11/09/2026
ገንዘብ አስቸኳይ ሆኖባችሁ ወይም ለቢዝነሳችሁ ማሳደጊያ ማስያዣ አጥታችሁ ተቸግራችኋል? በሀገራችን ያለ ምንም ማስያዣ (Collateral-free) ብድር በማቅረብ ላይ ከሚገኙ ተቋማት ውስጥ ፦
🏦 አበዳሪ ተቋማቱና የብድር አማራጮቻቸው
1. ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ (Coopbank): በ'ምቹ' አፕሊኬሽን አማካኝነት ግንባር ቀደም ሆኖ እያበደረ ይገኛል። ጥሩ የሂሳብ እንቅስቃሴ፣ ንግድ ፍቃድ እና መታወቂያ ካላችሁ በቀላሉ ብድር ማግኘት ትችላላችሁ።
2. አቢሲኒያ ባንክ: በ'አፖሎ' (Apollo) አፕሊኬሽን የባንክ እንቅስቃሴያችሁን መሰረት አድርጎ እስከ 100,000 ብር ድረስ ያበድራል።
3. ዳሽን ባንክ: ከቴሌብር ጋር በመተባበር 'መላ' በተሰኘው አገልግሎት የ10 ቀን፣ የ20 ቀን፣ የ45 ቀን እና እስከ 6 ወር የደሞዝ ብድር አማራጮችን አቅርቧል።
4. ስንቄ ባንክ: በተመሳሳይ ከቴሌብር ጋር በመተባበር 'ዋቢ' በተሰኘ አገልግሎት አጭር ጊዜያዊ ብድሮችን ይሰጣል።
5. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE): በ CBE Fast loan, በሲቢኢ ብር (CBE Birr) እና በቴሌብር በኩል ተመሳሳይ ያለማስያዣ የብድር አማራጮችን አዘጋጅቷል።
6. አዋሽ ባንክ: 'ጥላ' በተሰኘው የዲጂታል መተግበሪያ ከቴሌብር ጋር በመቀናጀት ፈጣን ብድር ያቀርባል።
7. የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት: በቡድን ዋስትና (Group Guarantee) መልክ ያለምንም ማስያዣ ብድር ማግኘት የምትችሉባቸው ተቋማት ናቸው።
📋 ብድሩን ለማግኘት የሚያስፈልጉ ኮመን መስፈርቶች
~ ጥሩ የብድር ታሪክ (Credit History): የወሰዱትን ብድር በወቅቱ የሚመልሱ ከሆነ የብድር መጠኖት እያደገ ይሄዳል።
~የአካውንት እንቅስቃሴ: ባንኮች አቅማችሁን የሚመዝኑት በሂሳብ እንቅስቃሴያችሁ (Transaction) ስለሆነ ይህ በጣም ወሳኝ ነው።
~ ህጋዊ ሰነዶች: የታደሰ ንግድ ፍቃድ ወይም መታወቂያ።
⚠️ እንደ ማሳሰቢያ
ከባንኮች በዲጂታል የምታገኙት ያለ ማስያዣ ብድር ወለዱ በጣም ከፍተኛ ነው። ስለዚህ ይህን ብድር በጣም አዋጭ ለሆነ ቢዝነስ ወይም እጅግ አስቸኳይ ለሆነ ችግር ብቻ ተጠቀሙበት እንጂ፤ የቅንጦት እቃዎችን ለመግዛት እንዳትጠቀሙበት እንመክራለን!
👇 እናንተስ ያለምንም ማስያዣ ብድር ለማግኘት ከነዚህ ውስጥ የትኛውን ትመርጣላችሁ? እስኪ ኮሜንት ላይ አጋሩን።
(ጠቃሚ መረጃዎችን በቀጣይም ለማግኘት ፔጁን Like እና Follow ማድረጎን አይርሱ!)