌታህ ወዳንተ የተወረደው እውነት ነው፤ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች
አያምኑም።
—————————————
“ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን… ”
(አል-ማኢዳህ 48)
ሱረቱ ሐ ሚም አል-ሰጅዳህ 41:2–(ይህ ቁርአን) እጅግ በጣም ርኅሩኅ በጣም አዛኝ ከሆነው (አላህ) የተወረደ ነው።
—————————————
“እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ዘንድ በእርግጥ አስረጅ መጣላችሁ ወደ እናንተም ገላጭ የሆነን ብርሃን(ቁርአንን) አውርደን።” (አል ኒሳል 174)
ሱረቱ አል-ሒጅር 15:9–እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡
እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡
————————————–
ሩህ(የህይወት መንፈስ)ቁርዓንን አወረድን ይላል።
“እንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን(ቁርኣንን) አወረድን።” (አል ሹራ 52)
ሱረቱ ሁድ 11:1–አ.ለ.ረ. (አሊፍ ላም ራ፤ ይህ
ቁርአን) አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰከኩ፣ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው፤ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ
(የተወረደ) ነው።
————————————–
ሱረቱ አል-አንዓም 6:7–ባንተም ላይ በወረቀት የተጻፈን
መጽሐፍ ባወረድንና በእጆቻቸው በነኩት ኖሮ እነዚያ የካዱት ሰዎች «ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም» ባሉ ነበር፡፡
————————————–
“አንቀጾቹ የተብራሩ የሆነ መፅሀፍ ነው። አረብኛ ቁርአን ሲሆን ለሚያውቁ ህዝቦች(የተብራራ) ነው። አብሳሪና አስፍራሪ ሲሆን(ተወረደ) አብዛኞዎቻቸውም ተዉት እነሱም አይሰሙም።” (አል ፋሲለት 3-4)
“እርሱ የከበረ ቁርአን ነው።” (አል ዋቂዐህ 77)
ሱረቱ አል-አሕቃፍ 46:2–የመጽሐፉ መውረድ አሸናፊ ጥበበኛ
ከሆነው አላህ ነው ::
—————————————
ሱረቱ አል-ጃሢያ 45:2–የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ፣ ጥበበኛ
ከኾነው አላህ ነው።
————————————–
ሱረቱ አል-አዕራፍ 7:2–(ይህ) ወደ አንተ የተወረደ መጽሐፍ
ነው፤ በደረትህም ውስጥ ከርሱ ጭንቀት አይኑር፤
—————————————
ሱረቱ አል-ፉርቃን 25:1–ያ ፉርቃንን (1) በባሪያው ላይ፣
ለዓለማት አስፈራሪ ይሆን ዘንድ፣ ያወረደው (አምላክ)፣ ክብርና ጥራት ተገባው።
—————————————-
ሱረቱ አል-ዱኻን 44:5–ከኛ ዘንድ የሆነ ትእዛዝ ሲሆን (አወረድነው) እኛ (መልክተኞችን) ላኪዎች ነበርን።
—————————————-
ሱረቱ አል-ዐንከቡት 29:48–ከርሱ በፊትም መጽሐፍን
የምታነብ በቀኝህም የምትጽፈው አልነበርክም፤ ያን ጊዜ አጥፊዎቹ በእርግጥ በተጠራሩ ነበር።
————— ————— ——–
ሱረቱ አል- አሕዛብ 33:2–ጌታህም ወደ አንተ የሚወርደውን
ተከተል፤ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነውና።
————— ————— ——–
አል-ዙመር 39:1–የመጽሐፉ መወረድ፣ አሸናፊው ጥበበኛው ከሆነው አላህ ነው።
39:2–እኛ ወደ አንተ መጽሐፉን በውነት (የተመላ) ሲሆን አወረድነው፤ አላህንም ሀይማኖትን እርሱ ብቻ ያጠራህ ሆነህ
ተገዛው።
ሱረቱ ጣሀ 20:2–ቁርአንን፣ ባንተ ላይ እንድትቸገር አላወረድንም።
20:3–ግን አላህን ለሚፈራ ሰው መገሰጫ
ይሆን ዘንድ (አወረድነው)።
20:4–ምድርንና የላይኛዎቹን ሰማያት ከፈጠረ አምላክ ተወረደ።
ሱረቱ ኢብራሂም 14:1–አ.ለ.ረ. (አሊፍ ላም ራ፤ ይህ
ቁርአን)፤ ሰዎችን በጌታቸው ፈቃድ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን፤ አሸናፊ ምስጉን ወደሆነው ጌታ መንገድ ታወጣ ዘንድ
ወዳንተ ያወረድነው መጽሐፍ ነው።
————— ————— ——–
ሱረቱ አል ከህፍ 18:1–ምስጋና ለአላህ ለዚያ መጽሐፉን
በውስጡ መጣመምን (1) ያላደረገበት ሲኾን በባሪያው ላይ ላወረደው ይገባው።
ሱረቱ አል-ሰጅዳህ 32:2–የመጽሐፉ መወረድ ጥርጥር
የለበትም፤ ከዓለማት ጌታ ነው።
32:3–ይልቁንም ቀጠፈው ይላሉን?
አይደለም፤ እርሱ ከጌታህ ዘንድ የኾነ እውነት
ነው፤ በርሱ ከአንተ በፊት አስፈራሪ (ነቢይ)፤
ያልመጣባቸውን ህዝቦች ልታስፈራራበት
(ያወረደልህ ነው)፤ እነርሱ ሊመረምሩ
ይከጅላልና።
ሱረቱ አል-ፉርቃን 25:32 እነዚያ የካዱትም፦ ቁርአን በርሱ
ላይ ለምን በጠቅላላ አንድ ጊዜ አልተወረደም? አሉ፤ እንደዚሁ
በርሱ ልብህን ልናረጋ፣ ( ከፋፍለን አወረድነው)፤ ቀስ በቀስ
መለያየትም ለየነው።
ሰላምም ቀጥታን በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡* (ጣሃ 47)
☞
Like ☑ Comment ☑ Share ☑