Abergelie Wereda Education Office/አብርገሌ ወረዳ ክንድጝ ጽህፈሽ ጝን/

  • Home
  • Ethiopia
  • Sokota
  • Abergelie Wereda Education Office/አብርገሌ ወረዳ ክንድጝ ጽህፈሽ ጝን/

Abergelie Wereda Education Office/አብርገሌ ወረዳ ክንድጝ ጽህፈሽ ጝን/ ይህ ገጽ የሚስራው በአበርገሌ ወረዳ ት/ት/ጽ/ቤት ስር ባሉ ትምህርት ቤቶች የሚከወኑ ትምህርታዊ እንቅስቃሴዎቹን ሁሉ የሚስራጩበት የሚዲያ ክፍል ነው።

11/06/2026

የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ዝውውር በጥራትና በፍትሀዊነት መሰራቱ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተገለጸ፡፡
=======
ግንቦት 29//2018 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018/19 ዓም የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ዝውውር ተጠናቆ ከዛሬ ጀምሮ በየደረጃው በሚገኝ የትምህርት መዋቅር ይፋ ይሆናል፡፡
የዝውውር ሂደቱን አስመልክ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ደምስ እንድሪስ በሰጡት ማብራሪያ በክልሉ ባለፉት 3 ዓመታት በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ለ2 ዓመት ያክል ተቋርጦ የቆየው የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ዝውውር በዚህ አመት ቢሮው በወሰደው አቋም አዲስ የዝውውር መመሪያ በማዘጋጀትና የበፊቱን መመሪያ በማሻሻል በየደረጃው ለሚገኙ አካላት ግንዛቤ በመፍጠር ዝውውሩን ተግባራዊ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
ዝውውሩ ተቋርጦ መቆየቱ መምህራን መደበኛ ዝውውር እንዲሰራላቸው ሲጠይቁ መቆየታቸውን የተናገሩት ሃላፊው ከታህሳስ 30-ጥር 10 ድረስ መምህራን በት/ቤት ደረጃ ዝውውር እንዲሞሉና በወረዳና በዞን ደረጃ ተጣርቶ ወደ ክልል እንዲላክ ተደርጓል ያሉት አቶ ደምስ በክልል ደረጃ መረጃውን የማጣራት ስራ ከተሰራ በኋላም የዝውውሩን ስራ ቀድሞ ለመጀመር ታቅዶ ከ55 በላይ የዞንና የክልል የትምህርት ቢሮ ባለሙያዎችና በተመሳሳይ የዞንና የክልል መምህራን ማህበር ስራ አስፈጻሚዎች ለአንድ ወር ከ15 ቀን ጊዜ በመውሰድ ዝውውሩን ግልፅና ፍትሀዊነት በተሞላበት ሂደት መስራት ተችሏል፡፡
የዘንድሮውን የዝውውር ሂደት የተለየ የሚያደርገው የቅድመ አንደኛ፣የአንደኛና የመካከለኛ ደረጃ መምህራን ራሱን ችሎ የተፈፀመበት መሆኑ ነው።
ከቅድመ አንደኛ እስከ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዝውውር ከሞሉ መምህራንና የትምህርት አመራሮች ውስጥ 6378 መምህራንና የትምህርት አመራሮች የዝውውር ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በዝውውር ሂደቱ በከተሞች ጊዜአዊ ምደባ ተመድበው የቆዩ መምህራን ቋሚ ምደባ የተደረገላቸው መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ዝውውሩ ቀድሞ መጠናቀቁ መምህራን ከስራቸው ሳይወጡ የዝውውር ቦታቸውን አውቀው አስፈላጊ ዝግጅት እንዲያደርጉ ታሳቢ ያደረገ ሲሆን ዝውውር ላኪና ተቀባይ ወረዳዎችም የመምህራንን መረጃዎችን አደራጅቶ በመላክና በመቀበል ወረዳዎች አስፈላጊውን ትብብር ሊያደርጉ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
በዞን ደረጃ የሚሰራው የወረዳ ዝውውርና በወረዳ ደረጃ የሚሰራው የትምህርት ቤቶች ዝውውር ከሰኔ 1 እስከ 18/2018 ዓም ተጠናቆ ለመምህራን ይፋ ይደረጋል ወደ ለክልሉ ትምህርት ቢሮ ሪፖርት ይደረጋልም ተብሏል፡፡
በዝውውር ሂደቱ ቅሬታ ያላቸው መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ዝውውሩ ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ውስጥ ለወረዳው ሪፖርት በማድረግ ዞኖች የወረዳዎችን አደራጅተው ወደ ክልል ትምህርት ቢሮ እንደሚላክ ሃላፊው የተናገሩ ሲሆን በቅሬታ ምክንያት ወደ ክልል መምጣት ሳያስፈልጋቸው መምህራን ባሉበት ወረዳ ሆነው ቅሬታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ አቶ ደምስ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ የመምህራን መብት የሆነውን ዝውውር በቀጣይ ዓመት ጀምሮ በቴክኖሎጅ በመታገዝ ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለማድረግ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁንም አቶ ደምስ አክለው ገልጸዋል፡፡
ከፍተኛ የሰው ሃይል የተንቀሳቀሰበትን ዝውውር በፍትሃዊነት፣ በታማኝነትና በትግስት ለረጅም ቀናት በመስራት ለተሳተፉ የዞንና የክልል የትምህርት ባለሙያዎች እንዲሁም ለዞንና የክልል መምህራን ማህበር ስራ አስፈጻሚዎች የክልሉ ትምህርት ቢሮ የላቀ ምስጋና አቅርቧል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የዝውውር ሙሉ መረጃውን ዛሬ በቢሮው የፌስቡክና ቴሌግራም ገጽ ይፋ የሚያደርግ ሲሆን በተጨማሪም የዝውውሩን ሙሉ መረጃ በየደረጃው ለሚገኙ የትምህርት መዋቅር የሚደርስ ይሆናል፡፡

#ትምህርትለትውለሰድ

11/06/2026
11/06/2026
11/06/2026
01/04/2026

Address

ዋግ ኽምራ ስቆጣ ዞን አበርገሌ ወረዳ
Sokota

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abergelie Wereda Education Office/አብርገሌ ወረዳ ክንድጝ ጽህፈሽ ጝን/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category