Pas. Daniel Mekonnen DRIM

Pas. Daniel Mekonnen DRIM North Eastern Regional President

07/10/2025
ይሄ እድል ለእናንተ ነው በመጀመሪያ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ለምትገኙ ቤተሰቦቻችን ሁሉ  እንኳን ለአዲሱ ዓመት 2018 አደረሳችሁ  እያልን   የፊታችን እሁድ መስከረም 10/2018 ...
23/09/2025

ይሄ እድል ለእናንተ ነው

በመጀመሪያ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ለምትገኙ ቤተሰቦቻችን ሁሉ እንኳን ለአዲሱ ዓመት 2018 አደረሳችሁ እያልን
የፊታችን እሁድ መስከረም 10/2018 " የአሰባበክ ዘዴ " (Homiletics) ላይ የኮርሱ ዓላማ ምን እንደሆነ መግቢያ የተሰጠ ሲሆን ሐሙስ መስከረም 15/2018 ላይ ትምህርቱ በይፋ ይጀምራል ።
አስተማሪው እግዚአብሔር በዚህ ዘመን ለምድራችን ካስነሳቸው ፍሬያማ መምህር ከሆኑቴ በቄስ ግርማ በየነ ይሰጣል ስለዚህ:-👇👇

✍️ " የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሰራተኛ ሆነህ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ"
2ኛ ጢሞ 2:15
👉 ዲቫይን ራዲያንት ቲዮሎጂካል ኮሌጅ በዲፕሎማና ድግሪ መርሐ ግብር በኦንላይን ማስተማር ጀምረናል
ስለዚህ በመንፈስ ቅዱስና በቃሉ ታጥቀንና ተዘጋጅተን እግዚአብሔር የሚያከብር ሕይወት ትውልድ የሚያንጽ ጠቃሚ ሰው ለመሆን በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ እንድትማሩ እድል በራችሁን እያንኳኳች ነው በመሆኑም ይህን ዕድል ተጠቀሙበት። እድል ሁልጊዜ አይገኝምና
መመዝገብ የምትፈልጉ በዚህ ስልክ ዛሬውኑ ይደውሉ 092 021 7243 የመመዝገቢያ ቅጽ እና የትምህርት ማቴሪያል ይላክላችኋል እግዚአብሔር ይባርካችሁ
ፓ/ር ዳንኤል መኮነን

ደረሰ! ደረሰ!! ደረሰ! በመጀመሪያ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ለምትገኙ ቤተሰቦቻችን ሁሉ  እንኳን ለአዲሱ ዓመት 2018 አደረሳችሁ  እያልን   የፊታችን እሁድ መስከረም 10/2018 ...
17/09/2025

ደረሰ! ደረሰ!! ደረሰ!

በመጀመሪያ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ለምትገኙ ቤተሰቦቻችን ሁሉ እንኳን ለአዲሱ ዓመት 2018 አደረሳችሁ እያልን
የፊታችን እሁድ መስከረም 10/2018 " የአሰባበክ ዘዴ " (Homiletics) ኮርስ እግዚአብሔር በዚህ ዘመን ለምድራችን ካስነሳቸው ፍሬያማ አስተማሪ ከሆኑቴ በቄስ ግርማ በየነ ይሰጣል ስለዚህ:-👇👇

✍️ " የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሰራተኛ ሆነህ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ"
2ኛ ጢሞ 2:15
👉 ዲቫይን ራዲያንት ቲዮሎጂካል ኮሌጅ በዲፕሎማና ድግሪ መርሐ ግብር በኦንላይን ማስተማር ጀምረናል
ስለዚህ በመንፈስ ቅዱስና በቃሉ ታጥቀንና ተዘጋጅተን እግዚአብሔር የሚያከብር ሕይወት ትውልድ የሚያንጽ ጠቃሚ ሰው ለመሆን በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ እንድትማሩ እድል በራችሁን እያንኳኳች ነው በመሆኑም ይህን ዕድል ተጠቀሙበት። እድል ሁልጊዜ አይገኝምና
መመዝገብ የምትፈልጉ በዚህ ስልክ ዛሬውኑ ይደውሉ 092 021 7243 ፓ/ር ዳንኤል መኮነን

ታላቅ የምስራች አሁኑኑ ፈጥነው ይመዝገቡዲቫይን ራዲያንት ቲዮሎጂካል ኮሌጅ በዲፕሎማና ድግሪ መርሐ ግብር በኦንላይን ማስተማር ጀምረናልስለዚህ በመንፈስ ቅዱስና በቃሉ ታጥቀንና ተዘጋጅተን እግዚ...
15/09/2025

ታላቅ የምስራች አሁኑኑ ፈጥነው ይመዝገቡ

ዲቫይን ራዲያንት ቲዮሎጂካል ኮሌጅ በዲፕሎማና ድግሪ መርሐ ግብር በኦንላይን ማስተማር ጀምረናል
ስለዚህ በመንፈስ ቅዱስና በቃሉ ታጥቀንና ተዘጋጅተን እግዚአብሔር የሚያከብር ሕይወት ትውልድ የሚያንጽ ጠቃሚ ሰው ለመሆን በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ እንድትማሩ እድል በሯን ወለል አድርጋ ከፍታለች ተጠቀሙበት። እድል ሁልጊዜ አይገኝምና
መመዝገብ የምትፈልጉ በዚህ ስልክ ዛሬውኑ ይደውሉ 092 021 7243 ፓ/ር ዳንኤል መኮነን

እግዚአብሔር ማንንም አይጥልም   ጽዮን ግን፣ “እግዚአብሔር ትቶኛል፤ ጌታም ረስቶኛል” አለች። “እናት የምታጠባውን ልጇን ልትረሳ ትችላለችን? ለወለደችውስ ልጅ አትራራለትምን? ምናልባት እርሷ...
14/09/2025

እግዚአብሔር ማንንም አይጥልም

ጽዮን ግን፣ “እግዚአብሔር ትቶኛል፤ ጌታም ረስቶኛል” አለች። “እናት የምታጠባውን ልጇን ልትረሳ ትችላለችን? ለወለደችውስ ልጅ አትራራለትምን? ምናልባት እርሷ ትረሳ ይሆናል፣ እኔ ግን እልረሳሽም። እነሆ፤ በእጄ መዳፍ ላይ ቀርጬሻለሁ፤ ቅጥሮችሽ ምንጊዜም በፊቴ ናቸው።”
ኢሳይያስ 49:14-16

ቅዳሜ የመንፈስ ቅዱስ ጉብኝት   ኢሳይያስ 60 :1-2" ብርሃንሽ መጥቶአልና፥ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፥ አብሪ። እነሆ፥ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል፤ ነ...
28/07/2023

ቅዳሜ የመንፈስ ቅዱስ ጉብኝት
ኢሳይያስ 60 :1-2

" ብርሃንሽ መጥቶአልና፥ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፥ አብሪ። እነሆ፥ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል፤ ነገር ግን በአንቺ ላይ እግዚአብሔር ይወጣል ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል፤
ነገ ሐምሌ 22/2015 ከጥዋቱ 3-8 ሰዓት በዲቫይን ራዲያንት ሚስዮናዊት ቸርች የመንፈስ ቅዱስ ጉብኝት በፓ/ር ግርማ ከበደ የጸሎትና የትምህርት ጊዜ ተዘጋጅቷል
ስለዚህ ሁላችንም ተጋብዘናል
አድራሻ :- ጉርድ ሾላ ባቡር መሻገሪያ ላይ ትህትና ህንጻ ጀርባ ባጃጅ ከሚቆሙበት ጎን ያለው ህንጻ ላይ
አገልጋይ መጋቢ ግርማ ከበደ

07/07/2022

የስኬታማነት መርሆዎች

ዳንኤል 6:28
“ስለዚህ ዳንኤል በዳርዮስ ዘመነ መንግሥትና በቂሮስ ዘመነ መንግሥት ሁሉ ኑሮው ተሳካለት።”

💖 ዳንኤል በስኬትና በሰመረ ኑሮ እንዲገኝ ያደረገው ሚስጥር ምን ይሆን?
ሕይወቱ በውጤታማነት እንዲጠናቀቅ ያበቃው ምክንያቱ ምን ይሆን? የእግዚአብሔር ሰው ዳንኤል የተለያየ የባቢሎን መንግስታት በተነሱበትና አገሪቱን በሚማሩበት ጊዜ ውስጥ በታማኝነት ያገለገለ ሰው ነበር።
ይሄም ብቻ ሳይሆን ነገስታቱ ሁሉ በዳንኤል ሕይወትና አገልግሎት ይማረኩና ይደነቁ ነበር ሁሉም ነገስታት በዚህ ሰው የሚፈሰውን ጥበብና ምክር ለመስማት ይጓጉ ነበር መገኘቱንም በብርቱ ይሹ ነበር።
ዳንኤል በሁሉም ቦታና ጊዜ ውስጥ በጣም አስፈላጊና ወሳኝሰው በዘመኑ አባባል VIP ነበር። በእድሜ እኩዮቹ እንደ role model ይታይ ነበር።
በዘመኑ ማህበራዊ ተቀባይነት ነበረው ባጠቃላይ የእረፍት ሰው ነበር።
👉 ታዲያ የኑሮው መቃናቱ ሚስጢር ፦
1ኛ. ውሳኔ
ውስጡ ያለውን ነገር በጥንቃቄ የሚጠብቅ በመብልና በጊዚያዊ ደስታ የማይዘናጋ ነገር ግን ዘለቄታ ባለው ነገር ላይ ትኩረት በመስጠት የሚኖር ሰው ነበር። ዳን1:8 “ዳንኤል ግን በንጉሡ ምግብና የወይን ጠጅ እንዳይረክስ ወሰነ ..." የምዕ.1 ቁ.8 ውሳኔ እስከ ምዕ 12:13 ድረስ አዘለቀው ““አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ፤ ታርፋለህ፤ በቀኖቹ መጨረሻም ተነሥተህ የተመደበልህን ርስት ትቀበላለህ።””

2ኛ. ጠንካራ ቁርኝት
“እርሱና ጓደኞቹ የሰማይ አምላክ ምሕረት ያደርግላቸውና ምስጢሩንም ይገልጥላቸው ዘንድ እንዲጸልዩ አሳሰባቸው።”
ዳን 2፥18
የጸሎት ህይወቱ አይነኬ ነበር በመሰዊያው አይደራደርም። ምንም ነገር ቢመጣ ያችን strong class አያስነካም ነበር። “ ዳንኤልን ሲጸልይና አምላኩን ሲማጸን አገኙት።”
ዳን 6፥11
ስለሆነም ዳንኤል ሲፈተሽ ከከበረው ከአምላኩ ህግ በቀር በሌላ ጉዳይ የማይከሰስ ፣ የማይተችና የማይነቀፍ ሕይወት ይዞ የተገኘ በተሰማራበት ቦታ ሁሉ ታማኝ የነበረ 6:1-3
3ኛ. ትሁት ሰው
በሱ ሕይወት በሚገለጠውና ከሚለቀቀው ፀጋ ምክንያት ክብርን ለራሱ የማይወስድ በነፃ የተቀበለውን ለማትረፊያነት የማይጠቀም በጥቅም ተደልሎ ከሰማይ የተገለጠለትን መልእክት በትህትና የሚሰጥ
"2: 30 “ይህ ምስጢር ለእኔ የተገለጠው፣ ከሰው ሁሉ ይልቅ ታላቅ ጥበብ ስላለኝ አይደለም፤ .."
ምን አይነት መንፈሳዊ አብርሆት ነው??? የተወደዳችሁ ስኬታማነት በትህትና ማገልገል ነው።

እኛስ ከዚህ ሰው ሕይወት ምን እንማራለን????
1. የምዕራፋችን መጀመሪያ ጠብቀን መቆምና ታማኝ መሆን
2. ብዙ ከመባዘንና ፍሬ ከሌለው ሩጫ ቆም ብለን መሰዊያችንን በማደስ አብዝቶ የእግዚአብሔርን ፊት መፈለግ
3. ለራሳችን የተሳሳተ ግምት ሳንሰጥ ሁሉንም ከእግዚአብሔር እንደተቀበልን አውቀን በትህትና ማገልገል።

👉 እንግዲህ የተወደዳችሁ ሕይወታችን ከጅማሬው ይልቅ ፍፃሜያችንን የተዋበ የሚያደርገው እነዚህን የከበሩ እሴቶች ተግባራዊ ስናደርጋቸው ነውና ነገራችን የተቃናና የሰመረ እንዲሆን ከዚህ መልዕክት ውስጥ ራሳችንን በመፈተሽ ህልውናችንን ልንታደግ እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ የምናነባቸውን ሰዎች ታሪክ እንዲፃፍ ያደረገው የኑሮአቸውን ምሳሌ እየተከተልን እንድንመስላቸውና ራሳችንንም በዚህ መንፈሳዊ ምሕዳር ውስጥ እንድንገኝ ነው።

17/06/2022
መንፈሳዊ መነቃቃት (Revival)                  እንዴት ይመጣል???        ለመንፈሳዊ መነቃቃት ወይም ለመለኮታዊ ጉብኝት መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች እንዳሉ ይታወቃል...
16/05/2022

መንፈሳዊ መነቃቃት (Revival)
እንዴት ይመጣል???

ለመንፈሳዊ መነቃቃት ወይም ለመለኮታዊ ጉብኝት መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች እንዳሉ ይታወቃል።
ልዩ የሆነ መንፈሳዊ ጉብኝት ወይም ሪቫይቫል በግለሰብ ደረጃ በቤተክርስቲያን እና በሀገር ደረጃ እንዲሆን የሰው ድርሻ ወሳኝ ነው።
ከሰው የሚጠበቀው መንፈሳዊ ርሃብ: ጥማትና ምጥ(እርግዝና) ነው
ኢሳይያስ 44:3
" በተጠማ ላይ ውኃን በደረቅም መሬት ላይ ፈሳሾችን አፈስሳለሁና፤ መንፈሴን በዘርህ ላይ በረከቴንም በልጆችህ ላይ አፈስሳለሁ፥"
በተጠማ ላይ እርካታን የሚሰጥ እግዚአብሔር ሲሆን መሻቱና ጥማቱ ግን የሰው ድርሻ ነው።
ዮሐንስ 7: 37
" .. ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል።"
ስለዚህ ሀገርችንን ትውልዳችንን ሊታደግ የሚችል መለኮታዊ ጉብኝት እንዲሆን በብርቱ ርሃብና ጥማት የአምላካችንን ፊት አብዝተን እንፈልግ
*ሉቃስ 11:10, 13
" የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልግም ያገኛል፥ መዝጊያውንም ለሚያንኳኳው ይከፈትለታል። .... በሰማይ ያለው አባት ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣቸው?
ሪቫይቫል እንዲመጣ ከላይ ያየናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ሃሳቦች በቅድሚያ መሆን ይገባዋል እነዚህ ምጥ:ርሃብና ጥማት በሌለበት ሁኔታ ጉብኝት ሊሆን አይችልም።
በ20ኛው ክ/ዘመን በታላቋ ብሪታኒያ (ስኮትላንድ) የተከሰተው መነቃቃት ህዝብን እንደ ሞገድ ወደ ቤ/ክ እንዲተምም ያደረገው ምክንያት ጆን ኖክስ የተባለ ሰው በነፍሱ ተወራርዶ እንዲህ በማለት ወደ አምላኩ ጸለዬ " ስኮትላድን ስጠኝ አለበለዚያ ግደለኝ" አለ። በተጨማሪም ሚስቱን ወይ እግዚአብሔር ይመጣልኛል አለዚያም እሬሳዬ ይወጣል " በማለት በመጾም ከእንጀራ ጋርና ከእንቅልፍ ጋር ተጣልቶ አብዝቶ በመጮኽ ስኮትላንድን ለክርስቶስ አስወረሳት።
በ1904 በዌልስ ምድር የተከሰተው ሪቫይቫል በአንድ የድሃ ቤተሰብ ከተገኘ ብዙ የትምህርት ዝግጅት በሌለው ኢቫን ሮበርትስ ምጥና ርሃብ የተነሳ ነው። አውሮፓን ያጥለቀለቀው እስከ 20 ሚሊዮን ለሚሆን ህዝብ እንደ ሰደድ እሳት የተመመ ታላቅ ጉብኝት ነው።
የተወደዳችሁ የጽሁፌ ቁም ነገር " በሚገኝበት ፈልጉት ቀርቦም ሳለ ጥሩት" ኢሳ 55:6 እንደሚል ምጥ: ርሃብና ጥማት ሲኖረን ከሰማይ እንጎበኛለን።
ሐዋ. ሥራ 2:17
" እግዚአብሔር ይላል፦ በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ጎበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ፤"
ፓ/ር ዳንኤል መኮነን

"የመንፈስ ቅዱስ እሳት "       ዘጸአት 40:38 "   በመንገዳቸውም ሁሉ በእስራኤል ቤት ሁሉ ፊት የእግዚአብሔር ደመና በማደሪያው ላይ በቀን ነበረና፥ እሳትም በሌሊት በዚያ ላይ ነበረና...
08/05/2022

"የመንፈስ ቅዱስ እሳት "

ዘጸአት 40:38
" በመንገዳቸውም ሁሉ በእስራኤል ቤት ሁሉ ፊት የእግዚአብሔር ደመና በማደሪያው ላይ በቀን ነበረና፥ እሳትም በሌሊት በዚያ ላይ ነበረና። "
ክርስትና በመንፈስ ቅዱስ ሃይልና ደስታ በማይቋረጥ ሁሌም በሃልዎቱ ውስጥ ሁነን የምንኖረው ሕይወት ነው።
በብሉይ ኪዳን ዘመን እሳት የፍርድ ምሳሌ ብቻ ሳይሆን፡ የኃይልና የክብር የድል ምሳሌ ነው። እሳቱ ይመራቸው ነበር እሳቱ ይዋጋላቸው ቅጥራቸውም ጭምር ነበረ … " እኔ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ፥ በውስጥዋም ክብርን እሆናለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። " ዘካ 2:5
እግዚአብሔር ራሱ እንደ እሳት እየተገለጠ ጠላቶቻቸውን ያጠፋቸው ነበር :- ዘዳግም 9:3
" አምላክህም እግዚአብሔር እንደሚበላ እሳት ሆኖ በፊትህ እንዲያልፍ ዛሬ እወቅ፤ እርሱ ያጠፋቸዋል፥ በፊትህም ያዋርዳቸዋል፤ እግዚአብሔርም እንደ ነገረህ አንተ ታሳድዳቸዋለህ፥ ፈጥነህም ታጠፋቸዋለህ።"

"………እግዚአብሔር ባሪያዎቹን በመንፈስ ቅዱስ እሳት ነክቶ ከአሰልቺና ከድግግሞሽ እንዲሁም ፍሬ ከሌለው ባዶ ድካም ይታደጋቸዋል።" አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ "
እብ 1:7

" ……እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤ "ማቴዎስ 3:11 .....ታዲያ መፍትሔው ወደ አጥማቂው ሁልጊዜም መቅረብ መራብና መጠማት አንኳኩ መንፈስ ቅዱስ ትቀበላላችሁ ብሏል ሉቃ 11:13
" ………በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤" ሮሜ 12:11
ከመንፈሳዊ ድንዛዜ ወጥተን ሕይወታችን በግለት እንዲቀጥል ሁል ጊዜ ትኩስ(fresh) እንዲሆን በመንፈስ ቅዱስ እሳት የተቀጣጠለ ሊሆን ያስፈልጋል
" ...ስለዚህ ምክንያት፥ እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው፥ እጆቼን በመጫኔ " 2ኛ ጢሞ 1:6
" ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና፥ መሥዋዕትም ሁሉ በጨው ይቀመማል።" ማርቆስ 9:49
ስለዚህ ትርጉም ያለው ሕይወት እና በመልካም ተፅእኖ የተሞላ ኑሮ እንድንኖር እሳቱን እንቀበል። መፍትሔ አልባ ከሆነ ንትርክና ጭቅጭቅ ወጥተን በመንፈስ ቅዱስ እሳት እንቀጣጠል።
ጥሪያችን ሰዎችን ከፍርድና ከጥፋት እሳት አውጥተን ወደ በረከትና ደስታ ወደ ሞላበት የመንፈስ ቅዱስ እሳት ማነሳሳት ነው::
እንዲህ አይነት ክብር ውስጥ ለመግባት ፍሬ ከሌለው ከማንኛውም ሕብረት ራሳችንን በመጠበቅ ከጨለምተኛ እይታ ካላቸው ራሳችንን በመጠበቅ ነው::
የተወደዳችሁ ያባቴ ብሩካን የመንፈሱንእሳት በብርቱ እንሻ
ፓ/ር ዳንኤል

✍ ጤናማ መንፈሳዊ ሕይወት                   ቅድስና  ለእግዚአብሔር (ዘጸአት 28:36)          ጤናማ ሕይወት የሚወጣው ከጤናማ ትምህርት ሲሆን እንዲሁ መንፈሳዊ ድካም የሚመ...
06/05/2022

✍ ጤናማ መንፈሳዊ ሕይወት
ቅድስና ለእግዚአብሔር (ዘጸአት 28:36)

ጤናማ ሕይወት የሚወጣው ከጤናማ ትምህርት ሲሆን እንዲሁ መንፈሳዊ ድካም የሚመጣው ደግሞ ጤናማ ካልሆነ ትምህርትና ከተሳሳተ ልምምድ ነው።
ሮሜ 6:18
".. ለተሰጣችሁለት ለትምህርት ዓይነት ከልባችሁ ስለ ታዘዛችሁ፥ ከኃጢአትም አርነት ወጥታችሁ ለጽድቅ ስለ ተገዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።
ጤናማና ውጤታማ ሕይወት የሚኖረን የእግዚአብሔርን አይነኬ ባህርይ ማለትም ቅድስና ለእግዚአብሔር የሚል ዓርማ ስንይዝ ብቻ ነው።
ቅድስና ማለት ምን ማለት ነው? አምላካችን ፍጹም ነው እንከን አልባ ነውር የሌለበት አጠቃላይ ልእልናውን ገናናነቱ እና ንጽሕናውን የሚያሳይ ነው።
ነገር ግን ቅድስና ለእግዚአብሔር የሚለው ብቻ በቂ አይደለም እናንተም ቅዱሳን ሁኑ ተብለናል። 1ጴጥ 1:15,
መቀደስ ማለት ደግሞ ከርኩሰት መለየት ከማይመጥን የሕይወት ምልልስ እና ከክፉ ልምምድ ራስን መጠበቅ ማለት ነው።
ዕብ 12 :14
" .. ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።"
👉 ጤናማ ሕይወት ከዚህ በላይም ሆነ በታች አይደለም:: ይልቁንም ቅድስና ኪዳን ነው።

🤝 አምላካችን ደግሞ ለኪዳኑ ነው ታማኝ የሆኑ ልጆቹን ይባርካቸዋል:: ኪዳኑ በረከት የመሳብ ጉልበት አለው ነገሮችንም በበጎ የመለወጥ አቅም በውስጡ ይዟል::
✈️ ስለዚህ ይሄ አምሳያ የሌለው የልዑል ኪዳን የሚታዘዙትን ያከብራል።
የቅድስና ኪዳኑን ያቃለለው ተላላው ሶምሶን!!!
😂 ለትልቅ ዓላማ የተመረጠና አቻ በማይገኝለት የጌታ ቅባት የተቀባው ሶምሶን::

🕺 በወላጆቹ ከፍተኛ እንክብካቤና ጥንቃቄ ያደገ በተለዬ ኪዳን የተጠራና የናዝራዊነት ህግ የተሰጠው
🏇ሶምሶን የስሙ ትርጓሜ ጸሀይ የሚል ሲሆን በምድሪቱ ላይ ካለው የከበደውን የ20 ዓመት የጨለማና ጭቆና ቀንበር የሚያስወግድ መሪ እንዲሆን መለኮታዊ እድል ያገኘ ነበር::
መሳፍንት 13-16
✍ እስኪ ናዝራዊነት ምንድነው የሚለውን እንይ:- ናዝራዊ ማለት ለጌታ ብቻ መሆን(መሰጠት) የሚል ፍች ያለው ሲሆን (ተው): (አትንካ): (ተለይ) ወዘተ የሚሉ መለኮታዊ ትዕዛዝ ያካተተ ከራስ ምኞትና መሻት መፋታት ነው:: ዘህ6:1-8

🕺 ለሶምሶን የተሰጡት 4ቱ ክልከላዎች

1ኛ. የሚያሰክር አለመጠጣት
2ኛ. ራሱን በምላጭ አለመላጨት
3ኛ. ሬሳ አጠገብ አለመድረስ
4ኛ. ከኪዳኑ ህዝብ ውጭ በጋብቻ አለመጠላለፍንም ያካትታል

👉 ሳምሶን ግን እነዚህን መለኮታዊ ትእዛዝ ቸል በማለቱና ወላጆቹ የነገሩትን የናዝራዊነት ኪዳን ቸል በማለት ጥሪውን አቃለለ: ብቃቱ እያለው ከባህሪ ጉድለት የተነሳ አጨራረሱ መራራ የሆነ አሳዛኝ የውድቀት ምሳሌ ሆነ::
የኖረው ኑሮ የተሰጠውን ታላቅ ተውህቦ(ስጦታ) የሚመጥን ባለመሆኑ እና ራሱን መግዛት ተስኖት በገዛ ምኞቱ ለጥፋት ተዳረገ::
" ቅጥር እንደሌላት እንደ ፈረሰች ከተማ፥ መንፈሱን የማይከለክል ሰው እንዲሁ ነው። " ምሳሌ 25:28

😭 ማብቂያ የሌለው ሴሰኝነቱ በመጨረሻም አወዳደቁን አሳዛኝ አደረገው:: በደሊላ ተደጋጋሚ ድለላ ተሸንፎ መለየት ከሚገባው ነገር ጋር ሲደራደር ለሕይወቱ ውድቀት ራሱን አሳልፎ ሰጠ::

👉 ተላላው ሶምሶን ከመለኮታዊ ጥሪው ይልቅ ለስጋዊ ፍላጎቱ ባሪያ ሆነ።
ሳምሶን ናዝራዊነቱን አቅልሎ በማየትና የከበረውን ጥሪ ያዝ ለቀቅ በማድረግ ቅባቱን አቃለለ::
🧏‍♂ ዛሬ እኛ ከሶምሶን ምን እንማራለን? ህይወታችን ሁል ጊዜ አንጸባራቂና በክብር የተሞላ ሊሆን ይገባል።
የተወደዳችሁ ቅዱሳን ለእኛም የሕይወት ዓርማችን የሆነውን ቅድስና ለእግዚአብሔር የሚለውን መርህ ይዘን እስከፍጻሜ መጓዝ ይሁንልን
❤️ ዳንኤል 12:13
" አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ፤ አንተም ታርፋለህ፥ በቀኑም መጨረሻ በዕጣ ክፍልህ ትቆማለህ።" ተባረኩልኝ የአባቴ ብሩካን ቅድስና ለእግዚአብሔር.....
ይቀጥላል...

ፓ/ር ዳንኤል መኮነን

Address

Tigray Region

Telephone

+251920217243

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Pas. Daniel Mekonnen DRIM posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Pas. Daniel Mekonnen DRIM:

Shortcuts

Share