22/04/2026
Canaan Jerusalem ከነዓን እየሩሳሌም
22/04/2026
Jerusalem
להשכרה
לטווח ארוך
ביפו ד' ת"א ברח' סומקן
3 חדרים מטופחת
קומה ג'
מרכזית ונגישה לתחבורה ציבורי,רכבת הקלה וקרובה לים.
לפרטים נוספים: 0503653311
ከ150 አመት በኋላ ዛሬ በህይወት ካለነው ሰዎች አንዳችንም በህይወት አንገኝም።
ዛሬ ላይ ከምንታገልላቸው ነገሮች 70 በመቶ የሚሆኑት ከ150 አመት በኋላ አንዳቸውም ለምልክት እንኳ አይገኙም፡፡ፈጽመው ይጠፋሉ ይረሳሉ፡፡
እስኪ ወደ ኋላ 150 አመት እንሂድ፡፡ወቅቱ 1872 ገደማ ነው የሚሆነው፡፡ያኔ የሰው ልጅ እንደ እቃ በአደባባይ ተደርድሮ የሚሸጥበት ወቅት ነበር፡፡
በወቅቱ ብርቅ የነበረውን የፊት መስታወት ለማግኘት ሲሉ የገዛ ዘመዶቻቸውን የሸጡ ሰዎች ዛሬ የታሉ? መስታወትንስ ዛሬ ላይ እንደ ሀብት የሚያስበው ማን ነው?
ማንም ጨው ወይም ጌጥ ወይም ሌላ ነገር ለማግኘት ሲሉ የተሻሻጡ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡
ዛሬ ላይ እነዚያ ሰዎች የሞቱላቸው የገደሉላቸው የተካካዱባቸው የተሻሻጡላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ይህ ነው የሚባል የረባ ዋጋ ያላቸው አይደሉም፡፡
በጊዜው ግን ለሰው ልጅ የሞትና የህይወት ልዩነት ነበሩ፡፡የሰው ልጅ በየጊዜው የሚታገልላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ዛሬ ላይ ዞር ተብለው ሲታዩ በጣም የሚያስቁ ናቸው፡፡
አሁን አሁን ላይ ዘመኑ የኢንተርኔት በመሆኑ ኢንተርኔት ትዝታችንን ያስቀምጥልናል ብለን እናስብ ይሆናል፡፡ግን ይህም አስተማማኝ አይደለም።
ማጠቃለያው፥ ህይወትን ቀለል አርገህ ኑር፡፡ምንም ሆነ ምንም ዘላለም የሚኖር የለም፥ ከዚህች ምድር በህይወት የሚወጣ ሰውም የለም፡፡
ዛሬ ልትሞትለት እና ልትገድልለት የተዘጋጀኸው መሬት ከዚህ ቀደምም ብዙዎች ተጋድለውለት ሞተው ጭራሽ እንዳልነበሩ ሁሉ ተረስተዋል፡፡
ከ150 አመታት በኋላ ዛሬ አንተ እንደ ትልቅ ሀብት የምታያቸው አብዛኞቹ ነገሮች ምንም ፋይዳ የሌላቸው ተራ ቁሶች ይሆናሉ፡፡
እና ምን ለማለት ነው ፥ ፍቅር ይግዛን ፥ መጠላለፍ ከጀርባ መወጋጋት መቀናናት መፎካከር ይቅርብን፡፡ህይወት ከማንም ጋር የምታደርገው ፉክክር አይደለችም፡፡
ቀደምንም ዘገየንም መጨረሻችን መቃብር ነው፡፡
ቅድሚያ ለሰብዓዊነት!
Priority for Humanity!
Amazing
Click here to claim your Sponsored Listing.