Fekad Menga

Fekad Menga

Partager

Informations de contact, plan et itinéraire, formulaire de contact, heures d'ouverture, services, évaluations, photos, vidéos et annonces de Fekad Menga, École, Paris.

25/06/2023
20/06/2023

ነጋዴው ፦ ''የነዳጅ ዋጋ ጨመረ'' በተባለ ማግስት ፣ ሌላው ቀርቶ የእንቁላል ዋጋ ሳይቀር በእጥፍ ይጨምርብናል። ለምን ስትለው ''ነዳጅ ጨመረ!'' ይልሃል። '' ዶሮ የምታምጠው በነዳጅ ነው እንዴ? ''ብለህ እንኳ መጠየቅ አትችልም። ጨዋታው ''ብትገዛ ግዛ ፣ አቅም ከሌለህ ተወው'' ብቻ ነው!

ገሀነም አስቀድሞ ቦታ የተያዘለት የኛ ሀገር አከራይ ደግሞ እንኳን ምክንያት አግኝቶ መሽቶ በነጋ ቁጥር ኪራይ መጨመር መገለጫው ነውና ''ፕሮፐርቲ ታክስ'' የሚል ወሬ ገና መወራት እንደጀመረ የቤቱን ኪራይ በእጥፍ ሰቀለው። 'ለምን' ስትል ''እስከዛሬ የምገብረው የጣራ ብቻ ነበር አሁን የግድግዳም ክፈሉ ተብሏል!>> ይልሃል!

ከሁሉም በላይ ግን ኢትዮጵያ ወህኒ ቤት ሆናበት በኑሮ ውድነት የሚሠቃየውን ከ2.4 ሚሊየን በላይ የሚሆን የመንግስት ሰራተኛ ሳስብ የምሬን ነው እንባ ሁሉ ይተናነቀኛል!

ጤፍ 2ሺ ሲሸጥም 10ሺ ሲሸጥም ደመወዙ ያው ነው። አንድ ክፍል ቤት በ500 ብር ሲከራይም 5ሺ ሲገባም ገቢው ባለበት ቆሟል። ለልጆቹ ት/ቤት 2 መቶ ሲከፍልም 1000 ሲገባም ገበያው እንጂ ገቢው ፈቅ አላለም። ሽንኩርት ፣ በርበሬ ፣ ዘይት ፣ ዳቦ ፣ ትራንስፖርት ፣ ልብስ ፣ ...... ኧረ ስንቱ ....!😭

Via - ዘሪሁን ገሠሠ

15/06/2023

ኧር ጉድ ነው


ቲማቲም በኪሎ 90 ብር ገባ❗️
ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ
ቲማቲም ለመብላት ቅርጫ እንግባ ወይ🤒

15/06/2023


ቲማቲም በኪሎ 90 ብር ገባ❗️
ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ
ቲማቲም ለመብላት ቅርጫ እንግባ ወይ🤒

13/06/2023

ጨነቀኝ ምን ላድርግ

11/06/2023

++ እንደ ግንደ-ቆርቁር ምቀኛ የለም! ++
❖ ❖ ❖ ❖

በምድራችን ካሉ እንስሳቶች እንደ ግንደ-ቆርቁር ምቀኛ የለም። ግንደ ቆርቆር ሕይወቱን የሚኖረው በምቀኝነት ነው። ጥርሶቹ ወደ መርዘነት ቢቀየሩ አንድ ግንደ ቆርቁር 40 የሚሆን የእባብን መርዝ መሸከም ይችላል ይላል ፖርቹጋላዊ ሳይንቲስት ስቶፈን ዲርቴስ። ግንደ ቆርቁር መኖሪያ ቤቱን ለመሥራት ለሦስት ወር ያለ እረፍት በሹል አፉ ሲቆረቁር ይኖራል። በ4ተኛ ወሩ ቤቱን ለምስጥ አስረክቦ ሌላ ቤቱን ለመቆርቆር ይሰደዳል። ይህ ምቀኛ አራዊት ዘለዓለም እንደቆረቆረ የሚኖረው ጓደኞቹን ላለማስጠጋት ባደረበት የምቀኝነት በሽታ ነው። በዚህ ምድር ላይ እንደምቀኝነት አይነት ክፉ በሽታ የለም። ምቀኛ ዘለዓለም እንደተሰቃየ ይሞታል። ግንደ ቆርቁርም እንደቆረቆረ በምሰጥ ተባሮ አንድ ቀን ሞቶም በምስጥ ተበልቶ ይበሰብሳል።

የሰው ልጅ ሕይወትም እንዲሁ ነው። የሰውን ልጅ መጥላትና መመቅኘት መግፋት ማሰቃየት በሽታ ቢሆንም እረፍት የሚያገኙት ሲሞቱ ነው። አሁን ላይ በብሔርና በእምነት በጎጥ በጥላቻ እየለዮ ሰውን ያህል ፍጡር የሚያሰቃዮት ሁሉ ሰው መሆናቸው እንጅ ያው ግንደ ቆርቁር ናቸው። አይበቃኝም የሚል ስሜት ያለው ስግብግብ ሁሉ ልክ እንደ ግንደ ቆርቁር እራሱን ያሰቃያል እንጅ መጨረሻው መሸነፍ ነው። እናም ወገኖቼ እርስበርስ መገፋፋትን የመሰለ መርዘኝነታችንን እናቁም። እንደ ግንደ ቆርቁር የሆናችሁ ሰዎችም ምቀኛውን ግንደ ቆርቁር ሆነን ከመኖር እራሳችንን እናውጣው። ኢትዮጵያ ሰፊ መሆኗን ስንቀበል ነው አንድ እርምጃ ወደፊት የምንራመደው። ክልሌ ወረዳዬ ፡ ከተማዬ ብለን ስንስገበገብ ኖረን መጨረሻው ውርደት ተከናንቦ መሳቂያ መሆን ነው። ከዚህ አይነቱ በሽታ እራሳችንን ማላቀቅ አለብን። ከዚህ በሽታ ሳንላቀቅ ስለ ልማትና አንድነት ሥልጣኔን መመኘት እራስን ማታለል ነው፡፡

እግዚአብሔር በጎ ልቦናውን ያድለን

ካነበብኩት አካፈልኳችሁ ከተማራችሁበት ለሌላው ያካፍሉ

07/06/2023

ህይወት በተሻለ መንገድ ለመረዳት ወደ 3 ቦታዎች መሄድ አለብህ:
* 1. ሆስፒታል *
* 2. እስር ቤት *
* 3. መቃበር *
ሀብታም ሰው መስኮቱን ተመለከተና አንድ ድሃ ሰው አንድ ነገር
ከቆሻሻ መጣያው ውስጥ ሲመርጥ አየ ። እርሱም እንዲህ አለ "ተመስገን
አምላኬ ድሀ እንኳ አልሆንኩ አለ"።
:
ድሃው ሰው ዘወር ብሎ ተመለከተና ራቁቱን በጎዳና የሚራመድ
ሰው አየ ። እርሱም እንዲህ አለ "ተመስገን አምላኬ እብድ እንኳ አልሆንኩ
አለ"።
:
እብዱ ሰውየ ወደ ፊት ተመለከተ እና አንድ አምቡላንስ አየ
አምቡላሱን ላይ በሕመም ምክንያት የሚሰቃይና የሚያለቅስ በሽተኛ አየ ።
እርሱም እንዲህ አለ " ተመስገን አምላኬ በሽተኛ እንኳ አልሆንኩ አለ"።
:
ከዚያም የታመመው ሰውየ በሆስፒታል ውስጥ የሞተውን ሰው
ሬሳ ተመለከተ ። እርሱም እንዲህ አለ " ተመስገን አምላኬ እንኳ አልሞትኩኝ
ምክንያቱም የሞተ ሰው እግዚአብሔር አያመሰግንምና አለ"። ዛሬ ስለ ሁሉም
የእግዚአብሔር በረከቶች እና ምሕረት ለምን አናመሰግንም ?
:
:
በሆስፒታሉ ውስጥ ከጤና በላይ ምንም ነገር እንደሌለ
ትገነዘባለህ ።
:
በእስር ቤት ነፃነት በጣም ውድ ነገር እንደሆነ ትገነዘባለህ ።
:
በመቃብር ውስጥ ሕይወት ምንም ዋጋ እንደሌለው ትገነዘባለህ

:
የዛሬ የምንሄደው መንገድ የነገ የሕይወታችን መሰረት ነው ።
:
ስለዚህ ትሁት እና አመስጋኝ ሁን ።

ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪ ይመስገን !!!
ሼርር ሼርር.....ሼርር ሼርር ሼርር.....ሼርር ሼርር

🌷ከደራሲያን አለም ፔጅ የተወሰደ 🌷

ብሩህ ቀን

Vous voulez que votre école soit école la plus cotée à Paris ?

Cliquez ici pour réclamer votre Listage Commercial.

Emplacement

Type

Site Web

Adresse

Paris