T KDM

T KDM

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from T KDM, Education, Jeddah.

07/11/2021
24/10/2021

ሞባይል ስልካችን በሌላ አካል መጠለፉን ወይም አለመጠለፉን በቀላሉ ማወቅ የሚያስችለን አጭር ኮድ * #21 # ነው።

ይህንን ኮድ ለመሞከር

✔ 1- ሞባይል ስልካችሁ ላይ * #21 # ብላችሁ ትደውላላችሁ። ከዚያ ልክ በመጀመሪያው ምስል ላይ እንደምትመለከቱት "Not Forwarded" የሚል ከመጣ ስልካችሁ አልተጠለፈም ማለት ነው።

✔2- ነገር ግን ሞባይል ስልካችሁ ላይ * #21 # ብላችሁ ስትደውሉ "Forwarded" የሚል መልዕክት ከመጣ ስልካችሁ ተጠልፏል ማለት ነው።

✔3- በተራ ቁጥር 2 መሰረት ሞባይል ስልካችሁ መጠለፉን ካረጋገጣችሁ በኋላ የስልካችሁ መጠለፍ ለማስቆም ሞባይል ስልካችሁ ላይ # #002 # ብላችሁ መደወል።

ሞባይል ስልካችሁ ላይ # #002 # ብላችሁ ስትደውሉ ፣ልክ በሁለተኛው ምስል ላይ እንደምትመለከቱት "Call forwarding all erase successful" የሚል መልዕክት ከመጣ ስልካችሁ ከመጠለፍ አዳናችሁ ማለት ነው።

በነገራችን ላይ ይህ ኮድ በሁሉም ስልኮች ላይ ይሰራል።

Photos from T KDM's post 15/12/2020
21/11/2020

💻 ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ እንዴት እንደሚፃፍ ያውቃሉ?ሲጽፉስ ምን ያህል ይፈጥናሉ?

❖መጀመሪያ Ge'ez 10 Software ያወረዱ እና install ያድርጉት ከዛም አማርኛ መፃፍ ስትፈልጉ power ge'ez status phonetic Unicode Mode (ፎ) ላይ ያድርጉት በ English መፃፍ ስትፈልጉ ደግሞ power ge'ez status English Mode (ኢ) ላይ አድርጉት ከዛም የሚከተሉትን ኣጭር መግላጫ በትክክል ይመልከቱ

◕ሀ➭H_ሁ➭Hu_ሂ➭Hi_ሃ➭Ha_ሄ➭Hy_ህ➭He_ሆ➭Ho

◕ለ➭L_ሉ➭Lu_ሊ➭Li_ላ➭La_ሌ➭Ly_ል➭Le_ሎ➭Lo

❖ሐ➭Shift+h_ሑ➭Shift+hu_ሒ➭Shift+hi_ሓ➭Shift+ha_ሔ➭Shift+hy_ሕ➭Shift+he_ሖ➭Shift+ho

መ➭M_ሙ➭Mu_ሚ➭Mi_ማ➭Ma_ሜ➭My_ም➭Me_ሞ➭Mo

❖ሠ➭Shift+s_ሡ➭Shift+su_ሢ➭Shift+si_ሣ➭Shift+sa_ሤ➭Shift+sy_ሥ➭Shift+se_ሦ➭Shift+so

◕ረ➭R_ሩ➭Ru_ሪ➭Ri_ራ➭Ra_ሬ➭Ry_ር➭Re_ሮ➭Ro

◕ሰ➭S_ሱ➭Su_ሲ➭Si_ሳ➭Sa_ሴ➭Sy_ስ➭Se_ሶ➭So

❖ሸ➭Shift+s_ሹ➭Shift+su_ሺ➭Shift+si_ሻ➭Shift+sa_ሼ➭Shift+sy_ሽ➭Shift+se ሾ➭Shift+so

◕ቀ፡➭Q ቁ፡➭Qu ቂ፡➭Qi ቃ፡➭Qa ቄ፡➭Qy ቅ፡➭Qe ቆ፡➭Qo

◕በ፡➭B ቡ፡➭Bu ቢ፡➭Bi ባ፡➭Ba ቤ፡➭By ብ፡➭Be ቦ፡➭Bo

◕ተ፡➭T ቱ፡➭Tu ቲ፡➭Ti ታ፡➭Ta ቴ፡➭Ty ት፡➭Te ቶ፡➭To

◕ ቸ፡➭C ቹ፡➭Cu ቺ፡➭Ci ቻ፡➭Ca ቼ፡➭Cy ች፡➭Ce ቾ፡➭Co

◕ነ፡➭N ኑ፡➭Nu ኒ፡➭Ni ና፡➭Na ኔ፡➭Ny ን፡➭Ne ኖ፡➭No

❏ኘ፡➭Shift +n ኙ፡➭Shift +nu ኚ➭Shift+ni ኛ፡➭Shift +na ኜ፡➭Shift +ny ኝ፡➭Shift + ne ኞ፡➭Shift +no

◕ከ፡➭Ka ኩ፡➭Ku ኪ፡➭Ki ካ፡➭Ka ኬ፡➭Ky ክ፡➭Ke ኮ፡➭Ko

❖ ኸ ☛capslock + Shift + h
ኹ ☛capslock + Shift + hu
ኺ ☛capslock + Shift + hi
ኻ ☛Capslock + Shift + ha
ኼ ☛Capslock + Shift + hy
ኽ ☛Capslock + Shift + he
ኾ ☛Capslock + Shift + ho

❏ኀ፡➭ Capslock + H ኁ፡➭ Capslock + HU ኂ፡➭Capslock + HI ኃ፡➭Capslock + HA ኄ፡➭Capslock + HY ኅ፡➭Capslock + HE ኆ፡➭Capslock + HO

❏አ፡➭Capslock X ኡ፡➭Xu ኢ፡➭Xi ኣ፡➭Xa ኤ፡➭Xy እ፡➭Xe ኦ፡➭XoDe

❖ዐ፡➭Shift +x ዑ፡➭Shift +xu ዒ➭Shift +xi ዓ፡➭Shift +xa ዔ➭Shift +xy ዕ፡➭Shift +xe ዖ➭Shift +xo

✪ወ፡➭W ዉ፡➭Wu ዊ፡➭Wi ዋ፡➭Wa ዌ፡➭Wy ው፡➭We ዎ፡➭wo

✪ዘ፡➭Z ዙ፡➭Zu ዚ፡➭Zi ዛ፡➭Za ዜ፡➭Zy ዝ፡➭Ze ዞ፡➭Zo

❏ዠ፡➭Shift + Z ዡ፡➭Shift + Zu ዢ፡➭Shift + Zi ዣ፡➭Shift +Zaዤ፡➭Shift + Zy ዥ፡➭Shift +Ze ዦ፡➭Shift + Zo

✪ፈ፡➭F ፉ➭Fu ፊ፡➭Fi ፋ፡➭Fa ፌ፡➭Fy ፍ፡➭Fe ፎ፡➭Fo

✪ ፐ፡➭P ፑ፡➭Pu ፒ፡➭Pi ፓ፡➭Pa ፔ፡➭Py ፕ፡➭Pe ፖ፡➭Po

✪ገ፡➭G ጉ፡➭Gu ጊ፡➭Gi ጋ፡➭Ga ጌ፡➭Gy ግ፡➭Ge ጎ፡➭Go

✪ደ፡➭D ዱ፡➭Du ዲ፡➭Di ዳ፡➭Da ዴ፡➭Dy ድ፡➭ዶ፡Do

❏ጠ፡➭Shift + t ጡ፡➭Shift + tu ጢ፡➭Shift + ti ጣ፡➭Shift+ta ጤ፡➭Shift + ty ጥ፡➭Shift + te ጦ፡➭Shift + to

❏ጨ፡➭Shift +c ጩ፡➭Shift +cu ጪ፡➭Shift +ci ጫ፡➭Shift+caጬ፡➭Shift +cy ጭ፡➭Shift +ce ጮ: ➭Shift +co

❏ጸ፡➭Capslock + t ጹ፡➭Capslock + tu ጺ፡➭Capslock + ti ጻ፡➭Capslock + ta ጼ፡➭Capslock + ty ጽ፡➭Capslock + t ጾ፡➭Capslock + to

❖ ፀ➭☞Capslock+Shift+t
ፁ➭☞Capslock+Shift+tu
ፂ➭☞Capslock + Shift + ti
ፃ➭☞Capslock + Shift + t
ፄ➭☞Capslock + Shift + ty
ፅ➭☞Capslock + Shift + te
ፆ➭☞Capslock + Shift + to

✪ጀ፡➭J ጁ፡➭Gu ጂ፡➭Ji ጃ፡➭Ga ጄ፡➭Gy ጅ፡➭Ge ጆ፡➭Jo

✪ቨ፡➭V ቩ፡➭Vu ቪ፡➭Vi ቫ፡➭Va ቬ፡➭Vy ቭ፡➭Ve ቮ፡➭Vo
▁▁▁▁▁▁▁▁▁▁

ቋ➭Capslock+qwa ቧ➭Capslock+bwa
ቷ➭Capslock+twa
ኟ➭Capslock +Shift+nwa
ቿ➭Capslock+cwa ሟ➭Capslock+mwa
ቷ➭Capslock+twa ጓ➭Capslock gwa
ፏ➭Capslock+fwa ሯ➭Capslock +rwa ዷ➭Capslock+dwa ቯ➭Capslock+vwa ኋ➭Capslock+hwa ዟ➭Capslock+zwa ዧ➭Capslock+Shif+zwa
ኗ➭Capslock+nwa ሏ➭Capslock+lwa
ኳ➭Capslock+kwa ሷ➭Capslock+swa
ጇ➭Capslock+jwa ጧ➭Capslock+twa

ለሌሎች እንዲደርሳቸው ያድርጉ

05/11/2020

ግፍ እና ጎርፍ
ሰሚ ካጡ የሶማሌ ተረቶች አንዱ እንዲህ ይላል፡፡
አንድ ሰው የጠፋች የአካባቢውን ግመል ፍለጋ ጫካ ይገባል፡፡ ከብዙ መከራ
በኋላ ያቺን ግመል አግኝቶ ከተማ ገባና ግመሏን ለባለቤቱ ሳይመልስ ሐሳቡን
ቀይሮ ራሱ ያልባትና ይጋልባት ጀመር፡፡ ግመሏን ከአውሬ ለማዳን ጫካ ገብቶ
የነበረው ሰውዬ እርሱ ራሱ ግመሏን መውሰዱ ብዙዎችን አስገረማቸው፡፡ ትንሽ
ቆየና ከዚያች ከአንዷ ግመል ወተት እያለበ በግመሏ ላይ ተቀምጦ እየዞረ
ለአካባቢው ሰው ወተት መሸጥ ጀመረ፡፡ ነገር ግን የግመሏ ወተት በአንድ ጊዜ
ሀብታም ሊያደርገው አልቻለምና ሌላ ነገር አሰበ፡፡ በወተቱ ውስጥ ውኃ
እየጨመረ ቀላቅሎ መሸጥ፡፡ ‹‹ሰውም ምነው የሰውየው አመሉም ወተቱም
ተቀየረሳ›› እያለ ዝም ብሎ ይገዛ ጀመር፡፡ (ይገዛ የሚለው ቃል ጠብቆ
እንዳይነበብ አሳስባለሁ)
ሰውዬውም በግመል ወተቱ ላይ ውኃን እያበዛው፤ የግመሉም ቁጥር እየጨመረ
ሄደ፡፡ እየቆየም በግመልና በግመል ወተት ከሚታወቁት የሀገሩ ነጋዎች በላይ እኔ
ነኝ ያለ፣ ቢጠሩት የማይሰማ ሀብታም ሆነ፡፡ የአካባቢው ሰዎችም ‹‹ይኼ ሰው
ትናንት ምንም አልነበረውም፡፡ የጠፋ ግመል ሊፈልግ ጫካ ገባ፤ ተመልሶ መጣ፤
ከተማ ገባ፤ በአንድ ጊዜ ተመነደገ›› እያሉ ይገረሙ ነበር፡፡ ወተት ብቻ ተሽጦ
እንዴት በሁለት ዓመት ሦስት መቶ ግመል ሊገዛ ቻለ፡፡ የሚለው የሕዝቡ ሁሉ
ወሬ ሆነ፡፡
ሰውዬው ግን ምንም አልመሰለው፤ በወተቱ ውስጥ ውኃውን እየጨመረ ቀጠለ፤
እንዲያውም እበላ ባይ ቱልቱላዎችን ቀጠረና የእርሱ ወተት ሰው ጠጥቶት
የማያውቅ መሆኑን እንዲለፍፉ አደረ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም ወተቱን
ለመልኩ ብቻ ይጨምርበትና የቀረው ውኃ ያደርገው ነበር፡፡ ‹‹ኧረ ሕዝቡ
እያማረረ ነው፤ በአንድ በኩል በድንገት ተነሥህ፤ ከተማ ገብተህ ቢጠሩህ
የማትሰማ ሀብታም ሆንክ፤ ይኼንን ስንታገሥህ ደግሞ ወተቱን ቀንሰህ ውኃውን
እያበዛህ መሸጥ ጀመርክ፡፡›› ሲሉት ‹‹ተውት ባካችሁ፣
ለመሆኑ የእኔን ወተት ከመግዛት ውጭ ሕዝቡ ምን አማራጭ አለው፤›› ይል
ነበር፡፡ በወተቱ ውስጥ የሚጨመረው ውኃም እየበዛ፣ ግመሎቹም እየበዙ ሄዱ፡፡
ግመሎቹም ሀገሩን ሞሉት፡፡ የሚያድሩበትና የሚግጡበት ልዩ የከተማ መሬት ተሰጣቸው፡፡ ወንዝ ዳር የሚገኝ ለም መሬት፡፡
አንድ ቀን ሸበሌ ወንዝ አጠገብ ግመሎቹን አሠማርቶ እርሱ አንድ ዛፍ ጥላ ሥር ሻሂ ከልጁ ጋር ይጠጣ ነበር፡፡ በዚህ መሐል ከደጋ የዘነበ ዝናብ ወንዙን ሞላውና በግራ በቀኝ ሲግጡ የነበሩትን ግመሎች ጠራርጎ ወሰዳቸው፡፡ የጎርፉን ድምጽ ሰምተው አባትና ልጅ ከጥሻው ሲወጡ ግመሎቻቸው ሁሉም ተወስደዋል፡፡
እሪታውን ሰምተው የተሰበሰቡ የሀገሩ ሰዎችም በአግራሞት የሆነውን ነገር ይመለከቱ ነበር፡፡
‹‹አየህ›› አሉት አንድ አዛውንት ‹‹ያ በወተቱ ላይ እየጨመርክ የሸጥከው ውኃ ተጠራቅሞ፣ ተጠራቅሞ ጎርፍ ሆኖ ግመሎቹን ወሰዳቸው፡፡ ግፍ እንደዚህ ነው፡፡ ሲሠራ ቀላል ይመስላል የተጠራቀመ ዕለት ግን ጎርፍ ሆኖ ይወስዳል፡፡ ተው ብንልህ አልሰማ ብለህ ነበር፤ አንተ በግፍ ግመል ስትሰበስብ የግፉ ውኃ ሌላ ቦታ እየተሰበሰበ መሆኑን ረስተህዋል፡፡ ቀን ጠብቆ ግን ይሄው ጎርፍ ሆኖ መጣ››
አሉት፡፡

02/09/2020

አንደኛው በር ሲዘጋብህ አላህ ሌላኛውን በር ይከፍትልሀል።

02/09/2020

❀━┅┉┈ያንተን ሪዝቅ ማንም አይበላውም┈┉┅━❀
አንድ ሰውዬ ነበር በአንድ ካንፓኒ ተቀጥሮ በሚሰራው
እናቱን ሚስቱን እና ልጆቹን ያስተዳድራል።
ዘውትር ስራውን በአግባብ እና በእምነት ለአለቃው
ይሰራ ነበር።
እናም አንድ ቀን ሙሉ ስራ ሳይገባ ይቀራል...
የካንፓኒው ባለቤትም፦"በርግጠኝነት ክፍያ አንሶት
ነው የቀረው ስለዚህ ነገ ሲመጣ ክፍያ
እጨምርለታለሁ።" ብሎ ይወስናል።
በነጋታው ይህ ሰው ስራ ቦታ ከመግባቱ ክፍያውን ከነ
ጭማሪው ሰጠው።ቆጥሮ ተቀበለው።
ግን ስለጭማሪው ምንም አልደነቀውም ለምን ክፍያ
እንደተጨነረለትም አለቃውን አልጠየቀም...ዝም ብሎ
ስራውን ቀጠለ።
ለተወሰኑ ቀናት እንደበፊቱ ስራውን በአግባብ ሰራ'ና
የሆነ ቀን ስራ ሳይገባ ቀረ።
አለቃው በቃ የለለ ተቆጣ የጨመረለትንም ደሞዝ
መልሶ ቀነሰበት።
እናም በማግስቱ መጣ ስራውን ጨርሶ ክፍያ
ሲቀበለው የጨመረለትን እንደቀነሰ አወቀ አሁንም
ምንም ሳይል ትቶ ወጣ።
በሰራተኛው ሁኔታ የተገረመውም አለቃው፦"ባለፈው
ክፍያ ስጨምርልህ ምንም አላልክም ዛሬም
ስቀንስብህ ምንም አይነት ጥያቄ አላቀረብክም
ለምንድነው?" ብሎ ጠየቀው።
እሱም፦"የመጀመሪያ ግዜ ስራ የቀረሁት የዛን ቀን
አላህ ልጅ ረዝቆኝ ነው(ምስቴ ወልዳ)።ያን ቀን ደሞዝ
ስትጨምርልኝ ስለጭማሪው ያልጠየቅኩህ የደሞዙ
ጭማሪ ያ አዲስ ለተወለደው ህፃን አላህ የመደበለት
ሪዝቅ እንደሆነ ስላወቅኩ ነው።
ትናንት ስራ የቀረሁት እናቴ ሞታ ነው።
አሁን ደሞ ደሞዝ ስትቀንስብኝ ዝም ያልኩት ያ ከዚህ
በፊት ትበላው የነበረው የእናቴ ሪዝቅ በሷ መሞት
ምክንያት አላህ አቋርጦት እንደሆነ ስላወቅኩ
ነው።"ብሎ መለሰለት።
❀━┅┉┈ሱብሀን አላህ┈┉┅━❀

02/09/2020

አስተማሪ #ታሪክ

@ለሌሎች ሰዎች በምትቆፍረው ጉድጓድ
እንዳትወድቅ ጥንቃቄ አድርግ !!

ከሚስቱ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት የተነሳ ሚስቱን
በያዘው ዱላ ይመታት ጀመር እርሷን መግደል ሳይፈልግ
በአጋጣሚ ሂወቷ አለፈ
በተከሰተው ነገር በእጅጉ ተደናገጠ ፍርሀት ተሰማው
ከቤተሰቦቿ ከሚደርስበት ቅጣት ለማምለጥ ምክኛት ቢፈልግም ሊያገኝ አልቻለም

ከቤቱ በፍጥነት ወጣ ወደ አንድ የሚያውቀው ሰው ዘንድ ሄደና የሆነውን ነገር አጫወተው ሚስቱን ለመግደል ሳያስብ እንደገደላት ነገረው ከገባበት አጣብቂኝ ውስጥ እንዲያስወጣው መላ ይዘይድለት ዘንድ ጠየቀው

ሰውየውም አንድ መልከ መልካም ወጣት ሰው ፈልግና ለእንግድነት ወደ ቤትህ ጋብዘው

ከዚያም አንገቱን ቆርጠህ የሚስት አስክሬን አጠገብ ጣለው
ለሚስትህ ቤተሰቦቿ ይህን ወጣት በሚስቴ ላይ ዝሙት ሲሰራ አገኘሁት ራሴን መቆጣጠር አቅቶኝ ሁለቱንም ገደልኻቸው በል አለው

ሰውየው በመፍትሄው ሀሳብ ተስማምቶ በር ላይ ቁጭ ብሎ የሰውን መምጣት ይጠባበቅ ጀመር አንድ መልከ መልካም ወፈር ያለ ወጣት ሲመጣ ለእንግድነት ቤቱ እንዲገባ ጠየቀው
ቤቱ ሲገባ ወዲያው ገደለው እንደተባለው አደረገ

የሚስቱ ቤተሰቦች ሲመጡ ሁለት አስክሬን ተመለከቱ
ሚስቴ ላይ ዝሙት ሲሰራ አገኘሁት ራሴን መቆጣጠር አቅቶኝ ገደልኻቸው አላቸው
በእጅጉ አዘኑ ትተውት ሄዱ

መፍትሄውን የነገረው ሰው ልጅ ነበረው

የዛን ቀን ወደ ቤቱ አልመጣም ነበር አባት ተጨንቆ ሚስቱን ወደ ገደለው ሰው ቤት ሄደ
የነገረውን ማምለጫ ዘዴ መተግበሩን ጠየቀው
ሚስቱን የገደለውም ሰው ምክሩን ተግባራዊ እንዳደረገ ነገረው
የገደልከውን ወጣት አሳየኝ አለው የተገደለውን ወጣት ጀናዛ ሲመለከት የራሱ ልጅ ነበር አባቱ የመፍትሄ የማምለጫ መንገድ ብሎ ሚስቱን ለገደለው ሰው በመከረው ምክር ሰበብ ተገድሎ ነበር

======================

ኢማም አልይ ቢን አቡ ጧሊብ ረዲየላሁ አንህ እንዲህ ብሎ ነበር ድንበር አላፊ የሆነችን ሰይፍ የሳለ ሰው በሳለው ሰይፍ ይገደላል ለወንድሙ ጉድጓድን የቆፈረ ሰው በቆፈረው ጉድጓድ ይወድቃል የሌሎች ሰዎችን ነውር የከፈተ ሰው የቤቱ ነውር ይከፈታል::

02/08/2020

በአንድ ሰው የግል ጉዳይ መግባት ሀሜት ነው። በቂያማህ ቀን በጣም ከሳሪዎች ማለት ሀሜተኞች ናቸው። ተራራ የሚያህል ሀሰና ይዘው ይመጣሉ። አላህም መልካም ስራቸውን ለታማው ሰው ሰጥቶ ጀነት ያስገባዋል፥ የእሱን ወንጀል ደግሞ ለሀሜተኞቹ አሸክሞ ጀሐነም ይከታቸዋል።

ነፍሱንም ለማይጠቅም የሚያነውረውንም ለማይጎዳው ዝባዝንኬ መልካም ስራውን ማጣት የሚፈልግ ካለ ወንድሙን ይማ። መጥፎ ወሬን ሲሰማ አጅር የፈለገ ደግሞ ወንድሙን በመልካም ይጠርጥር። አላህ እንዲህ ብሏልና፦

«ወሬውን በሰማችሁት ጊዜ ምእምናንና ምእምናት በጎሶቻቸው ለምን ደግን ነገር አልጠረጠሩም?»
(ኑር 12)

Want your school to be the top-listed School/college in Jeddah?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address


Jeddah