Wolkite Poly Technic College & Satellite Institute

Wolkite Poly Technic College & Satellite Institute Transferring up to date information about training ,technology transfer and industry extension activ

 !! ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1501ኛው የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላምና በጤና አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን እየገለፀ በዓሉ የ...
24/08/2026

!! ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1501ኛው የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላምና በጤና አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን እየገለፀ በዓሉ የመልካም ስነ-ምግባር፣ የርህራሄና የይቅርታ በመሆኑ ሁላችንም የእርስ በርስ ፍቅራችንን በማጠናከርና በመከባበር እንድታከብሩት ልባዊ ምኞታችንን እንገልፃለን!! 💚💚💚💚💚💚💚

!!💚💚💚

 ።=============================ነሐሴ 18/2018(ወልቂጤ)፡ የወላይታ ሶዶ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ የልዑካን ቡድን አባላት በወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ በመገኘ...
24/08/2026


=============================
ነሐሴ 18/2018(ወልቂጤ)፡ የወላይታ ሶዶ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ የልዑካን ቡድን አባላት በወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ በመገኘት ኮሌጁ ተግብሮ ባሳካው የISO 21001፡2025(Educational Organization Management System) ትግበራ ላይ የልምድ ልውውጥ አካሂደዋል።

በልምድ ልውውጡ ወቅት የኮሌጁ የISO 21001፡2025ን ትግበራ በኮሌጁ ISO ትግበራ Task Force አባላትና በት/ት ክፍል ተጠሪዎች አማካኝነት ለልዑካን ቡድኑ በዝርዝር ገለፃና ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል፤ በተጨማሪም አጠቃላይ በግቢው በመዘዋወር ከትግበራ ጋር ተያይዞ የተከናወኑ ተግባራትን ተዟዙረው ተመልክተዋል።

በመጨረሻም የልዑካን ቡድን አባላትም በጉብኝታቸው ያገኙት ተሞክሮ በራሳቸው ተቋም ISO 21001፡2025ን በተሳካ ሁኔታ ለመተግበር ጠቃሚ ግብዓት እንደሚሆን ገልጸው፤ ይህንን እድል ላመቻቸላቸው የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ ከልብ የመነጨ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
-----------------------------
!
!
-----------------------------

Facebook፡- https://www.facebook.com/wolkite poly technic college & satellite institute
Website:- https://wptc.gov.et/
Telegram:- https://t.me/wptc2000
!

 ።==============================ነሀሴ 14/2018 (ወልቂጤ)፡ የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ በሥራ ዘመኑ ለ2ኛ ዙር የሙያ ብቃት ምዘና ሰጠ።የሙያ ብቃት ...
20/08/2026


==============================
ነሀሴ 14/2018 (ወልቂጤ)፡ የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ በሥራ ዘመኑ ለ2ኛ ዙር የሙያ ብቃት ምዘና ሰጠ።

የሙያ ብቃት ምዘናው የተሰጠው ለሥራ ስምሪት ወደ አረብ ሀገራት ለሚሄዱ ከ260 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ሲሆን ለምዘናውን ከመቅረባቸው በፊት በማሰልጠኛ ካሪኩለሙ መሠረት ወደ ሥራው ዓለም ሲሰማሩ ባላቸው ሙያ ብቁና ተወዳዳሪ ሆነው እንዲቀርቡ የሚያግዟቸውን ክህሎቶች በበቂ ሁኔታ በንድፈ-ሀሳብና በተግባር ሥልጠና ወስደው ዝግጁ የሆኑ ናቸው።

በአጠቃላይ ኮሌጁ ዜጎች የተሟላ የሙያ ሥልጠናና የብቃት ምዘና እንዲወስዱና ብቃት እንዲኖራቸው ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።
-------------------------------
!
!
-----------------------------

Facebook፡- https://www.facebook.com/wolkite poly technic college & satellite institute
Website:- https://wptc.gov.et/
Telegram:- https://t.me/wptc2000
!

 !!==============================ነሀሴ 14/2018 (ወልቂጤ)፡ የዶዮ ገና ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የማኔጅመንት አካላት በወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት...
20/08/2026

!!
==============================
ነሀሴ 14/2018 (ወልቂጤ)፡ የዶዮ ገና ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የማኔጅመንት አካላት በወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ በመገኘት የልምድ ልውውጥ አደረጉ።

በልምድ ልውውጡ ትኩረት የተደረገባቸው ወቅት በሰው ሀይል ልማትና የተቋም አቅም ግንባታን፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት፣ የመያድ ረጂ ድርጅቶች የማፈላለግ ተግባራት እንዲሁም በኮሌጃችን ውጤታማ ስለሆነው የISO ትግበራ እና በውስጥ ገቢ ማመንጨት ላይ ተሞክሮ የማካፈል ስራ ተሰርቷል።

የልዑካን ቡድኑ በተለያዩ ኃላፊዎች ገለፃ ከተደረገላቸው በኋላ የኮሌጁን ግቢ፣ ሾፓችና እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ጉብኝት እንዲያደርጉ ተደርጓል።

በመጨረሻም የልምድ ልውውጡ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በቆይታቸው መደሰታቸውንና በተጨባጭ ሊተገበሩ የሚችሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን ማግኘታቸውን ገልጸው፤ ኮሌጁ ሳተላይት ላደረገላቸው አቀባበልና ትብብርና ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
-------------------------------
!
!
-----------------------------

Facebook፡- https://www.facebook.com/wolkite poly technic college & satellite institute
Website:- https://wptc.gov.et/
Telegram:- https://t.me/wptc2000
!

 ።===============================ነሀሴ 13/2018 (ወልቂጤ)፡ የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ ጋር በመ...
20/08/2026


===============================
ነሀሴ 13/2018 (ወልቂጤ)፡ የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር በሴቶች ሞዴስ አዘገጃጀት ላይ ስልጠና መስጠት ጀመረ።

ስልጠናው ዓላማው በሴቶች የግል ንጽህናና ጤና ዙሪያ ያለውን ፍላጎት በአካባቢው አቅም ለመሙላት፣ በአካባቢው የሚገኙ ግብዓቶችን በመጠቀም ጥራት ያላቸው የሴቶች ሞዴሶችን ማዘጋጀት የሚችሉ ሰልጣኞችን ለማፍራት እንዲሁም የሙያ ክህሎትን በማሳደግ የገቢ ማመንጫና የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማበረታታት ነው።

ስልጠናውን እየሰጡ የሚገኙት ከኮሌጁ ተመልምለው በፌዴራል ደረጃ የተዘጋጀው የአሰልጣኞች ስልጠና (Training of Trainers) በመውሰድ የተዘጋጁ መምህራን ሲሆኑ፣ ይህም ስልጠና በተገቢው ሙያዊ አቅምና በተግባር ተኮር አቀራረብ እንዲሰጥ አስችላል።

በስልጠናው እየተሳተፉ የሚገኙት ከጉራጌ እና ከየም ዞኖች ተመልምለው የመጡ በአጠቃላይ 15 ሰልጣኞች ናቸው። ሰልጣኞቹ በስልጠናው ወቅት የሴቶች ሞዴስ አዘገጃጀት መርሆዎችን፣ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችንና መሳሪያዎችን፣ የአሰራር ሂደቶችን፣ የምርት ጥራትና ንጽህና መስፈርቶችን እንዲሁም ምርቱን በተገቢው ሁኔታ ማዘጋጀትና ማሸግ የሚያስችላቸውን እውቀትና ክህሎት ያዳብራሉ።

ስልጠናው ለተከታታይ 10 ቀናት የሚሰጥ ሲሆን፣ በንድፈ-ሀሳብና በተግባር የተቀናጀ አቀራረብ በመከተል እየተሰጠ ይገኛል። በዚህም ሰልጣኞቹ በክፍል ውስጥ የሚያገኙትን የንድፈ-ሀሳብ ዕውቀት በተግባራዊ ልምምድ በማጠናከር የሴቶች ሞዴስን በራሳቸው ማዘጋጀት የሚያስችላቸውን ብቃት እንዲያዳብሩ ይደረጋል።

ኮሌጁም በስልጠናው የሴቶችን የጤናና የንጽህና ፍላጎት ለማሟላት ከሚደረጉ ጥረቶች በተጨማሪ፣ የሙያ ክህሎት ልማትን፣ የሥራ ዕድል ፈጠራን፣ የገቢ ማመንጨትንና በአካባቢው የሚገኝን የሰው ሀይል አቅም መጠቀምን ለማጠናከር የራሱን የሙያ ማስተላለፊያ ሚና እየተወጣ ይገኛል።
-------------------------------
!
!
-----------------------------

Facebook፡- https://www.facebook.com/wolkite poly technic college & satellite institute
Website:- https://wptc.gov.et/
Telegram:- https://t.me/wptc2000
!

❤❤❤
18/08/2026

❤❤❤

❤️❤❤
18/08/2026

❤️❤❤

 ።=============================ነሐሴ 12/2018 (ወልቂጤ)፡ የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ የ2018 የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አካል የሆነ በወልቂጤ...
18/08/2026


=============================
ነሐሴ 12/2018 (ወልቂጤ)፡ የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ የ2018 የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አካል የሆነ በወልቂጤ ከተማ የአንድ አቅመ-ደካማ ቤተሰብ የመኖሪያ ቤት ግንባታ በይፋ አስጀመረ።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ስርገማ እንዳሉት በዞኑ የሚገኙ ኮሌጆች የማህበረሰቡን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ አበረታች የበጎ ፍቃድ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑን ገልፀው፣ ዛሬ ኮሌጁ ያስጀመረው የአቅመ-ደካማ ወገኖች መኖሪያ ቤት ግንባታ የዚሁ አካል መሆኑንና በአጠቃላይ የበጎ ፍቃድ ተግባራትም የሰብዓዊነት፣ የአብሮነትና የመረዳዳት እሴቶችን የሚያጎለብቱ በመሆናቸው ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስገንዝበዋል።

የወልቂጤ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ አቅም ግንባታ ኃላፊ አቶ አስራት ታደለ በበኩላቸው በክረምት በጎ ፍቃድ በ17 ፓኬጆች እየተተገበሩ መሆኑን ገልፀው፣ ለአቅመ-ደካማ ወገኖች ቤቶች መገንባትና መጠገን አንዱ መሆኑን አስረድተው፤ ከተማ አሰተዳደሩ የቤት ግንባታው በቶሎ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግና፣ ድጋፍ ላደረገው ኮሌጁ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በመጨረሻም የኮሌጁ ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲን በበኩላቸው፣ ኮሌጁ ከሙያ ስልጠና በተጨማሪ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች ላይ በንቃት እየተሳተፈ መሆኑን ገልፀዋል። ዛሬ የተጀመረው ቤትም ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንደሚገነባ ገልፀው፤ በአጠቃላይ ኮሌጁ የጀመረውን ይህን የበጎ ፍቃድ ተግባር በማጠናከር፣ “ከሙያ ወደ ማህበረሰብ፣ ከእውቀት ወደ ተግባር!” በሚል መንፈስ ለተቸገሩ ወገኖች የተሻለ ኑሮ ለመፍጠር እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

በአጠቃላይ በመርሐ-ግብሩ ላይ የወልቂጤ ክላስተር ኮሌጆች ዲኖች፣ የወልቂጤ ከተማ አመራሮች፣ ከሰላም ሚኒስትር የተገኙ የልዑካን ቡድን አባላትና የኮሌጁ ምክትል ዲኖችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
-----------------------------------
!
!
-----------------------------

Facebook፡- https://www.facebook.com/wolkite poly technic college & satellite institute
Website:- https://wptc.gov.et/
Telegram:- https://t.me/wptc2000
!

 ።==============================ነሀሴ 02/2018 (ወልቂጤ)፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት፣ በጉራጌ ዞን የሚገኙ የወልቂጤ ክላስተር ኮሌጆች በ2018 ዓ.ም. በዲ...
08/08/2026


==============================
ነሀሴ 02/2018 (ወልቂጤ)፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት፣ በጉራጌ ዞን የሚገኙ የወልቂጤ ክላስተር ኮሌጆች በ2018 ዓ.ም. በዲግሪ እና ከደረጃ 1 እስከ 5 ባሉ የሥልጠና መርሃ-ግብሮች ሥልጠናቸውን ያጠናቀቁ በአጠቃላይ 1,041 ሰልጣኞችን በጋራ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመረቁ።

የምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ በወልቂጤ ክላስተር ሥር በሚገኙ ሰባት ኮሌጆች በተለያዩ የሥልጠና መስኮችና ደረጃዎች በመማር ሥልጠናቸውን በብቃት ያጠናቀቁ ሰልጣኞችን በአንድ የጋራ መድረክ ለማስመረቅ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የኢንዱስትሪ ተወካዮችና ባለቤቶች፣ የኮሌጆች አመራሮችና መምህራን፣ የተመራቂዎች ቤተሰቦች እንዲሁም የተጋበዙ እንግዶች በብዛት ተገኝተው ታድመዋል።

በተለይም የወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ በዲግሪ እና ከደረጃ 1 እስከ 5 ባሉ የሥልጠና መርሃ-ግብሮች ሥልጠናቸውን በብቃት ያጠናቀቁ 402 ሰልጣኞችን ማስመረቅ ችሏል። ይህም ኮሌጁ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ዘርፍ ብቁ፣ ተግባራዊ እውቀትና ክህሎት የተላበሱ የሰው ኃይል ለማፍራት እያከናወነ ያለውን ሚና የሚያሳይ ነው።

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የክልልና የጉራጌ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው ለተመራቂ ሰልጣኞች፣ ለኮሌጆች አመራሮችና ለመላው የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤተሰብ የማበረታቻ መልዕክትና የሥራ አቅጣጫ ሰጥተዋል። አመራሮቹ ተመራቂዎች በሥልጠና ወቅት ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በተግባር በመተርጎም ለራሳቸው፣ ለቤተሰባቸውና ለሀገራቸው የሚጠቅም የሥራ እንቅስቃሴ እንዲያከናውኑ አሳስበዋል።

በተጨማሪም የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና የሀገርን የሰው ኃይል አቅም በማጎልበት፣ የሥራ ዕድልን በመፍጠር፣ ምርታማነትን በማሳደግና የኢንዱስትሪውን የብቃት ፍላጎት በማሟላት የሚኖረውን ወሳኝ ሚና በማጉላት የሥልጠና ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች በቅንጅት እንዲሠሩ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

የወልቂጤ ክላስተር ኮሌጆች በተለያዩ የሥልጠና ደረጃዎች ያስመረቋቸው ሰልጣኞች የሰለጠኑትን የንድፈ ሀሳብ ከተግባራዊ ሥልጠና ጋር በማጣመር የሥራ ዓለምን ለመቀላቀልና የራሳቸውን የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል እውቀትና ክህሎት አግኝተዋል።

የምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ በከፍተኛ የደስታና የኩራት ስሜት የታጀበ ሲሆን፣ የክልልና የዞን አመራሮች፣ የተለያዩ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች አመራሮች፣ የመንግሥት ተቋማት ተወካዮች፣ የኢንዱስትሪ ባለቤቶችና ተወካዮች፣ የትምህርትና የሥልጠና ተቋማት አመራሮች፣ የተጋበዙ እንግዶች እና በርካታ የተመራቂ ሰልጣኞች ቤተሰቦች በመገኘት ለተመራቂዎቹ ደስታቸውን አጋርተዋል።

የወቂጤ ክላስተር ኮሌጆች በ2018 ዓ.ም. 1,041 ሰልጣኞችን በተለያዩ የሥልጠና ደረጃዎች ማስመረቃቸው በጉራጌ ዞንና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብቁ የሰው ኃይል ልማትን ለማጠናከር የሚያበረክቱትን አስተዋፅኦ የሚያሳይ ነው። በቀጣይም ኮሌጆቹ ከኢንዱስትሪውና ከሌሎች የሥራ ዕድል ፈጣሪ ተቋማት ጋር ያላቸውን ትስስር በማጠናከር፣ የሥልጠና ጥራትን በማሻሻልና በገበያው ፍላጎት መሠረት የተዘጋጀ ብቁ የሰው ኃይል በማፍራት ለክልሉና ለሀገር ልማት ያላቸውን አስተዋፅኦ ማሳደግ ይጠበቅባቸዋል።
---------------------------
!
!
-----------------------------

Facebook፡- https://www.facebook.com/wolkite poly technic college & satellite institute
Website:- https://wptc.gov.et/
Telegram:- https://t.me/wptc2000
!

08/08/2026

Address

Near To Wolkite Stadium
Welk'it'e

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251113301590

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolkite Poly Technic College & Satellite Institute posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Wolkite Poly Technic College & Satellite Institute:

Shortcuts

Share