If you need the best subtitle translation call me on 0912010031(Yared:-Senior article writter for some English newspapers, senior translation expert at different organizations and I have translated subtitles for over 20 Amharic movies as of now). And I am also a partener of Yezialem Habtemikael who is the Admin of this page before.
English Subtitle 4 Amharic Movies
Writing subtitles for Amharic movies
Translation
Editing and more. Translation jobs
Interpretation
Tutoring Amharic for foriegners
18/12/2015
25/11/2015
ጋዜጠኛ ወይስ የቡና ቤት አስተናጋጅ?
(አሌክስ አብርሃም)
ኢቢኤስ በተባለው የሚያቀርበው ነገር ግራ በገባው የቴሌቪዥን ጣቢያ አይን ያወጡ ማስታወቂያዎች በፕሮግራም ስም ወደህዝቡ እንዲደርሱ ሲደረጉ እየተመለከትን ነው,,,, ከእነዚህም በዋናነት "ሰሞኑን አዲስ" በሚል ፕሮግራም በየሆቴሉና መዝናኛው በመዞር በሆቴሎቹ የሚሸጠውን ምግብና መጠጥ በማሳየት የተጠመደ ፕሮግራም ዋነኛው ነው
,,,, አዘጋጇ ድግሷ እንዳማረላት ሴት ወይዘሮ ማይኳን እንደወጥ ማማሰያ ጨብጣ በድፍን አዲስ አበባ ከሆቴል ውጭ ሌላ ነገር የሌለ እስኪመስለን በየሆቴሉ ማድቤት መንጎራደድ ነበር ስራዋ,,,,,
ዛሬ ደግሞ ከቴሌቪዥን ፕሮግራምነት ይልቅ ወደቅልውጥ የተጠጋ የሚመስል ማስታወቂያ ከማሳየት አልፋ የአንድ ቢራ ፋብሪካ የለየላት መጠጥ አሻሻጭ ሁና ነበር,,,, አሳፋሪ ፕሮግራም! !
ለመሆኑ ማነው ይሄን የአየር ሰአዓትና ማይክ ለእነዚህ የጋዜጠኝነት ብቃቱም ሞራሉም ለሌላቸው ጀረሬዎች የሰጠብን? የቴሌቪዥን ፕሮግራሙ የራሱ ኤዲቶሪያል ፖሊሲ የለውም,,,, ወይስ እንደበረንዳ ማንም ቁሞ ያሻውን የሚቀባጥርበት ቤት ነው?
ይታያችሁ ቢራ ፋብሪካው በየፀጉር ቤቱ እየዞረ ፀጉር ለሚስተካከሉ ሰዎች በፀጉር አስተካካዮቹ በኩል ቢራ እንዲጠጡ ያሰብካል ,,,, ወጥመድ! ወጣቱ የት ይሂድላቸው ?
ከምር የሚያበሳጭ የሚያሳፍር ትውልድንም አገርንም ገዳይ ነገርነው,,,, መፅሔቱ ቢራ,,,, ቲቪው ቢራ,,,, መንገዱ ቢራ,,,, ስቴዲየሙ ቢራ,,,, ዘፈኑ ቢራ,,,, "በጎ አድራጎት" ተብየው ቢራ ጭራሽ ፀጉር ቤቱም ያውም በግዳጅ ቢራ,,,,,አተላ አየሩን ሞላው!!
ፀጉሩን ሊስተካከል የሄደ ሰው አንገቱ ላይ እንደደህና ሜዳሊያ የአልኮል መጠጥ ምስል የታተመበት ሽርጥ ታስሮለት እንደአሻንጉሊት በፀጉር አስተከሰካዪ እየተደባበሰ ቢራ እንዲጠጣ,,,, ከጠጣ እንደሚሸለም ሲሰበክ ይውላል! !
ይሄ ሳያንስ ይሄንኑ የአተላ ስብከት ይች ጋዜጠኛ በየፀጉር ቤቱ በመዞር ልክ ትልቅ ነገር እንደሚዘግብ ጋዜጠኛ የአተላ ጠርሙዝ ተደግፋ ትቀባጥራለች! ! ይሄ "ታላቅ " መረጃ ለህዝቡ እንዲደርስ መሆኑ ነው! !
"ይህ የማንትስ ቢራ ዘመቻ ለጊዜው በትቂት ፀጉር ቤቶች የተጀመረ ሲሆን ወደፊት " እያለች,,,,, አንዱ ፀጉር አስተካካይ በኩራት እንዲህ አለ " ከስተመሮቻችንን እዚህ ስለቢራው ስለሽልማቱ እንነግራቸዋለን , ቆስቁሰን, እልካቸዋለን ሌላ ቦታ ሂደው ይጠጣሉ,,,, አንዳንዶቹማ እዚሁ ቀዝቃዛ ቢራ ብለው ያዛሉ,,,,, " ቃል በቃል እንዲህ ነው ያለው!! "ጋዜጠኛ" ተብየዋ ትገለፍጣለች እፍረተ ቢስ ደነዝ! ስንት ወጣት ህይወ ት ላይ ስንት ሰው ትዳር ላይ መርዝ እየረጨች እንደሆነ አልገባትም! !
እንግዲህ ይሄንን መርዘኛ የትውልድ ጥፋት ለህዝብ ንቃትና መረጃ ሰጭነት ይጠቅማሉ ያልናቸው ሚዲያወች ወገባቸውን አጥብቀው ከሰበኩ የዚህ ህዝብ አስተማሪው ማነው? ፀጉር ቤት በብዛት የሚያዘወትረው ወጣት እዛም ስካር ሱስ ሲሰበክ ከምር ይሄ ነገር ዝም ይባል? ሙድ እየያዝን እስካፍንጫችን በአተላ ስንነከር ዝም እንበል?
እነዚህን ሆዳም ፍርፋሪ አሳዳጅ ለራሳቸውም ለህዝብም ግድ የሌላቸው ህሊና ቢስ የቴሌቪዥን በቀቀኖች በትምህርት ባልተሞረደ የጭፈራ ቤት ቆሻሻ ቋንቋቸው ህፃናትን ሲበክሉ ትውልዱን ሲያደነዝዙ ምናገባን ብለን ዝም እንበል???? ሌላው ቢቀር ፊት ለፊት ማውገዝ ይሄ ብልግናም ድድብናም ነው ማለት ይሳነን,,,??
የኛ ምላስ ጀግንነቱ ፖለቲካ ለመደስኮር ብቻ ነው? ህዝብ በጎርፍ በጦርነት ማለቁ ከአቅማችን በላይ ይሁን እሽ,,,, ግን ይሄን ምስኪን ህዝብ እንዴት ለእነዚህ እንጩጭ መጠጥ አሻሻጮችአሳልፈን እንስጥ? ህፃናት ወንድም እህቶቻችንን በዝምታችን እንሽጥ? ማንም የመንደር ዱርየ እየተነሳ ማይክ በጨበጠ ቁጥር አተላውን ይድፋብን?
25/11/2015
ዘመድ ጥይቃ
09/11/2015
Good to see u back.I personally wish u ALL z best!!
Tadias Magazine
By Tadias staff
Published: Friday, November 6th, 2015
New York (TADIAS) — Opening tonight the National Museum of African Art in Washington, D.C. is hosting
week-long screenings of Ethiopian independent filmmaker Haile Gerima’s most critically acclaimed films
including Adwa: An African Victory , Bush Mama , Sankofa , and Teza .
“Each screening will be followed by a panel discussion with activists, actors, journalists, and scholars,” the
museum announced.
The program, entitled Streams of a River African and African-American History and Identity in Haile Gerima’s
Films , is presented in partnership with Positive Productions Inc., Minab Arts, Humanities D.C., and the
Diverse City Fund.
In Adwa , which screens today, “Gerima uses paintings, rare historical photographs, music, recreations, and
interviews with elders to tell the story of the 1896 battle in which the Ethiopian peoples united to defeat the
Italian army.” Panelists include Kwasi Bonsou; Attorney Gabriel J. Christian and Associates, LLC & Founder
of In-iversial Development of Ras Tafari; Greg Carr Professor of African Studies, Howard University, and
Adjunct Faculty at Howard University School of Law; and Dagmawi Woubshet, Associate Professor of
African American literature at Cornell University.
ረቡኒ እና ኢየሱስ (The Jesus) film
ረቡኒ ፊልም ካየ ብኋላ ሳይሆን አይቀርም ዘነኛው የ Hollywood actor George Clooney "ከጥሩ የፊልም ፁሁፍ መጥፎ ፊልም መስራት እችላለሁ ከቀሽም የፊልም ፁሁፍ ግን ቆንጆ ፊልም መስራት አልችልም" ያለው;; እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው ፊልሙ በCinema ቤቶች የነበረውን ቆይታ ጨርሶ በእያንዳንዳችን እጅ መድረሱ ትንሽ ቆየት ቢልም በውስጥ መስመር በመጣብኝ ጥያቄ መሰረት ye filmu directorwa Kidest Yilma "ስለ ረቡኒ ፊልም የተሰማህን ማለት ትችላለህ ተፈቅደዋል" ይላል;; በነገራችን ላይ ቅድስት ይልማ ማለት ከረቡኒ ቀጥሎ : መባ : ፍቅርእናገንዘብ2 :ከእለታት... :ጢባጢቤ: የሚባሉ ስራዎችዋም የጥበብ በረከቶችዋ ናቸው;; እጅሽ የባረክ አቦ;; እኔስ ምንእላለሁ? ምንም ከማለት በቀር ብየ ነው;; ፊልሙ እ/ያውነት ይሰብካል;; ኢ/ያውነት ምንድነው? ፍቅርን ይሰብካል;; ፍቅር ምንድነው? ይተገበራል እንጂ አይነገርም;; “በእጅ ያለ ወርቅ እንደ መዳብ ይቆጠራል” የሚባለው ምሳሌ ያሳያል ረቡኒ ላይ;; ይህ ፊልም ከልጅነታችን ጀምረን እያየነው ያደግነው የእየሱስ ክርስቶስ ፊልም አመሳሱሉልኝ እማ;; ......አስታወሳችሁት? ....ይህ ...እንካን ረዘም ያለ ፀጉሩ... ጢማም. አቡጀዲድ የሚለብስ main characteru አ ...ዎ እሱ;; ይህ ፊልም ለማየት የከፈልነው መስዋእት ሳስታውስ ይገርመኛል;; አርብ ስቅለት በመጣች ቁጥር በየቤታችን TV ቢኖረንም ወደ video ቤት ነበር የምንሮጦው;; ለምን ቢባል? ወደ video ቤቱ ለመግባት መስዋእትነት ይጠይቃል;; ለእየሱስክርስቶስ መስዋእት መሆን ማለት ደግሞ እንደ ፅድቅ ይቆጠራላ;; ይክ ትዝታ ሌላ ግዜ እንመለስበታለን;; እና አደይ የምትባለውን character እንደ እየሱስክርስቶስ አድርጋቹህ ሳልዋት "የሴት አምላክ" እንደ ማለት (አምላክ ፆታ ባይነሮውም;; )
- እያንዳንድዋን dialog በምሳሌ በመሆኑ እንደነ :-
¤መልካም ለተዘራበት መልካም የሚሰጥ መሬት አለ;;
¤ሰማይ እና ምድር የቆመው በቃል ነው;;
¤ጭቃው በሸክላ ሰሪው እጅ ነው;;
¤ሰውም በአምላኩ እጅ ነው;;
¤ትክክለኛ ማሸነፍ በሰው ዘንድ የራስን ማንነት ማጋባት ነው;;
¤ውበት ቀልብን ይስባል ስብእና ግን ልብን ይማርካል;;
¤ጥሩ በልክ አይመዘንም ልክ ነው በጥሩ የሚመዘነው;;
¤የማትፈልገው ንነገር ስትሰጥ ጣልክ እንጂ ሰጠህ አይባልም;;
--ተፈጥሮን በመጋፋት የሚያመጣውን እዳ: ህመም በካንሰር ሞተች;; ፍቅርን አስተምራ :እነ ሉኡልን አንድ ላይ
አድርጋ: እንደውም አስረግዛ;; እየሱስ ክርስቶስም ፍቅርን አስተምሮ : መቻቻልን ሰብኮ : ለሰው ልጆች መኖር ሲል ሞተ;; አንዳንድ ኩፉዎች ባመጡት ሀሳብ;;
--የስምዋን አሰያየም
በቤት ውስጥ እየተጫወቱ ሳሉ አደይ እንቆቅልሽ ጠየቀች
"ስሄድ አገኘህዋት ስመለስ አጣህዋት" ብላ ስትል ኖህ (አቡሌ) ፈጠን ብሎ "አንቺ!" አላት አደይም አኮረፈች! መልሱ ግን 'ጤዛ' ነው;; እውነትም እንደ 'ጤዛ' ሆነች አደይ ዳግም ላትፈካ ዳግም አብባ ምድርን ላታስውብ እንደ ጤዛ ረገፈች;;
"አደይ
"ጠውልጋ ሳላያት ይህቺ አደይ አበባ
ለምን ትደርቃለች መስከረም ሳይጠባ!?"
እንደ ተባለው
የነ መምሩ : የነ ኖህ : ባነሳን;; ለናንተ ልተዎው;; ባጭሩ ከየእየሱስ ክርስቶስ ፊልም መነጣጠሩ ጥሩ መንገድ ይሆናቹዎል ብየ አስባለው;; እና ምን ለማለት ነው? እየሱስ ክርስቶስ ከሞት እንደተነሳ ሁሉ ረቡኒ ቁጥር 2 ብለንም መስራት እንችላለን ማለታችን ነው;;
¤የፊልሙን ሀሳብ ስለበለጠብኝ ነው ችግሮችን ያላወጣሁት ይውጣ ከተባለ ግን;;
ይቻላልን;;
23/10/2015